የቤንሻንጉል ጉምዝን የምናውቃት በለምለምነቷ እና በአከባቢው አገራችን ነው ብለው ለረዥም ዘመናት ሰፍረው ሲኖሩ በአንድ ጀንበር ተፈናቅለው በገዛ አገራቸው በተሰደዱ ዜጎች እና በተፈጠሩ ሁኔታዎች ነው። አከባቢውን በተመለከተ የጸጥታ ሁኔታዎች አስተማማኝ ከመሆናቸውም በላይ ህዝቡ ሰላማዊ እና ሰራተኛ መሆኑ የተረጋገጠ ነው።
ከተወሰኑ አመታት በፊት በሱዳን እና በአማጺ ጄኔራል መካከል በተደረገ ጦርነት ሸሽተው የገብ ወታደሮች ወደ ደቡብ ሱዳን ተላለፉበት እንጂ ….እንዲሁም ከደቡብ ሱዳን እየተነሱ ወያኔን የሚወጉ የጋምቤላ ክልል ተወላጆች ወደ አከባቢ ባይደርሱም የነሱ እንቅስቃሴ የተገደበ ሲሆን ለሰበብ የሚበቃ አይደለም እንዲሁም አማጽያኑ እንደተበተኑ መረጃዎች ፡ይጠቁማሉ በአሁን ወቅት ከጸጥታ ቁጥጥር አንጻር በሚል አከባቢው ከፍተኛ ጥበቃ እና የወታደራዊ ደህንነት መዋቅር ስለተዘረጋበት ይህንንም መዋቅር ከመሃል አገር አለቃ ጸጋይ እና ከምእራብ እዝ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በጋራ ተቀናጅተው ሲመሩት አስፈላጊውን መረጃ ከሁለቱ ሱዳኖች ጋር በመለዋወጥ ይቆጣጠሩታል። ለዚህ ቁጥጥሩ ጥብቅ መሆኑ ማርጋገጫው ባለፈው የተይዙትን የግብጥ ሰላዮችን እንደ ማስረጃ ማጣቀስ ይቻላል፡፤ እንድሁም ከደቡብ ሱድን ተፈናቅለው ከመጡ ኢትዮጵያውያን ጋር ተቀላቅልው ለመግባት የሞከሩ የሻ እብይ ስእላዮች ናቸው የተባሉ መያዛቸው የአከባቢውን የጽጥታ ቁጥጥር ያሳብቃል። ታዲያ ከዚህ መሃል እንዴት አማጽያን ሊሰርጉ ቻሉ ?
አሶሳ እና አከባቢው መጠቃት የጀመሩት አሁን ሳይሆን ጥቃት ደረሰበት በተባለው አከባቢ በህዳር 5/2013 ሰኞ ገበያ በሚኒባስ ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ አራት ሰዎች ሲሞቱ ቀሪዎች መቁሰላቸው ይታወሳል። በወቅቱ መንግስት ነኝ የሚለው ወያኔ ምርመራ ላይ ነው በሚል ሰበብ ሁኔታውን አድብስብሶ አልፎታል። እንዲሁም በተለያየ ጊዜ አውቶብስ እያስቆሙ የሚዘርፉ ጽጉረ ልውጦች በአከባቢው ከተሞች ሲንቀሳቀሱ ምንም ይየንካቸው እንዳልነበር እና ቆየት ብሎም ከጥር 2014 በኋላ አለመታየታቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ከአስሳ እና አከባቢው የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙን ወያኒ አደራጅቶ ያስታጠቃቸው የሽፍታ ቡድን ካልሆነ በስተቀር እስካሁን ለዚህ ጉዳይ ይህንን ሃላፊነት እወስዳለሁ ያለ ድርጅት የለም፡፤ በክልላችን የጥይት ድምጽ ሰምተን አናውቅም የሚሉት ነዋሪዎቹ ይህንን የሚፈጽሙት ቀን በአከባቢያችን የምናያቸው በማንም የማይነኩ ሽፍቶች ናቸው ሲሉ መንግስት ላይ ጣታቸውን ይጠቁማሉ። እንደ ሰሞኑ መረጃዎች በምእራብ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል … አዎ ተገድለዋል …ማን ገደላቸው ? ሰብስቦ የወሰዳቸው አካል ….. በአከባቢው በ6 ቡድኖች የተከፋፈለ በከፍተኛ ሁኔታ የሚመራ የደህንነት እና የወታደራዊ ቁጥጥር ይደረጋል፥ …. የወያኔን ወንጀል በሌላው ላይ ለመላከክ በአከባቢው የአማጺ ቡድን አለ የተባለው ሃሰት ነው …. ከስሜን ጎንደር ዉጪ በቀሪው የሰሜን እና ምእራብ ኢትዮጵያ ምንም አይነት አማጺ ቡድን የለም .. የአባይን ግድብ ለመቆጣጠር በሚል ከፍተኛ የደህንነት እና የወታደራዊ ቅኝት ቁጥጥር በዙሪያው እስከ 200 ኪሎሜትር ድረስ እንደሚደረግ እና ይህም ቡድን በቅንጅት በ አለቃ ጸጋይ እንደሚመራ ታውቋል። ተወስደው የተገደሉት ኢትዮጵያውያን በቅርቡ ከወሎ ተቆርሶ ወደ ደቡብ ትግራይ ከተካለሉት አከባቢዎች ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል ፡፤ ስለዚህ ወያኔ የፈጸመውን ወንጀል ሌላ እንደፈጸመው ተደርጎ አይላዘን።
ሚያዚያ 15 2014 አመት ምህረት እለተ ማክሰኞ ማለዳ የወያኔ መንግስት ቢክደውም ከአስስ 97 ኪ.ሜ. ርቃ በምትገኘው ሸርቆሌ ዞን ጠይባ ወረዳ ዘጠኝ ሰዎች ሲሞት በርካቶች ቆስለውል ተዘርፈዋል፡፤ የወያኒ ሰዎች በወቅቱ ብመኪና ግልበጣ አንድ ሰው ሞተ ብለው ለማድበስበስ ሞክረዋል። በውቅቱ የሆነው ግን ከሱዳን ድንበር አቅራቢያ የታጠቁ ግለሰቦች 28 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ አስቁመው ዘጠኝ ሰውችን እንደገደሉ እና በርካታዎችን አቁስለው እና ዘርፈው እንደተሰዉር ይታወሳል።በዚህ ከፍተና ወታደራዊ ጥበቃ በሚካሄድበት የአብባ ግድብ ይገነባበታል በተባለበት አቅራቢያክልል እንዲህ አይነት ጥቃት መፈጸሙ የሚያጠያይቅ ሲሆን የንጹሃን ህይወት ሲጠፋ እያድበሰበሱ ማለፍ ድርጊቱን ማን እየፈጸመው እንደሆን ግልጽ የሚያደርግ ነው፡፡
በአከባቢው እንቀሳቀሳለሁ ለዚህ ለሚደርሱ ጉዳዮች ሃላፊነት እወስዳለሁ የሚል ቡድን የለም። መንግስት ነኝ ባዩ ወያኔም ሁኔታው በምርመር ላይ ነኝ ከማለት፡ውጪ ምንም አይነት መረጃ ለህዝብ ሲሰጥ አልታየም። ጭራሽ ተድበስብሶ እንዲያልፍ ከማድረግ ውጪ እና አደናጋሪ ቅጥረኞችን በመረጃ እንዲያሳስቱ ከማብርታታት ውጪ ፤ ይህ ተደጋግሞ አከባቢውን እያጠቃ ያለው መንግስታዊ ሽብር በመቀጠል ንጹህንን እስከ ማረድ እና እስከማድበስበስ ቀጥሏል። የገባበትን ውትረት መወጣት ያልቻለው ግዢው ፓርቲ በሃገርው ጽጥ ራሱ ብፍጠረ ሽብር ራሱ በመሸበሩ እንዲሁም በዲፕሎማሲ ተሳክቶልኛል እያለ የውጪ ጠላቶች በግልጽ እና በጀርባ ወጥረው ስለያዙት ሰላማዊ የሆኑ አከባቢዎችን በማሸበር ውጥረት ውስጥ ከቶ የሕዝቡን አትኩሮት ወደ ሌላ አቅጣጫ ለመሳብ እንዲሁም የተጀመረውን የድልድይ ግንባታ የገጠመውን የፋይናንሰ እና የዲፕሎማሲ ቀውስ ቅጥረኞቹን በማሰማራት በፈጠራ የአማጺ ቡድን ላይ ለመላክከ የተሸረበ ሴራ ነው።
No comments:
Post a Comment