ግርማ ሠይፉ ማሩ
girmaseifu32@yahoo.com
ኢትዮጵያዊያን በተለያየ ፓርቲ አባል ሆንን ማለት ላለመግባባት ቃልኪንዳን ያሰርን እስኪመስል ድረስ መላቅድሳችን የጠፋብን ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ የመለስን ራዕይ እናሳካለን በሚለው ዙሪያ መስማማት ላይጠበቅብን ይችላል፡፡ እንጋባባ ሲባል ደግሞ አንድ እንሁን ማለታችን አይደለም፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም እንደሚሉት ከፋብሪካ እንደወጣ ሳሙና አንድ መሆን የህይወትን ቅመም ያሳጣል ብቻ ሳይሆን ለስው ልጅ ተፈጥሮውም አይደለም፡፡ በቤት ውስጥ እንኳን አንድ ዓይነት መሆን ለጫወታም አይመችም፡፡ ከኢህአዴግ ጋር ለመግባባት ብሎ እናስቀጥላለን የሚሉትን የሟች ጠቅላይ ሚኒስትር ራዕይ ማወቅ የሚፈልግ አንድ ቅን ሰው ቢገኝ ይህ የሚባለውን ራዕይ በግልፅ ከየትም አያገኝም፡፡
እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች፣ የወጣትና የሴት ሊግ አባላት፣ የሀርብቶ አደርና የሌሎችም መሰል ስብሰባዎች መሪ መፈክሮች ስለ መለስ ራዕይ የሚያወሩ ቢሆንም አንድም ተመሳሳይ የሆነ አጭር ሀረፍተ ነገር “የመለስ ራዕይ ይህ ነው” ብሎ የሚያስረዳችሁ አታገኙም፡፡ አሁን ደግሞ የመለስ አሰተምሮ የሚል ፈሊጥ መጥቶዋል፡፡
ለእኔ ራዕይ የሚባለው በረጅም ጊዜ ለመድረስ ያሰብንበት ግብ (የተለወጠ ደረጃ) ሲሆን እዚያ ግብ ለመድረስ ግን ብዙ የምናደርጋቸው ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች መኖር ይኖርባቸዋል፡፡ የእነዚህ ተግባራት ድምር ነው በእርግጥ ካስብንበት የሚያደርሰን፡፡ ራዕይ ያለ ትክክለኛ ተግባር የተሳሳተ ጅምር ከመሆን አያልፍም (Vision without proper action is a false start)፡፡ ስለዚህ ዛሬ “ራዕይ” እናሰቀጥላለን ከሚሉ የጅምላ መፈክሮች ወጥትን መቀጠል የሌለባቸውን የተሳሳቱ ተግባሮችን እያነሳን መወያየት ተገቢ መሰለኝ፡፡ መግባባት ያለብን ነው ብዬ ስለማምን፡፡
ከነዚህ የተሳሳቱ ተግባሮች አንዱ በተለያዩ ደረጃ ያሉ ሞዴል/አርሃያ ያላቸውን ሰዎች ያለማመስገን ሲሆን የሚከፋው ደግሞ እነዚህን ሰዎች እየተከታተሉ አንገት የማስደፋት ተግባር ነው፡፡ ባለ ራዕይ መሪዎች ይህን አያደርጉም፤ ይልቁንም እነዚህ ሰዎች እንዲበራከቱ እና ለጋራ ራዕይ ሌሎችን እንዲያስልፉ ያበረታታሉ፣ አርሃያም ይሆናሉ፡፡ ኢህአዴግ ከዚህ አንፃር ባህሪው እንዴት ነው የሚታየው የሚል ነገር በሃሳቤ መጣና ብንወያይበት እና ለመግባባት መንገድ የሚከፍት ከሆነ ብዬ ኡ! ኡ! ማላት ፈለግሁ፡፡ መጮኽ፡፡ ለዚህ ጩኸት መነሻ የሆኑኝ በአጭሩ የሚከተሉት ናቸው፡፡
በቅርቡ አሜሪካን ያለ አንድ ወዳጃችን (ግርማ ጌታቸው ካሣ የሚባል) በሳውዲ ጉዳት ስለደረሰባቸው ዜጎቻችን የተሰማውን መልዕክት ሲያስተላልፍ የኢህአዴግ ባለስልጣናትን በጅምላ ክፉና ጭራቅ አድርጎ መሳል ተገቢ አለመሆኑን አበክሮ አንስቶ ከእነ ሽመልስ ከማል ዓይነት አደገኞች ኢህአዴግንም ቢሆን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ እና እንደ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ዓይነቶችን ደግሞ ማወደስ እንደሚያስፈልግ ጠቆም አድርጎ ነበር፡፡ የዚህ መልዕክት በጎ መሆን የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ ይህ ፅሁፍ በደረሰኝ ዕለት ምሽት ደግሞ እንዲሁ በኢህአዴግ ሰፈር በደግ ስለሚነሳ ታታሪ ታጋይ እና የኢህአዴግ ሹመኛ የሆነ አቶ ሀይለሥላሴ ቢሆን የሚባል በዓለማችን ከጦር መሳሪያ ቀጥሎ አደገኛ ሙስና ውስጥ ለውስጥ የሚስራበትን የሕክምና መሳሪያዎችና መድሐኒት የሚቆጣጠር መስሪያ ቤት እየመራ በክፉ ሰሙ የማይነሳ ሰው መሆኑን ሰዎች ነገሩኝ፣ በስራ አጋጣሚ ግለሰቡን ስለማውቀው የሚሉትን ለማመን ብዙ አልተቸገርኩም፡፡
በዚያው ሰሞን በእድሜ ልክ እስር ነገር ግን ከህሊና ዕዳ ነፃ የሆነው ወንድማችን አንዱዓለም አራጌ በጻፈው መፅሃፍ ደግሞ ወደ 1997 ምርጫ ወስዶ አቶ አርከበ ዕቁባይ በአዲስ አበባ ምርጫ ያለመመረጣቸው አንዳንዴ ፍርዳችን ፍርደ ገምድልና የጅምላ እንደሆነ ጠቅሶ አስነበበን፡፡ የሚገርማችሁ ከ1997 ምርጫ ቀደም ብሎ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በሚመለከት ምንም ቃል በማይሉበት ወቅት አቶ አርከብ ዕቁባይ እራሳቸው ኤች.አይ.ቪ ተመርምረው በአዲስ አበባ አስደናቂ የመሪነት ሚና ሲጫወቱ ይህን እንደ ተምሳሌት ተደርጎ ቸርልችል ጎዳና ጫፍ ላይ ከአራዳ ሕንፃ ግርጌ ትልቅ ቢል ቦርድ እና በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ፖስተሮችን እንዲታተሙ ተደርጎ ነበር፡፡ በማግስቱ ቢል ቦርዱ ወደቀ ተብሎ ተነሳና ምን ተፈጠረ ሲባል ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር “የምን እዩኝ እዩኝ ነው” ብለው እንዲነሳ ትዕዛዝ እንደሰጡ ሰማን፡፡ በይፋ የተሰጠ ትዕዛዝ ስለአልነበረ በሚያስደንቅ ፍጥነት ፖስተሩን እንዳይሰበሰብ አድርገን በማስራጨት አቶ አርከበን ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን አስመልክቶ የሚያደርጉትን የመሪነት ሚና በመላው ሀገሪቱ እንዲስራጭ ተደረገ፡፡ ሟቹ ቢወዱትም ባይወዱትም ጥሩ ውጤት አመጣና ውሎ አድሮ እራሳቸው ተመርምረው “እዩልኝ ስሙልኝ” ለማለት አበቃቸው፡፡ አንዱን አንገት አስደፍቶ እራሰን ቀና ቀና ማድግ ተገቢ ባለመሆኑ ላይ ሁላችንም መግባባት ያለብን ጉዳይ ይመስለኛል፡፡
ከላይ እንደመግቢያ ያነሳሁትን ሃሳብ ያነሳሁት በኢህአዴግ ፖለቲካ ውስጥ በጎ ምግባር ያላቸው እና የተግባቦት ችግር የሌለባቸው ሰዎች እንዳሉ እሙን ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች አንሰቶ በበጎ ምግባራቸው ተገቢውን ቦታ መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ከልቤ አምናለሁ፣ ለነዚህም ሰዎች በበጎ ሰራቸው እንዲቀጥሉበት ስንቅ ሊሆናቸው እነደሚችል ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ አሰፈሪው ነገር ግን ኢህአዴግ በባሕሪው እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን እንዴት አድርጎ ነው የሚመዝናቸው የሚለው ነው፡፡ እነኚህ ሰዎች ከእኛ ከሚያገኙት ክብርና ሞገስ በተፃራሪ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ፓርቲ እንዳይሞቱ እንዳይድኑ አድርጎ ማኮላሸት ይችልበታል፡፡ ለእነደዚህ ዓይነት ተግባር የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚና ከፍተኛ እንደ ነበር በተግባር የተረጋገጠ ነው፡፡ እንግዲህ ይህ ተግባር መቀጠል አለበት የሚል እምነት የለኝም፡፡ ባለ ራዕዩ መሪ ካስቀመጡልን መጥፎ ተግባራት አንዱ ነው እና ላለማስቀጠል መግባባት ይኖርብናል፡፡
ግርማ ሰይፉ ማሩ
ምክንያቱ በውል ባይታወቅም/የተለያዩ መላ ምቶች አሉ/ ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በኢህአዴግቾ መንደር መነቃቃት የታየባቸው የኢህአዴግ ሰዎች እንዳሉ ሁላችንም የምንታዘበው መሬት የወረደ ሀቅ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች አንገታቸውን ቀና እንዳያደርጉ ሟቹ ጥላቸውን አጥልተው ነበር፡፡ አለበለዚያም የሆነ ፍላፃ ይዘው ከጀርባቸው ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ አሁንም ቢሆን እነዚህን ሰዎች በስም እያነሱ ማወደስ በተግባራቸው እንዲገፉበት ማበረታት በተገባ ነበር፡፡ ከኛ በኩል ውዳሴ ካገኙ በዚያ በኩል መጥረቢያ የሚሳልላቸው ከሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ለጊዜው ስማቸውን አለማንሳት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ እነሱም ይህን ይረዱታል፡፡ በእኔ እምነት አቶ ኃይለማሪያም ደሰለኝ ማስቀጠል ከሌለባቸው ተግባሮች አንዱ በእንዲህ ዓይነት ሰዎች ላይ የሚመሩት ፓርቲ መጥረቢያ መሳሉን እንዲያቆም ማድረግ ይመስለኛል፡፡ ለእርሳቸውም ለሌሎች ተተኪ መሪዎችም ከህዝብ በጅምላ ለፓርቲ ከሚሰጥ ድጋፍ በተጨማሪ ለግለሰቦች በአስተዋፅኦ ደረጃቸው የሚመሰገኑበትና የሚጠየቁበት ስርዓት ፓርቲውንም ቢሆን ይጠቅመዋ እንጂ አይጎዳውም፡፡ ቀና የሚሉትን እየተከተሉ አንገት ማስደፋት መቆም ይኖርበታል፡፡ ተግባባን!!
ኢሕአዴግ ማሸማቀቅ የሚፈልገው ግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን የፈለገ ቀን የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍል ብሎ በጅምላ ህዝቡን ሊሆን ይችላል፡፡ እንደምታስታውሱት በቅርቡ በተደረገው የፕሬዝደንት ለውጥ ኢህአዴግ የህዝብን አስተያየት ለመስማት ደንታ አልነበረውም፡፡ ይልቁንም ለማሳሳት ተግቶ የሰራ ይመስለኛል፡፡ ፓርቲው ለዕጩነት ያሰባቸውን ጥቂት ሰዎች መደበኛ ባልሆነ መልኩ ይፋ አድርጎ የህዝብን ይሁንታ ቢያዳምጥ ምንም አይጎዳውም ነበር፡፡ መግባባትን ከመፍጠር ውጭ፡፡ ህዝቡን አይደለም ለጥቅምም ይሁን ለመስዋዕትነት የተሰለፉ አባላቶቹን ባይተዋር አድርጎ ስራውን አጠናቀቀ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ኢህአዴግ ሲፈልግ ቡና ነጋዴዎችን፣ ከፈለገ የፋይናንስ ሴክተሩን፣ ባሻው ቀን የሪል እስቴት ሴክተር፣ ከፈለገ በአከራይ ተከራይ፣ ወዘተ ነጥሎ ይመታል፡፡ ዓላማውም አንገት ማስደፋት ነው፡፡
በዚህ በኩል በተቃዋሚ ጎራም ቢሆን የጠራ አቋም አለ ብዬ አላምንም፡፡ ምስጋና ለሚገባው ምስጋና ከመስጠት ይልቅ እየገፉ ከክፋተኞቹ ጎራ ለመቀላቀል ጥረት የሚደረግ ይመስለኛል፡፡ ለዚህ የሚቀርበው አመክንዬም ኢህአዴግን እንደ ስርዓት ነው መቃወም የሚል ነው፡፡ ይህን ስናደርግ ደግሞ ሁሉንም የፓርቲ አባላት በተለይም ከፍተኛ ሹሞች የሚያደርጉትን መቃወም ነው ብሎ የሚያምነው ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ይህ አስተሳሰብ ከመቀራረብ ይልቅ መራራቅን፣ ከመተማመን ይልቅ ጥርጣሬን፣ በማስፋት ሀገራችን ለምንላት ኢትዮጵያ እና ለህዝቡ አለን የምንለውን ራዕይ ማሳካት እንዳንችል እርስ በእርስ ተጠላልፈን እንድንቀር እያደረገ ነው፡፡ በእኔ እምነት ለብዙ የኢህአዴግ አባላት በሚፈፅሙት በጎ ምግባር የሚገባቸውን በቸርነት ለማድረግ ዝግጁ መሆን ይጠበቅብናል ከታቀፉበት ፓርቲ ሊወርድባቸው የሚችለውን ፍላፃ ከግምት ውስጥ በማስገባት ጭምር፡፡ የእኛን ሰፈር ፍላፃ ለመቋቋምም ቢሆን ጥንካሬ ይጠይቃል፡፡ እባካችሁ በፓርቲ ደረጃ ያሉን ልዩነቶች እንደተጠበቁ ሆነው ግለሰቦች በተናጥል ለሚያደርጉት በጎነት እውቅና ለመስጠት ብንግባባ አንዱን የልዩነት ግንብ አፈረስን ማለት ነው፡፡ ከዚያም ለመቀራረብ መንገድ እንጀምራለን፡፡ የዛሬ ሁሁታዬ ይህው ነው፡፡
ቸር እንሰንብት!!
ኢትዮሚድያ

No comments:
Post a Comment