Wednesday, October 15, 2014

ኦባንግ ስለ ሁለተኛው የአፍሪካ መሬት ነጠቃ

“ድርጊቱ የሚፈጸመው በእንግሊዝ ዕርዳታ ነው” አሉ
o meth o


ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ በሥራ ጉዳይ እንግሊዝ አገር ተገኝተው የነበሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ሎንዶን የሚገኘው Minority Rights Group International ጽ/ቤት ባደረገላቸው ግብዣ ቃለምልልስ አድርገው ነበር፡፡
በቃለምልልሱ ወቅት ሁለተኛው የአፍሪካ የመሬት ነጠቃ እየተካሄደ እንደሆነ እና እንዲህ ዓይነቱ አስከፊ ተግባር እየተፈጸመ ያለው በእንግሊዝና ሌሎች ምዕራባውያን አገራት ዕርዳታና ድጋፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ የአናሳ ቡድኖች መብት አይከበርም የሚባልበት ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ያለው እነዚህ ወገኖች መብት የሚባል ነገር እንደሌላቸው አቶ ኦባንግ ተናግረዋል፡፡ እንደ ማስረጃም በጋምቤላ አካባቢ መሬታቸውን በግፍ እየተነጠቁ ለስደት፣ ለግዳጅ ሰፈራ፣ ይህንንም የተቃወሙ ለስደት፣ እስራትና ግድያ የተጋለጡትን በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? ክፍል አንድ (ሊያነቡት የሚገባ)

ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? ምንስ እየሠራ ነው? የተዛባ አመለካከት የማይጋርደው ገሐድ እውነታ

ከማህበሩ ድረ-ገፅ የተወሰደ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ብራና ዳምጠው፤ ቀለም በጥብጠው፣ ብዕር ቀርጸው በየአብያተ ክርስቲያናቱ የመቃብር ቤቶች ውስጥ በማስተማር ትውልዱ የሀገር መሪ፣ የቤተክርስቲያን አለኝታ፣ የእግዚአብሔር ቅን አገልጋይ እንዲሆን ያበረከቱት አገልግሎት ከዘመን ዘመን እየተሸጋገረ ለትውልድ ሲተላለፍ የኖረና የሚኖር ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሀገራችን ሥልጣኔ በር ከፋች ሆና የኖረች ከመሆኗም በላይ ዛሬ ላለው ዘመናዊ ሥልጣኔም መሠረት የጣለች ባለውለታ ናት፡፡ ቀደምት የቤተክርስቲያን አበው ደከመን፣ ሰለቸን ሳይሉ ዐረፍተ ዘመን እስከገታቸው ድረስ ሲያገለግሉ ኖረው ቤተክርስቲያኒቱ አሁን ከምትገኝበት የዕድገት ደረጃ አድርሰዋታል፡፡

ከሐይማኖታዊ ይዘቱ ይልቅ ፖለቲካ ለሚሸተው የቤተ ክህነቱ ስብሰባ የትውልዱ ፖለቲካዊ ምላሽም ያስፈልገዋል

የሰሞኑ በቤተክህነት በአቡነ ማትያስ ሰብሳቢነት የተደረገው ጉባኤ እና በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተሰነዘረው የፈጠራ ክስ፣በመቀጠልም በኢቲቪ ዜና ላይ የተላለፈው ስብሰባውን አስታኮ ”ምዕመናን ነቅታችሁ ጠብቁ” መሰል ዜና ሁሉ አንድ ነገር ያሳያል – በቤተ ክርስቲያን ላይ አንድ የአደጋ ደወል ከቅርበት እየተሰማ መሆኑን።
Holy sinod addis ababa
ስብሰባው ላይ ወቀሳ የሰነዘሩት እና የፈጠራ ክሶችን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያወረዱቱ ባብዛኛው የሚጠቅሱት የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሳይሆን የአቶ መለስን ንግግርን እና በዓለም ላይ አሉ የተባሉ የፅንፈኛ አሸባሪ ድርጅቶች ስምን መሆኑን ስንመለከት ጉዳዩ ፖለቲካዊ መሆኑን እና ፖለቲካዊ ምላሽ የሚሻ መሆኑንም ጭምር ያመላክታል።
ስብሰባው ቤተክርስቲያንን የተዳፈረ ነው

ለሕገ መንግስቱ መቆም ሽብርተኝነት ሲባል (ዞን ዘጠኞችን በተመለከተ) ግርማ ካሳ

የተማሩ ናቸው። አገራቸውን የሚወዱ። በሕዝባቸውና በአገራቸው ዉስጥ የሚደረገዉ ግፍ እንዲቆም በጽሁፋቸው የሚመክሩ። ማንም ላይ ጥላቻ የሌላቸው። ኢፍትሃዊነትን የሚጠሉ ። አምባገነንነትን እንጂ ማንንም የማይጸየፉ።
Haile Mariamበጽሁፋቸው ፍቅርን ሰብከዋል። ነጻነትን አውጀዋል። «ዜጎች እንደ እንስሳ ታስረዉና ታፍነው መኖር የለባቸውም። ነጻነታቸውና ስብእናቸው ሊጠበቅላቸው ይገባል» እያሉ ተከራክረዋል። ለሰብአዊነት ተሟግተዋል።  ሰው ሲከብር እንጂ ሲዋረድ፣ ሲነሳ እንጂ ሲወድቅ፣ ሲድን እንጂ ሲሞት፣ ሲበለጸግ እንጂ ሲደኸይ ማየት አልፈለጉም።
በቢሯቸው፣ በቤታቸው፣ ሴቶቹ በቦርሳቸው፣ ወንዶቹ ደግሞ በኪሳቸው ቦምብ ወይም ፈንጂ አልተገኘባቸው። በድብቅ የዶለቱት ወይንም የሰሩት ነገር የለም። የተወሰኑቱ ካምፓላ ኡጋንዳ ሄዱ እንጂ በድብቅ አስመራ የሄደ ከነርሱ መካከል የለም።  የጻፉትና የተናገሩት ሁሉም በግልጽና በአደባባይ ነው። የተወሰኑቱ አርቲክል ዘጠኝ ከሚባል ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው።

የደብተሮቹ ጥምጣም ሲፈታ….የታየዉ …. ማህበረ ቅዱሳንን ለቀቅ አርጉት እስቲ!

ከበሲሊዮስ ዘዓማኑኤል
mahibere-kidusan“ሚሉሽን በሰማሽ ገበያ በሎጣሽ”…..  ይላል ያሀገር ሰዉ ሲተርት! ህዝብ ምን እንደሚላችሁና እንዴትስ  ምዕመኑ እንደታከታችሁ በወቃችሁና አፈችሁን ሞልታችሁ ማህበረ ቅዱሳንን ለመዝለፍ….. “አሸባሪ“ ምናምን እያላችሁ ስለማታዉቁትና በልግፅ ስላለገባችሁ ነገር ለመዘባረቅ ባልደፈራችሁ! “የራሷ እያረረ የሰዉ ታማስላለች“ እንዲል አሁንም የሃገር ሰዉ … ደብተሮቹ የሚያስተዳደሩትን ደበርና አጥቢያ በአግባቡ መምራት ተስኗቸዉ ከሙስና ማፅዳት አቅቷቸዉ ሳለ  በሚሊዮኖች መንፈሳዊ የትግል ፅናት ለሃያ አራት ዓመታት ሲገነባ የነበረን ማህበር ለማፈረስ ሲዶሉቱና ሲፈርጁ መዋለቸዉ ሲታወቅ አንግት ያስደፋል!
ሲናገሩ ካየኋቸዉ አንዱ ማንነቱን በቅጡ ያለወቀ ደብተራ ቅዱሳን አባቶችን ለማስፈራራት ሲሞከር ማስተወሌ መድረኩ የቱን ያህል የማሰብ ስንኩላን የተሰባሰቡበት እና መነፍሰዊነት በቦታዉ ያልተጋበዘበት የጠምጣሚዎች ስብሰባ እንደነበር ለመረዳት አያደግትም! አንዱ ተናጋሪ ብቻ ትንሽ አመክኖዊነት ያለዉ ይመስላል ነበር … የማህበረ ቅዱሳንን መሪዎች ዘልፎ አብዛኛዉን አባል ለመካከል የሞከረዉ (ገሎ ማዳን ሆነበት እነጂ) … ከሌሎቹ ደናቁርት ደብተራዎች ይሻል ይሆናል! በርግጥ እሱም የተንሸዋረረ አመለካከት አለበት! ንግግሩን ሲያበቃ እንደብዞወቹ በፍርጃና በማስፈራራት ነዉ የዘጋዉ….  ብዙ የኢህዴግ አባልና ደጋፊ የሆኑ የማህበሩ አባላት እንዳሉ ሲታወቅ “በፌደራሊዝም የሚያምኑ” ምናምን እያለ የማያወቀወን በጥራዝ ነጠቅነት ሲቀባጥረና ወጥ ሰረግጥ ነበር! ጠርዝ የመያዝና ፍረጅነት በሽታ የሆነበት ሃገር!

አገሩን ያልተቀማው ተመስገን!

ከጌታቸው ሽፈራው
ህዝብን ተስፋ ካስቆረጠው 97 ምርጫ በኋላ አዲስ ነገረ ጋዜጣ የመረጃ ምንጭ፣ የመወያያ መድረክና ነቃሽ መሆን ችላ ነበር፡፡ ብዕርን አብዝቶ የሚፈራውና ህዝብ አማራጭ መረጃ ሲያገኝ እንቅልፍ የሚያጣው ገዥ ፓርቲ የአዲስ ነገር ጋዜጠኞችን ማዋከቡን ተያያዘው፡፡ ጫናው እየተጠናከረ በሄደበት አንድ ቅዳሜ ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ‹‹ይህ አገር የማን ነው?›› በሚል ስርዓቱ የሚያደርገውን አፈና፣ አዲስ ነገር ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ዘርዝሮ አስረዳ፡፡ አገሩ የኢትዮጵያውያን ቢሆንም ገዥዎቹ እንደነጠቁን፣ መስራት እንዳልተቻለ በድንቅ የጽሁፍ ችሎታው ቀምሮ አስነበበ፡፡ ተወዳጇ አዲስ ነገር ከዛ ቀን በኋላ ለአንባቢዎች አልደረሰችም፡፡ አገራቸውን የተነጠቁት የአዲስ ነገር ጋዜጠኞችም የተቀሙትን አገር ትተው ተሰድደዋል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእስር ላይ ሳለ ያስተላለፈው መል ዕክት + (የክሱን ዶሴ ይዘናል)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶ፤ በአምስተኛ ፖሊስ ጣብያ ከቆየ በኋላ ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት ሊወሰድ በዝግጅት ላይ እንደነበረ፤ ትላንት በስፍራው ሄደው የጠየቁት ጋዜጠኞች ገልጸዋል። ከነዚህ ጋዜጠኞች መካከል ኤልያስ ገብሩ ስለሁኔታው በአጭሩ እንዲህ ብሏል።
ጋዜጠኛ ተመስገን በፌዴራል ፖሊሶች ታጅቦ ሲወሰድ
‹‹ለእስረኛ ማልቀስ/ ማዘን ሳይሆን የእስረኛውን መንገድ መከተል ነው››
‹‹የእስክንድር ሃሳብ ትክክል ነው›› ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከነገረን የተወሰደ
*******************************
‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ላይ በተስተናገዱ ሶስት ጽሑፎች ተከስሶ ለሁለት ዓመት ያህል የክስ ሂደቱ ሲታይ ቆይቶ በትናንትናው ዕለት በከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ‹‹ጥፋተኛ›› ከተባለ በኋላ ከትናንት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ዛሬ ጥዋት ላይ ከእስከዳር አለሙ፣ ይድነቃቸው ከበደ እና ስለሺ ሀጎስ ጋር ሄደን ጠይቀነው ነበር፡፡
ከተሜ ጋር በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳቦችን ተወያይተናል፣ በተወሰኑ ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በየግል እምነቶታችንን በማንሳት ሃሳቦችን ተለዋውጠናል፡፡ ጥያቄዎችን አንስተን ምላሾችን ተደማምንም ነበር፡፡ …