ከሮበሌ አባቢያ
የአንድነት ፓርቲ ያቀረበውን እጅግ በጣም ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ፣ አይኖቼ እምባ እያቀረሩ፣ ልቤን ደስታ ፈንቅሏት ነው እኔም እንደ ሰልፈኞቹ መፈክር እያሰማሁ ከናት ሀገሬ ውጪ ከምኖርበት ከተማ በቴሌቪዥን ከመኖሪያ ቤቴ ተቀምጬ ነበር የተመለከትኩት።
እሰይ! ድል ለወጣቱ ትውልድ!!! በማለት ይህቺን መጣጥፍ ለመክተብ ተነሳሳሁ።
ከዚህ ቀደም ደጋግሜ እንደጻፍኩት ግትር ኢትዮጵያዊ ነኝ። ያ እንዳለ ሆኖ፣ አንድነት ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ የተገኙት ታዳሚዎች በኦሮሞ ተማሪዎችና በደጋፊዎቻቸው ላይ የደረሰውን ፋሺስታዊ ጭፍጨፋ አበክረው በማውገዘቸው በወገኖቼ ኢትዮጵያን ኮርቻለሁ፤ አድሮብኝ ከነበረው ጥልቅ ሀዘንም ተፅናንቻለሁ፤ ለሰብአዊ መብት ዓላማ ስኬት ለመታገል ቃልኪዳኔን አድሻለሁ።
ባለቤቴ በተወለደችበት፣ አድጋ ተምራ በተጋባንበት፣ አሁንም ዘመዶቿ በሚኖሩበት፣ እኔም አዳሪ ት/ቤት ሁለት ዓመት በተማርኩበት በአምቦ ብቻ ሳይሆን፣ የኦሮሞ ተማሪዎች በያለበት የመብት ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ በማንሳታቸው የከፈሉት መስዋዕትነት ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር የበኩላችንን ድርሻ ለማበርከት እርሷም እኔም ዝግጁ ነን። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]
No comments:
Post a Comment