በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ባለ ሃብቶች በትግራይ ክልል ኢንቨስት እንዲያደርጉ የተደረገላቸው ቅስቀሳ በክልሉ ውስጥ ያለው ስር የሰደደ ብልሹ የአስተዳደር ሁኔታመጀመሪያ ይስተካከል ማለታቸውን ተገለፀ።
በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች ያላቸውን ሃብት በትግራይ ክልል እንዲያሰማሩ ይርዳው በተባለ ከፍተኛ የህወሃት ካድሬ ነሓሴ 3/2007 ዓ/ም በተካሄደው ቅስቀሳ የተሞላበት ስብሰባ በብልሹ አሰራራችሁ የተጨማለቀውን አሰራራችሁ ካልተስተካከለ ገንዘባችንና ግዚያችንን አናባክንም ብለው እንደተቃወሙ ታወቀ።
እኛ ሃብታችን ልናሰማራ ከሆነ በመጀመሪያ ከላይ እስከታች ያለውን የክልሉ ብልሹ አካሄድ አስቁሙት፤ የፍትህና የመልካም አስተዳድር ጠንቅ የሆኑ መሪዎችን አስወግዷቸው፤ በአባልነት ሰውን መለየት አቋርጡት፤ ኃላ ቀርነትና ድህነት በማስወገድ ዴሞክራሲና ልማት ለማግኘት የታገለውን ህዝብ ልክ እንዳለፉት ስርዓቶች እየገረፋችሁት ነው። ይህ አይነት አካሄድ ሳይወገድ ትግራይ ውስጥ ሄደን የምናሰማራው ሃብት አይኖርም ማለታቸውና በወቅቱ የነበረው የመድረኩ መሪም ሃሳባቸው ከመቀበል ውጭ የሰጣቸው ማብራሪያ ሃሳብ ስላልነበረ ስብሰባው ያለ ፍሬ እንደተበተነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።
No comments:
Post a Comment