የሚሊዮኖች ድምጽ አገር ቤት በአንድነት ፓርቲ ኤዲቶሪያል ቦርድ የምትታተም ነፃ ጋዜጣ ናት። በሁለተኛ እትሟ የሰማያዊ ሊቀመንበር አቶ ይልቃ ጌትነትን ይዛ ቀርባለች። ሊቀመንበሩ ከሕዝቡ የሚነሱ ፣ አብሮ ከአንድነት ፓርቲ ጋር አብሮ በመስራት ዙሪያ ያጠነጠኑ ጥያቄዎች የቀረበላቸው ሲሆን፣ የአንድነቱ መሪ አቶ በላይ ፍቃደ በአዲስ ድምጽ ራዲዮ ከሰጡት አስተያየት የተለየ በአብሮ መስራቱ ዙሪያ ተስፋን የሚሰጥ ሳይሆን ተስፋን የሚይጨለም መልሶችን ነበር የመለሱ።
አቶ በላይ ፍቃዱ ፣ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ መኢአድ እና ትብብር ተመሳሳይ የፖለቲካ ፕሮግራም ያላቸው እንደመሆኑ በተናጥል መሆናቸው ትርጉም የማይስጥ ነው የሚል ምላሽ በመስጠት ድርጅታቸው የሕዝብ ጥያቄ በአክበር ዓብሮ ለመስራት መደረግ ያለበትን ሁልሉ እንደሚያደርግ ማሳወቃቸው ይታወቃል። የሰማያዊ መሪ አቶ ይልቃል ጌትነት ግን፣ በተናጥል ሆኖ ፖለቲካውን ማራመድ ጎታች አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ከቃለ ምልልሱ የተወሰነውን እንደሚክከተለው ያንብቡ
ሚሊዮኖች ድምጽ – ትብብሩ ውስጥ ካሉ ፓርቲዎች ውጭ ከእናንተ ጋር ተመሳሳይ አቋም ያለው ፓርቲ አለ ብላችሁ ታስባላችሁ?
አቶ ይልቃል ጌታነት – የሌሎቹ አልጠራም፡፡ ግራ የሚያጋቡና ያልጠራ ነገር አላቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌሎች ፓርቲዎች ላይ አስተያየት ለመስጠት እቸገራለሁ፡፡ የሀገራችን ፖለቲካ ገና ነው፡፡ በጎንዮሽ ለመተቻቸት ቅንጦት የሆነበት ደረጃ ነው ያለው፡፡ ህዝባችንም በተቃዋሚዎች ላይ ተስፋ በሚያደርግበት ጊዜ መተቻቸት ብዙም ጠቃሚ አይደለም፡፡
ሚሊዮኖች ድምጽ – ‹‹ተመሳሳይ ፕሮግራም እና ዓላማ ያላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንድ ሆነው የማይሰሩበት ምክንያት አሳማኝ አይደለም›› የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ፤ እናንተ ደግሞ ‹‹በውህደት ከመሄድ ይልቅ ብቻችንን ሄደን ዓላማችንን እናሳካለን ነው›› የምትሉት፡፡ በዚህም ብዙ ሰዎች ትችት ይሰነዝሩባችኋል፡፡ መልሳችሁ ምንድን ነው?
አቶ ይልቃል ጌታነት – ተቺዎቻች መጀመሪይአ መብታቸው ነው። ሁለተኛ የአደባባይ ሰዎች ስንሆንና በጋራ ጉዳይ ላይ ስንቆም ተቺዎች ሊያወሩ እንደሚችሉ እናምናለን፡፡ ኢትዮጵያ ሰፊ ሀገር ናት፤ ብዙ ውጥንቅጦች ያሉባት ሀገር ናት፡፡ የሃይማኖት መሪዎች ወይም የሃይማኖት ሰዎች አይደለንም፤ ፖለቲከኞች ነን፡፡ በእኛ አመለካከት፣ በእኛ ሃሳብ የማይስማሙም የሚደግፉም አሉ፡፡ ያ በራሱ ጤናማና እንደመልካም የፖለቲካ እድገት ነው የምናየው፡፡ ከተቺዎቻችን የሚመጣው ሀሳብ ዋጋ ያለው ነገር ሆኖ ስናገኘው ደግሞ እንማራለን፡፡
ሚሊዮኖች ድምጽ – በተናጥል ሆኖ ፖለቲካውን ማራመድ ለለውጡ ጎታች አይደለም?
አቶ ይልቃል ጌታነት – ጎታች አይደለም፡፡ ቢተባበሩ የበለጠ ጥሩ ነው፡፡ በመርህ ደረጃ ችግር የለም፡፡ በተግባራዊነቱ ላይ ነው እንጂ ችግር ያለው፡፡ ያለችህን ኃይል ሁሉ አጠራቅመህ አንድ ላይ ብታደርጋት የተሻለ ጅረት እንደምትሰራ መገንዘብ የማይችል ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡
ሚሊዮኖች ድምጽ – ሰማያዊ እና አንድነት ቢዋሃዱ ሊቀመንበርነቴን ላጣ እችላለሁ የሚል ስጋት አለብህ?
አቶ ይልቃል ጌታነት – እኔ ስጋት የለኝም፡፡ አንደኛ ስኬትና ውጤት ሊቀመንበር በመሆን ብቻ ነው የሚመጣው ብዬ አላምንም፡፡ ክብርንም፣ ሞገስንም፣ ታሪክንም ሆነ ሰው የሚወዳቸው ነገሮችን በሙሉ ለማግኘት ሊቀመንበር መሆን የግድ አያስፈልግም፡፡ እኔ ሀገሬን ለመጥቀምም ሆነ ራሴ ተከብሬ ለመከበር የሚያስችለኝ ሊቀ-መንበርነቴ ነው ብዬ አላስብም፡፡ 70 ሊቀመንበር ነው እዚህ ሀገር ያለው፡፡ 70ዎቹን ሁሉ እኮ የምታውቀቸው አይመስለኝም፡፡ ምናልባትም አዲስ ጋዜጣ መስርተህ በጋዜጣህ ሁለተኛ ዕትም የመጣኸው እኔ ጋር ነው፡፡ያ የመጣው በተናጥል ሆኖ ፖለቲካውን ማራመድ ለለውጡ ጎታች አይደለም? መብታቸ ው ነው ፡ ፡ ሊቀመንበር በመሆኔ አይደለም፡፡ ስኬትና ውጤት በሥልጣን እርከን አይመጣም፡፡ሌላም አስተያየት አለ፡፡ ‹‹አንድነት እና ሰማያዊ እንዲዋሃዱ የማትፈልገው የመርህ ይከበር አባል ስለነበርክና ከዚያ ጋር በተያያዘ ቂም ነው›› ይባላል፡፡
አቶ ይልቃል ጌታነት – ይሄ የተሳሳተ መረጃ ነው የሚመስለኝ፡፡ በዛ ደረጃ ከሆነ ከሌሎች ፓርቲ ሰዎች የበለጠ ከአንድነት ሰዎች ጋር ጓደኝነትም ቀረቤታም አለን፡፡ እንዲህ አይነቱ አባባል በመላምት የሚሰጥ አስተያየት ነው፡፡ በጓደኝነት አንድነት ፓርቲ ቤት ካሉ ሰዎች ጋር እንቀራረባለን፡፡ በሥራ አስፈጻሚ ውስጥ ያሉት ሳይቀሩ የቅርብ ጓደኞቼ ናቸው፡፡የምንከባበር ሰዎች ነን፡፡ ቡናም ሻይም አብረን እንጠጣለን፡፡ እዛም ውስጥ እያለን፣ ትግሉ ላይ ባሉ አንዳንድ የመርህ ችግሮች ሳቢያ አብዮት ስናስነሳ ከሰዎቹ ጋር የግል ጠብ እኔ በበኩሌ አልነበረኝም፡፡ ሁሉንም ሰዎች በተለያየ ጊዜ እናገኛቸዋለን፡፡ ከዚያ ከአንድነት ጋር ወደፊት ለመስራትም ሆነ ላለለመስራት የሚወስነን ነገር በሚያራምዳቸው አቋሞች በሚወስዳቸው እርምጃዎችና በያዛቸው የጋራ አስተሳሰቦች መረጃ ነው መታየት ያለበት፡፡ እንደውም ሰማያዊና አንድነት ለመቀራረብ ከሌላው የተለየ ብዙ አጋጣሚዎች ያላቸው ድርጅቶች ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ ሌላም ሰው ብትጠይቅ እንደዛ የሚል ይመስለኛል፡፡በእኛ ሀገር ባህል ‹‹የተጣላ ሰው ተመልሶ አይገናኝም›› ከሚል የሚነሳ መላምት ካልሆነ በቀር እውነታው እንደሚባለው አይደለም፡፡
ሚሊዮኖች ድምጽ – ሰማያዊና አንድነት ባንተ የሥልጣን ዘመን አንድ የሚሆኑ ይመስልሃል?
አቶ ይልቃል ጌታነት – ፖለቲካ ተለዋዋጭ ነገር ነው፡፡ዛሬ አይሆንም ያልከው ነገር በአጭር ጊዜ ሆኖ የሚታይበት ጊዜ አለ፡፡ በተግባር ግን ዝብርቅርቅ ያሉ የአስተሳሰብ ርቀቶችና ልዩነቶች እንዳሉ ይታየኛል፡፡ አብረው ሊያደርጓቸው የሚችሉና ሊያከናውኗቸው የሚችሉ ተግባሮችም እንዳሉ ይሰማኛል፡፡በሂደት ደግሞ በሚያገናኟቸው ነገሮች መቀራረብ ሊፈጥሩ እንደሚችሉ እገምታለሁ፡፡ግን በሐሳብ ደረጃ እኔ ሳየው አሁንም ቢሆን በአንድነት በኩል ያሉት አስተሳሰቦችና ትግሉን የመረዳት ደረጃዎች ከእኔ እይታ ጋር በተወሰኑ ደረጃዎች መራራቆች እንዳሉ ማየት እችላለሁ፡፡ ትግሉን በሚረዱት ደረጃና እንደ ስብስብ በሚወስዷቸው አቋሞች ልዩነት አለ፡፡ አንድነት ከመድረክ ጋር ነበረ፡፡ለምን ከመድረክ ጋር ተለያየ? ወደ መድረክ ሲሄድ ያሻሻላቸው ፕሮግራሞች አሁንስ አሉ ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ጥርት ያለ ነገር ካለ አብሮ ለመስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎች የሚፈጠሩ ይመስለኛል፡፡
ሚሊዮኖች ድምጽ – በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ለውጥ ፈላጊዎች፣ “ግራ ተጋባን፤ ማንን እንደግፍ? በአንድነት በሰማያዊና በመኢአድ መሀከል እየዋለልን ነው፡፡” ይላሉ፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ምን ትላቸዋለህ?
አቶ ይልቃል ጌታነት – መዋለሉ በራሱ አንድ የአስተሳሰብ ደረጃ ስለሆነ በቀና ነው የማየው፡፡ በሂደት ወደ አንዱ ይጠቃለላሉ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግልጽ ያልሆኑ ሃሳቦች የሚጠሩበት ጊዜ ሩቅ አይመስለኝም፡፡ ያኔ መልስ ያገኛሉ፡፡
ሚሊዮኖች ድምጽ – የሰማያዊ ፓርቲን የፖለቲካ እንቅስቃሴ በአዎንታዊ ጎኑ የሚያዩት ሰዎች እንዳሉ ሁሉ “ጀብደኝነት የሚወዱ ትንንሽ ልጆች ናቸው፡፡ ፖለቲካውን አያውቁትም፡፡ ዝም ብሎ ከፖሊስ ጋር ከመጋፈጥ የራቀ ዓላማ የላቸውም” ብለው የሚተቿችሁም ሰዎች አሉ፡፡ውዳሴውንና ትችቱን እንዴት ታየዋለህ?
አቶ ይልቃል ጌታነት – ይሄ ለመተቸት ያህል የሚነገር ነገር ነው፡፡ የጠቀሱት ነገር የለም፡፡ ምን በማድረጋችን ነው የምንተቸው? በወሰድነው አቋም ነው? በፕሮግራማችን ነው? እኔ በተናገርኩት ነገር ነው? ወይስ ምንድን ነው? በያዝነው የፖለቲካ አስተሳሰብም ይሁን በአደባባይ በተናገርናቸው ነገሮች ላይ ማንም ሰው አንድ ሁለት ብሎ ነቀፌታ ሰጥቶ አያውቅም፡፡ እኔ ሶስት ዓመት ያህል በሰፊው ተናግሬያለሁ፡፡ በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ከተናገርኩት ውስጥ ምናልባት “ተቃዋሚዎችን አጣጣለ” ከሚለው አስተያየት ውጪ በፖለቲካዊ አመለካከቴና በፖለቲካዊ ብስለቴ አሳማኝ ትችት ያቀረበ አንድም ሰው የለም፡፡ ለነገሩ አዲስ ፖለቲካ ውስጥ ነው ያለሁት፡፡ በህይወቴ ብዙ የምማረው ነገር አለኝ፡፡ ትላንት የነበረኝ አስተሳሰብና የዛሬው ይለያያል ፡ ፡
No comments:
Post a Comment