Tuesday, August 11, 2015

ብቃት የተላበሰ አመራር የለንም ሲሉ አቶ አለምነው መኮንን ተናገሩ

Alemnew Mekonenየብአዴን የጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን ብአዴን የየተመሠረተበትን 35ዓመት ህዳር 11 ቀን 2008 ዓ.ምለማክበር በማሰብ፣ ከሚዲያ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ብአዴን የህዝቡን ፍላጎት የሚያሟላ ብቃት የተላበሰ አመራር የለውም ብለዋል።
በግዮን ሆቴል ብአዴን በጠራው የሚዲያና ኮምኒኬሽን ባለሙያዎች የተሳተፉበት ስብሰባ ላይ ማብራሪያ የሰጡት አቶ አለምነው መኮንን፤ ብአዴን ያለበትን ተግዳሮቶች በዘረዘሩበት መግለጫቸው፣ ባለፉት 24 ዓመታት የህዝቡን ፍላጎት የሚያረካ የተሟላ የአመራር ብቃት አለመታየቱን አምነዋል፡፡ “ሕዝቡ በመቶ ኪሎሜትር እየሄደ፣ አመራሩ በ80 ቢሄድ የ20 ኪሎሜትር ክፍተት አለ» በሚል በምሳሌ ያስረዱት አቶ አለምነው፣ በአመራር ብቃት በኩል ሕዝቡ የሚፈልገውን እርካታ ለማምጣት አልቻልንም ብለዋል።

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተመንግስት – ክፍል 2 “ሳሞራ የኑስ በበረሃ በርካታ የህወሓት ታጋይ ሴቶችን ድፍሯል”

መለስ ዜናዊ፣ ስብሀት ነጋ፣ ስዬ አብርሃ፣ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ገብሩ አስራት፣ አለምሰገድ ገ/አምላክ፣ አውዓሎም ወልዱ፣ አረጋሽ አዳነ፣ አርከበ ዕቁባይ፣ ፃድቃን ገ/ተንሳይ፣ አበበ ተ/ኃይማኖት እና ክንፈ ገ/መደህን ለረጅም ጊዜ መቀሌ ላይ በመዶለት በኢትዮጵያና ህዝቦቿ ላይ አሲረው የበቀል፣ የዘረፋ፣ የመከፋፈል እና የረጅም ጊዜ የአፈና ስርዐት እቅድ ነድፈው ሰራዊታቸውን በባሌ ልከው እነሱ በቦሌ አዲስ አበባ ገቡ፡፡
በአንድ ጃቸው መቀሌ ውስጥ ተጠፍጥፎ ተሰርቶ የተሳለ የበቀል ሰይፍ በሌላኛው እጃቸው የዘረኝነት ረጅም ዘንግ ጨብጠው አዲስ አበባ የገቡት የባንዳ ልጆች ስብስብ ሳይውሉ ሳያድሩ የጥፋት ተልዕኳአቸውን ዕቅድ አንድባንድ መተግበር ጀመሩ፡፡

ላለፉት 12 ዓመታት “ደብል ዲጂት” ያደገው ኢኮኖሚ

ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በምትጠቃበት የድርቅ መጠን እንደ ኬንያና ታንዛኒያ የመሣሰሉት ጎረቤት ሀገራትም እንደሚጠቁ ጥናቶች ያሳያሉ። ሆኖም ከተጠቀሱት ሀገሮች በከፋ ሁኔታ ድርቁ(የአየር ንብረት መዛባቱ)- ረሀብና የከፋ እልቂት የሚያስከትለው እኛ ሀገር ነው።የዚህም ምክንያቱ ከአጠቃላይ ህዝባችን ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ገበሬ ኢኮኖሚያዊ አቅሙ በቋፍ ላይ የሚገኝ በመኾኑ ነው።ይህ ምንም ምርምር አያስፈልገውም።

ኢህአዴግ በኤርትራ አራት አቅጣጫዎች ጥቃት ሊሰነዝር አስቧል

አሜሪካ ሃሳቡ ቀርቦላታል ተብሏል
ኢህአዴግ በአራት አቅጣጫዎች የጦር ጥቃት ለመሰንዘር ማሰቡ ተሰማ፡፡ ይኸው ሃሳብ ለአሜሪካ ቀርቦላታል፡፡
በቅርቡ የተጠናከረ እንቅስቃሴ የጀመረው የአርበኞች ግንቦት ፯ ኃይል በተደጋጋሚ በሚያወጣው መረጃ በተለያዩ ቦታዎች ጥቃት ማድረሱን በይፋ ቢገልጽም ኢህአዴግ ጥቃቱን በቀጥታ ለማስተባበል እስካሁን አልወደደም። ይሁን እንጂ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ “ህዝብ አስፈቅደን” ሲሉ ኤርትራን እንደሚወጉ ይፋ አድርገዋል። አብዛኞች እንደሚስማሙበት ዛቻው ግጭት ስለመኖሩ የሚያረጋግጥ ነው። በሌላው አንጻር ደግሞ ይህንን የሃይለማርያም ንግግር የኤርትራው ሹም በዓለምአቀፍ መድረክ ላይ የተለመደ የህወሃት/ኢህአዴግ ማስፈራሪያና ዛቻ በማለት አጣጥለውታል፡፡

ሠማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ሊያካሂድ ነው አዲስ አመራር መራር ይመረጣል

ሰማያዊ ፓርቲ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤ ነሐሴ 16 እና 17 የሚያካሂድ ሲሆን በዚህ ጉባኤ አዲስ መራር ይመረጣል
ተብሎም ይጠበቃል፡፡ በፓርቲው ህገ ደንብ መሰረት ጠቅላላ… ጉባኤ የሚደረገው በየ3 ዓመቱ መሆኑን የጠቀሱት የፓርቲው
ብሄራዊ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰይድ ኢብራሂም፤ ጉባኤው በሐምሌ መካሄድ የነበረበት ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች
ምክር ቤቱ ለ3 ወር የማራዘም ስልጣኑን ተጠቅሞ እስከ ነሐሴ ማራዘሙን ገልፀዋል፡፡ በጉባኤው ላይ የሚሳተፉ አባላት ቁጥርና
የጉባኤውን አካሄድ ለመወሰን ብሄራዊ ምክር ቤቱ በነገው እለት ስብሰባ እንደሚያደርግም ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡

የትግራይ እና የአማራ ክልል ገዢዎች እርስበርሳቸው እየተወነጃጀሉ ነው።

11257193_1694823434078480_9109119436834128683_o
በትግራይ እና በአማራ ክልል ገዢዎች መካከል ያለው አለመግባባት በተለያዩ አጋጣሚዎች ከፍ ዝቅ ሲል ቆይቶ ፣ ሰሞኑን ኢህአዴግ በአካሄደው ግምገማ ላይ እንደገና አገርሽቶበታል። የትግራይ ክልል ገዢ አቶ አባይ ወልዱ የተወሰኑ የህወሃት ደጋፊዎችን በመያዝ በሁለቱ ክልሎች መካከል ስላለው አወዛጋቢ መሬት ፣ ከአማራ ክልል ገዢ ጋር በድንበር አካበባ ያደረጉት ውይይት፣ በዘለፋና በጸብ ከተቋጨ ከወራት በሁዋላ፣ በሰሞኑ የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የመሳሪያ ምዘገባን ተከትሎ እንደገና አገርሽቷል።

በምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራሮች መካከል መከፋፈል ተፈጠረ፡፡

የምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራርና አባላት ከሀምሌ 29 እስከ ነሀሴ 1 2007 ዓ.ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ነው መከፋፈሉ ሊከስት የቻለው፡፡ የምዕራብ ጎጃም የብአዴን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሀብታሙ፣ የዞኑ ምክትል ከንቲባ አስፋው ገበየሁና የወረዳው የብአዴን ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አላምር ተሻለ የተባሉ የህወሓት አገልጋይ የመሩት በዱላ ቀረሽ ስድድብ፣ እርስበርስ መወነጃጀልና የተደበቀ ገመናን በመነስነስ ታጅቦ ለሦስት ቀናት የዘለቀው ስብሰባ ከመነሻው በዋናነት ለውይይት ያቀረባቸው አርበኞች ግንቦት 7 ባወጀው ጦርነት ላይ ተመስርቶ በሽበርተኝነት ላይ የሚያጠነጥን አንድ ሃሳብና የብአዴንን 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበርን የሚመለከት ሌላ ተጨማሪ እርዕስ ያነገበ ሁለት አብይ አጀንዳዎች ነበሩ፡