ካድሬዎቹ በባህር ዳር የተደረገውን ግድያ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመ ነው ሲሉ ተናግረዋል::
- ባለፈው አርብ በባህር ዳር ሰላማዊ የሆነ ጥያቄ ይዘው አደባባይ በወጡት ንጹሃን ዜጎች ዙሪያ እና በመጭው ምርጫ ዙሪያ በአዲስ አበባ ብአዴን ካድሬዎቹን በመሰብሰብ ያደረገው ውይይት ክለመስማማት መበተኑን ለምንሊክ ሳልሳዊ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል::
- ባለፈው አርብ በባህር ዳር ሰላማዊ የሆነ ጥያቄ ይዘው አደባባይ በወጡት ንጹሃን ዜጎች ዙሪያ እና በመጭው ምርጫ ዙሪያ በአዲስ አበባ ብአዴን ካድሬዎቹን በመሰብሰብ ያደረገው ውይይት ክለመስማማት መበተኑን ለምንሊክ ሳልሳዊ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል::
እንደ ምንጮቹ ዘገባ ከሆነ ካድሬዎቹ ሕዝብን ማሳመን የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል::ንጹሃን በአደባባይ መግደል የፖለቲካ ትርፉ ምንድነው የሚሉ እና በባህር ዳር የተደረገው ድርጊት በመጭው ምርጫ ላይ ከባድ ተጽእኖ ያጠላበታል ሲሉ አስተያየታቸን እና ጥያቄዎቻቸውን ሰንዝረዋል::
ይህንን ድርጊት ፖሊሶቹ እንዲፈጽሙ ለምን ከፌዴራሉ ትእዛዝ መቀበል አስፈለገ? የክልሉ መንግስት የተደረገውን ሰልፍ በሰላም ለመበተን ያደረገው ጥረት ምንድነው ማብራሪያ እንፈልጋለን ሲሉ ካድሬዎቹ ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ ለውይይት የተጠራው ስብሰባ ወደ ጫጫታ ተለውጧል::ካድሬዎቹ እንደሚሉት ማንኛውንም ጥያቄ በሃይል እየደፈጠጥን በምርጫው ወቅት ስንሸነፍ ሽንፈታችንን ተከትሎ በህዝብ ላይ ላለመተኮሳችን ማረጋገጫው ምንድነው ይህ ከባድ አደጋ ስለሆነ ባህር ዳር ላይ ለተፈጸመው ግድያ እና ድብደባ የክልሉ መንግስት እና መሪ ድርጅቱ ኢሕአዴግ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው::ሌሎች አስፈላጊውን ሮሮ ሳያሰሙ ለጉዳተኞች ካሳ ሊከፈል ይገባል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::
የካድሬዎቹ ውይይት ከመጭው ምርጫ ላይ ያላቸውን ስጋት እና በህዝብ ላይ ይደርሳል ያሉትን ጥፋት በመናገር ያላቸውን ስጋት የገለጹ ሲሆን እንደ አባልነታቸው ደህንነታቸው ላይ ያለውን ጉዳይ በተመለከተም ጥያቄ አንስተዋል:: ለ 6 ሰአታት ያህል የዘለቀው ስብሰባ በስተመጨረሻ በምክክር ተጨማሪ ስብሰባዎች ይኖሩናል በሚል ካለመስማማት በጫጫታ መበተኑን ምንጮቹ ለምንሊክሳልሳዊ ገልጸዋል::
No comments:
Post a Comment