በለው ግንባሩን በዚያው ይመለስ፤
አይቀርምና ተሰርቶ መፍረስ!! (አንተነህ ገብርየ)
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዘር ላለን የሁላችንም አገር ናት።የዘረኝነት ልክፍት እያጦዘው ያለው ህወሃት ወደ ሥልጣን ብቅ ካለ በኋላ ግን ኢትዮጵያ የህወሃት ባለሥልጣናት፤አባላትና የኮር አባላት እንዲሁም የሆዳሞችና አድር ባዮች ብቻ እንድትሆን ለማድረግ ከፍተኛ ሴራ ተሸረበ ዛሬም እየተሸረበ ይገኛል።ይህ የጥፋት ተላላኪ ድርጅት ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ በፊት ደርግ ሳይወድቅ ኢትዮጵያ ከየት ወደ የት? በሚል ርእስ አንድ መጣጥፍ አቅርቦ ለህወሃት/ኢህአዲግ የወደፊት ሥጋቶች የሚሆኑት ሻእብያና ኦነግ እንደሆኑ ደስኩሮ ነበር። ደርግ በወደቀ ማግስት ግን ዱላውን ማሳረፍ የተፈለገው በአማራው ነገድ ሕዝብ ላይ ሆነ።ህወሃት ከሻእብያም ሆነ ከኦነግ ጋር የምር ጠብ አለው የሚባለው ለማስመሰል እንጅ ውስጡን ለሚያውቅ ገልጽ ወዳጃሞች መሆናቸው ይታወቃል።ምክንያቱም የሥልጣን ሽኩቻው እንጅ በሌላው የዓላማ ጉዳይ አንድ የሚያደርጋቸው መነሻ በመኖሩ ነው።
ይኸውም አማራውን ከምድረ ኢትዮጵያ ማስወገድ፤የአማራውን ዝክረ ታሪክ መፋቅና እንዳልነበረ ማድረግ ነው።አሁን በተጨባጭ እየሆነው ያለውም ይኸው ነው። አንዳንድ ምሁራን እነዚህ ሰዎች አዲስ ናፋቂ ናቸው በማለት ሃሳባቸውን ያጋሩኝ ነበር እኔም ብሔራዊ ሞራልህ እስካልኮሰኮሰህ ድረስ ምንም ብታደርግ ሀፍረት አይሰማህም በማለት እመልስላቸው ነበር።ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዘር ላለን የሁላችንም አገር ናት።የዘረኝነት ልክፍት እያጦዘው ያለው ህወሃት ወደ ሥልጣን ብቅ ካለ በኋላ ግን ኢትዮጵያ የህወሃት ባለሥልጣናት፤አባላትና የኮር አባላት እንዲሁም የሆዳሞችና አድር ባዮች ብቻ እንድትሆን ለማድረግ ከፍተኛ ሴራ ተሸረበ ዛሬም እየተሸረበ ይገኛል።ይህ የጥፋት ተላላኪ ድርጅት ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ በፊት ደርግ ሳይወድቅ ኢትዮጵያ ከየት ወደ የት? በሚል ርእስ አንድ መጣጥፍ አቅርቦ ለህወሃት/ኢህአዲግ የወደፊት ሥጋቶች የሚሆኑት ሻእብያና ኦነግ እንደሆኑ ደስኩሮ ነበር። ደርግ በወደቀ ማግስት ግን ዱላውን ማሳረፍ የተፈለገው በአማራው ነገድ ሕዝብ ላይ ሆነ።ህወሃት ከሻእብያም ሆነ ከኦነግ ጋር የምር ጠብ አለው የሚባለው ለማስመሰል እንጅ ውስጡን ለሚያውቅ ገልጽ ወዳጃሞች መሆናቸው ይታወቃል።ምክንያቱም የሥልጣን ሽኩቻው እንጅ በሌላው የዓላማ ጉዳይ አንድ የሚያደርጋቸው መነሻ በመኖሩ ነው።
በኢትዮጵያ ላይ ጣታቸውን የቀሰሩ እግራቸውን የሰነዘሩ ጠመንጃቸውን ያነጣጠሩ በተደጋጋሚ ለወረራ የተነሱብን የሀገር ጠላቶች ሲመጡብን ብቻቸውን አልነበረም የመጡት የአገር ውስጥባንዳዎችን በማደራጀት በንዋይ በመደለል እያስመሩ ነው።ክብሩን ሽጦ ለገንዘብ የተገዛን ቅጥረኛ ደግሞ ስለሀገር ስለሕዝብ ያስባል ብሎ ና! ተመለስ ማለት በፍጹም የማይታሰብ ጉዳይ ነው ምክንያቱም ጓዙን ጠቅሎ ለአድርባይነት የቆመ በመሆኑ።አጼ ቴዎድሮስን ለማስገደል መቅደላ ድረስ የመራው ማን እንደሆነ እናውቃለን፤የሱዳን መሐዲስት(ድርቡሽን) ገፋፍቶ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት የሚኖረውን ሕዝብ፤መነኮሳት ካህናትና ዲያቆናት በግፍ እንዲጨፈጨፉ ያደረገው አብያተ ቤተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን እንዲወድሙ የሆነበት ምክንያትም በማን አማካኝነት እንደሆነ ግልጽ ነው።ጣሊያን ካንዴም ሁለት ጊዜ ለወረራ ስትመጣብን ያለ ዝግጅት አልነበረም የዝግጅቱ አበጋዞች ትውልደ ኢትዮጵያውያን ነበሩ።ግራኝ መሀመድና ዮዲት ጉዲትም እንዲሁ በአንድ ቀን ጀምበር ተነሳስተው አይደለም ያን ያህል ጥፋት ያደረሱት ገፊ ነበራቸው።
እንግዲህ በእንደዚህ አይነት አሳፋሪ ተግባር ተሠማርተው ከነበሩ የሚወለደው ትውልድ ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት የሚያዳግት አይሆንም።ለዚህ ግልጽ ማሳያ የሚሆኑት ከባንዳ ዘር የበቀሉትን ሻእብያና ህወሃትን ብቻ መጥቀስ በቂ መስሎ ይታየኛል።ሕግን በመጣስ ሰበብ የተወሰዱት ርምጃዎች እውን ሕጉን የሚጥስ ተግባር ተፈጽሞ ወይም ሙከራ ተደርጎ አለመሆኑን በርግጠኛነት መናገር ይቻላል።ዓላማው ሌላ ነው እቅዱ የኖረ የቆየ የምእራባውያን ፍላጎት በተለይም የእንግሊዝ ሲሆን አስተግባሪዎቹ(የጥፋቱ መልእክተኞች)የተሰጣቸውን የቤት ሥራ በተቀመጠለት የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ሊፈጽሙ ባለመቻላቸው የማንቂያ ደወል እንዲሆን ባልተሞከረው ወይም ባልተሄደበት መንገድ ሄዶ ያች ነጭን ድባቅ መትታ በዓለም ታሪክ ትልቁን ቦታ የያዘችውን ኢትዮጵያ የተባለች አገር ስሟ ተፍቆ ታሪኳ ተደልዞ ጀግኖቿ አልቀው ባዶ ሆና ማየት የቅጀት ህልም የሚያዩትን ጌቶቻቸውን እርካታ ለማሟላት ሲባል ብቻ አዛውንት ከቤታቸው በር ጸሐይ ሲሞቁ፤ተማሪዎች ደብተራቸውን አንግበው ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ፤መብቱን የተገፈፈው ህዝብ መብቴን አስመልሳለሁ ብሎ ሲሞግት፤ገበሬው ከማሳው የግብርና ተግባሩን ሲያካሂድ፤ጋዜጠኛው በሙያው ያየ የሰማውን እውነታ ሲዘግብ፤መምህሩ የተማረ ዜጋ ለማፍራት ሲጥር፤ነጋዴው ከሳንቲም ላይ ሳንቲም ጨምሮ ቤተሰቡን ለማሳደር ደፋ ቀና በሚልበት ሰዓት በቅልብ አልሞ ተኳሽ የህወሃት ዘረኛ ታጣቂ በየክፍለ ሀገራቱና የአገሪቱ ርእሰ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በጠራራ ጸሐይ መላ የኢትዮጵያ ህዝብ በጥይት እየተመታ በአፍ ጢሙ ሲደፋና ወህኒ ቤት ሲጋዝ፤አገር ጥሎ እንዲሰደድ በርሃብና ውሃ ጥማት እንዲሁም በአውሬ ተበልቶ እንዲያልቅ በማድረግ ደስተኛ የሚሆን የጠላት ኃይልን ተሸክመን ነው ያለን።
አንኳር አንኳሮቹን ወስደን እንመልከት፦
**የከተማ ማሀል ትረይን ላይን ለመዘርጋት ሲባል የፈረሱ ቤቶችና የሰማዕቱ ጴጥሮስን ሀወልት እስከ ማፍረስ ሲኬድ እውን ይህ ፕሮጀክት በዘመነ ህወሃት ይፈጸም ይሆን የሚል ጥያቄ ማጫሩ አይቀሬ ነው።ዋናው መነሻ ግን ለልማትና አገር እድገት ታስቦ ሳይሆን የሕዝቡን ትዕግስት ለክቶ አሻፈረኝ ካለ በኃይል ለማስተንፈስ ያለመ ነው።ለማንኛውም እቅዱ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የምናየው ይሆናል።
**የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም ተብሎ የተወሰደውን ርምጃ ስናይ ለዘመናት የቆየውን የመነኮሳት አጽም በዶዘር ማረስና የታሪክ ቅርሶችን ማራከስ የስኳር ፋብሪካው የሚቋቋምበት ቦታ ጠፍቶ አይደለም።የሕዝቡን ልብ ለመለካትና ነገር ለመጫር ነው።በመሆኑም ብዙ መነኮሳት ላይ ጉዳት ደረሰ ቅርሶችም እንዲራቆቱ ተደረገ የስኳር ፋብሪካው ግን በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነገር የለም።ይህ ፕሮጀክት ሲመረጥ እውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አንገብጋቢ ጥያቄ ስኳር ነበርን ብለን ራሳችን ብንጠይቅ ልናገኝ የምንችለው መልስ ከባለሥልጣቱ ጥቅም ዙርያ የሚያልፍ አይሆንም።በስኳር ሽያጭ ዲል ያለ ገቢ ማግኘትና መክበር ዛሬ መክበር ነገም መክበር ነው በህወሃት መንደር የሚታሰበው።ይህ ደግሞ አልጠግብ ባይነትና ሰፍሳፋነታቸውን የሚያመላክተው አንዱ መገለጫ ነው።
** አባይን መገደብ የማንኛውም በኢትዮጵያ ሥልጣን ላይ የሚወጣ የማንኛውም አካል ፍላጎት ሊሆን ይችላል ያ ግን ኧህ ብሎ ከሕዝብ አንደበት የሚመነጭ መነሻ አልነበረውም። የአሁኑ የህወሃት አባይን የመገደብ ጉዳይም የሕዝቡን አመለካከት ለማስቀየር እንጅ ባለሥልጣናቱ የአገሪቱን ካዝና ዘቅዝቀው በማራገፍ ገንዘቡን ተካፍለው ባሕር ማዶ አሻግረው በግላቸው አካውንት እንዳለ እያወቁ፤ ከህዝብ ጋር ተቆራርጠው፤ ከዲያስፖራው ጋር በተለያዩበት ወቅት አባይ እንዴት ብሎ ሊገደብ ይችላል?እዚህ ላይ አንድ እውነታ ጠቅሸ ልለፍ አብዛኛው በውጭ የሚኖረው ኤርትራዊ የኢሳይያስን መንግሥት አይደግፈውም ከአምባገነንነቱ አንጻር ይሁን እንጅ እያንዳንዱ ኤርትራዊ ዲያስፖራ ከሚያገኘው ገቢ ለኢሳይያስ መንግሥት መዋጮ ይከፍላል በኢትዮጵያ የሚታየው ግን የተለየ ጉዳይ ነው ለምን? ቢባል ቁጥር ሁለት ኤርትራውያን የሚገዟት አገር በመሆኗ።
በአባይ ወንዝ ሕይወታቸው የተመሰረተው ግብጽና ሱዳን ጋር ዲፕሎማሲው መስመር ባልያዘበት ወቅት አባይን እገድባለሁ ብሎ ማሰብ ከማስመሰልና የህዝቡን ሀብት በቦንድ ስም ዘርፎ የሚበላው ለማሳጣት የታለመ ነው።ሳትዋጋ ንገሥ እንደሉ በአባይ ገባሮች ብዙ ታሪክ መሥራት እየተቻለ ያልሆነ ወጥመድ ውስጥ መግባቱ ባልተገባ ነበር።አባይ ይገደብ አይገደብ የሚለው አከራካሪ ጉዳይ አይደለም ነጥቡ መጀመሪያ ህወሃት ምንድን ነው?ወራሪ ወይስ መንግሥት?ኢትዮጵያዊ ወይስ የውጭ ዜጋ? በዜግነት ኢትዮጵያዊ ናቸው በድርጅቱ ማእቀፍ ውስጥ የሚገኙት።መንግሥት ግን አይደሉም ወራሪዎች ናቸው።ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ያለው ተዛምዶ ሲታይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የድርጅቱ አባል ደጋፊ እስካልሆነ ድረስ ጠላት ነው።ሕዝብን ጠላት አድርገህ እንዴት ነው አባይን የምትገድበው?ነጋ ጠባ የሚሰማው ይህን ያህል ሰው ታሰረ፤ይህን ያህል ሰው ተገደለ ነው እንዲህ ባለው ተጨባጭና ነባራዊ ሁኔታ ህወሃት ልማትና የሀገር እድገትና ብልጽግናን ያስባል ብሎ መገመት ** ከእባብ እንቁላል የእርግብ ልጅን** እንደመመኘት ነው የሚሆነው።
**መሬት የግል እንዲሆን ካደረግን ገንዘብ ያለው አማራ ስለሆነ መሬት እየገዛ ስለሚከብር ያን አናደርገውም (ሟቹ መለስ ከተናገረው)። በዚህ ምክንያት መሬት የመንግሥት እንዲሆን እናደርጋለን የሚለውን የህወሃት መሪ ቃል ተከትሎ ለሙንና ውሃ ገቡን መሬት እየመረጡ ለባለሥልጣናቱ፤ለውጭ ባለሀብቱና ለአጎራባች አገሮች ስጦታ በማበርከት ጫካ መንጥሮ መንደር ቆርቁሮ አገር ያቀናውን ኢትዮጵያዊ ትውልድ ከቀየው በማፈናቀል አገር የለሽ ማድረግ ዘር ማጥፋት ነው፤የዚህ ዘረኛና ቅጥረኛ ድርጅት አባልና ደጋፊ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ከማእደ ኢትዮጵያ የተገለለ፤በሀገሩ ሰርቶ መብላት የማይችል ዜጋ እንዲሆን ተደርጓል።ይህን እንደ ቀላል ጉዳይ የሚመለከቱና ህወሃትን ልማታዊ መንግሥት እያሉ የሚያሞካሹ የልማትና የከተማ ቤት መሥርያ ቦታ እናገኛለን ብለው ያሰፈሰፉና በመጨረሻው ሰአት ላይ እጃቸውን ለህወሃት መስጠት ከውርደትም በላይ ውርደት ነው።ጊዜ ሊወስድ ይችል ይሆናል ያ እንደ እኛ ጥንካሬና ብርታት የሚታይ ሲሆን ሕዝብ የመሬት ባለቤት መሆኑ ግን አይቀርም።ደን መንጥሮ ቀን በሐሩር ሌሊት በቁር እየተሰቃየ ያቀናውን መሬት ለውጭ ባለሀብት ለወዳጅ ዘመድና ለአጎራባች አገሮች መቸብቸብ የሥርዓቱ አራማጆች የሚከፍሉትን ዋጋ በእጥፍ እንዲሆን ያደርገዋል።
**በነፍጥ ሆነ በሰላማዊ ትግል አትሞክሩኝ፤ የምርጫ ኮረጆ ስዘርፍና በሀሰት ተመርጫለሁ ስል አትናገሩኝ ማለት የድናቁርት የህወሃት መራር መለያ ባህርይ ሲሆን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መልስ ሳያገኝ በኃይል እየገዛሁ እኖራለሁ ማለት ዘበት ነው።በደርግ የአገዛዝ ዘመን ደርግን ሲኮንኑ፤ሲያወግዙና በነፍጥ ሲታገሉ የነበሩ ኃይሎች ትንሽ እንኳን ሳይቆዩ ከደርግ የከፋና የባሰበት ባህርይ ይዞ መገኘት ከባድ የሀገር ክደት ነው።ህወሃትን ከማኒፌስቶው አይን ስንመዝነው የለየለት ፋሽስትና ቅጥረኛ መሆኑን ብናውቅም ቢያንስ ወደ መሀል አገር ገብቶ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ሲገኙና አብረው መኖር ሲጀምሩ መንፈሳዊ ስሜትና ብሔራዊ ሞራልን አለመታደል የበደል በደል ነው።አውሬነት፤በሌሎች ስቃይ መደሰት ከሰብአዊ ፍጡር አይጠበቅም ነበር።ሕዝብን እያሰቃዩ በተለይም ወጣቱን ትውልድ የሱስ ተገዥ ማድረግ፤አገር ጥሎ እንዲጠፋ ማድረግ ከውጭ መንግሥታት ጋር በማሴር ኢትዮጵያውያን ተሰደው በሚኖሩበት አገር በደል እንዲደርስባቸው ማድረግ፤ኤምባሲዎች ከአንድ ጠባብና አናሳ ጎሳ የተመለመሉና ለድርጅቱ አባላት ብቻ የሚያገለግሉ ሆነው መገኘት የድርጅቱ ፀረ-ሕዝብነትን ከፍ አድርገው የሚያሳዩ ናቸው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
ሞት ለህወሃትና ሆዳሞች!!!
No comments:
Post a Comment