Tuesday, February 5, 2013

ኢቲቪ በኦርቶዶክስ የሃይማኖት አባቶች ላይ እንደ ሙስሊሙ ተመሳሳይ ፊልም ለማሰራጨት ዝግጅት ማጠናቀቁን ታወቀ


ጥር ፳፰ (28) ቀን ፳፻፭( 2005) ዓ/ም
በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በተመለከተ በዛሬው እለት ዶክመንተሪ ፊልም ለማሰራጨት ያስተዋወቀው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የሃይማኖት አባቶች ላይ ተመሳሳይ ፊልም ለማሰራጨት ዝግጅት ማጠናቀቁን ውስጥ አዋቂ ምንጮችን የጠቀሱ ዘገባዎች አመልክተዋል፤ቤተ ክህነት ለፊልሙ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጓ የተገለፀ ሲሆን ፤የሃይማኖት አባቶችም በሂደቱ ተዋናይ መሆናቸው ተመልክቶአል።

ኢትዮጵያዊ ውስጥ እውነት ማለት ወረት ማለት ነው እንዴ?


ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም "መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ" የሚል መጽሐፍ ጽፈዋል። በገጽ194 ላይ ደግሞ ስለ "ኢትዮጵያዊ እውነት" እንዲህ ይላሉ፦
"ዞሮ ዞሮ ኅብረተሰቡን ያጫጨው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምን አግኝቶ ለኑሮው እንዳያስብ፣ ኑሮውን እንዳያጣጥም፣ ሠርቶ ኑሮውን እንዳያዳብር፣ ሀብት አካብቶ ከችጋር እንዳይላቀቅ አስሮ የያዘው የአስተዳደር ማነቆ ነው። ይህ የአስተዳደር ማነቆ ከፈጠራቸው ክፍ ክፉ ጠንቆች አንዱ የሕግ እና የሥነ ሥርዓት አለመኖር ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ጉልበት ሥልጣን ነው። ጉልበት መብት ነው፤ ጉልበት ሕግ ነው፤ ጉልበት ሥነ ሥርዐት ነው። የገዢዎች መብት ያልተወሰነ ነው። የገዢዎችም ግዴታ ያልተወሰነ ነው።

ኢፍዴኃግ ከምርጫው እወጣለሁ ሲል ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ



የአራት ፓርቲዎች ግንባር የሆነውና ከገዢው ፓርቲ ጋር በፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ፍትህ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር (ኢፍዴኀግ) በምርጫው ያቀረብኩት ዕጩ ታስሮብኛል ሲል ቅሬታውን በመግለፅ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በምርጫው ለመቀጠል አስገዳጅ ሁኔታ ተፈጥሯል ሲል ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ። 

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በአሜሪካ በሚገኙ አባቶች ሲኖዶስ ላይም ሊዘምት ነው



ሐራ ዘተዋሕዶ

  • አራተኛውን ፓትርያሪክ ጨምሮ ሦስት አባቶች ተተኩሮባቸዋል
  • ጠ/ቤ/ክህነቱ ለዶክመንተሪው ስርጭት ከብር መቶ ሺሕ ብር በላይ መክፈሉ ተነግሯል
የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት በሰሜን አሜሪካ በስደት በሚገኙ አባቶች ላይ ያነጣጠረ ዶኩመንተሪ ለማቅረብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተሰማ፡፡

Letest Ethiopian Orthodox Church‹‹የነውጥን ጎዳና የመረጡ የሩቅ አገር ናፋቂዎች›› በሚል ርእስ መቀናበሩ የተነገረለት ይኸው ዶኩመንተሪ÷ በዋናነት፣ በአራተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ እና አቡነ መቃርዮስ ላይ የሚያተኩር ነው ተብሏል፡፡

ዝግጅቱ ለአንድ ሰዓት ከ30 ደቂቃ የሚዘልቅ ሲሆን በሁለት ተከታታይ ክፍል እንደሚቀርብ ተገልጧል፡፡ የዝግጅቱ ዓላማ/ፋይዳ÷ በውጭ በስደት የሚገኙ አባቶችን ‹‹የኋላ ማንነት እና የወቅቱን አቋም ማጋለጥ››፣ በዚህም ቀጣይ አካሄዶቻቸውን ‹‹ተቀባይነት ማሳጣት›› እንደኾነ ተመልክቷል፡፡

Monday, February 4, 2013

ፍትሕ ያስተፌሥሕ ልበ - ሰብ ( ፍትህና መልካም አስተዳደር )


መልካም አስተዳደር ያስተፌሥሕ ልበ - ሰብ፡፡ ፍትሕ ያስተፌሥሕ ልበ - ሰብ፡፡ ፍትሕ ያስተፌሥሕ አዕምሮ - ሰብ፡፡
ፍትሕ ያስተፌሥሕ አንጀተ - ሰብ፡፡ ፍትሕ ያስተፌሥሕ ሕይወተ - ሰብ፡፡ ፍትሕ ያስተፌሥሕ ኅብረተ - ሰብ፡፡ ፍትሕ ያስተፌሥሕ ሕዝብ፡፡
ፍትሕና መልካም አስተዳደር ለኅብረተሰቡም ሆነ ለግለሰብ የሚፈጥረው ደስታና እርካታ ከተራ የመልበስ፣ የመጉረስ፣ የመጎንጨት ደስታና እርካታ በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ ሰው በሰው ልጅነቱ፣ ሰው በዜግነቱ እንዲኮራ የሚያደርግና ይበልጥ አገሩንና ወገኑን እንዲያገለግል የሚያስችለው እርካታ ነው፡፡ ጊዜያዊ እርካታ ሳይሆን ዘላቂ፡፡
በዚህም ምክንያት ነው ደግመን ደጋግመን ልዩ ትኩረት ለመልካም አስተዳደርና ለፍትሕ ይሰጥ የምንለው፡፡ ደግመን ደጋግመን ፍትሕንና መልካም አስተዳደርን እውን የሚያደርጉ የሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች ተግባር ላይ ይዋሉ የምንለው፡፡ ለዚህም ነው ደግመን ደጋግመን የሕዝብን መልካም አስተዳደርና ፍትሕ የሚረግጡ፣ የሚሸጡ፣ የሚለውጡ ተጠያቂ ይሁኑ፣ ለፍርድ ይቅረቡ የምንለው፡፡
የውኃ ጥም የሚረካው ውኃ ፍሪጅ ውስጥ ስለተቀመጠ አይደለም፡፡ ሱቅ ውስጥም ስለተደረደረ አይደለም፡፡ ምንጮች ውኃ ስላላቸው አይደለም፡፡ የውኃ ማስታወቂያዎች ስለተሰሙ፣ ስለተነበቡና ስለታዩ አይደለም፡፡ በተጨባጭ የተጠማው ሰው ማግኘትና መጠጣት ሲችል ነው፡፡ 

ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር የሞከረው የህወሃት ጀሌ ተጋለጠ


(አዲስ ቮይስ) በጋዜጠኛ አበበ ገላው እና በቤተሰቡ ላይ  ህገወጥ በሆነ መንገድ  በተከታታይ ስልክ በመደወል ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር  የሞከረው ግለሰብ ማንነት ተጋለጠ።
ጋዜጠኛ አበበ ገላው የግለሰቡን ማንነት ለማጣራት ለበርካታ ሳምንታት ጥንቃቄ የተሞላበት ክትትልና ምርመራ መደረጉን  እና ድምጹም  ልምድ ባላቸው የፎረንሲክ ኤክስፐርቶች የተመረመረ መሆኑን ገልጾ በዚሁ መሰረት ይህን ህገወጥ የሆነ ድርጊት ሲፈጽም የነበረው ግለሰብ ሙሉጌታ ካህሳይ የተባለ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ጀሌ መሆኑእንደተደረሰበት  ገልጿል።
ግለሰቡ በተለይ በአለፈው ወር ላይ ወደ ኢሳት ሬድዮ የአድማጮች መልእክት መቀበያ በመደወል በተለይ ለጋዜጠኛው በተወው መልእክት ደምህን እንጠጣለን እንዲሁምቤተሰቦችህን እንፈጃለን፣ በአዲስ አበባ ያለህን ቤት እናቃጥላለን የሚሉ ሁለት ተከታታይ መልእክቶችን አስቀምጦ እንደነበር ታውቋል።
አበበ ገላው “ምንም እንኳን የሚቃጠል ቤት እና ንብርት ባይኖረኝም ከእኔ ስላማዊ የትግል እንቅስቃሴ  እና የጋዜጠኝነት  ስራ ጋር በተያያዘ ምንም በማይመለከታቸውን ደካማ ዜጎች ላይ ወንጀል ለመፈጸም መዛት የህወሃቶችን  አስነዋሪ ድርጊት ብቻ ሳይሆን የሞራል ዝቅጠት የሚያሳይ ድርጊት ነው ፣” ሲል ድርጊቱን አጥብቆ አውግዟል።

TPLF and the Culture of Violence


According to ESAT the FBI has foiled an attempt by the Ethiopian government to assassinate Ato Abebe Gelaw. GooshAccording to ESAT the FBI has foiled an attempt by the Ethiopian government to assassinate Ato Abebe Gellaw. Abera and his accomplices are under custody. Please note here I said the Ethiopian government since there seems to be no thin line between the TPLF party and the government. Why am I not surprised? I am not surprised because for the TPLF violence is sanctioned by the party leaders as a legitimate tool to achieve political, economic and military dominance.