Wednesday, September 9, 2015

የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ ምስረታ በማስምልከት የወጣ ድርጅታዊ መግለጫ

editorial of alliance
የኢትዮጵያ ህዝብ የኣገሩን ሉዓላዊነትና ኣንድነት ኣስከብሮ የኖረ ብቻ ሳይሆን ኣፍሪካውያን ወንድሞቹና እህቶቹ ከቀኝ ኣገዛዝ ነፃ እንዲወጡ የራሱ ኣስተዋፅኦ ያደረገ ጀግና ህዝብ ነው። ሆኖም ይህ ጀግና ህዝብ ከኣብራኩ በወጡ ገዢዎች ነፃነቱ ተገፎ፤ መብቶቹ ተረግጠው የመከራ ኑሮ እየገፋ ኣያሌ ዘመናት ኖZል። ይህ የመከራና የሰቆቃ ኑሮ ዛሬም ኣላበቃም፤ እንዲያውም “ከጭቆና ነፃ ኣወጣንህ” እያሉ የሚሳለቁበት ግፈኛ ገዢዎች የጫኑበት የስቃይ ቀንበር ተሸክሞ የውርደት ኑሮ እየኖረ ነው።

የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት /ህወሃት በተለየ ሁኔታ በኤርትራ ላይ ዛቻ እያሰማ ነው።

-ኤኤፍፒ የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመጥቀስ እንደዘገበው፣ የኢህአዴግ መንግስት በኤርትራ ላይ የሚያሰማው የጦርነት ዛቻና አገሪቱን እወራለሁ እያለ የሚያሰማው መግለጫ ጨምሯል። የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት /ህወሃት በተለየ ሁኔታ በኤርትራ ላይ ዛቻ እያሰማ ነው።
በክረምቱ ወር ይሰማ የነበረው ፉከራ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ተጠናክሮ መቀጠሉን የማስታወቂያ ሚኒስቴሩ ገልጿል። የህወሃት አገዛዝ ኤርትራን እንዲወር ከአሜሪካ ፈቃድ አግኝቻለሁ እያለ በመናገር ላይ መሆኑን የገለጸው የኤርትራ መንግስት፣ በተለይም ከኤርትራ ጋር ግንኙነት አላቸው ብሎ የሚጠረጥራቸውን ሃይሎች ለማሸማቀቅ እየጣረ መሆኑን ገልጿል።

‹‹ተንጠልጥሎ መቅረት እንደኢትዮጲያ !›› (አሌክስ አብርሃም)

freedom.jpg
አንዳንዴ ምን ይገርመኛል መሰላችሁ እኛ ኢትዮጲያዊያን ነገሮችን ሞቅ በማድረግና ወዲያው እርግፍ አድርጎ በመተው (በመርሳት) በሽታ የተለከፍን ይመስለኛል ….ለዛም ነው ታሪካችን በእንጥልጥል ፣ እውቀታችን በእንጥልጥል ፣ ስልጣኒያችን በእንጥልጥል ፣ፍቅራችን በእንጥልጥል ሁሉም ነገራችን በእንጥልጥል የሚቀረው !! …እንደኔ እንደኔ የፕሮፌሰር መስፍን የ‹‹መክሸፍ›› ቲዎሪ ከመክሸፍ ይልቅ ‹‹ተንጠልጥሎ መቅረት›› የሚለው ቃል በትክክል የሚገልፀው ይመስለኛል …መክሸፍ የተጀመረ ነገር ዳግም ላይመለስ ላያንሰራራ እንደገናም ከቆመበት ላይቀጥል መበላሸት መጨናገፍ መቆም ነው ትርጓሜው …እንደውም መክሸፍ እረፍት ነው !! በቃ አንድ ነገር ላይመለስ መኮላሸቱን አውቆ ከ ሀ ለመጀመር ሳያበረታታ አይቀርም ! ለመክሸፍማ አልታደልንም!

በሶርያ .የኢትዮጵያውያን ስደተኞች አቤቱታ.

” በጦርነት ውስጥ እያለን የዜግነት ማረጋገጫ አቅርቡ ተባልን “
* ” ማጣራት ካስፈለገ ከወጣን በኋላ ያጣራ !”
* ” በሊባኖስ ቤሩት ኢንበሰሲያችን አይተባበረንም !”
* ” የምንኖረው በኢትዮጵያ አምላክ ጥበቃ ብቻ ነው! “
የሻም ታሪካዊ ምድር ጥንታዊዋ ደማስቆስ ሶርያ በጦርነት አረንቋ ተዘፍቃ ትገኛለች ። በዚህችው ምድር በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ ደላሎች እየታለሉ ለስራ ይገባሉ ። ይህ ሁኔታ አሁን ድረስ መቀጠሉን ከሶርያ ደማስቆ የደረሰኝ ተጨባጭ መረጃ ያስረዳል ። ከደማስቀስ የደረሰኝን ይህንን መረጃ መሰረት አድርጌ በዚያው ስላሉ እንደ ጨው የተበተንን ዜጎች ጩኸት በዛሬው የማለዳ ወጌ የምለው አለኝ …

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከአስመራ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ተናገሩ

ብረት አንስተው የሕወሓትን መንግስት እጥላለሁ ብለው አስመራ የዘመቱት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከአንድ ወር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር ቆይታ አድርገዋል:: ዶ/ር ብርሃኑ እርሳቸው ከዘመቱ በኋላ ሕዝብ እያወራው ስላለው ነገር ሲናገሩም “ጆሮ ሰጥቼ ስከታተለው አልነበረም” ብለዋል:: ሙሉውን ያድምጡት::

‹‹ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል›› በእስር ላይ ያሉ ጦማሪያን

‹‹አንድ ዳኛ ምንም ማድረግ አይችልም›› ዳኛ ዘሪሁን ደሳለኝ ‹‹ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል›› በእስር ላይ ያሉ ጦማሪያን በተጠረጠሩበት የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸው በኋላ የከሳሽ ዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ቀርቦባቸው ለብይን የተቀጠሩት አራት ጦማሪያን፣ ለአራተኛ ጊዜ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ተቃወሙ፡፡ ተከሳሾቹ ጦማሪያን ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፍ ብርሃኔና በፍቃዱ ኃይሉ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ብይን እንደሚሰጥ የጠበቁ ቢሆንም፣ ጉዳያቸው በሦስት ዳኞች የሚታይ ከመሆኑ አንፃር በዕለቱ አንድ ዳኛ አቶ ዘሪሁን ደሳለኝ ብቻ የተገኙ በመሆናቸው ብይኑ ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡

ሰበር ዜና ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት የሚመራዉ ጽንፈኛ ቡድን ድንጋጤ ላይ ወድቋል፤፤

asee
ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት የሚመራዉ ጽንፈኛ ቡድን ድንጋጤ ላይ ወድቋል፤፤
ዛሬ ይህዉ ወንጀለኛ ቡድን በመከላከያ ሚኒስቴር በኩል የመከላከያ ሰራዊቱ አጠቃላይ አዛዦችን ባጠቃላይ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል። በተለይም የሰሜኑና የምስራቁ እዝ አዛዦች ላይ ትኩረት ያደረገዉ ይህዉ ድንገተኛ ጥሪ የጦርነት ነጋሪትን ለመጎሰም ይመስላል ይላሉ መረጃዉን የላኩልን ግለሰብ።