Friday, October 25, 2013

የኢህአዴግ መንግስት መለያ ባህሪያት – (ከአቶ አስገደ ገብረስላሴ)

1. ህግ የማያከብር መንግስት
የኢህአዴግ መንግስት የፍትህ የዳኝነትና የፖሊስ አካላት እንዲቋቋሙ አድርጓል፡፡ እነዚህ የፍትህ አካላት አንዳንድ የሚወስዱትን ህገ-ወጥ እርምጃ ሳይ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሳይሆን የኢህአዴግን መንግስት ለሚቃወሙ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች በአጠቃላይ የተለየ ሐሳብ የሚያራምዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመጫን የተመሰረቱ ይመስሉኛል፡፡ በማንኛውም ወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ ፖሊስ መጀመርያ ግለሰቡን ..ከኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች.. አንዱ መሆኑን እና አለመሆኑን ከኢህአዴግ ባለስልጣናት ይሁንታ ካላገኘ የማሰር አቅም አይኖረውም፡፡

የጌታነህ ትሬዲንግ ባለቤት ራሳቸውን በሽጉጥ ገድለው እንዲሞቱ የተደረገበት ምስጢር ከ4 ዓመት በኋላ ወጣ

(አራጣ አበዳሪው ከተማ ከበደ እኚህ ናቸው)
(ዘ-ሐበሻ) አንድ ሰሞን በአዲስ አበባ በዋጋ ቅናሽ የሆኑ ልብሶችን በማስመጣትና ትላልቅ ሱቆችን “ጌታነህ ትሬዲንግ” በሚል ከፍተው እየሰሩ ከፍተኛ ታዋቂነትን እና ተወዳጅነትን ካተረፉ በኋላ ወዲያውኑ ራሳቸውን አጠፉ ተብሎ በ2009 ዓ.ም ተነግሮላቸው የነበሩት የዚህ ትልቅ ድርጅት ባለቤት አቶ ዮሐንስ ጌታነህ ከ4 ዓመት በኋላ የአሟሟታቸው ምክንያት ይፋ ሆነ።

የአውራምባ ታይምሱ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል

ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ Journalist Dawit Kebede
“እጅግ አስደንጋጭ ዜና ነው” ሀገር ቤት ያሉ ጋዜጠኞች

Ethiopia Zare (ዓርብ ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 25, 2013)፦ በሀገር ቤት ይታተም የነበረው “አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ እና የድረ ገጹ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከሁለት ዓመት በሰሜን አሜሪካ የስደት ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚበር ገለጸ። በጉዳዩ ላይ ከአቶ ያሬድ ጥበቡ ጋር በቪዲዮ ቃለምልልስ አድረጓል።
የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ዛሬ ከዋሽንግተን መነሳቱንና ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገባ ገልጸዋል። የጋዜጠኛ ዳዊት ውሳኔን አስመልክቶ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ጋዜጠኞችን ከኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ የዚህ ዜና አጠናካሪ አነጋግሯል። እነዚሁ በሀገር ውስጥ የሚገኙት ጋዜጠኞች ዜናውን አለመስማታቸውን ገልጸው፤ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን አስተያየት ሲጠየቁ፤ “እጅግ አስደንጋጭ ዜና ነው” በማለት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

100,000 children live in the streets of Addis Ababa!

You must see this heartbreaking documentary about our innocent children.This documentary is truly heartbreaking and unforgettable. My heart and soul cries out for these beautiful Ethiopian children because they are our future. The negatives of Ethiopia are so great that the people are either too numb or too ashamed to want to talk about it.
The TPLF regime care little about the millions of Ethiopians who are struggling for survival, particularly our children, women and elders because they have no strength to oppose the regime. If some are strong enough to fight back, the regime call them terrorists and send the ruthless TPLF-controlled military apparatus to collectively punish everyone from their ethnicity.

ፋሺሽቶች በኢትዮጵያ ላይ ስለ ፈጸሙት ግፍና ስለሚጠበቀው ፍትሕ በዳላስ ከተማ የተከናወነ ውይይት


  • የውይይቱ አስተናባሪ፤ አቶ ይልማ ዘርይሁን፤ በዳላስ የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ማሕበር ሬዲዮ ያቀረቡት መግለጫ፤
  • ፋሺሽቶች በኢትዮጵያ ላይ ስለ ፈጸሙት የጦር ወንጀል፤ ሁለት ኢጣልያውያን ፊልም እያዘገጁ ነው።
የዳላስ/ፎርት ወርዝ የኢትዮጵያውያን የጋራ መረዳጃ ማሕበር እና ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ GLOBAL ALLIANCE FOR JUSTICE: THE ETHIOPIAN CAUSE (www.globalallianceforethiopia.org) ፋሽስት ኢጣልያኖች በኢትዮጵያ ላይ ስለ ፈጸሙት ግፍና ስለሚያስፈልገው ፍትሕ እንዲሁም ስለ ጉዳዩ በዶክመንታሪ መልክ ስለሚዘጋጀው ፊልም፤ ኤል.ቢ.ጄና ኮይት ላይ በሚገኘው ግራንድ ሆቴል፤ ቅዳሜ፤ October 19, 2013፣ ከሰዓት በኋላ 3:00 pm እስከ 6 ፒ. ኤም
ተከናውኗል።

አገርና ፖለቲካ በዛሬው የለውጥ ትግል – ዶ/ር ተስፋዬ ደምመላሽ ( ክፍል አንድ )

Tesfaye Demmelashኢትዮጵያ ውስጥ ዘረኛ አምባገነናዊ አገዛዝ ተወግዶ በምትኩ ሌላ የተሻለ የአገሪቱን መላ ዜጐችና ማህበረሰቦች የጋራ ብሔራዊ ጥቅም የሚጠብቅ መንግሥት የሚቋቋመው እንዴት ነው? ዛሬ ይህን ጥያቄ የማያነሳና የማይጥል አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የለም። ጥያቄውን ለመመለስ የሚሞክሩ ተፎካካሪ አስተያየቶች፣ ትችቶችና ክርክሮች ከአገሪቱ ጋዜጠኞች፣ ምሁራን፣ ተንቀሳቃሽ ግለሰቦችና ተቆርቋሪ ዜጐች በመገናኛ ብዙሃን፣ በአለም አቀፉ ድርና በፓልቶክ ከመሰራጨት ቦዝነው አያውቁም። ሆኖም በየፊናው ሲደረጉ የነበሩ፣ አሁንም የሚደረጉ የለውጥ ትግል ሃሳብ ልውውጦችና ግጭቶች በሚገባ የማይፈትሹት አንድ ዋና ነባር ችግር አለ። ይህ ጣጣ የዛሬው የለውጥ ትግል መወጣት ያለበት፣ በአገር ጉዳዮችና በፖለቲካ መካከል ያሉ ከሥር መሠረታቸው የተዛቡና የተመሳቀሉ ግንኙነቶችን የሚመለከት ነው። በዝች መጣጥፍ የማነሳው ይህን ዋና ጉዳይ ነው።

“ባድሜ የኤርትራ ነው:: ” አቶ በረከት ስምኦን

dd
የድሪምላየን ሆቴል ባለአክሲዮን የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን በኤርትራውያን የፓልቶክ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው መንግስታቸው ባድሜ የኤርትራ ህዝቡም እርትራዊ ነው ሲሉ መስክረዋል::ይህም በሕወሓት ኢሕኣዴግ ውስጥም የሚታመንበት እንደሆነ የተናገሩት አቶ በረከት ከኢትዮጵያ የድንበር ከተሞች አብዛኛዎቹ የኤርትራ ስለሆኑ ሊመለሱ ይገባል ፌዴራል መንግስታችን ደሞ ይህን ያምናል ብለዋል::