ጽንፈኝነት ኢትዮጵያ ከምትታወቅባቸው ከፍተኛ የሞራልና የሥነ ምግባር እሴቶች መርህ ጋር በእጅጉ የተራራቀና የላሸቀ መንፈስ መገለጫ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን፣ በፍቅር አብሮ መኖርና መተሳሰብን የሚንድ የዝቅጠት ማሳያ ነው፡፡
ጽንፈኝነትን የሚያራምዱ ኃይሎች ደግሞ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ የሚታወቀውን የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆነውን አገር ወዳድነት የሚፃረሩ ናቸው፡፡ ኩሩውና ጀግናው ሕዝባችን ለጽንፈኝነት ቦታ ባይሰጥም፣ የዚህ አስከፊ ድርጊት አራማጆች ግን በየጊዜው ብቅ ጥልቅ ሲሉ ይታያሉ በህወሃትና ጀሌዎቻቸው፡፡ የአገርን ክብር ለማዋረድ ላይ ታች ይላሉ፡፡
አገሩን ከራሱ በላይ አስበልጦ የሚወድ ማንም ኢትዮጵያዊ የገዛ አገሩን ለማዋረድ የሚቅበዘበዙ ኃይሎችን አይታገስም ለዚህም ነው ዛሬ ብዙ ታጋዮች መስዋትነት እየከፈሉ ያሉት፡፡ የፓን አፍሪካኒዝም ርዕዮተ ዓለም መሠረት የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ ከጠባብ መንደርተኝነት አስተሳሰብ እስከ አክራሪነት ድረስ ያሉትን ሞራል አልባ ተግባራት ህዝብ አይታገስም፡፡
ኢትዮጵያችን ከ90 ሚሊዮን በላይ እንደሚሆን የሚገመተው ሕዝባችን የጋራ ቤት ስትሆን፣ የአፍሪካውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንም እናት ናት፡፡አገሩን ከራሱ በላይ አስበልጦ የሚወድ ማንም ኢትዮጵያዊ የገዛ አገሩን ለማዋረድ የሚቅበዘበዙ ኃይሎችን አይታገስም ለዚህም ነው ዛሬ ብዙ ታጋዮች መስዋትነት እየከፈሉ ያሉት፡፡ የፓን አፍሪካኒዝም ርዕዮተ ዓለም መሠረት የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ ከጠባብ መንደርተኝነት አስተሳሰብ እስከ አክራሪነት ድረስ ያሉትን ሞራል አልባ ተግባራት ህዝብ አይታገስም፡፡
በኢትዮጵያ ምድር ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ባሉ ግዛቶች ውስጥ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦቻችን የእዚህች እናት አገር ውድ ልጆች ናቸው፡፡ አንዳቸው ካንዳቸው አይበልጡም ወይም አያንሱም፡፡ ይህም በመሆኑ የባህል፣ የሃይማኖት፣ የቋንቋ፣ የዘር፣ የፆታ፣ የፖለቲካ አመለካከት፣ ወዘተ ልዩነት ቢኖር እንኳ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን ናት፡፡ አገራችን የጋራ መኖሪያችን ናት፡፡ ስለዚህ ልትከበር ይገባታል፡፡ ሊያዋርዱዋት የሚፍጨረጨሩ ካሉ ሊወገዙ ይገባል፡፡ በአገር ቀልድ የለም፡፡ በኢትዮጵያዊነት ቀልድ የለም፡፡
በህውሃት በተለያዩ ጨቋኝ ገዥዎች መዳፍ ሥር በድህነት እየማቀቀ ሲኖር ያለው ሕዝባችን መቼም ቢሆን እርስ በርሱ ተጋጭቶ አያውቅም፡፡ ይልቁንም በታሪካችን የተመዘገቡ የውጭ ወራሪዎችን በአንድነት ቆሞ ሲመክት ኖሯል፡፡ በፀረ ኮሎኒያሊስት ትግል በዓለም ዙሪያ የናኘ ታላቅ ስም አለው፡፡ የዓለም ጥቁር ሕዝቦች አርዓያ ነው፡፡ ዘር፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ፣ ባህልና የተለያዩ አመለካከቶች ሳይለያዩት በገዛ አገሩ ጉዳይ በባለቤትነት ስሜት አብሮ ኖሯል፡፡ አሁንም እየኖረ ነው፡፡ ነገር ግን ትልቁን ብሔራዊ ጉዳይ ወደ ጐን እየገፉ አገርን የሚያዋርድ ተግባር ውስጥ የሚዘፈቁ ወገኖች እየታዩ ነው፡፡ ለጠባብ የፖለቲካ ዓላማ የአገርን ስምና ክብር የሚያዋርዱ እነዚህ ወገኖች በጭፍንነት እየተመሩ ኢትዮጵያችንን ጥላሸት እየቀቡ ናቸው፡፡ በተስፋ መቁረጥ ይሁን ወይም በጠላት በመገዛት የኢትዮጵያን ገጽታ አፈር ለማልበስ ይርመሰመሳሉ፡፡ እነዚህ ጽንፈኞች በቃችሁ መባል አለባቸው፡፡ የአገሩ ጉዳይ የሚያገባው ኢትዮጵያዊ ጽንፈኞቹን ማጋለጥ፣መታገል ይኖርበታል፡፡ የፖለቲካ ልዩነት ሌላ፣ የአገር ጉዳይ ሌላ፡፡
ይህ ዘመን ወደድንም ጠላንም ጥላቻን የምናወግዝበት ዘመን ነው። የሕዝብ ድምፅ ወሳኝ የሚሆነው ዲሞክራሲ በተሟላ ሁኔታ ሲሰፍን ነው፡፡ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ዋነኛ ፀር አምባገነንነትና ጽንፈኝነት ናቸው፡፡ እነዚህን አሉታዊ ተግባሮች የሚያራምዱ የህውሃት ወገኖች ጠባቸው ከማንም ጋር ሳይሆን ከባለ ድምፁ ሕዝብ ጋር ነው፡፡ በዚህ ዘመን የሕዝብን ወሳኝነት አለማመንና ጭልጥ ብሎ ወደ ሕገወጥነት መንጐድ የትም አያደርስም፡፡ ማንም የፈለገውን የመደገፍ ወይም የመቃወም፣ የመምረጥ ወይም ያለመምረጥ መብት አለው፡፡ ይህ መብት ደግሞ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ በሕግም ዋስትና ያገኘ ነው፡፡ መብቴ ተጓድሏል የሚል ሕግና ሥርዓቱን ተከትሎ እስከመጨረሻው ድረስ በመጓዝ መብቱን የማስከበር ኃላፊነት የራሱ የህዝብ ብቻ ነው፡፡
ህውሃትና ጀሌዎቹ ከሕጋዊው መንገድ ይልቅ ሕገወጥነትን የሚመርጡ የአካሄዳቸው ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል ጠንቅቀው ካላወቁ መዘዙ ብዙ ነው፡፡ በተለይ አገርንና ሕዝብን አንገት የሚያስደፉ ተግባራት መፈጸም በሕግም በታሪክም ያስጠይቃል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት አለ ይሉናል በምንም መልኩ ሲተገበር አላየንም፡፡ በዚህ ሥርዓት መሠረትም አገር የሚመራ መንግሥት አለ ይሉናል ሲመራ ሳይሆን ሲያበጣብጥ ነው የምናየው ታዲያ ይህንን መንግሥት አለመፈለግ ወይም መጥላት መብት ነው፡፡ ከዚያም አልፎ ተርፎ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ህዝብ ድምፁን ለሚፈልገው ሰቶ ሲያሸንፍ አላሸነፍክም ብሎ በጉልበት መርገጥ ምን እንበለው ታዲያ፡፡ ከዚያ ውጪ በሥርዓት አልበኝነት ተነስቶ ህውሃት ትርምስ ለመፍጠር መሞከር ተቀባይነት የለውም፡፡ በሕገወጥ መንገድ ህውሃት የህዝብን ድምጽ መለወጥም አይችልም፡፡ የአገሩ ጉዳይ የሚያገባው ማንም ዜጋ ሆነ ፖለቲከኛ የፈለገውን ያህል አስቸጋሪና ውስብስብ ቢሆንም፣ የፖለቲካ ትግል ተፈላጊውን መስዋዕትነት በመክፈል የሕዝብን ይሁንታ ለማግኘት የተቻላቸውን መሥራት አለባቸው፡፡
ጽንፈኝነት የአንድን ሕዝብ የጋራ የሞራል እሴቶችን በመሸርሸር በሕዝብ ውስጥ ሽብር የሚነዛ አስተሳሰብ ነው፡፡ይህን አድራጊው ህውሃትና ጀሌዎቹ ናቸው።ይህ ደግሞ አምባገነንነት ነው፡፡ አጉራ ዘለልነት ነው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት እስካልን ድረስ ባለቤትነታችንን ማስመስከር ይኖርብናል፡፡ የሕዝብ አመኔታና ተቀባይነትን ማግኘት ያልቻለ መንግስት ሊወርድ የግድ ይላል፡፡ለዚህ ደግሞ ድመት አይጥ እንዲይዝ ተብሎ ችቦ አይበራለትም። የኢትዮጵያዊያንን ጀግናና ኩሩ ሕዝብ ታሪካዊ የጋራ እሴቶች እየናዱ ስለዲሞክራሲም ሆነ ስለሰብዓዊ መብት መናገር አይቻልም፡፡ አገሩን የሚወድ ማንም ዜጋ በአገሩ ውስጥ ሆኖ በማንኛውም ዓይነት ፈተና እየተፈተነ ሕዝባዊነቱን ማስመስከር አለበት፡፡ ፈተናው የፈለገውን ያህል ቢከብድ፣ መንገዱ ምንም ያህል ቢረዝም የአገር ፍቅርና ቀናዒነት ያለው ዜጋ አይታክትም፡፡
የእናት አገራችን ገጽታ እየተለወጠ፣ ክብሯና ዝናዋ እንዲመነደግ የሚፈልጉ ልጆቿ በሙሉ ራሳቸውን ከህውሃት ጽንፈኝነትና ከዘቀጠ አስተሳሰብ ሊያርቁ ይገባል፡፡ህዝቡ የህውሃት ቡድን ጥቅምንና የአገር ጥቅምን መለየት አለበት፡፡ ህውሃትና ጀሌዎቹ ‹‹የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው›› የሚለው ዕርባና ቢስ መፈክር ጠቃሚ አለመሆኑን ሊረዱት ይገባል፡፡ ፡፡ ከአገራችን የበለጠ ምንም ነገር የለምና።
ከሰብኣዊ
Goodd day! Do you use Twitter? I'd like to follow you
ReplyDeleteif that would be ok. I'm absolutely enjoying your blog and look forward to new updates.
umpan tikus