Tuesday, January 8, 2013

ሕዝቦች የስልጣን ባለቤቶች ናቸው፡፡ የምርጫው ውጤትም በእጃቸው ላይ ነው፡፡ኢትዮጵያ ውስጥስ ?

ኢትዮጵያ ለዘመናት የነገሰና ስር የሰደደ ድህነት፣ ስራ አጥነትና ማህበራዊ ቀውስ የተንሰራፋባት ሃገር ናት፡፡ ኑሮ ያደቀቃቸው ዜጎች ከመተዳደር ለመገዛት የተመቹ መሆናቸው ዓለም የመሰከረው እውነታ ነው። የስራ እድል፣ ትምህርት፣ የቀበሌ ራሽን፣ የጤና አገልግሎት፣ የመሰረተ ልማት ፍጆታ፣ የመኖርያ ቤት አቅርቦት በገዢው ፓርቲና በመንግስት ችሮታ ስር በተያዙባት ኢትዮጵያ፤ የኢህአዴግ አባል መሆን በተለይ ደግሞ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኘው ማህበረሰብ የመብት ጉዳይ ሳይሆን አማራጭ የሌለው የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ በ2002 ምርጫ ኢህአዴግ 99.6 በመቶ ማሸነፍ ባልቻለ ነበር፡፡ 

Monday, January 7, 2013

ሕገ መንግሥቱ ይናገር

ሕገ መንግሥት የአንድ መንግሥታዊ ሥርዓት መሠረታዊ ሕግ በመሆኑ በአንድ አገር መንግሥትና ሕዝብ መካከል ያለውን የመብትና የግዴታ ግንኙነት የሚወስን፣ የሕግን ልዕልና የሚያረጋግጥ፣ ለማንኛውም ሥልጣን ገደብ የሚያበጅ፣ በዓበይት የመንግሥት አካላት መካከል የሥልጣን ክፍፍልን የሚያደርግ፣ በአሠራራቸውም ላይ ቁጥጥርን የሚያሰፍን፣ የዜጎችን መብቶችና ነፃነቶች የሚያረጋግጥና ግዴታዎችንም የሚጠቁም መሠረታዊ ሰነድ ነው፡፡

ብዙ ያልተነገረለት የወያኔ ራዕይ - የአፍሪካ አውራ ፓርቲ መሆን!



መቼም የፖለቲካ ኮሜዲው ደራሲያንና ተዋንያን ማን እንደሆኑ አይጠፏችሁም ብዬ አስባለሁ፡፡ ፖለቲከኞቹ ናቸዋ! ተደራስያኑ ደግም ምስኪኑ ህዝብ! (“ልማታዊ ህዝብ” ይባላል እንዴ?) ለነገሩ “የበይ ተመልካች” ወይም ታዛቢ ብንባልም አይከፋንም (ሃቅ ነዋ!) እናላችሁ ---- ፖለቲከኞቹ ይበላሉ፤ እኛ ኩራዝ እንይዛለን፡፡ ፖለቲከኞቹ ይወስናሉ፤ እኛ እንሰማለን፡፡ ምን ይደረግ … እጣ ፈንታችን እኮ ነው፡፡ (ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም!) ለነገሩ ተሰጥኦ ከሌለን ቀሽም ኮሜዲ ነው የምንሰራው (አያስቅ አያስለቅስ!) አያችሁ የፖለቲካ ኮሜዲ ችሎታ ይጠይቃል - ልዩ ተሰጥኦ!
እኔ መቼም የፖለቲካ ኮሜዲ ዘመን መሆኑ በጣም ነው ደስ ያለኝ (ምርጫ የለኝማ!) ግን እኮ በምናብ ባቡር (እውነተኛው ባቡር እስኪጀመር--) ወደ ኋላ ሸተት ብላችሁ የ60ዎቹን የፖለቲካ ተውኔቶች ብትመረምሩ የአሁኑን የፖለቲካ ኮሜዲ “ተመስገን!” ማለታችሁ አይቀርም፡፡ መቼም ከፖለቲካ ትራጄዲ የፖለቲካ ኮሜዲ ይሻላል፡፡ እኔ በበኩሌ ከምናዝን ቢቀለድብን እመርጣለሁ (Choosing the lesser evil እንደሚባለው!)

Friday, January 4, 2013

ከመለስ ወደ “መለሶች”



(በተመስገን ደሳለኝ)
እንደ መነሻ
በ1983 ዓ.ም. ወርሃ ግንቦት መንግስታዊ ስልጣን በሃይል የተቆጣጠረው ኢህአዴግ፣ ከጥቂት ወራት በኋላ ሃያ ሁለተኛ ዓመቱን ይደፍናል:፡ በእነዚህ አመታት አገዛዙ ያነበረውን ስርዓት በሶስት የዘመን ክፍፍሎች (Historical Periodization) ወይም ገፅታዎች ከፍለን (በጊዜ እና በግለሰቦች ላይ በተመሰረተ መስፈርት) ማየት እንችላለን፡፡ ከ1983 እስከ 1993 ዓ.ም-‹‹ቡድናዊ››፣ ከ1993-2004 ዓ.ም-‹‹ግለሰባዊ›› እና ከ2005…? ዓ.ም-‹‹ቡድናዊ›› በሚል፡፡
ከ1983-93
በእነዚህ አመታት ስርዓቱ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የፖለቲካ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል የሚል ተስፋ ከውስጥም ከውጭም ተጥሎበት ነበር፡፡ ይህንን ተስፋ ያጠናከረው በኃይል የወደቁት ቀደምት ስርዓታት በአዋጅ ያገዷቸውን፤ ማንኛውም ሰው በመረጠው የፖለቲካ አመለካከት መደራጀት እና ሀሳብን በነፃነት የመግለጽን መብቶች በአዋጅ በመፍቀዱ ነው፡፡ ከዚህ ክልከላ መሻር በኋላም በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶች መፈጠራቸው እና ነፃነታቸው ገደብ አልባ የነበረ ለቁጥር የሚያታክቱ የግል ፕሬሶች እንደ አሸን መፍላታቸው፣ እንዲሁም ለትችት ከተጋለጡት ጥቂት አንቀጾቹ በቀር የተወደሰለት ህገ-መንግስት መጽደቅ እና የመጀመሪያው ምርጫ መካሄድ በለውጡ ላይ የተጣለውን ተስፋ ያጠናከሩ አዎንታዊ ክስተቶች ነበሩ፡፡

Thursday, January 3, 2013

ሽምግልናውን ሲያካሒድ ከነበሩ አስታራቂዎች የቤተክርስትያን ኣባቶች መካከል ኣንደኛው ከኢትዮጲያ ሲባረሩ ሁለተኛው የደረሱበት ኣይታወቅም


የኣዲስ ኣበባዎቹ ተደራዳሪ ኣባቶች ባለፈው ሳምንት ያወጡት መግለጫ ተገደው የፈረሙበት መሆኑም ተገለጸ።በቅርቡ በዳካስ ቴክሳስ የረካሄደውን ሶስተኛ ዙር በሶሳንጀለሰ ካሊፎርንያ ለማካሔድ ቀጠሮ ይዘው ከተነሱት ኣባቶች ኣንደኛው የሆኑት ብጹነ ብጹነ ኣቡነ ገሪማ በገጠማቸው የጤና ችግር ኣሁንም በዮኤስ ኣሜሪካ አንደሚገኙ ለማወቅ ተችሉኣል።ቅዳሜ ታህሳስ 20/2005 ኣሜሪካ የደረሱት ሊቀ ካህናት ኃይለሰላሴ ኣለማየው ታግደው መባረራቸውን ለሾይስ ኦፍ ኣሜሪካ የአማርኛ አገልግሎት አረጋግጠዋል::

24 injured in ethnic conflict among university students

ADDIS ABABA - At least 24 students were injured on Thursday when ethnic-based clashes erupted among university students on Arat Kilo campus of Addis Ababa University.
The fights broke out when students heading to the cafeteria in the morning saw the walls of the main library on campus and other places covered with graffiti that denigrate the Oromo people.
ADDIS ABEBA UNVIVERSITY MAIN CAMPUS 
The violent clashes included window smashings and physical fights continued into the middle of the day, though police tried to quell the unrest several times. Police also threw into custody a handful of students suspected of playing leading roles in the unrest.

‹‹ሹመት ካልሠሩበት ምን ይፈይዳል?››

ሙስና እንደ ሸረሪት ድር በየቦታው አድርቷል፡፡ መልካም አስተዳደር ጠፍቷል፡፡ የሕግ የበላይነት አለ በሚባልበት አገር ፍትሕ ርቋል፡፡ በሕገ መንግሥት የተረጋገጡ መብቶች ተጨፍልቀዋል፡፡ ሥርዓቱን ሙስና እንደነቀዝ እየበላው ስለሆነ የመፍትሔ ያለህ እየተባለ ነው፡፡ እኔ የምለው ተሿሚዎቹ ይህንን ችግር ለማስወገድ ካልሠሩ ሹመታቸው ምንም አይረባንም እላለሁ፡፡ ይህንን ሐሳቤን ለጓደኛዬ ብነግረው በመገረም እያየኝ፣ ‹‹አስተያየትህን በአስቸኳይ ለኢቲቪ ለምን አትልክም?›› አለኝ፡፡ እኔስ ምኔ ሞኝ ነው? ‹‹ኢቲቪ ሐሳቤን ቆራርጦ በ‹‹አበረታች›› ሊተካው ስለሚችል ፌስቡክ ላይ ለጥፈዋለሁ፤›› ስለው አንገቱን እየወዘወዘ ሳቀብኝ፡፡ ወደ ስራችን ስናመራ፣ ‹‹ሹመት ካልሠሩበት ምን ይፈይዳል?›› ስለው፣ ‹‹ምንም! ነገር ግን ያስተዛዝባል፤›› አለኝ፡፡ ሹመት ችግር ካልፈታ ፋይዳቢስነቱ ገዝፎ ታየኝ፡፡ 
                                                  ከሰብኣዊ