Sunday, August 16, 2015

አይነጋ መስሏት...

በየትኛውም የአለም ሃገራት ድርቅ ሊከሰት ይቻላል፡፡ ድርቅ ማለት በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ በሆነ ምክንያት የሚፈጠር የአየር ፀባይ መዛባትን ተከትሎ የሚከሰት የውሃ እጥረት ነው፡፡ 
ይህ የውሃ እጥረት በእፅዋት እና እንስሳት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እንደ ህዝቡ ነቃተ ህሊና እና እንደ መንግሥቱ አርቆ አሳቢነት ይወሰናል፡፡ ለዚህም ነው <ድርቅ ረሃብ አይደለም> የሚባለው፡፡ 
እንደ ዶሮ ከህዝብ አፍ ስር የሚለቅም መንግሥት ባለበት ሀገር ድርቅና ረሃብ አንድ ናቸው፡፡ 


እርሻ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ከበሬ ጫንቃ ያልወረደ ከዝናብ ጠባቂነት ያልተላቀቀ ከእጅ ወደ አፍ የማይደርስ ያረጀ ያፈጀ የአስተራረስ ዘይቤ የሚከተል ግብርና ባለበት ሀገረ ያለድርቅም ረሃብ ይከሰታል፡፡
ሠርቶ ለማደር በሚውተረተር ህዝብ ላይ <እንዝራት እንብላት?> ሲባል <እንብላት> የሚል በልቶ አደር መንግሥት የሥልጣን ኮርቻ ላይ ሲቆናጠጥ ረሃብ ከድርቅ ይቀድማል፡፡
ለማንኛውም የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን ለአደጋ ጊዜ የሚሆን በቂ የምግብ እህል ክምችት አለን ሲል አልነበር እንዴ?
የታለ....ወይስ...ክምችቱ ያለው በለጋሽ ሀገሮች እጅ ነው?
አይነጋ መስሏት...

No comments:

Post a Comment