ጋዜጣዊ መግለጫ
ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ-የኢትዮጵያ ጉዳይ በፍትሕ ለሚያምኑ ድርጅቶችና ሰዎች በሙሉ መልካም ምኞቱን እየገለጸ በቫቲካን ድጋፍ በመርዝ ጋዝ ጭምር በመጠቀም ኢትዮጵያ ላይ ስለ ተፈጸመወ የፋሺሽት የጦር ወንጀል የሰው እልቂትና እጅግ ከፍ ያለ ውድመት የካቲት 12-14 ቀኖች 2007 ዓ/ም ወይም በዚያን ሰሞን በየሐገሩና በየከተማው የመታሰቢያ ክብረ በዓል በማዘጋጀት እንዲዘክሩት ግብዣውን በትሕትና ያቀርባል።
እንደሚታወቀው፤ ፋሺሽት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረችበት በ1928-34 ዘመን አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከመጨፍጨፋቸው በላይ 2,000 ቤተ ክርስቲያኖችና 525,000 ቤቶች ወድመዋል። እንዲሁም በሚሊዮን የሚቆጠሩ እንስሳት አልቀዋል። በተለይ፤ በየካቲት 12-14 ቀኖች 1929 ዓ/ም ፋሺሽቶች አዲስ አበባ ከተማ 30000 ኢትዮጵያውያንን እንደ ጨፈጨፉ የታወቀ ነው። ስለዚህ ማሕበራችን በሚያከናውነው ዓለም አቀፍ ዘመቻ:
(ሀ) ኢጣልያ ተገቢውን ካሣ ለኢትዮጵያ እንድትከፍል፤
(ለ) ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤
(ሐ) ኢጣልያና ቫቲካን ከኢትዮጵያ የተዘረፉትን ንብረቶች እንዲመልሱ፤
(መ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢጣልያኖች በኢትዮጵያ ላይ የፈጸሙትን ወንጀል እንድትመዘግብ፤ እና
በዚህም ዓመት በየካቲት 12 ሰሞን እንዲከናወን የሚጠበቀው የመታሰቢያ ክብረ በዓል ቀን፤ በጸሎት፤ በጉባኤ/በስብሰባ፤ እና/ወይም በሰላማዊ ሰልፍ እንዲሆን ይጠበቃል። ማሕበሩ፤ በዚያን ጊዜ የሚሰራጭ የአቤቱታ ደብዳቤዎች ያዘጋጃል።
ማሕበሩ ከፍ ካለ ምሥጋና ጋር የሚያስታውሰው፤ ባለፈው ዓመት የካቲት 12 የመታሰቢይ ቀን የተከበረው በ30 ከተሞች ሲሆን እነርሱም አዲስ አበባ፤ ዋሺንግተን ዲ.ሲ.፤ ኒው ዮርክ፤ ዳላስ፤ ሒዩስተን፤ አትላንታ፤ ሚኒያፖሊስ፤ ሲያትል፤ ሎዛንጀለስ፤ ዴንቨር፤ አውሮራ፤ ቺካጎ፤ ቦስተን፤ ታምፓ፤ ላስቬጋስ፤ ማያሚ፤ ኮሎኝ፤ ሙኒክ፤ ስቶክሆልም፤ ሮም፤ ኢየሩሳሌም፤ ቴልአቪቭ አምስተርዳም፤ ዘሔግ፤ ጃሜይካ፤ ሲድኒ፤ ቫንኩቨር፤ ጆሐንስበርግ፤ ዱባይ፤ እና ለንደን ነበሩ። በዚህ ዓመትም በነዚህና በሌሎች ከተሞች በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ክብረ በዓሉ በሞቀ ሁኔታ እንደሚከበር ይታመናል።
ለተጨማሪ መረጃ ከላይ የተጠቀሰውን ድረ-ገጽ መመልከት ይቻላል።
ቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ፤ ለሐገራችን የሚያስፈልገውን ፍትሕ እንድናስገኝ ያበርታን።
PRESS RELEASE
The Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause (GAJEC) presents its compliments to all institutions, and people who believe in justice and calls on them to join and participate in the international event for the commemoration, during or around February 19-21, 2015, of the Ethiopian martyrs, victims of the Italian Fascist war crimes in Ethiopia, with the complicit support of the Vatican, as well as the vast destruction that was inflicted using various war materials including the forbidden mustard poison gas.
It is recalled that during the 1935-41 Italian Fascist occupation of Ethiopia, one million Ethiopians were massacred, 525,000 homes and 2,000 churches as well as millions of animals were destroyed. Therefore, GAJEC has been conducting a global campaign for:
(a) adequate reparations by Italy to Ethiopia;
(b) a Vatican apology to Ethiopia;
(c) restitution of looted Ethiopian properties by Italy and the Vatican;
(d) UN recognition of the Italian war crimes in Ethiopia; and
(e) dismantlement of the mausoleum recently established at Affile, Italy for the Fascist war criminal, Rodolfo Graziani.
The February, 2015 commemoration event is expected to be conducted in the form of public demonstrations at the Italian/Vatican embassies/consulates to which GAJEC’s formal letters of appeal would be submitted, meetings/conferences/symposia, and/or prayers.
GAJEC recalls with appreciation all those supporters of justice who arranged the commemoration event in February, 2014 at Addis Ababa; Washington, DC; New York; Dallas; Houston; Atlanta; Minneapolis; Seattle; Los Angeles; Denver; Aurora; Chicago; Boston; Tampa; Las Vegas; Miami; Cologne; Munich; Stockholm; Rome; Jerusalem; Tel Aviv; Amsterdam; The Hague; Jamaica; Sidney; Vancouver; Johannesburg; Dubai; and London. It is greatly hoped that supporters of justice against Fascist war crimes in Ethiopia in these and other cities throughout the world would arrange the event during February, 2015.
____________________________________________________________________________________
Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause:
www.globalallianceforethiopia.org; info@globalallianceforethiopia.com
4002 Blacksmith Drive, Garland, TX 75044; Phone: (214)703 9022
____________________________________________________________________________________
Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause:
www.globalallianceforethiopia.org; info@globalallianceforethiopia.com
4002 Blacksmith Drive, Garland, TX 75044; Phone: (214)703 9022
No comments:
Post a Comment