በአንዳርጋቸው ጽጌ ስም ሊወጣ የታቀደውን መጽሀፍ ያዘጋጁት አቶ በረከት
ስምዖን መሆናቸው ታወቀ:: ከብአዴን ቁልፍ ባለስልጣናት የተገኘው ጥብቅ
መረጃ ላይ እንደተብራራው አቶ በረከት መጽሀፉን እንዲያዘጋጁ ከተወሰነ
በሁዋላ ከመንግስት መደበኛ ስራም ሆነ ከመድረክ ለረጅም ወራት ጠፍተዋል::
መጽሀፉ በጥንቃቄ እንዲዘጋጅ ከፍተኛ ሃላፊነት የተሰጣቸው አቶ በረከት
ከደህንነት መስሪያ ቤቱ ጋር በመሆን መረጃዎችን ሲሰበስቡ ከርመዋል::
የአቶ
አንዳርጋቸውን ግላዊ ህይወት ከማጥናት አንስቶ የቤተሰባቸውን ሁኔታ
በኤርትራ የነበራቸውን ቆይታ በአጠቃላይ የአቶ አንዳርጋቸውን የአጻጻፍ ስልት
ሳይቀር በማጥናት የሰዉን ጥርጣሬ በ�ሚያጠፋ መልኩ እያዘጋጁት
እንደሆነም የተገኘው መረጃ ያመለክታል:: የግንቦት ሰባት አመራር ውስጥ
የነበሩና ሀገር ቤት የገቡት(ቪላ ቤት ተሰጥቷቸው እየተቀለቡ ያሉት) 3
ግለሰቦች የድርጅቱን መረጃና በኤርትራ የአቶ አንዳርጋቸውን የዕለት ከዕለት
እንቅስቃሴ ምን እንደነበረ መረጃውን በዝርዝር ለአቶ በረከት እንዳቀበሉም
ይነገራል:: የመጽሀፉን ይዘት በተመለከተ በዝርዝር መረጃው የሚወጣ
ይሆናል:: አቶ አንዳርጋቸውን በተቆራረጠ ምሥልና ድምጽ መጽሀፉ የራሱ
መሆኑን ሲገልጽ የሚያሳይ ቃለመጠይቅም ሊዘጋጅ እንደታቀደም ከውስጥ
የመጣው መረጃ ያመለክታል::

No comments:
Post a Comment