Sunday, July 5, 2015

በምስራቅ ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች በጅምላ እየታሰሩ ነው ተባለ

ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸው ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው
በምስራቅ ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች ‹‹የማዳበሪያ ዕዳ አልከፈላችሁም›› በሚል በገፍ እየታሰሩ መሆኑን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ ወስዳችኋል የተባሉትን የማዳበሪያ እዳ እንዲከፍሉ እየተጠየቁ እንደሆነ የገለጹት ምንጮች በአንድ ቀበሌ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች በጅምላ መታሰራቸውን ገልጸዋል፡፡ አርሶ አደሮች እነሱ ወስደውታል የተባለውን ብቻ ሳይሆን በሞት የተለዩትን ዘመዶችን ዕዳ ጭምር ካልከፈላችሁ ተብለው ለእስር እየተዳረጉ መሆኑም ተሰምቷል፡፡ የጅምላ እስሩ ከሰኔ 15/2007 ዓ.ም እንደተጀመረ የገለፁት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ለሳምንት ያህል የታሰሩት አርሶ አደሮች ሰኔ 21/2007 ዓ.ም ቢለቀቁም ሌላ ዙር እስር በመጀመሩ በርካታ አርሶ አደሮች ለእስር ሰለባ ሆነዋል ብለዋል፡፡

ሮን አለማየሁ 6 ወር ተፈረደባት

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስራ ‹‹ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ በማወክ›› የተከሰሰችው ሜሮን አለማየሁ የ6 ወር እስር ተፈረደባት፡፡ ሜሮን አለማየሁ ሚያዝያ 14 በተጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት የለም፣ አትነሳም ወይ፣ የታረደው ወገን ያነተ አይደለም ወይ›› በሚል ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራለች ተብላ በተከሰሰችበት በዋስ ወጥታ ጉዳዩን ስትከታተል የቆየች ሲሆን ዛሬ ሰኔ 26/2007 ዓ.ም በጎፋ ፍርድ ቤት ቀርባ 6 ወር ተፈርዶባታል፡፡

በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች መካከል ተፈጥሮ የቆየው መከፋፈል ተካሯል

በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ተፈጥሮ የቆየው መከፋፈል በሁለት ፅንፍ የቆመ ሲሆን አንደኛው ቡድን በኤታማጆር ሹሙ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ስር ሁለተኛው ቡድን ደግሞ የምስራቅ ዕዝ አዛዥ ከነበረው ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርያም ጎን የተሰለፉ ናቸው፡፡ ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርምን ከዕዝ አዛዥነቱ አንስቶ ወደ መከላከያ መምሪያ የማዛወሩ የእነ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ቡድን ዕቅድ በሌ/ጀነራል አብርሃ ቡድን የበላይነት ሊከሽፍ ችሏል፡፡ ሆኖም ግን ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርያም ከምስራቅ ዕዝ ተነስቶ የደቡብ መስራቅ ዕዝ አዛዥ መሆኑ ታውቋል፡፡

ተቃዋሚዎች የኦባማን ጉብኝት ተቃወሙት

በኢትዮጵያ ስላለው የመብት ረገጣ 90 ሚሊዮን ህዝብ ምስክር ነው”
– ለእድገታችን አሜriካ ምስክር ሆነችልን ማለት ውጤት አያመጣም – ዶ/ር መረራ
በአለማቀፍ ታላላቅ የሚዲያ አውታሮች መነጋገሪያ ሆኖ የዘለቀው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን የመጐብኘት ውጥን አሜሪካ አምባገነን መንግስታትን ከመደገፍ የመነጨ በመሆኑ እምብዛም ትኩረት የሚሠጠው ጉዳይ አይደለም ብለዋል – የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፡፡
ዶ/ር መራራ ጉዲና
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ መምህር እና የመድረክ የፖለቲካ ማህበር አመራር ዶ/ር መረራ ጉዲና የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ዋነኛ ትኩረቱ የሽብር ጉዳይ ነው ይላሉ፡፡

ወያኔ አርበኞች ግንቦት 7 የከፈተበትን ጦርነት ከህዝብ ለመደበቅ እየሞከረ ነው

ባለፉት ሦስት ቀናት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ትግራይ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የወያኔን ሃይል ገጥመው የወያኔ መኮንኖችን ጨምሮ በርካታ የወያኔ ሰራዊት አባላትን እንደገደሉ በቃል-አቀባያቸው አማካኝነት ለኢሳት ቴሌቪዥን ገልጸዋል። ለጥቀውም እስከ ትላንት ድረስ ውጊያው ቀጥሎ እንደሚገኝ በድጋሜ ዜናውን አብስረዋል።

በወያኔ ዘረኛና ግፈኛ አገዛዝ የተንገፈገፈው የኢትዮጵያ ህዝብም ጆሮውን አቅንቶ ሁኔታውን በመከታተል ላይ ነው። ቀድሞውንም የወያኔ ሥርዓት ያለ ሃይል ትግል አይንበረከክም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካም ሆነ የሥርዓት ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በተቃውሞው ጎራ የተሰለፉት ተባብረው በወያኔ ላይ ክንዳቸውን ሲያሳርፉ ብቻ ነው ብለው የሚያምኑት ኢትዮጵያውያን አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ የከፈተውን ማጥቃት በከፍተኛ ደስታ ነው የተቀበሉት።
አንዳንዶች አርበኛውን በገንዘብ ለመደገፍ እና ለማጠናከር ከወዲሁ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

በህወሓት አገዛዝ እየተሰቃዩ ላሉ ወገኖቻችን ደህንነት የሚደረገው ዓለም አቀፍ ጫና ይቀጥል!

def-thumbከሣምንት በፊት የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የሚመለከት አንድ መግለጫ አውጥቷል። በዚህ መግለጫው፣ አንዳርጋቸው ጽጌ ለአንድ ዓመት ሙሉ መሠረታዊ የሆኑ የታሳሪዎች መብት እንኳን ተነፍጎት ባልታወቀ እስር ቤት የሚገኝ መሆኑ እና በእንግሊዝ ባለሥልጣናትና በቤተሰቦቻቸው እንዲጠየቅ፣ ቋሚ የቆንስላና የህግ ምክር እንዲያገኝ በተደጋጋሚ የቀረበው ጥያቄ በወያኔ አገዛዝ ውድቅ መደረጉ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው መልካም ግንኙነት የሚያሻክር መሆኑ ከወትሮው ጠንከር ባሉ ቃላት ገልጿል። አዲስ አበባ የሚገኘው የብሪታኒያ አምባሳደርም እንደዚሁ ከተለመደው ዲፕሎማሲያዊ ለስላሳነት ወጣ ያለ ያለ መግለጫ አዲስ አበባ ውስጥ ለሚታተመው ሪፓርተር ጋዜጣ ሰጥቷል።

አይቀሬዉ የድል ፊሽካ ተነፋ!! አርበኞች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል በወያኔ ሰራዊት የኃይል ጥቃት ሰነዘረ



 ሀሙስ ዕለት ሰኔ 25 2007 ዓ.ም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በትግራይ ክልል ቀፍታ መሲል፣ ሆርጃሞ እና ማይሰገል ላይ ህወሓት ከሚቆጣጠረው የ24ኛ ክፍለ ጦር፣ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ኃይል ጋር ባደረገው ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ከባድ ጦርት ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ተጋዮች በትግራይ ቀፍታ መሲልና ሆርጃሞ ላይ መሽጎ ያገኙትን ከሶስት ክፍሎች ማለትም ከ24ኛ ክፍለ ጦር፣ ከፌደራል ፖሊስና ከልዩ ኃይል የተውጣጣና እስከ አፍንጫው የታጣቀ ቁጥር ስፍር የሌለው ጦር ከቀኑ ሰባት ሰዓት እስከ አስር ሰዓት ለተከታታይ ሦስት ሰዓታት በጥይት ቆልተውታል፡፡