Wednesday, April 15, 2015

በስለላ ከሆላንድ የተባረረው የጋዜጠኛውን አንገት እቆርጣለሁ አለ

ክንፉ አሰፋ
እለተ እሁድ ከቀትር በሁዋላ አንድ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። ቁጥሩ +251 945226530 ነበር። ስልኩን አነሳሁት።
“ሃሎ”
“አቤት”
“አለማየሁ ነኝ። መን አባክ ነው የምትጽፈው። እኔ አላማዬ ነው። አንተን ግን አንገትህን ቆርጬ ነው የማሳይህ። ለማየት ያብቃህ። ያን የምትጽፈውን ጽሁፍ… እኔ ምንም ልሁን ምን እንደዚህ አይደለሁም። እሺ። እናትክን…(ይህንን ጸያፍ ቃል በድምጽ ስሙት)። … ደግሞ ኢህአዴግ ዘርህን… (ይህንንም ጸያፍ ቃል በድምጽ ስሙት)
TPLF spy in Netherlands
ከሆላንድ የተባረረው የወያኔ ሰላይ አለማየሁ ስንታየሁ(ሀለቀ ፎላ)
ይህ ጸያፍ ዘለፋ እና ማስፈራርያ እንግዲህ ወያኔ ምን ያህል እንደወረደ ያሳየናል። ከነውረኛ ስድቡ ባሻገር ደግሞ ቀላል የማይባል ድንበር ዘለል ሽብር ነው። ለዚህ ሽብር ተጠያቂ የሚሆነውም ተላላኪውና ሆድ አደሩ ብቻ ሳይሆን ላኪውም ጭምር ነው። ህወሃትን በመጠለል ልክ እንደ ISIS አንገትህን እቆርጥልሃለው ሲል መናገሩ መንግሥታዊ አሸባሪነት ለለመሆኑ ግልጽ ነው። ለዚህ ሰው ሲከራከር የነበረው ተሾመ ቶጋም ይህንን ሰምቶ ዝም የሚል ከሆነ የወንጀሉ ተባባሪ ይሆናል።

የምሥራች! የአንድ ደሮ ዋጋ የዐርባ አምስት በሬ ዋጋ ሆነ!

ነፃነት ዘለቀ (አዲስ አበባ)
ክርስቲያን አንባቢዎቼ እንኳን ለ2007ዓ.ም የጌታችን የመድሓኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፡፡ ሙስሊሞችና ሌሎችም እንኳን ለኛ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ለእናንተም በዓል(ላት) በሰላም እንዲያደርሰን የጋራ የሆነውን ፈጣሪን በጋራ እንለምነው፡፡Easter preparations on Holy Saturday in Ethiopia
ይቺ የዘንድሮ የትንሣኤ በዓል ከቀደሙት ትንሽ ለዬት ሳትል አትቀርም፡፡ ይሄ ግፋፎ ብር እዬለየለት መጥቷል፡፡ የሰሞኑ ገበያ በጣሙን ተበሻቅጧል፡፡ መንግሥቶቻችን ሲያቀብጣቸው ብሩ ላይ የወፍ ስዕል አኑረውበት ብሩ በዓለማችን የመጨረሻው ፈጣን ወፍ ሆነ፡፡ ሲበር ፍጥነቱ ልዩ ነው፤ በሣይንሳዊ መሣሪያ እገዛ ካልሆነ በዐይን ብቻ አይታይም፡፡ አቶ ብሩ ጉድ አፍልቷል፡፡ በአብዛኛው ከሆዱ ባለፈ የማይጨነቅ የልምድ ነጋዴ በሞላባት ሀገራችን ውስጥ በአቋራጭ ለመክበር የሚስገበገበው ሰው በዛና አቅልን የሳተ የገንዘብ ግንኙነት ነግሦ ሁላችንንም አቅል እያሳጣን ከሰውነት ተራ እያስወጣን ይገኛል፡፡ የዛሬው አዋዋሌ ራሱ ከወትሮው የተለዬ ሆኖብኝ በጣም ሲገርመኝ ውሎ አመሸ፡፡ ከማን ጋር እንደማወጋው ጨንቆኝ ሳለ እናንተ ትዝ አላችሁኝ፡፡ እስኪ ተንፈስ ልበል፡፡

የአክራሪዎች፣ የተስፈንጣሪዎችና የአሸባሪዎች ዘመን

ይሄይስ አእምሮ (አዲስ አበባ)
ወቅቱ ለክርስቲያኖች የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል ሰሞን እንደመሆኑ በዓሉ የሚመለከታቸውን አንባቢ ወገኖቼን “እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው [በሰላም] አደረሳችሁ” ማለትን እወዳለሁ፡፡ የደርግ ጊዜ አንድ ትዝታ አለኝ፡፡ በአብዛኛው በሀገር ወዳድ ደናቁርት የታጨቀው የደርግ መንግሥት ሠለጠንኩ ብሎ ሃይማኖተቢሱንና ሃይማኖተኝነትን ከልካዩን የሶሻሊዝም ሥርዓት ካወጀባት ጠማማ ዕለት ጀምሮ በዓል በመጣ ቁጥር በተለይም የአብዮቱ በዓል በሚከበርበት ወቅት “እንኳን ደረሳችሁ” ይል ነበር – ያ ለአገራችን ባዕድ የነበረ የአገዛዝ ሥርዓት አንዲት ፊደል ላይ እንዲያ ይጨነቅ የነበረው፣ ሰው ለበዓሉ የደረሰው በራሱ እንጂ በፈጣሪ እንዳልሆነ ለማጠየቅ ነበር፤ የሥርዓቱ አቀንቃኞች በአብዛኛውና በግልጽ ይዞታቸው ሶሻሊስትና ኮሚኒስት እንጂ የሃይማኖት ሰዎች አልነበሩም – አንዳንዶች አምልኮታቸውን በኅቡዕ ያከናውኑ እንደነበርና ልጆቻቸውን ሣይቀር በድብቅ ክርስትና ያስነሱ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡

ህዝባዊ እምቢተኝነት ለነጻነት (የዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል)

የዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል
የኢትዮጵያ ህዝብ እሩብ ምእተ አመት በትከሻው ላይ የተሸከመው የባርነት ቀንበር እየተነቃነቀ ነው። እኛን ያስጨነቀን ደም ጠገቡ የወያኔ ስርዓት ወይስ ሃገራዊ ህላዌ ነው መንኮታኮት ያለበት? በኛ ልብ ውስጥ ከሚነደው የሃገር ፍቅር እሳት ብንነሳ መልሳችን የሚሆነው እየተነቃነቀ ያለው ስርዓቱ ነው ፤የሚንኮታኮተውም የስርዓቱ አራማጅ ህወሃት ነው የሚል መልስ እንሰጣለን። ይህ መልስ ግን ከቀቢጸ ተስፋ ወይም ከነጻነት ጥማት የመነጨ ምኞት ሳይሆን የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታን ተመርኩዘን በየአቅጣጫው ፈነዳሁ ፈነዳሁ የሚለውን ህዝባዊ አመጽ መነሻ በማድረግ ነው።

የአማራዉ ሕዝብ ሁኔታ፣ ለኢትዮጵያዉያን ሁሉ

ኢምሩ ዘለቀ | የካቲት ፪ሺ፯
ለማስታወስ ያህል የዛሬ ሶስት ዓመት “ሞረሽ የአማራ አብሮነት ድርጅት” ብለን እኔ ራሴ፡ አምባሳደር አያሌው ማንደፍሮ፡ አቶ ይስሃቅ ክፍሌና ዶክተር ምስማኩ አስራት ሁነን ግቡ ለአማራዉ እርዳታ ለመስጠት የሆነ ማሃበር አዘጋጅተንና አስመዝገበን ነበር፤ የድርጅቱም አላማ ከማናቸዉም የፖሊቲካ ንቅናቄ ነጻ የሆነ የመረዳጃ ማህበር ብቻ እንዲሆን ነበር።Amhara Ethnic group members Ethiopia
ይህንን እርምጃ ለመዉሰድ የገፋፋን ባለፉት ዓመታት በተለይ የወያኔ ቡድን የመንግሥት ስልጣን ከያዘ ወዲህ በተለይ በአማራዉ ሕዝብ ላይ የሚያካሂደው ወሰን የለሽ ጭቆናና ግፍ፤ ሕዝቡን ለማጥፋት የምያደርገው ሙከራ በጣም አሳስቦንና አስጭንቆን ነው። በዚህም አንጻር በየቀኑ የሚወርድብት በደል አንሶ የአማራዉ ሕዝብ ቁጥር እስከ ስድስት ሚልዮን ተቀንሷል ይባላል። ይሄም የሕዝቡ ቁጥር ከሃገሪቷ ጠቅላላ እድገት ጋር እየተመዛዘነ እንዲካሄድ፤ እርጉዝናን ለመቆጣጠር በሚሰጠዉ ክትባትና ልዩ ልዩ መድሃኒት ስበብ፤ ሴቶችን ጭርሶ የሚያመክኑትን እንዲሰጥ ተብሎ በተቀናጀ ሴራ መደረጉ የማያጠራጥር ሆኗል።

የኤርትራ ነገር የኛ ጉዳይ ፣ ትችትን በቅኝት ( ሄኖክ የሺጥላ )

ወዳጄ ልጅ ተክሌ የጻፈውን ” የኤርትራ ነገር ፣ የኛ ችግር ፣ መርህ አልባ ፍቅር ” የምትለዋን አየሁ ። መስመር በመስመር ደግሜ ደጋግሜ አነበብኩ ። ከዚያ ተመለሼ ወዳጄ መሳይ መኮንን በዳላስ ስለ ኤርትራ ቆይታው ያደረገውን ውይይት ተመለከትኩ ፣ እኔ በነበርኩበት በሲያትል ላይ ስላደረገው ውይይትም ለማስታወስ ሞከርኩ ፣ ከዚያ የፕሮፌሰር መስፍን ወለደማርያምን ጽሑፍ በድጋሚ አነበብኩ ፣ ከዚያ ስለ ጸሐፊ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወለድ እና በጸሐፊ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወለድ የተነገሩ እና የተከተቡ ነገሮችን አነበብኩ ፣ ከዚያ ያንዳርጋቸው ጽጌን ንግግር ( ስለ ኢሳያስ አፈወርቂ የተናገረውን ) ቪዲዮ ሄጄ ተመለከትኩ ፣ ከዚያ ባንድ ወቅት ( ምናልባት ከ 3 ወይም አራት ወር በፊት ) ዔፍሬም ማዴቦ ከውህደቱ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ በ ሎስ አንጀለስ አድጎት የነበረውን ንግግር ለማስታወስ ሞከርኩ ( ስለ አርበኞች ግንቦት ሰባት ውህደት ) ፣ ከዚያ እኔ ስለ እውነት ስለ ኤርትራ መንግስት የሚሰማኝን አሰብኩ ። ባንድ ወቅት ከወዳጄ መሳይ መኮንን ጋ ባደረኩት ቃለ መጠይቅ እንዲህ ነበር ያልኩት ። ” እኔ ተኩላ ሊበላኝ ነው ብዬ ለጅብ አላመለክትም !” ፣ ይህንንም ስል ወያኔ ተኩላ ሻቢያ ደሞ ጅብ ነው ማለቴ ነበር ።

Saturday, April 11, 2015

መተማመን በጠፋበት መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ሹም ሽሩ ቀጥሏል * ኮረኔል ጋይም እና ኮረኔል እሸቴ ከስልጣናቸው ዝቅ ተደረጉ

በስልጣን ላይ ያለው ገዢው ስርዓት በከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ላይ እምነት በማጣቱ ምክንያት እንዱን በማውረድ ሌላኛውን በመሾም ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ ምንጮቹን ጠቅሶ ደህሚት ዘገበ:: ዜናው እንደወረደ እንደሚከተለው ተስተናግዷል::
Photo File
Photo File

ከመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ በደረሰን መረጃ መሰረት ውስጣዊ አሰራሩ በስብሶ በሰራዊቱ አዛዦች እምነት አጥቶ የሚገኘው የኢህአዴግ ስርዓት በ31ኛ ክፍለ ጦር ውስጥ እየሰራ የቆየውን ኮነሬል ጋይም የተባለውን አዛዥ በስርዓቱ ላይ እምነት የለውም በሚል ምክንያት ከነበረበት የአዛዥነት ደረጃ በማውረድ። በምትኩ ኮነሬል ዘነበ የተባለውን ከ23ኛ ክፍለጦር በማስመጣት ኮነሬል ጋይም ምክትል ሆኖ አዲሰራ መደረጉን የተገኘው መረጃ አስረድቷል::