ሥልጣንን ይዞ ሀገርንና ሕዝብን ለማሥተዳደር ሁለት የትግል አማራጮች አሉ፡፡ በሀገራችን ሁለቱም ዓይነቶች በሚገባ ይታወቃሉ ተሞክረዋልም፡፡ አንደኛው ሕዝብ በሚያደርገው ምርጫ የመንግሥትነት ሥልጣንን መያዝ መሠረቱ ያደረገው ሰላማዊ የትግል አማራጭ ሲሆን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ይህ ሰላማዊ የትግል አማራጭ ዝግ ሲሆን ወይም ሊሠራ በማይችልበት ጊዜ በሕዝብ ላይ በኃይል የተጫነን አንባገነን አገዛዝን በኃይል ለማስወገድ የሚደረግ የኃይል እንቅስቃሴዎችን መሠረቱ ያደረገ የትጥቅ ወይም የዐመፅ የትግል አማራጭ ነው፡፡ እስኪ ሰላማዊው የትግል አማራጭ በዘመነ ወያኔ ምን እንደሚመስል በአጭሩ ዕንይ፡፡
ወያኔና ምርጫ፡-
በዘመነ ወያኔ ምርጫ እየተባለ ለአራት ጊዜያት ያህል በሕዝብና በሀገር ላይ ከባድ ቀልድና ሹፈት ሲቀለድና ሲሾፍ ሲፌዝ ተቆይቷል አሁን ደግሞ ለአምስተኛ ጊዜ እየተሾፈና እየተቀለደ ይገኛል፡፡ በዘመነ ወያኔ ምርጫ ተደርጎ አያውቅም፡፡ ይህ ሐቅ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (State department) እስከ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ድረስ በሚሰጧቸው መግለጫዎች በተደጋጋሚ ያረጋገጡት ሀቅ ነው፡፡ ዐይኑን ጨፍኖ ለመሞኘት የፈቀደ ካልሆነ በስተቀር በሁሉም ዜጋም በሚገባ ይታወቃል፡፡ አገዛዙ ፍትሐዊና ትክክለኛ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል አቅም ፍላጎትና ተፈጥሮ ከቶውንም ኖሮት አያውቅም መቸምም ደግሞ አይኖረውም፡፡
ለዚህ በርካታ ምክንያቶችን ልንጠቅስ እንችላለን፡፡ አንዱና ዋነኛው ግን አገዛዙ እንደዚህ ዓይነቶችን የዲሞክራሲያዊ (የበይነ-ሕዝባዊ) መንግሥታት መርሆዎችን ለመቀበልና ለመተግበር የሚያስችለው ተፈጥሮና አስተሳሰብ የሌለው በመሆኑ ነው፡፡ ይሄንን ባሕርይውን ከትግል ዘመኑ ጀምሮ ባለው ታሪኩ ማንነቱና ሰብእናው ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ነገር ግን በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አሁን ድረስ ንጉሣዊ የመንግሥት ሥርዓት ካላቸው ጥቂት ሀገራት በስተቀር በመላው ዓለም ኅብረተሰብ ዘንድ “ሥልጣን የሚያዘው በሕዝብ ምርጫ ይሁንታ ነው” የሚለው አስተሳሰብ ገዥና ተቀባይነትን ያገኘ አስተሳሰብ በመሆኑ ምክንያት እንደ ወያኔ ያሉ አንባገነናዊ አገዛዝ ከእነሱ አስቀድመው የነበሩትን መንግሥታት በኃይል ካስወገዱ በኋላ በያዙት ሥልጣን ላይ ለመቆየት ያላቸው አማራጭ ምንም ዓይነት ፋይዳና ትርጉም የሌለው የይስሙላ ምርጫ አዘጋጅቶ በማኪያሔድና በሕዝብ ተመረጥን እያሉ በማጭበርበር ሥልጣንን ጨምድዶ ይዞ መቆየት ግዴታ ስለሆነባቸው በከፍተኛ ሸርና ጥንቃቄ ያንን የይስሞላ ምርጫ ወቅቱን እየጠበቁ ያደርጋሉ፡፡
የሚገርመው ግን አሁንም ድረስ ዜጎች እውነት መስሏቸው የወያኔን ተፈጥሮና አቋም ካለማወቅ ይሁን ተስፋ ካለመቁረጥ አገዛዙ አካሂደዋለሁ በሚላቸው ምርጫዎች በመምረጥና በመመረጥ ለመሳተፍ ፓርቲ እያቋቋሙ መንቀሳቀቃቸው ነው፡፡ የሚያሳዝነው እነኝህ ፓርቲዎች የመድብለ ፓርቲ የመንግሥት ሥርዓት ደንብና ሕግ በሚፈቅድላቸውና በሰጣቸው መብት መሠረት ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት በነጻ መደራጀትና መታገል የሚችሉበትን ዕድል ለአንድም ጊዜ እንኳን አግኝተው አለማወቃቸው ነው፡፡ አገዛዙ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሌላ ሥራ ትቶ ዲሞክራሲያዊ (በይነሕዝባዊ) ነኝ እያለ ግን ለሀገርም ለወገንም ለማንም በማይጠቅም ሁኔታ ሥራየ ብሎ መንገዳቸውን በመሰናክሎችና ሸር አጥሮ እንዳይፈናፈኑ እንዲኮሰምኑ ሲያደርጋቸው ቆይቷል፡፡ ይሄንን ሁሉ ተቋቁመው ለመውጣት ሲሞክሩም መከፋፈልና መሰነጣጠቅ አንድን ፓርቲ ምን ያህል እንደሚያሽመደምድ እንደሚዶዳ ከማንም በላይ ከበረሃ ጀምሮ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ በኋላም በራሱ ላይ በተደጋጋሚ ደርሶበት ያውቀዋልና ሰርጎ እየገባ ይከፋፍላቸዋል ይሰነጥቃቸዋል ከዚያም ይበትናቸዋል፡፡ እንዲህ ያደርግና ሲያበቃ ደግሞ ለባዕዳኑ “ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲ አላደለንም ለዚህ ነው ሥልጣኑ በእኛ ብቻ የተያዘ ሊሆን የቻለው” እያለ ይሳለቃል፡፡ በዘመነ ወያኔ የፓርቲዎች ሕይዎት በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ የተመሰቃቀለ እንደሆነ ዛሬም ድረስ አለ፡፡
አገዛዙም በተለያየ ጊዜ በሚያደርጋቸው የይስሙላ ምርጫዎች የበይነ ሕዝባዊ (የዴሞክራሲያዊ) ሥርዓት ያለ ለማስመሰል ብቻ በጣት የሚቆጠሩ ተወዳዳሪ ወገኖችን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት እንዲገቡ ከሚያደርጋቸው ውጭ ሕዝብ በሰጠው ድምፅ መሠረት መንግሥት እንዲመሠረት ፈቅዶና ፈልጎ አስቦም አያውቅም፡፡ በእርግጥ ከምርጫው ሐሰተኝነት የተነሣ እነኝህ ዜጎች በተሳተፉባቸው የውሸት ምርጫዎች ውጤት አግኝተው ትርጉም ያለው የፖለቲካ (የእምነተ-አሥተዳደር) ሥርዓት ሽግግርና እድገት ማስመዝገብ ባይቻልም ምንም የተከሩት የፈየዱት ነገር የለም ማለት ግን አይቻልም፡፡ ቢያንስ የአገዛዙን የምርጫ ድግሶችን ሐሰተኝነት በሚገባ ማጋለጥ ችለዋልና ከዚህ አንጻር የነበራቸው ተሳትፎ ፋይዳ ነበረው ማለት ይቻላል፡፡
ወያኔ እነዚያን ሐሰተኛ ምርጫዎች ሲያስፈጽም መጨረሻ ላይ እሱ የሚፈልገው ውጤት እንዲገኝ የሚያደርግባቸው 3 ዋና ዋና ስልቶች ወይም መንገዶች ዘሉት፡-
- የምርጫውን ሒደት እሱ በፈለገው መንገድ የሚዘውር ለእሱ ታማኝ የሆነ ምንደኞች ርካሾችና ቆሻሾች የሞሉበት የይስሙላ የምርጫ ቦርድ ማቋቋም፡፡
- ወደ ፖለቲካ ፓርቲዎች (የእምነተ-አሥተዳደር ቡድኖች) አባሎቹን አስቀድሞ አስርጎ በማስገባት የተለያየ ሴራ እንዲሸርቡ በማድረግ ፓርቲዎቹ የሚጠበቅባቸውን የፖለቲካ ሥራዎች በአግባቡና በብቃት እንዳይከውኑ ማድረግ፣ ስምምነትና አንድነት ማሳጣት፣ አቅማቸው የተዳከመ እንዲሆን ማድረግ፣ በተፈለገ ጊዜ መሰንጠቅና ማፍረስ ወይም መበተን ወዘተ.
- ትክክለኛና ፍትሐዊ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዳይኖር ማድረግ፡፡ ለምሳሌ፡- ምርጫ በመጣ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከምርጫ ወቅት ውጭ ባሉ ወቅቶችም ጭምር የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከሕዝብ ጋር ሊገናኙና አቅድ መርሆዎቻቸውን ለሕዝብ ማድረስ ማስተዋወቅ የሚችሉባቸውን ሕገ መንግሥታዊ የብዙኃን መገናኛዎችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ቅድመ ምርመራ የመጠቀምና በስብሰባ በሰላማዊ ሰልፎች ገጽ ለገጽ ከሕዝብ ጋር ሊገናኙ የሚችሉባቸውን ሕገ መንግሥታዊ መብቶችንና ዕድሎች እንዳያገኙ እንዳይጠቀሙ በመንፈግ በመከልከል፣ ሕዝቡ በሕገ መንግሥታቸው የተረጋገጠለትን መብት ተጠቅሞ ያለ ሥጋትና ፍርሐት ያመነባቸውንና የተቀበላቸውን ፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዳይደግፍ በአባልነትም እንዳይሳተፍ ማድረግ፣ አድርጎት ሲገኝም የሥራ ዋስትናውን ከማሳጣት ጀምሮ በዜግነቱ ሊያገኛቸው የሚችላቸውን መብትና አገልግሎቶች እንዳያገኝ በማድረግ ከዛም አልፎ እስር እንግልትና ሰቆቃ በመፈጸም በተለያየ መንገድ ሌላው እንዲያውቀውና በመቀጣጫነት እንዲገነዘበው በማድረግ ሕዝብ እንዲርቃቸው እንዳይከተላቸው ማድረግ ወዘተ. ናቸው፡፡
እነኝህን የሚያካክሉ ግዙፍ ግዙፍ መሰናክሎች ባሉበት ሁኔታ በምንም ተአምር ቢሆን እንደየትም ተሁኖ ትክክለኛና ፍትሐዊ ምርጫ ማድረግ የሚታሰብ አይደለም፡፡ አገዛዙ በእነኝህ ሠርና ክፋትና ኢፍትሐዊ ተግባሮቹ ውጤቶች በመመካትና በተሳሳተ ግንዛቤ ለሕዝብ ከነበረው ንቀትና ዝቅጠኛ ግምት ተደፋፍሮ ለምዕራባዊያን አጋሮቹ የገባውን ቃል ለመጠበቅ ሲል በምርጫ 97ዓ.ም. ሰጥቶት በነበረው ሰፋ ያለ ዕድል ፈጽሞ ያልጠበቀውና ያላሰበውን ውጤት ስላስከተለበት “ኧረ! እኔ ውጤቱ እንደዚህ የሚሆን ስላልመሰለኝ ነው እንጅ እንደዚህማ በጭራሽ አይሆንም አይደረግም!” በማለት በአንጻራዊ መልኩ ሲታይ መልካም የነበረውን የምርጫ ሒደት ከምርጫው ማግስት ጀምሮ በመቀልበስ የሕዝብን ድምፅ በሕዝብ ደም አጥቦ ገደል በመክተት ሁለተኛ በእንደዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ቅሌት ውስጥ እንደማይገባ ለራሱ ምሎ ወደ ነበረበት ቦታው ተመልሷል፡፡ በዚህም ምክንያት በ2002ዓ.ም. ላይ አስቂኝ በሆነ ሁኔታ ምርጫ አደረኩ ብሎ 99.6 በመቶውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫን አሸንፌ መንግሥት መሠረትኩ ብሎ እየገዛ ይገኛል፡፡
ወያኔ በምንም ተአምር ትክክለኛና ፍትሐዊ ምርጫ ሊያደርግ እንደማይችልና የማይችልበትን የማይፈልግበትን ምክንያት ከዓመታት በፊት ጀምሮ ስገልጽ እንደቆየሁ ይታወሳል፡-
- አገዛዙ ከማንነቱና የሚታወቅባቸው በግልጽም በስውርም የያዛቸው ፖለቲካዊ ዓላማና ጥቅሙ የተነሣ ለምሳሌ፡- ከገጠር እስከ ከተማ ሕዝቡ በትውልደ ትውልድ እየወረሰው የመጣውን የኖረበትን መሬቱን እየተነጠቀ ለባለ ሀብት እየተሰጠበት በገዛ ሀገሩ ሀገር አልባ መኖሪያ አልባ ስደተኛ የሚያደርገው ፖሊሲው (መመሪያው) እና በሌሎቹም የሀገርንና የሕዝብን ጥቅም የሚጎዱ ሥራዎቹ በኃይል ካልሆነ በስተቀር በትክክለኛና ፍትሐዊ በሆነ ምርጫ በሕዝብ ዘንድ ተመራጭ እንደማያደርገው ስለሚያውቅ፡፡
- አገዛዙ ከቅጥረኛነቱና አንባገነንነቱ የተነሣ በፈጸማቸው ኢፍትሐዊና ከባባድ የሀገር ክህደቶች፣ በርካታና እጅግ የገዛዘፉ የሙስና ወንጀሎች፣ በግፍ ባፈሰሰው የንጹሐን ዜጎች ደም በመሳሰሉት ወንጀሎቹ ምክንያቶች ሥልጣን በለቀቀ ማግስት እየታነቀ ለፍርድ እንደሚቀርብ ስለሚያውቅ፡፡
- ፀረ ኢትዮጵያና ሕዝቧ የሆኑ ከጠባብ ደንቆሮና ጎጠኛ ማንነቱ የተነሣ የፈጸማቸው እየፈጸማቸው ያሉትና ሊፈጽማቸው የሚፈልጋቸው የጥፋት ዓላማዎቹ በአስተማማኝ መልኩ ገና ከግብ ስላልደረሱለትና እነሱን ከግብ ለማድረስ ካለው ጽኑ ዓላማና ፍላጎት የተነሣ፡፡
- አገዛዙ ማንነቱ በሕዝቡ ዘንድ ከመቸውም ጊዜ በላይ በሚገባ ከመታወቁ ጋር በተያያዘ ከደረሰበት የሞራል ኪሳራ የተነሣ በራስ መተማመኑ ስለጠፋ፡፡
በእነዚህ ሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች ወያኔ በኃይል ተገዶ ካልሆነ በስተቀር ምርጫን መሠረቱ ባደረገ ሰላማዊ የትግል አማራጭ መሸነፉን አምኖ ፈጽሞ ሥልጣንን እንኩ ብሎ ሊያስረክብ ስለማይችል በምርጫ ሥልጣን መረከብን ተስፋ አድርገው እየተሳተፉ ያሉ ወገኖችን ለወያኔ የሕዝብ ግንኙነት ፍጆታና የውጭ የፖለቲካ ግንኙነት ፍጆታ መጠቀሚያ ከመሆን በስተቀር የምታልሙትንና የምትመኙትን ያህል ምንም ልትፈይዱ የምትችሉት ነገር የለም ጊዜያቹህን በከንቱ እያጠፋቹህ ሕዝብንም ተስፋ የማይደረግ ነገርን ተስፋ አድርጎ ቶሎ ነቅቶ ማድረግ ያለበትን ነገር አድርጎ ሀገሩንና እራሱን እንዳይታደግ እንዲዘናጋ እያደረጋቹህትና ወያኔ ለጥፋት ዓላማው ተጨማሪ የማጥፊያ ጊዜ እንዲያገኝ እየረዳቹህት ነውና ኧረ እባካቹህ ንቁ? እያልኩ ሳሳስብ መቆየቴ የሚታወስ ነው፡፡
ዘንድሮ ግን ወያኔ ማንነቱን ሕዝቡ ጠንቅቆ ከማወቁና በሚፈጽማቸው በደሎችና ግፎች ከመንገሽገሹ የተነሣ በተፈጠረበት እጅግ በጣም ከባድ በራስ ያለመተማመን ችግር እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ለተቃዋሚ ወይም ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዛ ሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች በተጻራሪ ነጻነታቸውንና መብቶቻቸውን እየከለከለ በራሱ ፍላጎት ብቻ በጠባቡ ከልሎ የሚሰጣቸውን የመጫዎቻ ሜዳም እንኳን ሊሰጥ በፍጹም አልፈለገም፡፡ እንደወያኔ አስተሳሰብ ይሄ ስልቱ ጊዜው አልፎበታል ተበልቶበታል፡፡ ቢያደርገው “ልቆጣጠረው በማልችለውና ባልጠበኩት አቅጣጫ ሄዶ ያስበላኛል” ብሎ ያምናል፡፡ በመሆኑም ብቻውን ሮጦ አሸነፍኩ ብሎ በማስጨብጨብ አሁንም መንግሥት ነኝ ሊል ፈልጓል፡፡
በዚህም መሠረት መኢአድንና አንድነትን ሕገ ወጥነት ሸፍጥና ሸር በተሞላበት መልኩ ከምርጫ ፉክክር ውጪ አድርጎ ሲያበቃ ከፉክክር ውጪ ማድረጉን አውጇል፡፡ ባወጀ ማግስትም እንዲያው ለማስመሰል እንኳን ያህል የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባልተያዘበት ወይም በሌለበት ሁኔታ ዐይን ባወጣ የውንብድና ተግባር ጽ/ቤቶቻቸውንና የየፓርቲዎቹን ንብረቶች ነጥቆ ለቅጥረኞቹ አስረክቧል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲንም ጥረት እያደረገባቸው እንዳለው ሁሉ አንድ ሰበብ ፈጥሮ መሸኘቱ የማይቀር ይመስላል፡፡ ፓርቲውን ባያስወጡትና በምርጫው ቢሳተፍም እንኳ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት ምርጫዎች ሁሉ ይሄኛውም የይስሙላ ከመሆን አይድንምና ብቻ ለማስመሰል ያህል ሦስት አራት ለሚሆኑት የፓርቲው ተመራጮች ተመርጣቹሀል ብሎ ወንበር ከመስጠት ባለፈ ሕዝብ የሰጠው ድምፅ ቅቡል ሆኖ መንግሥት የሚመሠረትበት አሠራርና ዕድል ስለሌለ ከአጫፋሪነትና አዳማቂነት የተለየ ሊፈይደው የሚችለውና የሚመጣም ለውጥ አይኖርም፡፡ ሰላማዊ የትግል አማራጩ ፍጹም ዝግ ቢሆንም ሰማያዊ ፓርቲ እንደ መኢአድና አንድነት ሁሉ ወያኔ ካላስወጣው በስተቀር በምርጫው ሒደት ውስጥ የሚያጋጥሙትንና በወያኔ የሚፈጸሙትን ውንብድናና ማጭበርበሮች እያጋለጠ በምርጫው ሒደት ውስጥ ቢቆይ መቆየቱ የሆነ ሰዓት ላይ ለሕዝባዊ ትግሉ ሊጠቅም የሚችልባቸው ሁኔታዎች አሉና ከሒደቱ ባይወጣ መልካም ይመስለኛል፡፡
እንግዲህ እውነት ለሥልጣን ሳይሆን ለሀገርና ለሕዝብ ነጻነትና ደኅንነት በማሰብ በመቆጨት በመብከንከን በፖለቲካው መስክ የተሠማራ ወገን ካለ የሚለየው አሁን ነው፡፡ ይህ የሀገርና የወገን ፍቅርና ኃላፊነት እንዳለበት የተገነዘበ ዜጋ ቀድሞውንም ያልነበረውን ወያኔ ያልሰጠውን የሰላማዊ ትግል አማራጭ እንዳለ ቆጥሮ ከነበረ አሁን እንደማይቻል በተግባርና በይፋ መታወጁ መነገሩ ሀገርንና ሕዝብን ለመታደግ ያለበትንና ያመነበትን የዜግነት ግዴታና ኃላፊነት ለመወጣት የቀረውንና ብቸኛውን የትግልን አማራጭ እንዲጠቀም ያደርገዋልና በዚያ መንገድ ይሄንን አንባገነናዊ አገዛዝ ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ከመታገል ወደ ኋላ ባለማለቱ የምናየው የምናውቀው የምንለየው ይሆናል፡፡ ሀገርናንና ሕዝብን ከወያኔ አንባገነናዊና ፀረ ሕዝብ ፀረ ሀገር አገዛዝ ነጻ ልናወጣ የምንችልበት ቀሪ ብቸኛው አማራጭ የኃይል አማራጭ ነው፡፡ መሬት አንቀጥቅጥ በሆነ ሕዝባዊ ዐመፅ ወይም የትጥቅ ትግል፡፡
የሀገርና የወገን ፍቅር አለኝ የሚል ወገን ከሁለቱ የኃይል አማራጭ መንገዶች አንደኛውን ወይም ሁለቱንም መንገዶች በመጠቀም ትግሉን ይቀጥላል እንጅ በቃ! ሰላማዊ የትግል አማራጭ አይቻልምና መንገዱ ተዘግቷልና ብሎ ሀገርና ሕዝብን ለጅብ አሳልፎ ሰጥቶ አርፌ ልቀመጥ አይልም፡፡ ይሄንን የሚያደርግ ካለ ይሄ ሰው ቀድሞውንም ቢሆን ሥልጣንን ይዞ በተራው ለመብላት ነበረ ዓላማው እንጅ ዋጋ ከፍሎ ሀገርንና ሕዝብን ከግፍ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ሲል ለትግሉ ነፍሱንም እስከመስጠት ድረስ ታማኝ አልነበረም ማለት ነው፡፡ ሀገርንና ሕዝብን እመራለሁ ብለው በፖለቲካው የሚሳተፉ ሰዎች ሊያውቁት የሚገባው ቁምነገር ቢኖር እንዲህ ዓይነት ሰው የሚያስፈልገው ምላስ ብቻ ሳይሆን ልብም ጭምር ዋነኛ አስፈላጊው ነገር መሆኑን ነው፡፡ በእንዲህ ዓይነት አጋጣሚ ላይ ቆራጥ አቋም ወስዶ ዋጋ ለመክፈል የማይደፍር ሰው ወይም ለዚህ የሚበቃ ልብ ወኔ የሌለው ፖለቲከኛ ነኝ ባይ ካለ በዚህ በፖለቲካው ትግል ሁለተኛ ዝር ላይል አርፎ እቤቱ ይቀመጥ፡፡ በዚህ መስክ ቢሠማራም እንደ መይሳው ካሳ (ዐፄ ቴዎድሮስ) በቆራጥነትና ድፍረት ጀግንነት የሀገር ፍቅር የደረጀ የተሞላ ብልህነትና አርቆ አሳቢነትን ለሚጠይቀው ሀገርንና ሕዝብን ያህል ነገር ለመምራት የሚያበቃ ሰብእና የለውምና፡፡
ስለሆነም የሰላማዊ የትግል አማራጭ ዕድል የተነፈጋቸው ወገኖች እንደፍላጎታቸው ሁሉ ሕዝብንና ሀገርን የመምራት ብቃቱ አለን የሚሉ ከሆነ ወያኔን በሕዝባዊ ዐመፅ ወይም በትጥቅ ትግል በኃይል ከሥልጣን ለማስወገድ ወገባቸውን አስረው መንቀሳቀሳቸው ግዴታቸው ነው ማለት ነው፡፡ ይሄንንም ሲያደርጉ ትግሉ በሚጠይቀው የተቀናጀና የተጠና የበሰለ ስልታዊ መንገድ እንጅ የግድ በግልጽ አዋጅ እያወጁ ዘራፍ በማለት እንዳልሆነ ልብ ይሏል፡፡ ይህ የትግል ስልት እንደ ሰላማዊ ትግል ባለመሆኑና ከበድ ያለ በመሆኑ ወዳለፍነው ዘመን እንድንመለስ ተገደናልና እንደ የኢሕአፓ ዘመን ወጣቶች ላቅ ያለ ብስለት ቁርጠኝነት የዓላማ ጽናትና ጀግንነት የሚጠይቅ በመሆኑ ለዚህ ከባድ ትግል ከሥነልቡና ጀምሮ እራስን በበቂ ሁኔታ ማዘጋጀት ግድ ይላል፡፡ ኢሕአፓ ከነበረበት ደካማ ጎኖች ትምህርት በመውሰው ጠንካራ ጎኖቹን ደግሞ እንዳሉ መውሰድ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ አማራጭ የለምና መቁረጥ ግድ ነው፡፡
ከሰው በታች ሆኖ ተንቆ ተረግጦ ተዋርዶ ለሀገር ምንም ሳይፈይዱ ከማለፍ እንቢ ለውርደት እንቢ ለጭቆና እንቢ ለባንዳ እንቢ ለሞት (ለወያኔ) በማለት እንደሰው የሰውነት ክብርን ለራስ አውጆ አስጠብቆ ለሀገርና ሕዝብ ክብር ማለፉ በእጅጉ ተመራጭ ነው፡፡ ይሄ ግዴታ የፖለቲካ መሪዎችና አባላቱ ብቻ ሳይሆን የሴቱም የወንዱም፣ የሽማግሌውም የወጣቱም፣ የተማሪውም የሠራተኛውም፣ የሀብታሙም የድሀውም፣ የምሁሩም የጨዋውም (ያልተማረውም)፣ የእስላሙም የአማራውም፣ የሃይማኖት መሪውም የሕዝባዊውም የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የዜግነት ግዴታ ነው፡፡ ሁሉም እንደ አቅሙና ችሎታው ሊወጣው የሚገባው ተልእኮ ነው፡፡ ለሕዝብና ለሀገር ሲል መሥዋዕትነት የመክፈል ግዴታ ያለበት የተለየ ዜጋ ስለሌለ፡፡
ዋጋ ተከፍሎ በሚገኘው ነጻነት ተጠቃሚው ሁሉም ስለሆነ፡፡ አሁን ሀገራችን ተጋፍጣው ባለችበትና ከመከራ ከጥፋት ለመዳን የዜጎቿን ርብርብና ተሳትፎ በእጅጉ በምትሻበት የፈተና ወቅት ለመሀል ሰፋሪ ቦታ የለም፡፡ ወይ ከአጥፊዋ ከወያኔ ወገን መሆን ወይ ሊታደጓት ከቆረጡት ወገን እንጅ በመሀል ተንጠልጥለው የሚንሳፈፉበት በመሀል ያለ የመሀል ሰፋሪ ቦታ የለም፡፡ ጥቂቶች እራሳቸውን ለመሥዋዕትነት አሳልፈው ሰጥተው እየታገሉ እየተፋለሙ አብዛኛው ይሄንን ሁኔታ እንደተውኔት ዳር ሆኖ የሚመለከትበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም፡፡ ሁሉም ዜጋ በትግሉ የመሳተፍ ግዴታ ይኖርበታል፡፡ በደርግ ዘመን የኢሕአፓ ወጣቶች በምን ያህል ብስለት የዓላማ ጽናትና ቁርጠኝነት ትግላቸውን ይከውኑ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከደርግ ይልቅ ወያኔ ሩቅ ነው፣ ባዕድ ነው፡፡ በደርግ ዘመን የበሰለ የተቀናጀና የተደራጀ ኅቡዕ ወይም ሥውር ትግል ማድረግ ከተቻለ ሕዝቡ ባዕድ አድርጎ በሚመለከተው በወያኔ ዘመን ይሄንን ማድረግ ሊያቅት አይችልም፡፡ እስከታሰበበት ጊዜ ድረስ የማይቻል ነገር የለም ይቻላል!
ወያኔ ቅዘናም ነው አንድ ሁለቱ ባለሥልጣናት ላይ እርምጃ ቢወሰድ ፍርስርሱ የሚወጣ ድንብርብሩ የሚጠፋ ቡድን ነው፡፡ ወያኔ ሕዝቡን የዚህን ያህል የናቀውና መጫወቻ መቀለጃ ሊያደርገው የቻለው እንዲህ ዓይነቱ ቆራጥ እርምጃ በባለሥልጣናቱ ላይ ሊወሰድ ስላልቻለ ነው፡፡ በአንድ ሁለቱ ላይ እርምጃ ቢወሰድ ግን እመኑኝ ወያኔን ባለበት ቦታ ላይ አታገኙትም፡፡ በትውልደ ኢትዮጵያዊነታቸው እንዳዘንላቸው እንዳሰብንላቸው በፍጹም ሊረዱ ሊገባቸው አልቻለምና መጨከን ግድ ነው፡፡ እንዲህ ካልተጨከነባቸው በስተቀር ወያኔ ልክ ሊገባ የሚችል ዓይነት ቡድን አይደለም፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ሥራ ለመሥራት የግድ በስፋት መደራጀት አያስፈልግም ሦስት አራት የሚተማመኑ ጓደኛሞች እየተሆነም ብዙ ሥራ መሥራት ይቻላል፡፡ መከላከያ ውስጥ ያሉ የወያኔ እርኩሰት የሚያንገሸግሻቸው ወገኖች ለዚህ ቅርብ ናቸው፡፡ በትጥቅ ትግል ያሉ የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይልም በሚገባ የሠለጠኑ ኮማንዶዎችን ቢያሠማራ ግሩም ግሩም ሥራ መሥራት ይቻላል፡፡ እያንዳንዱ ዜጋም ቢሆን ወያኔን ከማዳከም አኳያ እንደየ አቅሙ ብዙ ሊሠራቸው የሚችላቸው ተግባራት አሉ፡፡ ረዘም ያለ ጊዜ ከሚጠይቀው ከትጥቅ ትግልና የተለየ አጋጣሚ ከሚያስፈልገው ከሕዝባዊ ዐመፅ ይልቅ በፍጥነት ለውጤት የሚያበቃው ይሄኛው በባለሥልጣናት ላይ የሚወሰድ እርምጃ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደዚህ ዓይነት ትግል ውስጥ ዳግም እንደገና እንዲገባ በመገደዱ እጅግ እጅግ እናዝናለን ሙሉ ኃላፊነቱንና ተጠያቂነቱንም የሚወስደው ወያኔና ደጋፊዎቹ ያሆናሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ደግመን እንዳንገባ ነበር የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሄንን ያህል ዘመን ሊታገሱት የማይቻልን ነገር እየታገሰ የቆየው፡፡
የሕወሀት መሥራቾች (ወያኔዎች) በደርግ ላይ ተስፋ ቆርጠው ወደ ትጥቅ ትግል ሲያመሩ ከአንድ ዓመት በላይ ደርግን ታግሶ ማየት አልቻሉም ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ወያኔን ይሄንን ያህል ዘመን እጅግ በጣም በሰፋ ትዕግስት የማይቻል ነገር እየቻለ ታግሶ ቆይቷል፡፡ ወያኔ ዕለት ተዕለት እየባሰበት እንደመጣው ሁሉ ከዚህም በላይ ሌላ 23 ዓመታት ቢጨመርለት እያከፋ ይሄድ እንደሆነ ነው እንጅ ተምሮና ተጸጽቶ ሰው ይሆናል ብሎ ማሰብ ጨርሶ የሚቻልበት ሁኔታ የለም፡፡ እስከ አፍንጫው የተጋተው የተነከረበት የወንጀል ዓይነትና ድርጊትም ካለበት ተመልሶ ሰው ለመሆን ዕድል የሚሰጠው አይደለምና፡፡ ገና 40 እና 50 ዓመታት እንገዛለን በሥልጣን ላይ እንቆያለን እያሉ ሲደነፉ አልሰማንምን? ይታያቹህ! በዚህ መራር የአገዛዝ ሁኔታ ሌላ 40 እና 50 ዓመታት እየገዙ ከስርህ ተነቅለህ እስክትጠፋና እነሱ እንደዋርካ እስኪሰፉ ድረስ ለመቆየት ለመኖር ነው እየተመኙና ያንን ያህል ለመቆየትም እየጣሩ ያሉት፡፡ ያንን ያህል መቆየት ከቻሉማ ከዚያ በኋላ ማን ኖሮ ለማን ሲሉ ሥልጣን ያስረክባሉ? አንተ እንደሆንክ ያን ጊዜ አትኖር! መንጥረው ይጨርሱህ አይደል እንዴ? ስለሆነም ከዚህ በኋላ ለወያኔ ያለህ ትዕግሥት እርባናና ጥቅም አልባ እንደሆነ ተረድተህ ሁልህም ወገን ቆርጠህ ተነሥ፡፡ ከዚህ በኋላ የሚኖርህ ዝምታ የከፋ አደጋ በራስህና በሀገር ላይ ካለማምጣት ካለመጋበዝ በስተቀር የሚጠቅምህ የሚፈይድልህ ነገር የለምና፡፡
የምናደርገው ሕዝባዊ ትግል ፈተናዎች፡-
አሁንም ደግሜ ማሳሰብ የምሻው ነገር ቢኖር ይህ ተገደን የምንገባበት ትግል መራራና ከባድም ነው፡፡ ይሁን እንጅ ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ ስለሌለን የፈለገውን ያህል መሥዋዕትነት ቢያስከፍልም ወደ ኋላ ልንል አንችልም፡፡ መታወቅ ያለበት የምንፋለመው ዝም ብንልም ከማይምረንና ቀረጣጥፎ ከሚበላን ጭራቅ ጋር መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም ካለ መቁረጥ መጨከን በቀር ሌላ አማራጭ የለንም፡፡ ቀጥሎ የምጠቅሳቸው የትግል ወቅት ፈተናዎቻችንን አውቀናቸው እንዘጋጅባቸውና እንጠነቀቅባቸው ዘንድ በጣም ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን ፈተናዎች ትእግስት ጥበብና ቆራጥነት በተሞላበት መልኩ ለመቆጣጠር ለመፍታት ካልቻልን በስተቀር እጣ ፋንታችን ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ በተራ ቁጥር አራት ላይ ያለው አሳሳቢ ችግር ወያኔ በእድሜ ዘመኑ አወሳስቦ ሲተበትባቸው የቆዩ ዋና ዋና ችግሮች በመሆናቸው የአምላክ እርዳታም ሊጠየቅበት ይገባል፡፡
- በደርግ ዘመን የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ወቅት የነበረው የቀይ ሽብርና የነጭ ሽብር ጠባሳዎች አሁንም ድረስ ያሉና ያልተረሱ በመሆናቸው በሕዝቡ ዘንድ ሊኖር የሚችል ፍርሐት፡፡
- የአገዛዙ የስለላ ሥራዎች፡፡
- አገዛዙ ትግሉን ለማጨናገፍ የሚወስዳቸው የጭካኔ እርምጃዎች፡፡
- አገዛዙን ታግሎ ለመገርሰስ የቆረጡ ኃይሎች በፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ምክንያቶች ጥቅምና ፍላጎቶቻቸው የተለያየ የማይጣጣምና የተቃረነ መሆን ናቸው፡፡
አራተኛውን ነጥብ ጥቂት ማብራራት የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ እንደሚታወቀው በሀገራችን ወያኔን የሚታገሉ የፖለቲካ ኃይሎች ዓላማና ግብ ሲታይ አንደኛው ከሌላኛው ተቃራኒ ነው፡፡ አንደኛው በወያኔ የሚራገብ እሱም ከኢትዮጵያ መገንጠልን ዓላማና ግብ ያደረጉ መኖራቸው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ መገንጠልን አጥብቀው በመቃወም የሀገርን ህልውናና አንድነትን ማስጠበቅ ዓላማና ግባቸው ያደረጉ መኖራቸው ነው፡፡ ዓላማቸው እንዳለመጣጣሙና እንደመቃረኑ ሁሉ እነኝህ ሁለቱን ማጣጣም ማስታረቅ የሚቻል አይሆንም፡፡ የሚለያቸው አንደኛው በሌላኛው ላይ የሚያገኘው የጦር ድል ነው፡፡ የተለያዩ የባዕዳን የጥፋት ኃይሎች እጅ በመሀል ስላለ ነው እንጅ ሁሉም ብሔረሰቦች በእኩልነት በነጻነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያ የምትኖር ከሆነ እገነጠላለሁ የሚሉ ወገኖች የሚገነጠሉበት ምንም ዓይነት ምክንያት ሊኖር ባልተገባ ነበር፡፡
ሌላኛው እስካሁን በበቂ ያልተነገረለትና ያልታወቀ ነገር ግን ብዙ ሊያውከንና ከባድ አደጋ ሊያደርስብን የሚችል ሃይማኖትን ሽፋን ያደረገ ተጨባጭ ሥጋት ነው፡፡ እሱ ምንድን ነው? ሰሞኑን አንድ “የፈረንሳዩ ቻርሊ ሂብዶ ጋዜጣ አሸባሪዎችና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት” የሚል ርእስ ያለው ጽሑፍ አስነብቤ ነበር፡፡ በዚህ ጽሑፍ ላይ እስልምናን የሚከተሉ ወገኖቻችንን በዘልማድ የሚያደርጓቸውን ነገር ግን ሃይማኖታዊ ትእዛዝ የሌለባቸውን ከኢትዮጵያዊነታችን ጋር የሚቃረኑ አንዳንድ ተግባራት በመጥቀስ ለሀገርና ለማንነት ቅድሚያና የበለጠ ትኩረት እንዲሰጡ አበክሬ ለማሳሰብ ሞክሬ ነበር፡፡ መጀመሪያ ጽሑፉ በተለጠፈበት የመጽሐፈ ገጽ (የፌስ ቡክ) ግድግዳ ላይ 180 ያህል አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡ ከአምስቱ እስልምናን የማይከተሉ ወገኖች አስተያየቶች በስተቀር የተቀሩት አስተያየቶች እስልምናን ከሚከተሉ ወገኖቻችን የተሰጡና “ከሀገር ከማንነት ከነፍሳችንም በላይ ነቢያችንንና ሃይማኖታችን እንወዳለን ለእሱም ነፍሳችንን እስከመስጠት ድረስ ቁርጠኞች ነን በዚህ አንደራደርም” በሚል የአስተሳሰብ አስኳል ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው፡፡ ልብ በሉ እኔ ያልኩት ባልጠራ ግንዛቤና ከቁርአናቸው ትእዛዝ ውጭ ኢትዮጵያዊ ማንነታቹህን እየሸረሸራቹህና የራሳቹህን ማንነት ጥላቹህ ዓረባዊ እየሆናቹህ ነውና ይሄ ከእስልምና ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ እስልምናቹህን መከተል ትችላላቹህ ሀገራቹህንና ማንነታቹህን ግን ጠብቁ አልኩ እንጅ እስልምናቹህን ጣሉ አለማለቴ እየታወቀ የተሰጡት አስተያየቶች ግን እነዚያ የጠቀስኳቸው ነገሮች ከሃይማኖት ጋር እንደማይገናኙ እያወቁ የሚገናኙ አድርገው በመቁጠር “ሀገር ማንነት አይገባንም ለኛ ነቢያችንና ሃይማኖታችን ይበልጡብናል” በማለት ኃይልና ቁጣ ስድብና ዘለፋ የተሞላበት አስተያየቶችን ነው የሰጡት፡፡
የእነዚህ ሰዎች ችግር እስልምናንና ዓረብነትን፣ እስልምናንና የዓረቦችን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ባሕላዊ ጥቅሞች መለየት አለመቻል ነው፡፡ ዓረቦች ጥቅማቸውን ለማስተበቅ ሲሉ ሁለቱንም ቀላቅለው ሲሰብኳቸው ስለኖሩ ይሄ ችግር ሊከሰትባቸው እንደቻለ እገምታለሁ፡፡ እስልምናን መቀበል ማለት የዓረብ ባሪያ ሎሌ ባንዳ መሆን ማለት አይደለም፡፡ ዓረቦች የራሳቸው ማንነት እንዳላቸው ሁሉ እኛም ሐበሾች ከነሱ የተሻለ ማንነት አለን፡፡ የራስን ጥሎ የዓረብን መያዝ ማለት የውዴታ ባርነት ነው፡፡ ችግሩ ይሄንን አለመረዳታቸው ብቻ ሳይሆን ለመረዳት አለመፈለጋቸው ነው፡፡ የዚህን ጉዳይ አደገኛነት የማይረዳ ሰው የሚኖር አይመስለኝም፡፡ እነኝህ ወገኖች በደም ኢትዮጵያዊ መሆናቸውንና በኢትዮጵያዊነታቸውም ዜጋ በመሆናቸው ብቻ ሀገራቸውንና ማንነታቸውን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸው ጨርሶ መቀበል አይፈልጉም፡፡ ዓረቦች በሃይማኖት ሽፋን የዓረብን ጥቅሞች እንዲጠብቁ እንዳደረጓቸው አያውቁም ማወቅም አይፈልጉም፡፡ ዓረቦች ወገኖቻችንን እያሳቱ ያለበት ዘዴ ከቁርአን ውስጥ የሌለና ያልታዘዘ መሆኑ ነው የሚደንቀው፡፡
ስለ አለባበስ በዚያ ጽሑፍ ላይ የገለጽኩት በመሆኑ አልደግመውም፡፡ ቋንቋን በተመለከተ ግን “እስልምናን የተቀበለ ሁሉ የራሱን ቋንቋ ጥሎ ዓረብኛን ይያዝ” የሚል ትዕዛዝ በቁርአናቸው እንደሌለ እየታወቀ ዓረቦች የባሕል ወረራ ለማድረግ ሲሉ “ዓረብኛ ቁርአን የወረደበት ቅዱስ ቋንቋ ስለሆነ እስላም ለሆነ ሁሉ ዓረብኛን ማወቅ ግዴታው ነው” እያሉ እየሰበኩ ቋንቋቸውን ያስፋፋሉ፡፡ የሚያሳዝነው ይህ አባባላቸው ስድብ መሆኑን ከዓረብ ውጭ ያለው ሌላው እስልምናን ተቀባይ ዘር አለመረዳቱ ነው፡፡ ለመሆኑ የቋንቋ እርኩስ አለ እንዴ? ከእግዚአብሔር ውጪ ከዓረብኛ ውጪ ያሉ ቋንቋዎችን የፈጠረ ሌላ እርኩስ ፈጣሪ አለ እንዴ? በዓረብኛ ቋንቋ እርኩስ ነገር ሊወራ አይችልም እንዴ? ይሄንን እያሉ ከሚያታልሉት ዓረቦች ይልቅ ደግሞ ማን ይገርመኛል መሰላቹህ? ይሄንን የዓረቦችን አባባል እውነት አድርገው የተቀበሉ ከዓረብ ውጭ ያሉ ሌሎች እስልምናን የተቀበሉ ዘሮች፡፡ ዓረብኛ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቋንቋዎችንም ማወቁ ይጠቅማል እንጅ አይጎዳምና ቋንቋን ማወቅ መልካም ነው፡፡ ቋንቋውን ማምለኩና የራስን ርኩስ ሌላውን ቅዱስ ማለቱ ግን ችግር ያለበትና እጅግ ያልበሰለ አስተሳሰብ ነው፡፡ ሰውን የሚቀድሰውም የሚያረክሰውም ሥራው ነው እንጅ ቋንቋ አይደለም፡፡ ሰው ዓረብ ስለሆነ ቅዱስ አይሆንም ሌላ ዘር ስለሆነም እርኩስ አይሆንም፡፡ እናም ወገኖቸ ሆይ! የቱንም ያህል የኢትዮጵያዊነትን አሻራ እየጣላቹህ የዓረብን ማንነትና አሻራ ብትላበሱት ከጥቁርነታቹህ ከኢትዮጵያዊ ቀለማቹህ ከሐበሻነታቹህ ተቀይራቹህ ዓረብ ልትሆኑ አትችሉምና የማይቻል ነገርን በማድረግ ለመሆን በመጣር በማንነት ቀውስ በሽታ እራሳቹህን ባታውኩ ባታሰቃዩ እራሳቹህን ብታከብሩ ለራሳቹህ ዋጋ ብትሰጡ እራሳቹህን መሆን ብትችሉ ለጤናቹህ መልካምና ሰላምም ነው ለማለት እወዳለሁ፡፡
እኔ ይሄንን ነገር ለማመን ከመቸገሬ የተነሣ ሳስበው ሕልም ሕልም ሁሉ ይመስለኛል፡፡ እንዴት ሰው የራሱን ማንነት ጥሎ ለሌላው ምናልባትም ለጠላቱ ማንነት ነፍሴን እሰጣለሁ ይላል? እኔ ክርስቲያን ነኝ ክርስቲያን በመሆኔ ግን ሀገሬንና ከቋንቋየ ጀምሮ እስከ ባሕሌ ድረስ ማንነቴን እንድጠላ እንድንቅ አላደረገኝም፡፡ በእርግጥ ከአውሮፓ የመጣ ክርስትና ነው ብለው ፕሮቴስናንትና ካቶሊክ የሆኑ ወገኖች ለሀገራችንና ለማንነታችን ያላቸው ግምት እንደ ላይኞቹ ነው፡፡ የሚያስጠብቁት ጥቅም የሰበኳቸውንና የሚረዷቸውን ምዕራባዊያን ጥቅሞች ነው፡፡ ተግባሮቻቸውም ሁሉ ኢትዮጵያዊነትን በማጥፋት ላይ ያተኮረ በዚህም የተጠመዱ ናቸው፡፡ በእርግጥ የተለያዩ ሀገራት የሀገራችንን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊና ባሕላዊ ጥቅሞች በማጥፋት የየራሳቸውን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊና ባሕላዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ሥራ እንደሚሠሩ እንደሚጥሩ ከድሮ ጀምሮ የሚታወቅ ጉዳይ ቢሆንም የዚህ ግብ ግብ ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወገኖችንና ተግባራቸውን ስናይ ግን እጅግ መገረማችን የሚቀር አይመስለኝም፡፡
ለማንኛውም ሀገርንና ማንነትን በተመለከተ የእኔ ሃይማኖት ግን ከምንም በላይ ሀገሬንና ማንነቴን እንድወድ እንድጠብቅ እንድኮራባት እንድሞትለትም አድርጋ ቀረጸችኝ እንጅ የራሴን አስጥላ ሃይማኖትህ መጣበት የምትለውን ሀገር ጥቅም እንድይዝና የራሴን ጥየ ለነዚያም ጥብቅና እንድቆም አላደረገችም፡፡ ለነገሩ የኔ ሃይማኖት ከየትም አልመጣም በዚህ ርእሰ ጉዳይ ሰፊና መረጃ ሰጪ ንባብ እንዳስነበብኳቹህ ይታወሳል፡፡ የኔ ሃይማኖት ለዚህች ሀገርና ማንነት ካላት የላቀ ቦታ የተነሣ እንዲያውም ይህች ሀገር የተቀደሰችና ልዑል እግዚአብሔርም ከእናቱ ጀምሮ ዋና ዋና ለሚላቸውና ከፍተኛውን ተጋድሎ ለፈጸሙ ቅዱሳን የዐሥራት በገራቸው እንድትሆን የሚሸልማት ብርቅ ድንቅ ቅድስት ሀገር እንደሆነችና ለዚህች ሀገር ነፍሴንም ጨምሮ ምንም የምሰስተው ነገር እንዳይኖር መክራና አስተምራ ነው ያሳደገችኝ፡፡ እንኳን እኔን ኢትዮጵያዊውን ሐዋርያዊ ተልእኮ ለመስጠት በሄደችባቸውና በምታገለግልባቸው ሀገራት ላሉ ባዕዳን ሁሉ ኢትዮጵያን በዚህ መልኩ እንዲያስቧት ነው የምትሰብከው፡፡ እኔ የማውቀው ይሄንን ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ ሳይሆን አይቀርም እነዚህ ወገኖች በደም ኢትዮጵያዊያን ሆነው ሳለ የገዛ ሀገራቸውን በመክዳት ለባዕዳን ከዚያም ባለፈ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው እንደ ጠላት ለሚቆጥሯቸው ሀገራትና ሕዝቦች እሴቶችና ማንነት ጥብቅና ሲቆሙና ሲዋደቁ እጅግ እጅግ የሚገርመኝ የሆነው፡፡ አንድ የዓረቦች አባባል ትውስ አለኝ ዓረቦች ምን ይላሉ “በመንገድህ ላይ መርዘኛ እባብና ኢትዮጵያዊ ቢያጋጥሙህ ቀድመህ ኢትዮጵያዊውን ግደለው” የሚል አይገርሟቹህም? ይሄንን ያህል ከእባብም በከፋ መልኩ ለሚጠሏቸውና ለሚጠየፏቸው ሊያጠፏቸውም ሌት ተቀን ለሚያሴሩት እኩዮች እንዲህ እንደሚያስቧቸውና እንደሚጠሏቸው እያወቁ እንሞትላቹሀለን ሲሉ? ይሄ የጤና ነው ትላላቹህ?
እንደምታውቁት አሁን በዚህ ወቅት ሁሉም ባይሆኑም የሚበዙቱ በተሟሟቀ ሁኔታ ከዚህ ብዥታ ጋር ሆነው ለእስልምና እየታገሉ እየመሰላቸው ለዓረብ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ባሕላዊ ጥቅሞች እየታገሉ ያሉ እስልምናን የሚከተሉ ወገኖች አሉ ዋጋም እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡ አደጋው ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ዓረቦች ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ይህችን ሀገርና ሕዝቧን በተመለከተ የተለየ ፍላጎት ይዘው በሀገራችን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ባሕላዊ ጥቅሞች ጉዳይ ላይ እጃቸውን እያስገቡ የራሳቸውን ጫና ሲፈጥሩ፤ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊና ባሕላዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ አውዳሚ ጦርነቶችን ከማድረግ ጀምሮ ብዙ ነገር ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ዛሬም ላይ ዓረቦች እንደወትሮው ሁሉ በዚህች ሀገር ላይ ላላቸው ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊና ባሕላዊ ጥቅም በሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት ጫናና ፍልሚያ አጋጣሚው ባመቻቸው ጊዜ ሁሉ እጃቸውን በሚያስገቡበት ወቅት እነኝህ ወገኖች መጠቀሚያ መሆናቸው የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ይሄ ከባድ አደጋ ነው፡፡
በእርግጥ ፊት ለፊት ወጥተው ከወያኔ ጋር እየተጋፈጡ ያሉት ወገኖች ቁጥር ያን ያህል ላቅ ያለ ላይሆን ይችላል፡፡ ከጀርባ ግን በሚሊዮኖች (አእላፋት) የሚቆጠሩ የዓላማ ተጋሪ እንዳላቸው የሚጠረጠር አይመስለኝም፡፡ የሚያሳዝነው የእነሱ ትግል ግብ የሀገርንና የሕዝብን ክብር ሉዓላዊነት ታሪክ ባሕል ማንነት እሴቶችን ሁሉ በተመለለከተ ቢሳካላቸው ከወያኔ በከፋ መልኩ የከፋ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን ብዙዎቹ የሚያውቁ አለመሆናቸው ነው፡፡ ይሄንን አብዛኞቻቸው በቅጡ ሳያውቁት የሚያደርጉትን ደግሞ ሌላው ኢትዮጵያዊ የማይፈልገው የማይፈቅደውም ከመሆኑ የተነሣ የጥቅምና የዓላማ ግጭት መነሣቱ የማይቀር ይሆናል በዚህ መሀል የጠላት እርስ በእርስ እያፋጀ ሀገሪቱን የማዳከም ሰትራቴጂ (ስልት) ተሳክቶላቸው እንደቆየው ሁሉ ወደፊትም ይሳካላቸው ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በሃይማኖትና በዘር ሳንለያይ ለጠላቶቻችን ሳይሆን ለእኛ የምትሆን ነጻ እኩልነት የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ለማምጣት ስንል የማይቀርልንንና የሚገጥመንን ፈተና በብቃት ተወጥተን ዓላማና ግባችንን ለማሳካት ከወዲሁ መዘጋጀቱ ግድ መሆኑን ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ የገባቸውና ፈተናው ተግዳሮቱ አጋጣሚውን ለመጠቀም ጠላት ሃይማኖትንና ዘርን ሽፋን አድርጎ እንደሚመጣ በመረዳት በሀገራቸውና በሕዝባቸው ጥቅሞች ላይ ፈጽሞ ያለመደራደር ጠንካራ አቋም የያዙ የእስልምና ተከታይ ወገኖቻችን እነኝህን የሳቱና ያልገባቸውን የጠላት መጠቀሚያ ወገኖቻችንን ከያዙት የጥፋት ዓላማ እንዲመለሱና ለገዛ ሀገራቸውና ለሕዝባቸው ዋጋ መሥዋዕትነትን እንዲከፍሉ የመምከርና የማስተማር ተግባራቸውን ሳይደክሙና ሳይሰለቹ ጠንክረው እንዲወጡ በዚህ አጋጣሚ አበክሬ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
No comments:
Post a Comment