(ነገረ ኢትዮጵያ) የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በሰላማዊ ሰልፍ ስም የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ በተመለከተ›› መረጃ እንዲሰጡት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቅጽ እያከፋፈለ መሆኑ ታወቀ፡፡
ምንም እንኳ በቅጹ ላይ ዜጎች ስለ ሰማያዊ ‹‹ጥሩና መጥፎ›› አስተያየት እንዲሰጡ ቢልም መጀመሪያ ላይ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ በሰላማዊ ሰልፍ ስም የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ›› ሲል ፓርቲው የህዝብን ሰላም እያደፈረሰ ነው ሲል ፈርጆታል፡፡
ቅጹ ከተሰጣቸው መካከልም አንድ የኮልፌ ቀራኒዮ ነዋሪ ቅጹን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ሲል ለኢትዮ ምህዳር የላከ ሲሆን ‹‹ይህንን አስገራሚ ቅጽ እንድንሞላ በአንድ ክ/ከተማ በተገኘንበት ስብሰባ ላይ ለተሰብሳቢው ሁሉ ታደለ፡፡ ታዲያ ሁሉም ቅጹን ወስዶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ እኔም የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ለጋዜጣችሁ ዝግጅት ክፍል ልኬዋለሁ፡፡ አይገርምም ሕገ-መንግስት የሚፈቅደው ሰላማዊ ሰልፍ አንቀጽ በመንግስት አስፈጻሚዎች ሲጣስ›› በሚል አስተያየታቸውን አስፍረዋል፡፡
No comments:
Post a Comment