ወያኔና ንብ ከአፋቸው ማር ከሆዳቸው መርዛማነት አላቸው።
ምርጫ ሊደርስ በወራቶች የሚቆጠር ግዜ ቀርቶታል ልዩ ምልክቱ ንብ ስሙ TPLF ስራው ጥፋት። ንብ የመረጡት ሰራተኛ ነኝ ለማስባል በሆዳቸው ያለውን መርዝ መናገር የማይወዱ ግን መርዘኝነታቸውን ህብረተሰቡ የተረዳቸው በዲሞክራሲ ስም አደናቋሪ የግን ሞት (ግንቦት) ምርጫ እየደረሰ ነው።በግን-ሞት (በግንቦት) ምርጫ ንብ ይዘው ማሯን ሳያሳዩ መርዟን ታቅፈው ሳይመረጡ ተመረጥን ሳይሾሙ ተሾምን ሳይፈለጉ ተፈለግን የሚሉበት ግዜ እየተቃረበ ነው። ወያኔ ከህዝቡ ልቦና ከወጣ ህዝቡም አንቅሮ ከተፋው ቆይቷል። በመርዝ የተለወሰ የጣፈጠ የሚመስል ወሬ ለአለም መንግስታት በተቆጣጠረው ሚዲያ እና በተለያዩ አገራት በሚጋበዘው መድረክ ላይ ዲሞክራሲ፣ ልማት፣ የህዝቦች እኩልነት፣ እያለ በሚደሰኩረው ዲስኩር ካደጉ አገራት እርዳታን በመለመን እና ብድራትም በመሰበሰብ እራሱን በማደለብ አገሪቷን እና ህዝቧን ደሃ በማድረግ ሊቆይ የሚችልበትን የጥፋት ስራውን ሽር ጉድ ማለት ከጀመረ ውሎ አድሯል። ወያኔ በመርዝ የተለወሰ ማር በየግዜው በማቅረብ በሆዱ ያለውን መርዝ መሸፈኛ አድርጎ በምርጫ ሸፍኖ ቆይቷል። እስቲ ንብና ወያኔን እንዴት እንደተስማሙ እናያለን።
ንብ፡- በአንድ የንብ ቀፎ ውስጥ ሶስት የተለያዩ ንቦች አሉ
- ንግስቲቷ(አውራ) ንብ
- ድንጉላ ንብ
- ሰራተኛ ንብ
ንግስቲቷ ንብ በይዘቷ ረዘም ብላ ሽንጥ ያላት ስትሆን በቀፎ ውስጥ አንድ ብቸኛ ንግስት ሆና የምትኖር ናት። የሁሉ መሪ ሁሉን አስተዳዳሪ በቀፎ ውስጥ ያሉት ንቦች የሚታዘዙላት የንግስቲቷ መኖር የቀፎው ንብ መኖር የንግስቲቷ መጥፋት የንቦቹ መጥፋት ሆና በቀፎ ውስጥ ተከብራ እና ነግሳ የምትኖር ንግስት ናት።
ድንጉላ ንብ በይዘቱ ከሰራተኛው ንብ ከፍ ያለ ሲሆን በቀፎ ውስጥ በጣም ትንሽ ቁጥር ያለው ሆኖ የሚኖር ሲሆን ሁል ግዜ ሳይሆን ዘር ለመተካት ከመጣ በኃላ ለተወሰነ ግዜ ታይቶ የሚጠፋ ነው።
ሰራተኛ ንብ በይዘታቸው ከንግስቲቱ እና ከድንጉላው ያነሱ ሲሆኑ በብዛት እና በቀፎ ውስጥ ያለውን ስራ በመሰራት ድርሻ ያላቸው ንግስቲቷንም እንደወታደር ሆኖ በመጠበቅ የሚያገለግሉ ሆነው የሚኖሩ ናቸው።
በወያኔ፡- መንግስት ሶስት የተለያዩ አካል አሉ
1.ንጉስ
2.ሚንስተሮች
3.ካድሬዎች
ወያኔ በአንድ ንጉስ የሚመራ ሁሉም በንጉሱ የሚስተዳደሩ ሁሉን ፈላጭ ሁሉን ቆራጭ ሁሉን አድራጊ ሁሉን ሰሪ ለወያኔ ጠቢብ የሆነ ንጉስ የነበረ።
ሚንስተሮች በንጉሱ የሚመሩ ያለንጉሱ ፈቃድ መስራት የማይችሉ የንጉሱ ትዛዝ ተቀባዮች እና ትዛዝ አስፈጻሚዎች ያለንጉሱ ህይወት የሌላቸው ያለንጉሱ መስራት የማይችሉ ንጉሱ ሲፈልግ የሚሾማቸው ሲፈልግ የሚሽራቸው ያለ ንጉሱ ህይወት የሌላቸው ሲሆኑ በቁጥርም ብዙ ጥቂት ናቸው።
ካድሬዎች በቁጥራቸው የበዙ ሲሆኑ ንጉሱ የፈለፈላቸው በየስርቻው ያሰማራቸው ንጉሱ አድርጉ ያላቸውን የሚያደርጉ አታድርጉ ያላቸውን የማያደረጉ የንጉሱን ንግግር እንደ ጸሎት መጽሐፍ እየደጋገሙ የሚጠቀሙ እንደ መድኃኔዓለም ምስል የንጉሳቸውን ፎቶ በኪሳቸው ይዘው የሚዞሩ በቢሮአቸው በትልቁ ግድግዳ ላይ ሰቅለው ሲገቡና ሲወጡ የሚሳለሙት የንጉሱን አላማ የሚያራምዱ የንጉሱን ቃል የሚጠብቁ ናቸው።
ወያኔዎች ንጉሳቸውን አርቀው ነው የሾሙት አርቀው ነው የካቡት ሊደርሱበት በማይችሉት አኳሃን። ንጉሳቸው ለእነርሱ ሁሉን አዋቂ እርሱ ህግ አርቃቂ እርሱ ህግ ተርጓሚ እርሱ ጥበባቸው እርሱ ፈላስፋቸው እርሱ መመሪያቸው እርሱ መሪያቸው እርሱ ሁሉ ነገራቸው ነው። እንደዚህ የካቡት መሪያቸው ምን አይነት ስራ ይሰራ እንደነበረ ታሪክ እራሱን ሲደግም ስራው ሁሉ የሚነበብበት ግዜ እሩቅ አይደለምና ያኔ የስራው ስራ በግልጽ የምናየው ጉዳይ ነው።
ወያኔዎች ንጉሳቸው ሁሉን ነገር የሚሰራላቸው ትግሉን ሁላ ሳይቀር የሱ ድል አድርገው የሚያምኑ በንጉሳቸው መልክ የሚደሰቱ በስራው የሚያምኑበት ሁሉ ነገር ለንጉሳቸው የሰጡት የተናገረውን ንግግር እንደ አየር መልሰው መልሰው ወደ ውስጥና ውጪ በማውጣትና በማስገባት እንደ እስትንፋስ ንጉሱ የተናገሩትን ንግግራቸውን የሚደጋግሙት መሪያቸው የነበሩ ነበረ።
ወያኔዎች ንጉሳቸውን እሳት ብለው የሚጠሯቸው ካድሬዎቹ ደግሞ ብረት የሆኑላቸው የብረት ጫፏን እሳታዊው ንጉሳቸው ሲነኳት በሙሉ የሚግሉላቸው ከዛም ንጉሱ በሚፈልጉት ቅርጽ ቀጥቅጧቸው የሚሰሯቸው እና የሰሯቸው ናቸው። ንጉሱ በራሱ ሞዴል ቀርጾ የሰራቸው ካድሬዎች የአስተዋዩን ህዝብ ጆሮ የንጉሳቸውን ንጉስነት ማህበረሰቡ ሳይቀበላቸው ሳይፈልጋቸው የሁሉም ንጉስ እንደሆነ ሲያደናቁሩ ይከርማሉ። ምን ያድርጉ ወያኔዎች ከንጉሳቸው ውጪ ህይወት የሌላቸው እንደሆነና ስራም መስራት እንደማይችሉ የንጉሱ የስራ ውጤቶች እንደሆኑ ይታወቃል።
የወያኔ ንጉሳቸው ሁሉንም የሚያዝ ነው ልክ እንደ ንግስቲቷ ንብ። በቀፎ ውስጥ ያሉት ንቦች መኖር የሚችሉት ንግስቲቷ እስካለች ድረስ ነው። ንግስቲቷ የለችም ማለት በቀፎ ውስጥ ያሉት ንቦች ሁሉ ቃስ በቃስ እየሞቱ እና እየተፉ በኋላ ቀፎው ባዶ ይሆናል። ወያኔም ንጉሳቸው ስለሞቱ ቃስ በቃስ እየሞቱ እና እየጠፉ ይመጣሉ። አጠፋፋቸው ግን በሁለት መንገድ ነው።
1ኛ. ንጉሳቸው ስለሌለ የሚሰበስባቸው ባለመኖሩ ሁሉን አጠቃሎ የሚሰራላቸው ስለሞተ ወያኔዋች እርስ በራሳቸው መደማመጥ ስለማይችሉ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ በመሃላቸው ስላለ እኔ ትክክል ነኝ እኔ አዋቂ ነኝ እኔ ቀዳሚ መስራች ነኝ በሚል ስለማይግባቡ ለኔ ይህ ይድረሰኝ ለኔ ይሄኛው ይገባኛል እያሉ ያገሪቷን ንብረት የግል ለማድረግ ስለሚፈልጉ ሃሳባቸው ሁሉ ስለግል ጥቅማቸው እና የሰሩትን ወንጀል ለመደበቅ በሚያደርጉት ፍትጊያ እርስ በራሳቸው ይጠፋፋሉ።
2ኛ. ንብን መርዝ እንዳላት ያወቀ ሰው መከላከያ አድርጎ ሄዶ የፈለገውን ነገር ማድርጎ ጣፋጥ ምግቧን እንደሚወስድ ከፈለገም ማጥፋት እንደሚችለው ሁሉ ወያኔንም መርዛማ እንደሆነ ስለተረዳነው መከላከያን ተጫምተን በመሄድ መርዙን ሳይተፋው ሆድ ውስጥ እንዳለ እስከመርዙ በቀላሉ ማጥፋት የምንችልበት ግዜ ነው። ከአሁን በኋላ በወያኔ መርዝነት ተወግቶ በቀላሉ የሚሞት የለም ያለፉት ግዜያቶች ህዝባችንን ገድሎ የፎከረበት ዘምን አይደገምም ለመርዛማው ወያኔ መርዙን የሚያስተፋ አልያም ከነመርዙ የሚያጠፋ ሙሉ ትጥቅ ታጥቀን ቀርበናል። ይሄ አይደለ ሁለት ሞት የሚባለው ላይመለስ የሚጠፋበት አንድም በቀመመው መርዝ እርስ በራስ በመወጋጋት ሲጠፋፉ ሁለተኛውና ዋንኛው ደግሞ መርዘኛነታቸውን የተረዳው ሰፊው ህዝብ የሚያጠፋቸው ነው።
ወያኔ አዲስ አበባ ተንደርድራችሁ ስትገቡ ሰፊው ህዝብ በሩን ከፍቶ ምግብ እየመገበ ውሃ እያጠጣ የቆሰለ እያከመ በጉያው እየደበቀ አስገብቶአችሁ ነበረ ። ያንን ግን ረስተውታል ወይም ማውራት አይፈልጉም። አሁን ግን ከአዲስ አበባ በህዝቡ እንቢተኝነት ስትወጡ በሩን ዘግቶ መርዘኛነትህን ሁሉም ስለተረዳችሁ በሩን ዘግቶ ሊያጠፋችሁ ወደ ውጪ ይወጣል። ያኔ ከደደቢት ተንደርድራችሁ አዲስ አበባ እንደገባችሁ ከአዲስ አበባ ተንደርድሮ ደደቢት መግባት የለም። በየት በኩል ሊኬድ በየት በኩልስ ሊታለፍ አሁን በግፍ የጋገራችሁት እንጀራ የምትመገብበት ግዜ መጥቷል የሳቃችሁበት ጥርሶቻችሁም መራገፊያቸው ደርሷል የተደሰቱ ልቦናችሁ ማዘኛችሁ ደርሷል በግፍ የዘራችሁት ስለሆነ በመከራ ታጭዱታላችሁ፣ ስትቀዱት የነበረውን የደም ጽዋ ያኔ ትጎነጩታላችሁ። ድንፋታችሁ ከንቱ ድንፋታ ቀረርቶአችሁ ከንቱ ቀረርቶ እንደሆነ በማሳወቅ ወያኔዎችን ሁለት ግዜ በመግደል የሰፊው ህዝብ የበላይነት ይረጋገጣል። የኛ ምርጫ ይሄ ነው። ሁሌም ህዝብ አቸናፊ ነው።
ከ-ከተማ ዋቅጅራ
No comments:
Post a Comment