Friday, January 2, 2015

ወያኔ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ የህዝቡን ሰላም ለማደፍረስ ስለሚያደርገው እንቅስቃሴ›› መረጃ ስጡኝ በሚል ለህዝቡ ቅጽ እያደለ ነው

(ነገረ ኢትዮጵያ) የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በሰላማዊ ሰልፍ ስም የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ በተመለከተ›› መረጃ እንዲሰጡት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቅጽ እያከፋፈለ መሆኑ ታወቀ፡፡
ምንም እንኳ በቅጹ ላይ ዜጎች ስለ ሰማያዊ ‹‹ጥሩና መጥፎ›› አስተያየት እንዲሰጡ ቢልም መጀመሪያ ላይ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ በሰላማዊ ሰልፍ ስም የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ›› ሲል ፓርቲው የህዝብን ሰላም እያደፈረሰ ነው ሲል ፈርጆታል፡፡

“ለኢትዮጵያ አንድነት በጽናት እንቆማለን” (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

(የፀሐፊው ማስታወሻ — ይህን ፅሁፍ በነጻነት ለሀገሬ ስም ለአማርኛ አንባቢዎቼ አቀርባለሁ። የነፃነት ለሀገሬ ትርጉሞች የረቀቁና የተጣሩ ናቸው። የነፃነት ለሀገሬን ድጋፍ በማግኘቴ ታላቅ ደስታና ክብር ይሰማኛል። ነፃነት ለሀገሬ ያልተዘመረለት/ያልተዘመረላቸው የኢትዮጵያ ጀግና/ጀግኖች ናቸው። ከፍተኛ ክብርና አድናቆቴን ለነፃነት ለሀገሬ አቀርባለሁ/አቀርብላቸዋለሁ! ትግሉ ይቀጥላል ለነፃነት ለሀገሬ!!!)
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የአፍሪካ አሜሪካዊ ደራሲ፣ ገጣሚ፣ የዳንስ ተወዛዋዥ፣ ተዋናይ እንዲሁም የሙዚቃ አቀንቃኝ የሆነችው ማያ አንጌሉ እንዲህ በማለት አውጃ ነበር፣ “የእኛን ጀግኖች እና ጀግኒቶች ማስታወስ እና መዘከር እንዴት ያለ ጠቃሚ ነገር ነው!“እኛም እነዚህንም የሀገር ጀግኖች እና ጀግኒቶች ተራ በተራ እያነሳን እናክብራቸው፣ እናወድሳቸው ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ሀገሪቱ ከገባችበት ማጥ ውስጥ እንድትወጣ ለማድረግ እና ነጻነት እና ዴሞክራሲ በሀገራችን እንዲሰፍን እራሳቸውን ለመስዋዕትነት ያቀረቡ የሀገር ዕንቁዎች ናቸውና፡፡

መልዕክት ከቂሊንጦ እስር ቤት! አብርሃ ደስታ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
‹‹እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም›› አብርሃ ደስታ
እዚህ እስር ቤት ውስጥ በሽብር ስም የገባ ሰው በፈጠራ ወንጀል እንደገባ ነው የሚታመነው፡፡ ስለዚህ የሽበር ክስ ተመስርቶባቸው የታሰሩትን ሰዎች ማንም ወንጀለኛ አድርጎ አይመለከታቸውም፡፡ በእርግጥም አሸባሪ የለም፤ የፈጠራ ክስ ነው ያሳሰራቸው፡፡ አሸባሪ አለ ከተባለም እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም፡፡
ነጻ መውጣት ያለበት ቡድን አለ፣ እሱም ኢህአዴግ ራሱ ነው፡፡ እኔ አልታሰርኩም፡፡ የታሰሩት ኢህአዴጎች ናቸው፡፡ እስር የአዕምሮ ነው፡፡ እኔ አዕምሮየ አልታሰረም፡፡ ነጻ ሰው ነኝ፤ ውስጤ በጣም ነጻነት አለው፡፡ የታሰሩት ኢህአዴጎች ናቸው፡፡Ethiopian political activist Abraha Desta
እኔ እስር ቤት እንድገኝ ያደረገኝ ወንጀል አይደለም፡፡ መቃወሜና ይህን ተቃውሞየን በጽፍም በፊት ለፊትም መግለጼ ነው፡፡ ይህን ደግሞ ብዙ ኢትዮጵያውያን ያውቁልኛል፡፡ ሌላው ቢቀር ጥቂት የህወሓት ሰዎችም ያለ መረጃ እንደታሰርኩኝ በማመን እስሩን እየተቃወሙ ይመስለኛል፡፡ አንድ ቀን ወደ ህሊናቸው ከተመለሱ ስህተታቸው በህዝብ ፊት ያዋርዳቸዋል፡፡

መለስ ሰርቶ ያልጨረሰው አሻንጉሊት

ቹቸቤ
ለኃይለማርያም ደሳለኝ የተጻፈ ሽሙጥ
ይህን ለሕዝብ ጆሮ ብሎ መጻፉ በራሱ ሰቅጣጭ ቢሆንም አንዳንዴ ስቆ ለማለፍም መጋራት ይበጃል እናም ለሳቸው እንዲህ ብዬ ብነግራቸው ጥሩ ነበር ያልኩትን ለናንተም አካፍላለሁ።Hailemariam Desalegn, Meles Zenawi's unfinished toy
አቶ ሐይለማርያም ሆይ ስለ እርስዎ ማፈራችን እስከመቼ ይቀጥላል? ገና መናገር ሲጀምሩ ስቅቅ ይለኛል። ተናግረው ሲያበቁ ሙሉ ሰው መሆንዎንም ማመን ያቅተኛል። እንዲያውም አሁን አሁንማ መለስ ጀምሮ በወጉ ያልጨረሰው አሻንጉሊት ይመስሉኛል። መለስ ኮርጀን ገልብጠን ቢል ያምርበታል መገልበጥም መኮረጅም ማስመሰልም ማድበስበስም የክብር የዶክትሬት ዲግሪ የሚያሰጠው ብልጥ ሰው ነው በቃ ሞላጫ አራዳ የሚሉት አይነት ነው።

የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እንኳን አደረሰን !

ከምንም በላይ ግን ያኔ ከመነሻው ለአገር እና ለህዝብ የሚጠቅም ፓርቲ እንመስርት ብለን፣ገንዘባችን፣ ጊዜያችን፣ እውቀታችን ሳንሰስት በመስጠት፤በወቅቱ ፓርቲ እንመስርት ማለታችን ትክክል እንደነበር የዛሬ ውጤታችን ምስክር ነው ! 
-----------------------------
ሰማያዊ ፓርቲ ከተመሰረተ አሁን ሦስተኛ ዓመቱ ነው፣የአገራችን አሉታዊ እና አዎንታዊ ፖሊቲካ ድርጊቶችና ክስተቶችን በመመርመር የመፍትሔ አካል ለመሆን በአገር ወዳድ ኢትየጵያዊያን ታህሳስ 22/2004 ዓ.ም በይፋ ተመሰረተ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በእውነት እና በእውቀት ላይ የተመሠረተ ሰላማዊ ትግል በማድረግ ፣የዜጎች የሥልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ አባላቱ እና ደጋፊዎችሁ እያሣየነው ያለው ቁርጠኝነት እና ታማኝነት ለፓርቲያችን ጥንካሪ ዋንኛ መሠረት ነው፡፡ 
ሰማያዊ ፓርቲ ከምስረታው ጀምሮ ያስመዘገባቸው አኩሪ ድሎች፣ በአገራችን እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ ቁጥራቸው ከበዛ ፓርቲዎች ተርታ፣ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠሩ አንዱ ለመሆነ ችሎአል፡፡ፓርቲያችን ከተመሠተር እና ወደ እንቅስቃሴ ከገባ አጭር ጊዜ ቢሆነውም ፣በኢትዮጵያዊያን ካለው ተቀባይነት እና በገዥው መንግስት ላይ እያሣደረ ያለው አስጨናቂ ተፅኖ በመመልከት አንዳንድ ታዛቢዎች ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ? በማለት ይጠይቃሉ፣ መልሱ ግን አጭር ነው፡፡

አላስፈላጊ ልማት ከጥፋት አይተናነስም!

ቅድሚያ ተሰጥቷቸው መከናወን ያላባቸው የልማት ስራዎችን በአስተማማኝ መልኩ ባልተረጋገጡበት ሁኔታ ወቅቱን ያልጠበቀና የብዙሀኑን የልማት ጥያቄ መመለስ የማይችል ልማት ተገቢ ልማት ተደርጎ አይወሰድም። ቅድሚያ መሰጠት የሚገባቸውን አንገብጋቢ የህዝብ ጥያቄዎችን ቅድሚያ መሰጠት ሲገባ የተጀመሩ ሰፋፊ የልማት ስራዎች በጅምር በቀረቡት ሁኔታ ከአቅም በላይ የሚደረግ ዝላይ ለመፈጥፈጥ ካልሆነ በቀር ፋይዳው አይታየኝም። ከፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ውጪ በገጠር ዝናብን ጠብቆ መሬት በመርፌ እየጫረ የሚተዳደር አርሶ አደር ይዞ፣ በከተማ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ስራ አጥ ወጣት እያርመሰመሱ፣ አገሪቱ በአለም የስደተኛ ምንጭ በመሆን ቀዳሚውን ቦታ በያዘችበት በአሁኑ ወቅት ሮኬት የማስወንጨፍ ልማት የሚለው ፉገራ ተቀባይነት የለውም።

Friday, December 26, 2014

ለሥልጣን ለውጥ ወይስ

ይድነቃቸው ከበደ
ይህን ለማለት የሚያስደፍረው በአገራችን የሚካሄደው ምርጫ፣ የፖለቲካ ወይም የዲሞክራሲ ቅንጦት ሣይሆን፣ የአገር እና የዜጎች የእልውና ጉዳይ መሆኑ የሚያረጋገጥ የበዛ ምክንያት በመኖሩ ነው፡፡
----------------------
የትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ እራሱን ለምርጫ በማቅረብ ያወዳድራል፤በምርጫም ካሻነፈ የመንግሥትነትን ሥልጣን ይይዛል፡፡በምርጫ ዕድል ካልቀናው የተቃዋሚውን ቦታ ይዞ መንግስት ለሚያቀርበው ፓሊስ እና ፕሮግራም ነቀፌታ ወይም አማራጭ አሳብ በማቅረብ የተለመደው የፖለቲካ ሥራ ይሰራል፡፡ እንዲህ አይነቱ የፓርቲዎች አደረጃጀት እና አሰራር በሰፊው የተለመደ ጤናማ አካሄድ ነው፡፡የፖለቲካ ሊቃውንት ከላይ የተገለፀውን አካሄድ ጤናማ ነው ሲሉ፣ዋንኛ መመዘኛቸው ያልተንዛዛ በዛ ቢባል ፣ከሁለት ዙር ያለፈ የስልጣን ዘመን እንደማይኖር ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡በተለይ እንዲህ አይንቱ የፓርቲዎች እንቅስቃሴ ፣በከፍተኛ ዲሲፕሊን እና በተቀናጀ የሙሉ ጊዜ የፓርቲ ስራ ላይ በሚያሳልፉ ታጋዮች የሚከናወን ጥበባዊ ስራ ነው፡፡