አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 14፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የፌደራል አቃቤህግ በ2001 ዓ.ም አቶ ተፈራ ማሞን ጨምሮ 46 ሰዎች በሽብር ወንጀል ክስ ሲመሰርትባቸው፤ 39ኛ ተራ ቁጥር ላይ ነበር ስማቸው የሰፈረ ሲሆን፥ በወቅቱ እድሜያቸው 53 አመት ነበር ።
አቃቤህግ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ ሁሉንም ተከሳሾች ራሱን የዴሞክራቲክ ጋርድ ብሎ በሚጠራው የሽብር ቡድን ውስጥ ከአባልነት አስከ አመራርነት ተሳትፎ አድርገዋል በሚል ነው የከሰሳቸው ፤ ይሄ የሽብርና የአመጽ የሲቪል ቡድን በህቡዕ የተደራጀው በ1998 ዓ.ም ነው።
አቃቤህግ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ ሁሉንም ተከሳሾች ራሱን የዴሞክራቲክ ጋርድ ብሎ በሚጠራው የሽብር ቡድን ውስጥ ከአባልነት አስከ አመራርነት ተሳትፎ አድርገዋል በሚል ነው የከሰሳቸው ፤ ይሄ የሽብርና የአመጽ የሲቪል ቡድን በህቡዕ የተደራጀው በ1998 ዓ.ም ነው።
ቡድኑ በ2000 ዓ.ም መንግስትን በሃይልና በአመጽ ለመጣል ራሱን ችሎ ከተቋቋመውና ራሱን የኢትዮዽያ የነጻነትና ዴሞክራሲ ሃይል ብሎ ከሚጠራው ወታደራዊ ቡድን ጋር ግነኙነት የፈጠረ ሲሆን፥ እነዚህ በተናጠል የተቋቋሙ ቡድኖች የገንዘብና የሎጀስቲክ ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችላቸውን ስምምነትም ያደርጋሉ
የቡድኑ አባላት በሃገር ውስጥ የአሸባሪው ግንቦት 7 አባላትን አገኘናቸው ብለው እጅ እግራቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም፥ ይልቅስ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማግኘት ዱባይ አቀኑ ነው የሚለን የአቃቤህግ ክስ።
ዱባይ ያቀኑት የዴሞክራቲክ ጋርድ እና የኢትዮዽያ የነጻነትና ዴሞክራሲ ሃይል የተባሉ የሽብር ቡድን ተወካዮች ፤ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ትውውቅ ካደረጉ በኋላ የአድማ ስምምነታቸውን አጠናክረው ተመልሰዋል፤ ከዚያም በአዲስ አበባ ጎጃም በረንዳ በተባለው አካባቢ ተሰብስበው በቡድኑ መተደደሪያ ደንብና ስትራቴጂ ላይ መክረው፣ ኮሚቴ መርጠው የስራ ክፍፍል አድርገዋል።
መጋቢት 2001 ዓ.ም ሁለት የወታደራዊ ቡድኑ ተወካዮች በድጋሚ ዱባይ አምርተው፥ ከግንቦት 7 ድርጅት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ተገናኝተዋል።
ዱባይ ላይ በነበራቸው ውይይት ግድያ የሚፈጸምባቸው ባለስልጣናት ፤ የሽብር ጥቃት የሚሰነዘርባቸው የመንግስትና የልማት ተቋማት ላይ ሰፊ ውይይት አካሂደው ውሳኔ አስተላልፈዋልም ይላል የክስ መዝገቡ።
ከአዲስ አበባ ለዚህ የሽብር ተልእኮ ዱባይ ያቀኑት የወታደራዊ ቡድን ተወካዮችም ይህንን ተልእኮ ለማሳካት ገንዘብ ያስፈልገናል ሲሉ ለዶክተር ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ጽጌ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፥ የአሸባሪው ግንቦት 7 ድርጅት መሪዎቹ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ጽጌ ለቡድኑ ተወካዮች 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ሰጥተዋል።
የቡድኑ ተወካዮች የገንዘብ እና የፖለቲካ ድጋፉን ከእነ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከተቀበሉ በኋላ ሃገር ቤት ተመልሰውም ከእነርሱ ጋር በያንዳንዷ የሽብር እንቅስቃሴ በአንድነት መስራታቸውን ተያይዘውታል።
ከውጭ ሃገር ከእነ አቶ አንዳርጋቸው የሚላክላቸውን ማናቸውንም አይነት ድጋፍ የሚያገኙት የወታደራዊ አና የዴሞክራቲክ ጋርድ የተሰኙ የሽብር ቡድኖች በአዲስ አበባ በአማራና በሌሎች ቦታዎች አባላትን መልምለዋል ነው የሚለው ክሱ።
እነ አቶ አንዳርጋቸው በሻዕቢያና ኦነግ እየተደገፉ ሃገር ቤት ላደራጇቸው የሽብር ቡድኖች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አድርገዋል።
አቃቤህግ የሀገሪቱን የፖለቲካ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ህገ መንግስታዊ ተቋማትን በማፍረስ በመንግስት ላይ ተጽእኖ ለማሳደር በማሰብ፤ የአድማ ስምምነት በማድረግ የወንጀል ድርጊትን አላማ ግቡንና ውጤቱን ሙሉ በሙሉ በመቀበል በአመራር ሰጪነት ፈጻሚነት እና አስፈጻሚነት የሽብር ተልዕኮ በመስጠትና በመቀበል፣ የሽብር ድርጊቶችን ለመፈጸም በማሴር ፣ በማቀድ፣ በማነሳሳትና በማዘጋጀት ነው አቃቤህግ አቶ አንዳረጋቸው ጽጌን ጨምሮ በጋራ 46ቱንም የከሰሳቸው።
ከፌደራል አቃቤህግ ይህ ክስ የደረሰው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 2ኛ የወንጀል ችሎት በግንባር ቀርበው የተከራከሩትን የቅጣት ማቅለያቸውን ተቀብሎ ተመጣጣኝና አስተማሪ ቅጣት ሲጥልባቸው፤' አይደረስብኝም ብለው በባእድ ሃገር ሆነው የዚህ የወንጀል ድርጊት ጠንሳሽ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ቅጣት ለማቅለል የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት ባለማግኘቱ፤
ችሎቱ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በዜጎች እና በመንግስት ላይ ጉዳት ማድረስን ሙያ አድርገው የያዙ ተደጋጋሚ አጥፊ ናቸው በማለት በ2002 ዓ.ም በሞት ይቀጡ በማለት ነው ውሳኔ አስተላልፎባቸው የነበረው።
ችሎቱ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በዜጎች እና በመንግስት ላይ ጉዳት ማድረስን ሙያ አድርገው የያዙ ተደጋጋሚ አጥፊ ናቸው በማለት በ2002 ዓ.ም በሞት ይቀጡ በማለት ነው ውሳኔ አስተላልፎባቸው የነበረው።
ግለሰቡ ከዚህም ሌላ አቃቤህግ በ2004 ዓ.ም በተመሳሳይ የሽብር ወንጀል ከሷቸው፤ በእነ አንዷለም አራጌ መዝገብ በ9ኛ ተራ ቁጥር ላይም ስማቸው ሰፍሯል።
በክስ መዝገቡ ከተጠቀሱ ሌሎች 23 ግለሰቦች ጋር በመሆን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በአሸባሪነት ከተፈረጁ ኦነግ፣ ኦብነግ እና ከኤርትራ መንግስት ጋር ኢትዮዽያ ውስጥ አመጽ በማነሳሳት፣ ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል የሚል ይዘት ያለው ክስ ነው የተመሰረተባቸው ።
ለዚህ አመጽ የተዘጋጁ ሃይሎች በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ባለስልጣኖችን እንዲገድሉ፣ የገንዘብ ተቋማትን እንዲዘርፉ የሚል ተልእኮ ተሰጥቷቸው የነበር ሲሆን፥ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሚመሩት በአሸባሪነት የተፈረጀው የግንቦት 7 ድርጅትም የዚህ የወንጀል ጥንስስ መሪ መሆኑን ነው ክሱ የሚያመላክተው።
ስርዓቱን በትጥቅ አመፅ ለመጣል የጋራ የወንጀል አድማ ስምምነት በመፍጠር፥ በመደራጀታቸው፣ በማደራጀታቸውና በመምራታቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ ናቸው ሲል አቃቤህግ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ 24ቱንም ግሰለሰቦች ከሷቸዋል።
አቶ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ሁሉም ተከሳሾች ህገ መንግስቱንና የተቋቋመውን ስርአት በሃይል ለማፍረስ ለመለወጥ ሞክረዋል የሚለውም በክሱ ውስጥ ተጠቅሷል።
በተለይም በክስ መዝገቡ ተጠቅሰው ነገር ግን በውጭ ሃገር የሚኖሩ እነ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፤ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ፣ አበበ ገላው እና ሌሎችም ፤ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በትጥቅ አመጽ ለመናድ በህቡዕ ተደራጅተው የጦር መሳሪያ በመግዛት ቁሳዊ እና የገንዘብ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወታደራዊ እና ሲቭል ቡድን በመፍጠር፤ ደንብና መመሪያ አውጥተዋል፣ የሽብር እቅዶችን ስትራቴጂ ስልትና የማስፈጸሚያ አማራጮችን ለይተዋል ነው የሚለው የአቃቤህግ ክስ።
በዚህ የክስ መዝገብ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጎላ ብለው ቢታዩም ከጥቂት አጋሮቻቸው ጋር በሌሉበት ነው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤተ 3ኛ የወንጀል ችሎይ ጉዳያቸውን የተመለከተ ሲሆን፥ አቃቤህግ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወንጀሉ የነበራቸውን ተሳትፎ በዝርዝር አስቀምጧል።
የአሸባሪው የግንቦት 7 ድርጅት ከፍተኛ አመራር እና መስራች የነበሩት አንዳረጋቸው ጽጌ ከጥር 2003 ጀምሮ፤ ከሃገር ውስጥ ተመልምለው ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ኤርትራ የተላኩ የአሸባሪው የግንቦት 7 ድርጅት አባላትን ኤርትራ ሆነው አቀባበል አድርገውላቸዋል የሚለው ክስ እርሳቸው ላይ ብቻ የተመሰረተው ነው።
ከኤርትራው የደህንነት ክፍል ሃላፊ ኮለኔል ፍጹም እና ተስፉ ከሚባሉት ጋር በመሆን ምልምሎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ካለ በኋላ ወደ ወታደራዊ ስልጠና እንዲገቡ አድርጓል ይላል ክሱ።
አቶ አንዳርጋቸው ሰልጣኞቹ ለሽብር ድርጊታቸው የሚረዳቸውን የኮምፒውተር አጠቃቀም፤ ምስጢራዊ መረጃ አያያዝና የመልእክት ልውውጥ ዘዴን እንዲሁም ፤ በኤርትራ ወታደሮች አማካኝነት መሳሪያ የመፍታትና የመገጣጠም የፈንጅ አጠማመድ ስልጠና እንዲያገኙም አስደርገዋል ይላለ ክሱ።
ምልምሎቹ ስልጠናቸውን አጠናቀው ከተመለሱ በኋላ በሃገር ውሰጥ ለአሸባሪው የግንቦት 7 አባላትን እንዲመለምሉ፣ እንዲያደራጁና ለሽብር ተልእኮ ምቹ እንዲሆኑ የማድረግ አላማ አስታጥቋቸዋል የሚለውም በክሱ ተዘርዝሯል።
ይህ ብቻ አይደለም ፈንጂ እንዲያፈነዱ የመንግስትን ተቋማት እንዲያወድሙ የገንዘብ ተቋማት ላይ የዘረፋ ተግባር እንዲያካሂዱና መሰል የሽብር ድርጊቶችን እንዲፈጽሙ፥ ከገንዘብ ጉርሻ ጋር ይህንን እኩይ ተልእኮ አስረክቧቸው ነው ወደ ሀገር ቤት የላካቸው አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ።
ጉዳያቸውን በግንባር ተገኝተው የተከራከሩት እነ አቶ አንዷለም አራጌ ፣አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ እና ሌሎች ተከሳሾች ፍርድ ቤቱ የቅጣት ማቅለያዎቻቸውን ከግምት ውስጥ አስገብቶ ቅጣታቸውን ሲያቀልላቸው ፤ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንደ ቀደመው በግንባር ተገኝተው አልተከራከሩምና ችሎቱ ቅጣት ለማቅለል የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት አላገኘሁም በማለት ፤ በዚህኛው መዝገብ ግለሰቡ ጥፋተኛ በተባሉባቸው 3 ክሶች ችሎቱ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እና ለ5 አመት ከህዝባዊ መብታቸው ይሻሩ በማለት ነው ቅጣት ያሰተላለፈባቸው።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቀደም ሲል በ2002 ዓ.ም ጠፋተኛ በተባሉበቸው ክሶች በሞት እንዲቀጡ ፣ በ2004 ዓ.ም ደግሞ በእድሜ ልክ ፀኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላለፎባቸው የነበር ቢሆንም እስካሁን ቅጣቶቹ ተግባራዊ አለመሆናቸው ይታወሳል።
በጥላሁን ካሳ
No comments:
Post a Comment