በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአጋዚ ጦር አባላት እየተገደሉ እየተገኙ እንደሚገኙ ከተለያዩ ሥፍራዎች ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች አመለከቱ:: ታክስ ሰብሳቢዎችም እንዲሁ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረው ግብር ለመሰብሰብ ሲሞክሩ በሚደርስባቸው ጥቃት የተነሳ ሥራ መስራት እንደተቸገሩም ለማወቅ ተቻለ:: የዘ-ሐበሻ የመረጃ ምንጮች እንዳመለከቱት በ አርሲ በባሌ በምስራቅ እና ም ዕራብ ሐረርጌ, በምስራቅ ሸዋ; በ ም ዕራብ ሸዋ የተለያዩ ቦታዎች በየቀኑ የአጋዚ ጦር አባላት ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ በየጫካው ሥር እንደሚገኙ ታውቋል””
Sunday, March 20, 2016
"ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል"አሉ
"ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል"አሉ አበው።በውሸት አለም ውስጥ እውነትንም በተደጋጋሚ ለማረጋገጥ መሞከር ለማያውቅ ትውልድ"ውሸት ይሆን?" የሚል ጥርጣሬ ሊያስነሳ ይችላል።ብዙ ልጆች "ወልቃይት አማራ ነው!"እያሉ ሲፅፉ አያለሁ።እኔ ደግሞ ይህን አባባል ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን"እየሱስ ጌታ ነው"የማለትን ያህል ዘግይቶ መመስከር ይመስለኛል።ለቀባሪ ማርዳት አይነት የተደጋገመ አባባል በሉት ከፈለጋችሁ።የወልቃይት ማንነት አያጠራጥርም እኮ።የማያውቅ አለ እንዴ?እኔ የምስማማው "የወልቃይቶች መብትና ነፃነት ይከበር!" በሚለው ነው።ለወልቃይት እኔም ያገባኛል ባይ ነኝ።
ነገሩ የሆነው በ1997 ምርጫ ወቅት ነው ።
ከአዲስ አበባና ከተለያየ አካባቢ በአጋዜ ጦር ያታፈሱ ሰላሳ ሁለት ወጣቶች አዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ይታሰራሉ ወቅቱ የተረጋጋ ባለመሆኑ ወጣቶቹ ላይ የሚወሰደውን እርምጃ የሚያውቀው አንድ ሰው ብቻ ነው ። የሚጠበቀው የእሱ ትዕዛዝ ነው ከስር ያሉት የህዝብ ግብር ተሰብስቦ ደሞዝ የሚበሉ ፓሊስ ሜስጥረኞች የስርአቱ ዘብ ጠባቂዋች በወቅቱ የነበሩት ስምንት ነበሩ የእነዛ ሰላሳ ሁለት ሰዋች ነብስ በእነሱ እጅ ሆነ እነሱን የሚያዝ ያ አንድ ግለሰብ ይሰበስብና ይወገዱ የሚል ትዕዛዝ ያዛል ያን ትዕዛዝ ለመፈፀም ሲባል ከባድ መሳሪያ ይመጣል እነዛ ንፁሀንን በእነዛ ስምንት ሰዋች ፊርማ ተረሽነዋል ።
Sunday, January 31, 2016
ቋሚ ሲኖዶሱ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተገለጸ፡፡

ቋሚ ሲኖዶሱ ፓትርያርኩን ያስጠነቀቀው፣ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ፣ ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ሳምንታዊ ስብሰባውን ባካሔደበት ወቅት ነው፡፡ የቤተ ክህነቱ የፋክትምንጮች እንደተናገሩት፣ የማስጠንቀቂያው መንሥኤ÷ አቡነ ማትያስ ምክራቸውን ለሥልጣነ ፕትርክናቸው አይመጥኑም ከተባሉ አማሳኝ ግለሰቦች እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ክብርና ነፃነት በመጋፋት ከሚወቀሱ አፅራረ ሃይማኖት አካላት ጋራ በማድረግ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔና ልዕልና የሚፃረር ተግባር በየጊዜው መፈጸማቸው የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት ክፉኛ በማሳሰቡ ነው፡፡
የህዝባችን እንባ ለማቆም ሁላችንም አምርረን እንታገል !
ኢትዮጵያ አገራችን ከፍተኛ የሆነ የህልውና ስጋት ተደቅኖባታል። ልጆቿ በያቅጣጫው ዋይታቸውን እያሰሙ ነው። የወያኔ የተበላሸ ስርዓት እና የስግብግብነት ተፈጥሮ ተደማምረው ህዝባችንን በቃላት ሊገለጽ በማይቻል ሰቆቃ ውስጥ ከተውታል። ህሊና ይዘው መፈጠራቸው ጥያቄ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ፣ ቅልብ የወያኔ ገዳይ ወታደሮች በኦሮሞ እናቶችና ህጻናት ላይ የፈጸሙት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በረጅሙ ታሪካችን ያላየነውና ያልሰማነው ነው። ባለፉት መንግስታት ለነጻነታቸው የጮሁ ወጣቶች በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸው ታሪክ የመዘገበው ሃቅ ነው፣ ነገር ግን ህጻናትና ታዳጊዎች እጅግ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ግንባራቸውንና ደረታቸውን በጥይት እየተመቱ ሲወድቁ ስንመለከት ይህ በታሪካችን የመጀመሪያ ነው። አለም በፍጥነት እየተለወጠ ባለበት በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መወሰዱ ደግሞ የአገዛዙ ቁንጮዎችንና እነሱን ተከትለው ወደ ጥፋት አረንቋ የሚተሙትን ሁሉ ከሰው መፈጠራቸውን እንድንጠይቅ የሚያደርግ ነው። የኦሮሞ ህዝብ በአጋዚ ወታደሮችና በፌደራል ፖሊሶች በግፍ ለተነጠቀው ልጆቹ ድምጹን ከፍ አድርጎ አልቅሷል፤ ቁጭቱን በቻለው መንገድ ሁሉ ሊገልጸው ሞክሯል።
ሰበር መረጃ የአባይ ግድብ እና የቦንድ ገንዘብ ዘረፋ (ወያኔ)

February 6, 2014 8:15AM የአል ጀዚራ ባልደረባ የሆነዉ ሃሰን ሁሴን (Hassen Hussein) እንደዘገበዉ ጃንዋሪ 8 ላይ ግብጽ የአባይ ግድብ ግንባታ እንዲቋረት ጠይቃለች ይህዉም በሁለቱ ሐገራት መካከል ዉስጥ ለዉስጥ እየተካረረ የመጣ ዲፕሎማሲያዊ ጸብ ወደ ተለያየ አቅጣጫ እንደሚሄድ ሲነገር ቆይቶ ሰንብቶ ነበር። በ2017 ይጠናቀቃል የተባለዉ የአባይ ግድብ የተለያየ ችጎች ሲገጥሙት ቆይተዉ በስተመጨሻ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከግብጽ ጋር ሚያደርጉት አለመግባባት ከተካረረ ግብጽ በኤርትራ የሚገኙ ተቃዋሚዎችን በማስታጠቅ ትጎዳናለች ወደሚል ስጋት ስለጣላቸዉ ብቻ የካዮዉን መንግስት (Cairo’s collaboration) ለድርድር በመጥራት እሹሩሩ ጀመረች በስተመጨረሻም ግድቡን ዉሃ ላለመሙላት በመስማማት አጭብጭባና ተጨብጭባ ወደ ወደምትዋሸዉ ህዝብ ተመለሰች።
በኑዌር እና አኝዋክ መካከል የተፈጠረው ግጭት ለግዜው ጋብ ቢል ከፍተኛ ውጥረት አለ ።



* ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ም/ዲንና የክልሉ ምክትል ፕሬዝደንት ሹፌር መካከል በመኖርያ ቤት መሬት ጉዳይ በተፈጠረ የግል ፀብ ም/ዲኑ የአኝዋኩን ተወላጅ ሹፌር እጅ በጥይት መምታታቸውን አምነው ተናግረዋል ። ከዛ በኋላ ግጭቱ ከግለሰቦች ወደ ተማሪዎች የቡድን ፀብ ተጠናከረ ።
* በግጭቱ የተነሳ ቆስሎ የነበረ አንድ ወጣት በሆስፒታል ሲታከም ቆይቶ ህይወቱ በማለፉ የወጣቱ ወንድም ትምህርት ላይ ያሉ የአኝዋክ ተማሪዎች ላይ ቦንብ በመወርወር ብዙዎችን አቆሰለ ።
Subscribe to:
Posts (Atom)