በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
ዘደብረጊዮርጊስ
ቤተክርስቲያንን ትጠብቋት ዘንድ የተሾማችሁ ሆይ፤ ለቤተክርስቲያን ከእኛ ወዲያ ላሳር ያላችሁ ማኅበረ ቅዱሳን ሆይ፤ ውስጥ ገብተን እንታገላለን ያላችሁ ሰላምና አንድነት አደፍራሾች ሆይ ወዴት አላችሁ ???
ሰሞኑን በባሕር ዳር ከተማ የቤተክርስቲያን ታላላቅ በአላት ከሆኑትና ኃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነት ባሕልም የሚገለጽበትን የጥምቀት በአል የሚከበረበትን ቦታ ለልማት ይፈለጋል በሚል በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ እጅጉን አሳዝኖናል አስቆጭቶናል።
ቤተክርስቲያንን ለማዳከምና ለማጥፋት የተነሳው በስልጣን ላይ ያለው ኃይል በልማት ስም በተደጋጋሚ የቤተክርስቲያንን መብትና ይዞታ ሲደፍር ሁሌም የሚገርመኝ አባቶች ተብለው ቤተክርስቲያንን እንዲጠብቁ የተሾሙት ሰዎች ዝምታ ነው። እነኝህ አባቶች በዛ ደረጃና ሥልጣን የሚሾሙት ቅዳሴ እንዲቀድሱ እና ስብከት እየተዘዋወሩ እንዲሰብኩ አይደለም። ለዛ አገልግሎት የቅስና ማዕረ ብቻ ይበቃዋል።

አባቶች ከሁሉ በላይ ባሉበት ደረጃ በቤተክርስቲያን የሚሾሙት ሥልጣነ ክህነት ከመስጠት ባለፈና ለቤተክርስቲያን ዘመኑን እየዋጁ የተለያዩ ውሳኔዎችን ከመስጠት በዘለለ ዋናው ኃላፊነታቸው ቤተክርስቲያንን፣ ሐብቷን እና ንብረቷን እንዲሁም የምእመኖቿን ደህንነት እንዲጠብቁና እንዲያስጠብቁ ነው።
በቤተክርስቲያን ላይ ለሚደርሰ የመብት መጣስም ሆነ በምእመኖቿ ላይ ለሚደርሰ ግፍ በመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂ የሚሆኑት ይጠብቋት ዘንድ የተሾሙት አባቶች ናቸው። እንዲህ ተብሎ በአርድእቱ ቅዱስ ሉቃስ የእግዚአብሔር ቃል እንደተጻፈ፦
“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ
እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ “ ሐዋ.፳፥፳፷
ነገር ግን በዚህ ዘመን አባት አለን ብሎ ለመናገር የማንደፍርበት ደረጃ ላይ መሆናችን እጅግ ያሳዝናል።
“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ
እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ “ ሐዋ.፳፥፳፷
ነገር ግን በዚህ ዘመን አባት አለን ብሎ ለመናገር የማንደፍርበት ደረጃ ላይ መሆናችን እጅግ ያሳዝናል።
ካልጠፋ ቦታ ሁል ጊዜ የቤተክርስቲያን የሆነውን ይዞታ ለማጥፋት እየተደረገ ያለውን ታላቅ ሴራ እንዴት ሁሌም ዝም በማለት ይታለፋል ???
በርግጥ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው ኃይል እየፈጸመ ያለው ሁሉ በአጋጣሚ ሳይሆን ወይንም ይህን ያህል ለልማትና ለህዝብ እድገት ተጨንቆ ሳይሆን የራሱ የድርጅቱ የቀድሞ መሪ የነበሩት ዶ/ር አረጋዊ በርሔ በመጽሐፋቸው ውስጥ ያጋለጡት ቤተክርስቲያንን የማጥፋት ታላቅ ሴራ አካል ለመሆኑ ብዙም የሚያጠራጥር አይደለም። ዶክተር አረጋዊ ይህንን የጥፋት እቅድ እንዲህ ሲሉ ነው በመጸሐፋቸው የገለጹት፦
“ ኅወሐት የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በማኅበረሰቡ ሕይወት ውስጥ ያላትን ሚና፣ ለአገር አንድነት ያላትን ድጋፍ፣ በመሬት የመንግስት ይዞታነት ላይ፣ በሶሻሊዝም ሥርአትና በመገንጠል ላይ ያላትን አቋም ጠንቅቆ ስለሚያውቅት፤ ለእርሱ ፖሊሲዎች እንቅፋት እንደምትሆንበት በሚገባ ያውቃል። ስልሆነም ቤተክርስቲያንን የራሱ አይዲዎለጂ ጥገኛና ሚና አልባ ለማድረግ ተከታታይ ርምጃዎችን ወስዷል።

ከነዚህም ርምጃዎች የመጀመሪያው በደርግ ሥርዓት ተስፋ የቆርጡትንና በትግራይ ይንቀሳቀሱ የነበሩትን እንደነ ኢዲዩ ያሉትን ብሔራዊ ድርጅቶች ለመያዝ እ.ኤ.አ በ1979 ዓ.ም ከተመረጡ አጥቢያ ቤ/ክ ለተዉጣጡ ካህናት ሰሚናር እንዲሰጥ ተደረገ። የዚህ ሰሚናር ድብቅ አላማ ግን የትግራይን ቤተክርስቲያን ከተቀረው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በመገንጠል የሕወሀት ፖሊሲንና የትግራይን ብሔርተኝነት ለማስረጽ የተደረገ ነው። ይኽንንም ለማስፈጸም በአቶ ስብሐት ነጋ የሚመራ ሥውር የስለላ ቡድን ተቃቁሞ የቤተክርስቲያኗን አመራር ከድርጅቱ ፍላጎት አንጻር እንዲቆጣጠሩ ሰዎች ተመልምለው እንደ ደብረ ዳሞት በመሳሰሉ ገዳማት መነኮሳት መስለው እንዲገቡ ተደረገ።
በ1987 እና በ1989 ዓ.ም በወረዳና በክልል ደረጃ ለካህናት ጉባኤያት በማዘጋጀት የትግራይ ክልል ቤተክህነት ከማእከላዊው አስተዳደር እንዲለይ በማድረግ በ1990ዓ.ም በትግራይ ውስጥ ሁለት የቤተክህነት ጽ/ቤቶች እንዲፈጠሩ ተደረገ።
ከማእክላዊው አስትዳደር የተመደው ጽ/ቤት ወደ ደሴ በመዛወር እንዲሁም የሕወሀት ተወካይ የሆነው ደግሞ በመቀሌ ሆኖ ሕወሀት ማእከላዊውን መንግስት እስከተቆጣጠረበት 1991 ዓ.ም ድረስ ሁለቱም ሲሰሩ ነበር። በማለት ዶ/ር አረጋዊ በርሔ የቀድሞ ይሕወሀት ሊቀመንበር በቤተክርስቲያናችን ላይ የታቀድውን ታላቅ ሴራ አጋልጠዋል ”
Aregawi Berhe political History of the TPLF pp244-246
በእንግሊዝኛ የጻፉት የዚህ መጽሐፍ ክፍል እንዲህ ይነበባል።
በእንግሊዝኛ የጻፉት የዚህ መጽሐፍ ክፍል እንዲህ ይነበባል።
“ The pragmatic TPLF understood the church’s role in village social life and its support for the unity of the country. It also understood against socialism and nationalization of the land as well as against separatism. The church was viewed as a force standing in the way of TPLF but one should although its Marxist ideology called for that. Nevertheless there was no doubt that to subordinate the church to its cause. The TPLF therefore took a series of coordinated steps to neutralize the church’s influence… The first was to uphold the Dergue’s measure of power and frustrated hopes of resurgence among the rightist multi national movement in Tigrai, such as the EDU. …….the TPLF launched a series of conferences or seminars’ for selected parish priests in 1979 to win them over. The underlying motive of the seminars was to isolate the church in Tigrai from the wider Ethiopian church in order to foster Tigrian nationalism along the lines of the TPLF’s strategy objective. Suppressed Tigraian nationalism was invoked to challenge the dominant Ethiopian Orthodox Church. The initial woreda seminars for priests were conducted by an eloquent TPLF fighter, Gebre- Kidan Desta, a graduate of the Theological College of Addis Ababa University. The themes of the seminars were to replace the Ethiopian church’s authority by a TPLF-minded church and the language in the church with Tigrigna and ultimately, to further Tigraian nationalism and identity. This process involved the mobilization of parish priests and ordinary Christians to isolate them from the church’s national hierarchy. To weaken church authority, an intelligence group was formed under Sibhat Nega to infiltrate the well-established monasteries in Tigray, such as Debre Damo, by planting TPLF members camouflaged as monks and influencing church activities in the interest of the TPLF. In 1987 and 1989, regional and national conferences for priests were organized by the TPLF in liberated territories to reshape the Tigray Church in line with the TPLF’s program. A separate secretariat of the Orthodox Church as formed in the liberated areas of Tigray and was supposed to operate under TPLF guidelines. Particularly, the Ethiopian church was divided in two separate secretariats, one under the regime and the other under the TPLF. Both worked in Tigrai 1990, when the TPLF overran meqele, the capital of Tigray. The regime’s secretariat fled Meqele for Dessie and the secretariat in the liberated territories entered Meqele and operated there until the TPLF seized state power in 1991. “
Aregawi Berhe political History of the TPLF pp244-246
Aregawi Berhe political History of the TPLF pp244-246
ይህ እንግዲህ የሚያሳየን አሁን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ጳጳሳት ተብለው ከተሾሙት እና የየመምሪያው ኃላፊዎች ከሆኑት ውስጥ በዚህ እቅድ ተዘጋጅተው የመጡ እንደሆኑ ነው።
ለዚህም ነው ይህን አይነት በደል በቤተክርስቲያን ላይ ሲፈጸም አንዳችም የተጨበጠ ርምጃ ወንም ተቃውሞ በቤተክርስቲያኗ መሪዎች ዘንድ የማይወሰደውና የማይሰማው።
እዚህ ላይ በቤተክርስቲያን ላይ በሚደርሰው መከራ ተወቃሽ የሚሆኑት አባቶች ብቻም አይደሉም። ብዙ የተማረ ወጣት ይዞ ይህ የሕብረተሰብ ክፍል ኃይማኖቱ ስትጠቃና ወገኖቹ ሲጨፈጨፉ አድርባይና ጥቃትን በዝምታ እንዲቀበል እያደረገ ያለው ማኅበረ ቅዱሳንም ጭምር ነው።
ምንም እንኳን ጠመንጃ የታጠቀ ኃይል ቢሆን ሕዝብ እነደ ሕዝብ በቃ ካለና ተቃውሞውሁሉን አቀፍ ከሆነ በተለይም ተሰሚነትና የለውጥ መሪ የሆነው የተማረው ክፍል ከሆነ የራሱን ሕልውና ለማቆየት ሲል ቢያንስ እንዲህ አይነቱን ድርጊት ከመፈጸም ሊገታው የሚችል ነበር እንደማኅበረ ቅዱሳን አይነት ድርጅት። ይህም ፖለቲካ ውስጥ መግባት ሳይሆን የቤተክርስቲያናችን መብት ይከበር እዲህ አይነት ጭፍጨፋን እንቃወማለን ማለት ኃይማኖታዊ ግዴታም ጭምር ስለሆነ ነው።

አለበለዚያ በአንድ ወቅት ጆሞ ኬንያታ አሉ እንደተባለው፤ ተንበርከኩ፣አይናችሁን ጨፍኑ እኛ የመጣነው ወንጌል ልናስተምራችሁ ነው ብለውን ቀና ቀና ስንል አገራችንን ወስደውታል አሉ እንደተባለው ዛሬም ለቤተክርስቲያን ደርሶ ከእኛ ወዲያ ጠበቃ የሚሉት ማኅበረ ቅዱሳኖችስ ይህ ሁሉ ግፍ በቤተክርስቲያን እና በልጆቿ ላይ ሲፈጸም ወዴት አላችሁ ይሆን ??? ወይንስ እንደቅኝ ገዚዎቹ ሁሉም ነገር በጸሎት ነው እያላችሁ ምእመናንን ታዘናጋላችሁ ??? ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የተለያዩ ሰዎች በተለያዩ ወቅቶች የተናገሯቸው ነገሮች አሉ። ከነዚህም ውስጥ ቤተክርስቲያን በመንግሥት ስትጠቃ ድምጽ አያሰማም እናም በውስጥ የመንግሥት ጉዳይ አስፈጻሚ ነው የሚል ነው። ይህንንም አባባል እውነተኝነቱን የሚያጎላው በተለይ በእደዚህ አይነት ወሳኝ ወቅት ማኅበሩ በተግባር ቀርቶ በመግለጫ እንኳን ድርጊቱን አለመቃወሙ ነው።
ከዚህ ባሻገር በተለይ በውጪው ዓለም ውስጥ ገብተን መታገል አለብን እያሉ የቤተክርስቲያናትን ሰላምና አንድነት እየበጠበጡ ያሉት ደርሶ ለቤተክርስቲያ አንድነት ተቆርቋሪ ነን ባዮች ጉዳይ ነው። የቤተክርስቲያን ምእመናን ስለቤተክርስቲያን መብት ብለው በአላዊ መንግሥት ሲገደሉ ወዴት አላችህ ይሆን??? ውስጥ ገብታችሁ የፈየዳችሁት ምን ይሆን??? ወይንስ እንደአዝማቻችሁ ማህበረ ምናምን እናንተም እንደ ቅኝ ገዢዎች በጸሎት ነው???
በክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ሁላችንም ልናውግዘው የሚገባ የአረመኔዎች እና የሽብርተኞች ሥራ ነው።
ሁሌም ቤተክርስቲያንን የሚጠብቃት መድኃኔዓለም ዛሬም ብዙ ናቡቴዎች የአባቶቻችንን እርሻ አናስወስድም ብለው ሰማእትነትን መምረጣቸው በተውሰደባቸው አረመኔያዊ ግድያ ለጊዜው ብናዝንም ደግሞም ቤተክርስቲያን ለዘለዓለም ስትዘክራቸው ትኖራለች። በከፈሉት ሰማዕትነትም አኩርተውናል። እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይቀበል።
ሁሌም ቤተክርስቲያንን የሚጠብቃት መድኃኔዓለም ዛሬም ብዙ ናቡቴዎች የአባቶቻችንን እርሻ አናስወስድም ብለው ሰማእትነትን መምረጣቸው በተውሰደባቸው አረመኔያዊ ግድያ ለጊዜው ብናዝንም ደግሞም ቤተክርስቲያን ለዘለዓለም ስትዘክራቸው ትኖራለች። በከፈሉት ሰማዕትነትም አኩርተውናል። እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይቀበል።
No comments:
Post a Comment