እኔ ወንድማችሁ ማነፍነፍ እወዳለሁኝ በሳሙኤል ግደይ አስተባባሪነት ተጠለፈ የሚባል ዜና ከጅምሩ ለወሬውም አልተመቸኝ። እስኪ ትንሽ ልታገስ ብዬ ቆይቻለሁኝ። አሁን ግን አንድ ፍንጭ አግኝቼያለሁ።
ለወትሮ እንዲህ ኣይነት ነገር ሲከሰት ወያኔ የውሸት መግለጫ ነው የምታወጣው። የቴክኒክ ችግር፡ ነዳጅ ምናምን። ይህን በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ችግር ሲገጥመው ታዝበናል። ለምሳሌ ሃይለመድህን ጠለፈ የተባለ ጊዜ የተሰጠውን መግለጫ አስታውሱ። በ2010 እኤአ በሊባኖስ ያጋጠመውንና እስከ መጨረሻ ድረስ ይሰጥ የነበረውን የውሸት ምክንያት ልብ በሉ።
ዛሬ ግን በፍጥነት ወደ ኤርትራ መጠለፉን ነገሩን። አያይዘው ከዛቻ የማይተናነስ ጠንካራ የአቋም መግለጫ አስቀምጠዋል።
ከመለስ ብኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚደረግ አገር አቀፍ ምርጫ፤ ኢህአዴግ/ወያኔ ከውስጥም ከውጭም አመፅ ሊነሳበት እንደሚችልና እንደሚያሰጋው የዛሬ ዓመት ገደማ የፃፍኩት ነገር ነበር። ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉም ከዚህ በፊት ከነበረው ሁኔታ በመነሳት አንዳንድ ግምቶቼን አስቀምጬ ነበር። ከነዚህ መካከል በምርጫ ሰሞን የኢትዮጵያን በተለይም የትግራይን ሰማይ በልምምድና በምናምን ሰበብ በተደጋጋሚ በጦር ጀቶች ሊያርሱት እንደሚችሉ ነው። ለምን ቢባል በሰላም አገር ህዝብን ለማሸበር።
ታድያ ይቺ ነገር ከነከነችኝ በጣም። ሳሙኤል ግደይ በስኮላርሺፕ እየሰለጠነ የነበረ ትውልደ ኤርትራ ቢሆንስ? የፈለገውን ይሁን ታዝዞ ቢሆንስ? ለምን ምክንያት አላችሁ? መከላከያ ሰራዊቱን ግሪን ካርድ ለመስጠት ነዋ!
እንሆ መግለጫው፥
"የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊትም የህገ መንግስቱና የህዝቡ አለኝታና መከታ በመሆን የሻዕቢያን ተላላኪዎችና ቅጥረኞች በከፍተኛ ህዝባዊነትና ጀግንነት ከተቀበሩበት መቃብር ለአፍታም ቢሆን ቀና እንዳይሉ በማደርግ የሀገሪቱን ሰላምና ልማት እንሳካለን ብሏል፡፡"
ልብ ብላችሁ አጢኑት!
የመከላከያ ሰራዊቱን እዚህ ላይ ምን አመጣው?
ጠላት ላይ ሳይሆን የጠላት ተላላኪዎችና ቅጥረኞች ላይ ብቻ ያነጣጠረ ዛቻ፤ በዛ ላይ መቀበራቸውን እያስታወሰ ለአፍታም ቢሆን ቀና እንዳይሉ ለማድረግ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ይነግሩናል። በሌላ አነጋገር መብቴን ምኔን ብሎ የሚነሳ ካለ ከተቀበረበት መቃብር ለአፍታም ቢሆን ቀናይ ሳይል መከላከያ ሰራዊቱ ይመክተዋል ማለት ነው። መከላከያ ሰራዊቱ ህዝብን ለመመከት እንጂ የአገሪቱን ጠላት ለመመከት የቆመ አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ። ይህ ዜና በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ መከፋፈል እንዳይፈጠር እንደ ምክንያት/ ፕሮፓጋንዳ በመጠቀም ታማኝ ውሾቻቸውን ህዝብ ላይ ለመልቀቅ ያስችላቸዋል።

እናም! እኔ ተጠለፈ ብዬ ሳይሆን ተቀነባበረ ብዬ ተረድቼዋለሁ። እናንተስ?
No comments:
Post a Comment