ጀግናዋ ጎንደሬ ጣይቱ ብጡል የተንጎራደደችበት ለሃገራችን ኢትዮጲያ የስልጣኔ ምልክት የነበረው ጣይቱ ሆቴል ሲቃጠል አንጀቴ ቅጥል ነው ያለው ፡፡
ያቺ ያገር እናት እመት መላይቱ
ዛሬም በልቤ ውስጥ በርታለች ጣይቱ
ዛሬም በልቤ ውስጥ በርታለች ጣይቱ
ከሃይለስላሴ ዘውድ መጫን በኋላ ታሪኳ ሆን ተብሎ እንዲደበዝዝ የተደረገችው የደብረታቦሯ የብጡል ወሌ ልጅ ጣይቱ በአፍሪካ ምድር በጊዜው እንደሷ ገናና ጀግና ሴት ተነስቷል ብሎ መናገር ይከብዳል፡
አንዳንድ የታሪክ ጸሃፊያን የአድዋ ድል በጣይቱ ብጡል ሞራል የተሰነቀ ድል ነው ብለውላታል እቴጌ ጣይቱ ንጉስ ምኒሊክ ግዛቱን ለማስፋፋት እና ማእከላዊ መንግስት ለማቋቋም በነበረው የመስፋፋት ፍላጎት ወደ ደቡብ እና ወላይታ ለመዝመት ባቀደ ጊዜ የምኒሊክ ጦር የሚወስደው ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ስለነበራት ከመኳንንቱ ጋር በከፍተኛ ሁኔታ በብስጭት ትከራከር እንደነበት ይነገርላታል፡፡
እቴጌ ጣይቱ ጣሊያን ትግራይን ለመውረር እና ግዛቱንም ወደ ኤርትራ ለማካተት ባሰበ ጊዜ ንጉስ ምኒሊክ ቸል ማለታቸውን ተመልክታ "ትግራይ ተቆርሶ አንተ የማን ንጉስ ልትባል ነው" ብላ ንጉሱን በአሽሙር እንደሸረደደቻቸው ይነገራል።
ጣይቱ ብጡል ምንም እንኳን መጨረሻዋ የሚያሳዝነኝ ብትሆንም እጅግ በርካታ ጉልህ ታሪክ ያላት ጀግና ሴት ነበረች።
ታዲያ መሃል ፒያሳ ከእነ ግርማ ሞገሱ የተኮፈሰው የስሟ መጠሪያ ሆቴል በእሳት ሲነድ ከምር በጣም ያበሳጫል ይሄ ብርቅየ ታሪካዊ ሆቴል ለባለ ሃብት ከመሸጥ እና ማገልገል ካለበት እድሜ በላይ አገልግሎት እንዲሰጥ ከማድረግ ይልቅ በሙዚየምነት ቢጠበቅ ኖሮ ይሄንን ዘግናኝ ሁኔታ ማየት ባልቻልን ነበር።
በጣም ያሳዝናል----በቃ እኔ በጣም አዝኛለሁ።
No comments:
Post a Comment