Wednesday, September 9, 2015

አይ ኦነግ አላማ የሌለው

አይ ኦነግ አላማ የሌለው ስብስብ አንዳንድ ጊዜ ለምን ኦነግ 3 ሆነ ብዬ እራሴን ጠይቅና እናም ለራሴ ስመልስ እንወክለዋለን ወይም ነፃ እናወጣዋለን የሚሉትን የኦሮሞን እዝብ ስለማያውቁት ወይም እዝቡ አንቅሮ ስለተፋቸው/Rejected by the peoples / ይመስለኝና።
** ግን ለምን እዝቡ አንቅሮ ተፋቸው ስልና ምክንያቴን ሳስቀምጥ በእርግጥ የኦነግ መሪዎች ለስልጣን እንጂ ለእዝቡ ነፃነት ግድ እ
ንደሌላቸው እዝቡ ስላወቀ ነው የኦሮሞ እዝብ ስነ ልቦና ከቀሪው እዝብ ስነ ልቦና የሚለይ አይመስለኝም በዚህ የወያኔ 25 ክፉ አመታትን አብረን ኖረናል ይህ ለአንድነታችን ምስክር ነው ከዚህም በኋላ አብረን እንኖራለን።


**የኦነግ እድሜ ከእኔ በእጥፍ ይበልጣል የመሪዎቹ እድሜ ደሞ ከወላጆቼ ይበልጣል ታዲያ ለምንድነው የማይለወጡት? ለምንድነው ወጣቶች ኦነግን የማይቀላቀሉት? ምክንያቱም የኦሮሞ ወጣቶች ኦነግ የወያኔን ፓለቲካ እንደሚጫወት ያውቃሉ ይህ የወያኔ ፓለቲካ ደሞ ለ25 ዓመታት በህዝብና በሀገር ኪሳራ ተሞክሮ የማያዋጣ ብቻ ሳይሆን አደገኛ መሆኑን በተግባር ስላዩት ኦነግን ከመደገፍ ይልቅ ሀገር ውስጥ በሚገኙ ፓርቲዎች ዙሪያ መንቀሳቀሱን መርጠዋል።
*** ኦነግና ወያኔ ከቋንቋ በስተቀር አንድ አይነቶች ናቸው ስማቸውን እንኳን እስካሁን አልቀየሩም ሁለቱም በግድ ነፃ አውጪዎች ነን ይላሉ ሁለቱም ፓለቲካቸውን እንደ አይማኖት ነው የሚያመልኩት ሁለቱም ጠባቦች ናቸው ብዙ ማለት ይቻላል ስለዚህ የኦነግ ታጋዬች ቆም ብለው የመሪዎቻቸውን መመርመር ይጠበቅባቸዋል ይህንን ሁሉ ዘመን በበረሃ ለምን? ብለው ማሰብና ወደ አንድነት አይሉ መቀላቀል ይኖርባቸዋል እኔ ኦነግ እንደ ድርጅት በዚህ በአዲሱ ጥምረት ውስጥ ባለመግባታ አላዘንኩም ምክንያቱም ከኦነግ ጋር መስራት ማለት ከወያኔ ጋር መስራት ማለት ነው ይዘር ፓለቲካ ማብቂያው ደርሷል ኦነግ ብቻ ነው የቀረው ከ10 ዓመት የማይበልጥ እድሜ ያላቸው የብሔር ድርጅቶች ወደ አንድነት ሲመጡ ማንም አስገድዷቸው አይደለም እዝቡን አክብረው ነው አረጋውያኑ ኦነግና ወያኔ ግን ዛሬም ከእዝቡ ይልቅ የራሳቸውን የማይሰራ ፍልስፍና የሙጥኝ ብለው አሉ እነዚህ ሁለት ከንቱዎችን የማክሰም ስራ የእዝቡ ነው እንጂ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ወይም የጥምር ሀይሉ አይደለም።
ድል ለኢትዮጵያ አንድነት ታጋዬች!

No comments:

Post a Comment