ዜና ከወደ ደቡብ አፍሪካ
በትናንትናዉ እለት 02/08/2015 እሁድ ዘ ፋርም ኦፍ ሆፕ የተባለ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በደቡብ አፍሪካ ኤ. ኤን.ሲ ወይም አፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ፣ የሃዉተን አስተዳደር፣ የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አገልግሎት፣ የደቡብ አፍሪካ ሜትሮ ፖሊስ አገልግሎት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በመተባበር ባዘጋጁት የተቀደሰ ሐሳብ ላይ የመጀመሪያ ተሳታፊ በመሆን የተገኘዉ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ፡ ደቡብ አፍሪካ ላይ በድግምግሞሽ የተከሰተዉን ዜኖፌቢያ ጥቃት በመለወጥ ረገድ አጋርነቱን አሳይቷል።
የሐዉተን አስተዳደር ቺፍ ዊፒ፣ የደቡብ ሌኔዢያ የኤ.ኤን.ሲ አስተዳደር፣ የሌኒዢያ ኮሚኒቲ ፖሊስ ፎረም መሪዎች እንዲሁም የደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ታምሩ አበበ የተገኙበት ይህ ስብሰባ ዋና አላማዉ በደቡብ አፍሪካ የተወለዱ ኢትዮጵያዊያን ህጻናቶችን ደቡብ አፍሪካዊ ከሆኑ ህጻናቶች ጋር በማዋሃድ የባህል ልዉዉጥ እና መሐበራዊ ግንኙነትን የማጠንከር በተለይም በዜኖፌቢያ ጥቃት ምክንያት በአለም ዙሪያ ደቡብ አፍሪካ ላይ ያጠላዉን የስጋት ድባብ ወደ መልካም እና ሰላማዊ ገጽታ ( image ) ማሸጋገር ነበር።
በእለቱ 50 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ህጻናትን እና ወላጆቻቸዉን ይዞ ከጆሐንስበርግ ጂፒ መንገድ በሁለት ባሶች በመታገዝ ወደ ሶዌቶ ሌኔዢያ ወደ ሚገኘዉ ገጠር ( location ) የተጓዙት ኢትዮጵያዊያን በስፍራዉ ሲደርሱ የደቡብ አፍሪካ ህጻናት የማርሽ ሙዚቃ ቡድን የተቀበላቸዉ ሲሆን ኢትዮጵያዊያን ህጻናቶችም በእስክስታና በሆታ አካባቢዉን አስዉበዉታል በዝግጅቱ ወቅት የፋርም ኦፍ ሆፕ ፕሬዘዳንት ንግግር ያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ብዙዎች ሊመጡበት ወደሚፈሩት መንደራችን ልጆቻቸዉን ያለምንም ስጋት ይዘዉ በመምጣታቸዉ የዜኖፌቢያ ጥቃት በሐገራችን እንደማይኖርና ነገር ግን አስከፊዉን ጥቃት በመንተራስ ዝርፊያ የሚያካሄዱ ግለሰቦች መንሴዎች መእንደነበሩ ጠቅሰዉ በስደተኛ ወገኖች ላይ ጥቃት የፈጸሙ ወንጀለኞች ፍርድ ይጠብቃቸዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ወክለዉ የቀረቡት የኮሚኒቲዉ ዋና ጼሐፊአቶ ደረጄ በበኩላቸዉ በደቡብ አፍሪካና በኢትዮጵያዊያን ዙሪያ የለዉን መተባበርና መተሳሰብ ባጎለበተ መልኩ አብሮ የመስራቱ ሂደት ጅማሮ እንደሆነ ያሳሰቡ ሲሆን የሐዉተን አስተዳደር ቺፍ ዊፒ በበኩላቸዉ ዛሬ ለኤ. ኤን . ሲ እዚህ መድረስ እና ለደቡብ አፍሪካ ህዝብ ነጻነት መቀናጀት ኢትዮጵያ ባለዉለታ መሆንዋን ገለጸዋል።
በመሆኑም በኢትዮጵያዊያንና በደቡብ አፍሪካዊያን ልጆች የግጥምና የባህል ዉዝዋዜ ዉድድር ቀርቦ የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያዊቷ ሜላት ገበረ መስቀል አሸናፊ ሆና ተሸልማለች።
No comments:
Post a Comment