ጠሀይቱ ስንቅ ቤት
(ጣይቱ ውቴል)-
ይህ ሜዳው ላይ የሚታየው ግርግር እ.ኤ.አ በ1925 ዓ.ም ላይ የአፋር ማህበረሰብ ልዑካን ዘውዱን ተነጥቆ ዘብጥያ የወረደውን ልጅ እያሱን ለመጠየቅ ከብዙ ቀናት የእግር ጉዞ በሁዋላ አዲስ አበባ እንደደረሱ በዝች ታሪካዊ ውቴል ፊት ለፊት ከምሳ ግብዣው ቀድመው የተቀረፁት ታሪካዊ ምስል ነው።እንዲሁም በ110 ዓመት እድሜዋ ውስጥ ከዚህ በፊት እና ከዚህ በሁዋላ የተደረጉ የተለያዮ ዕልፍ ዐእላፍ ውስጥ ታሪካዊ ትዕይንቶች በዝች ታሪካዊ ውቴል ውስጥ ተፅፈው በሰነድ ይገኛሉ።
እ.ኤ.አ በ1903 ዓ.ም ላይ ራስ ሞኮንን የአውሮዻ ጉዞቸውን ጨርሰው ሲመለሱ በጉብኝታቸው ላይ የማረካቸውን የአውሮዻውያን ውቴሎች አጠቃቀም ለአጤ ምኒሊክ አማክረው ንጉሱም ምክሩን ተቀብለው ይህችን ጥንታዊ ኮረብታ መርጠው Muse Minase የተባለውን የአርመን ሰው የዘመኑ ድንቅ ግበኛን ቀጥረው አመት ተኩል በፈጀ የግንባታ ስራ ተጠናቃ እ.ኤ.አ በ1905 (1898)E.Cተመርቃ ተከፈተች።በዚህ የሩቅ ትውልድ ውቴል ቤት ገብቶ መሰንቅ እንደነውር ለሚቆጥረወ ህብረተሰብ አርዓያ ለመሆን ተብሎ ለተወሰነ ጊዜ አጤ ምንሊክ አጋፋሪ እቴጌ ጣይቱ ደግሞ ወጥቤትና አስተናጋጅ በመሆን በዝች ውቴል ቤት ውስጥ መስራታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ።በተጨማሪ በጥሊያን ወረራ ጊዜ ስሞ ተቀይሮ Hotel Grande ተብላ በምትታወቅበት የ5 አመት ዘመን አባ ማዘንጊያ የተባለ አንድ አርበኛ በዝች ስንቅ ቤት ማጀት ውስጥ ተደብቆል ተብሎ ጥቆማ የደረሳቸው የፋሽስት ወታደሮች ለሰአታት ያህል ከበው በጥይት ናዳ ደብድበዋታል።ዛሬ መቃጠሎ ታሪኩንና አገሩን ወዳድ ለሆነ ሰው እጅግ ያሳዝናል ግን የስሜት ተሸናፊ ሆኜ ብዙ አልናገርም።

No comments:
Post a Comment