(ተፈራ ድንበሩ)
1
በሰዎች መካከል በጥቅም ላይ በሚደረግ ግጭት ጦርነት ከተደረገበት ጊዜ አንሥቶ ተሸናፊዎች በባርነት እንደተገዙ የታወቀ ሲሆን ሰውን እንደ ዕቃ የመሸጥ-መለወጥ ሥራ የተጀመረው በአረብ ነጋዴዎች ነበር። “Hugh Thomas” የሚባል መጽሐፍ ፀሐፊ “The Slave Trade and Robin Blackburn’s The Making of the New slavery“ በሚል ርዕስ በጻፈው መጽሐፍ ላይ እንዳስቀመጠው ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ እሰከ 869 (ኢኤአ) አረቦች ሸቀጥ ይዘው ወደ አፍሪካ ሲወስዱ የአፍሪካ መሪዎች በገዛ ሕዝባቸው ሸቀጣቸውን ይለውጧቸው ነበር ብሏል። ከዚህ በታች ከመጽሐፉ በቀጥታ የተጠቀሰውን ይመለከቷል፦
“…it [slave trade] was pioneered by Arabs, its economic mechanism was invented by the Italian and Portuguese, it mostly run by Western Europeans, and it was conducted with the full cooperation of many African kings.” 1
ጎርዶን ሙሬይ ስለባሪያ ንግድ ከሬጂናልድ ኮፕላንድ ሥራ ጋር በማገናዘብ ያጠናቀረውን ጥናት እንደሚከተለው ገልጾታል፦
Now the European Slave Trade did not begin till the 16th century, it did not reach its full volume till the 18th, and in the course of the 18th, and in the course of the nineteenth it was suppressed. But the Arab Slave Trade, as has been seen, began before the Christian era, and did not stop till some fifty years ago; and though its output in any single year can never have reached the highest figures of the European trade, the total number of Africans it exported from first to last through all those centuries have been prodigious. (Reginald 137)
በአውሮፓ ኢንደስትሪ እያደገ ሲሄድ የሰው ጉልበት በማስፈለጉ የባሪያ ንግድ ተስፋፋ። በመፈንገልና በማስፈንገል አረቦች የባሪያ ገበያው ስለደራላቸው ከአፍሪካ ወደ አውሮፓና ወደ አዲሱ አሜሪካ፣ ብራዚልና ወደ ካረቢያን ደሴቶች ጭምር ንግዱ ስለተስፋፋላቸው ለነዚህ አገሮች ከአፍሪካ በዓመት እስከ 80,000 ሰው ያቀርቡ ነበር። ለአውሮፓና አሜሪካ እርሻና ሌሎች
1 http:..www.Scaruffi.com/Politics/slavetra.html.
2
ኢንደስትሪዎች መሠረት በመሆን ከፍተኛ ኃይል ሆኖ ያገለገለው ከመላው ዓለም በተለይም ከአፍሪካ በባርነት ተሸጦ የተወሰደው ሰው ነው። በ19ኛውና 20ኛው መቶ ክፍለ ዘመናት ፖርቱጋሎችና አውሮፓውያንን ተከትለው የአረብ ነጋዴዎች በመካከለኛው ምሥርቅ የባሪያ ንግድ ቱጃሮች ሆኑ። እስከ 1,900 ዓ. ም ድረስ እስከ 18 ሚሊዮን የአፍሪካ ዜጎች ተፈንግለው እንደ ኢራቅ፣ ኩዌት፣ ኢራን ቱርክ በመሣሰሉት አረብ አገሮች እስከ ሕንድ ድረስ ለባርነት ተልከዋል። ወንዶቸ ባሪያዎች የአረቡን ዘር እንዳይበርዙ ተብሎ ይኮላሹ ነበር። በሳኡዲ አረቢያ በ1930ዎቹ ዓመታት የባሪያዎች ቁጥር 700,000፣ በ1,960ዎቹ ዓመታት 450,000 የነበረ ሲሆን፤ ይህ ከአገሩ ሕዝብ ውስጥ 32% እና 20% ነበር። (Gordon 225-234)
የታሪክ ምሁራን ያደረጉትን ጥናታዊ መረጃዎች በመጠነኛ ዝርዝር ለመገንዘብ የሚከተሉትን የታሪክ ሰኖዶች በተጨማሪ ይመለከቷል፦
ክርስትያኔ በርድ በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ተዘዋውራ ካደረገችው ጥናት በመነሣት በጻፈችው መጽሐፍ በመካከለኛው ዘመን አረቦች ስላቮችን እየፈነገሉ ይሸጡ አንደነበረና “slave” የሚባለው ቃል የተገኘውም ከነዚሁ ከእስላቮች ስም እንደሆነ ገልጻ፤ አረቦች አፍረካን በባርነት መግዛት መሸጥ የጀመሩት 1,000 ዓመታት ከምእራባውያን በፊት ሲሆን ምእራባውያን የባሪያ ንግድ ካቆሙ በኋላም ንግዱን እንደቀጠሉበት አስረድታለች። እ.ኤ.አ. እስከ 2,000 ዓ.ም. ድረስ የቀይ ባህርን ተሻግረው ወደ ኦማን ብቻ በዓመት 7,200 ባሮች ይሻገሩ እንደነበርና ባርነት ከእስልምና ሃይማኖት በፊት የነበረ ሲሆን ሃይማኖቱ በተለይ የወንድ እስላሞችን መሸጥ መለወጥ እንዲቀር የደነገገ ቢሆንም በተለይ የእምነቱ ተከታይ ባልሆኑት ላይ ሕጉ ትግባራዊ ያልሆነና፤ ያደረገው ነገር ቢኖር ጭካኔ የተሞላበት የባሪያ አያያዝ እንዲሻሻል ነው ብላለች። ሆኖም ወንዱም ቢሆን ጥፋት ከተገኘበት ግድያ እንደማይቀርለትና ለሙሉ ሰው የሚሠራ ሕግ ለባሪያ እንደማይሠራ ገልጻለች። (Christiane 27-31)። ሮሞሎ ጂ. ፓሻ የሚባል አውሮፓዊ አገር አሣሸ በ1,892 ዓ.ም. በጻፈው መጽሐፍ እንደገለጸው፣ አረቦች ጥቁሮችን ብቻ ሳይሆን ስላቮችንም ይሸጡ እንደነበረና በሰሜን አፍሪካ 20,000 በባሪያ ንግድ የተሠማሩ የአረብ ነጋዴዎች በዓመት 180,000 ሰዎችን ከአፍሪካ ወደ ግብፅ፣ ቱርክ፣ ኢራቅና ፋርስ ገዝተው ወይም ፈንግለው ይወስዱ ነበር። በአፍሪካ ቀንድ ለባሪያ ንግድ ኬላነት ሲያገለግሉ የቆዩት ባጋምዩ፣ ዛንዚባር እና ኪቱራ በታንዛኒያ፣ ሶፋልያ በሞዛምቢክ፣ አሰብ፣ ምፅዋ፣ ነፋሲት፣ ዘይላ፣ ታጁራ፣ ሞቃዲሾ፣ በረበራ፣ ኪስማዩ ሆብዮ (ሶማሊያ) ነበሩ። በ1,860ዎቹ ውስጥ በሱዳን በኩል ወደ አረብ አገሮች ይደረግ የነበረው የባሪያ ነግድ በ14 ዓመታት ውስጥ ውስጥ ነጋዴዎቹን የባለሚሊዮን የአሜሪካን ደላር ቱጃር ሊያደርጋቸው እንደቻለ የሮሞሎ ጥናት (Romolo 2, 386) ያመለክታል። ሬጂናልድ ኮፕላን የሚባል ሌላ የታሪክ ምርምር እንደሚያመለክተው የባሪያ ንግድ በአረቦች አንደተጀመረና በኦማን (አረቢያ) ቅኝ ግዛት ሥር በነበረችበት 200 ዓመታት ውስጥ ዛንዚባር በምሥራቅ አፍሪካ ዋና የባሪያ ንግድ መናኸሪያ ነበረች። ሁለት እጆቻቸው ከኋላ እየታሠረ አፋቸው ተለጉሞ፣ 200 የሚሆኑት ተፈንጋዮች እርስበርሳቸው ተሣሥረው እየተነዱ ተወስደው ምድር ቤት ውስጥ በተገነባና በአንድ ጊዜ ብዙ ሺ ሰዎችን በሚይዝ መጋዘን ውስጥ ወደውጭ በመርከብ እስከሚጫኑ ድረስ ታጉረው ይጠባበቁ ነበር። በዚህ ሂደት ውስጥ ብዙዎች ሲሞቱ የተረፉት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቀይባህርን ተሻግረው በመሸጥ ከ60% እስከ 100% ድረስ ትርፍ ይገኝባቸው ነበር። (Couplan 138 146)
በዓለም-አቀፍ ኢኮኖሚክስ ዋጋ ጥናት ፕሮፌሰርና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በፋይናንስ ሙያ የሠሩት እና ከሐረቫርድ በዶክትሬት ተመርቀው በመካከለኛው ምሥራቅ ከሠሩ በኋላ በለንደን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ፕሮፌሰር ከሆኑት ከልጃቸው አላን ጂ.ቢ. ፊሸር ጋር በጋራ በጻፉት
3
መጽሐፍ ላይ እንደገለጹት ደግሞ በ1,870 ዎቹ ዓመታት ናይጄሪያ ውስጥ በቦርኖ ክፍለ ሀገር በኩካ ገበያ ላይ የአንድ ሰው ዋጋ ከ$4.00 እስ $80.00 እንደነበርና ዝቅተኛ ዋጋ ከሚያወጣ ሽማግሌ ከፍተኛ ዋጋ እስከሚያወጣው የተኮላሽ ወንድ ልጅ ያለውን የመገበያያ ዋጋ ዘርዝረው በሰንጠረዥ አስቀምጠዋል (197) ። ከምሥራቅ አፍሪካ በ1,839 ዓ. ም. ብቻ 30,000 ሰዎች ወደመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች እንደተሸጡ፤ ሳይሞቱ ከደረሱ ከ300% እስከ 500% ትርፍ ይገኝባቸው እንደነበረ (74)፤ ባሮች ከማርያ ትሬዛ ቀጥሎ ለውጭ ምንዛሪ መለዋወጫነት (currency) ያገለግሉ አንደነበረም ትሪፖሊ ከሚገኘው የእንግሊዝ ካውንስል ጋር የጉዞ መረጃዎችን ጭምር በማገናዘብና ከመካከለኛው አፍሪካ አህጉር ምሥራቅ አፍሪካን አቋርጦ እስከመካከለኛው ምሥራቅ ድርስ የሚያሳየውን በካርታ የተደገፈ የባሪያ ንግድ መነሻና መድረሻ አስረድተዋል (Allan 73, 74, 188,197)። ጎርዶን ሙሬይ በጻፈው መጽሐፍ ላይ እንደገለጸው በአረቦች ዘንድ ለባርነት ሁለት ዋና ምክንያቶች እንዳሉት፤ ይኸውም አንዱ በጂሐድ ምርኮኛ መሆንና በእስልምና አለማመን ናቸው ብሎ፤ ሐበሻ የሚለውን ስያሜ ለኢትዮጵያውያን የሰጡት አረቦች ሲሆኑ በ19ኛው መቶ ክፍለዘመን ሁለተኛው አጋማሽ ሐበሻ ልጃገረዶች በሜካ ገበያ ላይ ከፍተኛ ትርፍ ያስገኙ እንደነበረ እና በምሥራቅ አፍሪካ በሚደረግ የንግድ ትርኢት ላይ እንደሸቀጥ ተኮልኩለው ይታዩ እንደነበረም ገልጿል። አላን ፊሸር በመጽሐፉ ሲገልጽ ባሮች ከአራዊት ጋር ፍልሚያ በማድረግ ሕይወታቸውን በማጣት ጭምር ትርኢት በማሳየት የአረብ ሀብታሞችን ያዝናኑ ነበር። በአንዳንድ አገሮች ደግሞ በአምልኮታቸው ወቅት ለመስዋዕት ይገደሉ እንደነበር ገልጿል (19) ጊዜ የሴቶች ባሮች ለግብረሥጋ ግንኙነትና ለቁባትነት መመረጥን እንደትልቅ ዕድል ይቆጥሩት ነበር (126)።
አውሮፓውያን አፍርካን በቅኝ ለመያዝ ሃይማኖትን እና ሥልጣኔ የማምጣትን ምክንያት እንደተጠቀሙ ሁሉ፣ የአረብ ባሪያ ነጋዴዎችና የመንግሥት መሪዎቻቸው ቁራን ባሪያ ማሳደርን ይፈቅዳል በማለት ሕጋዊ ቅርጽ (legitimacy) ለመስጠት ሞክረዋል። ቁራን ሙካታባ በሚባል ስምምነት አንድ ባሪያ የራሱን ዋጋ ገዝቶ ነፃ መውጣት እንደሚችል ቢገልፅም በትክክል ተግባራዊ የተደረገበት የአረብ አገር አልነበረም፤ አባቱ ዳኛ ልጁ መልከኛ እንደሚባለው ሕጉም የአስገዳጅነት ኃይል አልነበረውም። በተለይ የሺያ ፈለግ በሚከተሉት ውስጥ ነፃ መውጣት የሚችሉት የእስልምና ተከታይ ባሮች መሆናቸው ቢገለፅም ተፅዕኖው በተለይ በሴቶች ላይ ከፍቶ ቆይቷል ።
የባሪያ ንግድ ሕጋዊ በነበረበት በዚያ አስከፊ ዘመን ፍንገላ ሲደረግ የባላገር መንደሮች ስለሚወረሩ የቤት እንሰሳት ጭምር እተየዘረፉ ቤት ንብረታቸውም ይቃጠል ስለነበር፤ ሰላም ስለሌለ ልማት የሚባል ነገር ስለሚቆም ሕይወት እንደነበረች አትቀጥልም። በአጋጣሚ የሚተርፉት የመኖር ዋስትና ስለሚያጡ ሌላ ምርጫ በማጣት እጃቸውን ለፈንጋዮች በመስጠት በገዛ ፈቃዳቸው ባሪያ ለመሆን ይገደዱ እንደነበር የክርስትያኔ ጥናት ያመለክታል(144) ። ይህን ነገር አሁን እየተደረገ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ስናስተያየው ከ30 ዓመት በላይ (አንድ ትውልድ) ንብረት አፍርተው ከኅብረተሰቡ ጋር ተጋብተውና በማኅበራዊ ኑሮ ተስማምተው ከሚኖሩበት አካባቢ ከሌላ ዘር ናችሁ በሚል ብቻ ቤትንብረታቸውን ተወርሰው ያለምንም መድረሻ በግፍ ከደቡብ የአገራችን ክፍል እንዲፈናቀሉ የተደረጉ፤ በሰሜን የአገራችን ክፍል ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎና መኖሪያቸውን ጥለው እንዲሰደዱ የተገደዱ ዜጎቻችን እጣ ፈንታ ቀድሞ ለባርነት ከተዳረጉት ሕዝቦች እንዳልተለየ ይመለከቷል። በተለይ ከአፍሪካ የተገዙ ባሮች ንዳድ በሚኖርባቸውና ለኑሮ አስቸጋረ በሆኑት የተምር፣ የጥጥና ስኳር እርሻ ቦታዎች፣ በባስራ ባነዳር፣ አባስ፣ ምናብ፣ ሂጃዝ አንዲሁም በባህሬን በሐር እርሻ ላይ እንደሚሠሩ ታውቋል። (ሙሬይ 19፤24፤49)
4
እንዲሁም “Arabs and Slave Trade” በሚል ርእስ Shirley Madany የተሰኙ ፀሐፊ ባወጡት ጽሑፍ ያስቀመጡትን እንደሚከተለው ያነቧል፦
Arabia was another major center for the slave trade. The flow of slaves from Africa into Arabia and through the Gulf into Iran continued for a long time. The extension of British, France, and Italian control around the Horn of Africa deprived the slave traders of their main ports of embarkation …The way in which slavery was practiced in Islamic countries had both bright and dark sides. What is regrettable now is that this practice among Muslims is seldom openly discussed – as if slavery was exclusively a Western phenomenon. This deliberate silence enables Islamic propagandists in America to represent Muslims as liberators of the people of African origin, contrary to historical fact2.
እ. ኤ. አ. በሚዚያ 1998 Le Monde diplomatique ላይ ኤሊክያ ምቦኮሎ ባወጣው ጽሑፍ በየተኛውም ኬላ እንደ አፍሪካ ክፍለ አህጉር የሰው ልጅ የተፈነገለበት አልነበረም ብሏል። ይኸውም በሳሃራ፣ ቀይ ባህር፣ ሕንድ ውቅያኖስንና አትላንቲክ ውቅያኖስን በመሻገር ንግዱ የደራ ነበር። በምሥራቅ አፍሪካ የቀይ ባህርና ሕንድ ዳርቻ የአረብ ባርያ ፈንጋዮች ምፅዋንና ደህላክን ጭምር በመጠቀም ከኢትዮጵያ ሲነግዱ እንደነበር Periplus of the Erythraean Sea የሚባል በግሪክ የሚታተም የባህር ጉዞና ንግድ መመሪያ /travel guide/ በተደጋጋሚ ዘግቦ ተገኝቷል። በተለይ በ19ኛው መቶ ክፍለዘመን ለፖርቹጋልና ፈረንሳይ ጋር በባሪያ ንግድ የአረቦች ተሳትፎ ከፍተኛ ነበር።
ግራኝ ሞሐመድ ከ1,520 እስከ 1,535 ዓ.ም. በቱርኮች ተረድቶ የእስላም መንግሥት በኢትዮጵያ ሊመሠርት ሲሞክር በጦርነቱ ወቅት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ አረቢያ ተግዘዋል። እ.ኤ አ. በ1,453 ኮንስታንቲኖፕልን በመያዝ አውሮፓን በተቆጣጠሩበት ዘመናት ኦቶማኖች ነጮችን በብዛት በባርነት ሸጠዋል፤ ለውጠዋል። የኦቶማን ቱርክ ግብጽን ይዞ ሲገዛ በተለይም ከ1,821 ዓ.ም.ጀምሮ በሞሐመድ አሊ ፓሻ እየተመራ ሱዳንን በቅኝ በያዘ ጊዜ ብዙ የሱዳንና የኑብያ ዜጎች ለባርነት ቀይባህርን ተሻግረው ተሸጠዋል።
ዶክተር ዓለማየሁ ገብረማርያም የተባሉት ምሁር “Masters of African Slavery since Antiquity” በሚል መስተአምር/article/ ያጠናቀሩት ጽሑፍ በባርነት ወደ አሜሪካ የገቡት የተለያዩ ዜጎች ከአውሮፓ ከመጡት ዜጎች ቁጥር ጋር ሲነፃፀር የባሪያዎቹ አምስት ጊዜ እንደሚበልጥ ዘግበዋል3። ይኸው ጽሑፍ ቀደም ሲል በአረቦች ሲፈጸም የነበረው የባሪያ ንግድ አሁን ከሚፈጸመው ፍለሳ ጋር የታሪክ ተመሣሣይነት እንዳለው ያረጋግጣል።
ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ ያ ታሪክ በያዝነው ዘመን ውስጥ በአዲስ መልክ ቀጥሎ ማየት ይቻላል። በቅርብ ጊዜ በየመን በተፈጠረው የመንግሥት አለመረጋጋት የተነሣ ከ12,000 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል ልዩ ልዩ ጥቃት ደረሶባቸዋል፣ በግብረሥጋ ተደፈረዋል፣ ይህን አስከፊ ሁኔታ ለማምለጥ ጥቂቶቹ ወዳልታወቀ ቦታ ጠፍተዋል፤ የሞቱም ይገኙበታል። እንዲሁም ከሦስት ወራት በፊት 700 የሚሆኑ ጥገኝነትን የጠየቁ ኢትዮጵየውያን በሮርዌይ መንግሥት ጥያቄያቸው
2 www.answering-Islam.org/ReachOut/slavetrade.html
3 http://www.ethiomedia.com/broad/3656.html
5
ተቀባይነት በማጣቱ በግዳጅ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ከነ አቶ መለስ ዜናዊ አስተዳደር ጋር ሲደራደሩ የነበረ ሲሆን ከእነዚህ አብዛኛዎቹ በፖሊቲካ ምክንያት ከአገራቸው የወጡና ከ15 ዓመታት በላይ በኖርዌይ የኖሩ ሲሆን፤ ሕጋዊ የይለፍ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ስለሌላቸው ተገደው ከመመለስ ወደ ሌላ አገር ጠፍተው ሰብአዊ ክብራቸውንና መብታቸውን አዋርደው ሊኖሩ እንደሚችሉ እና የዘመኑ ፈንጋዮች ሰለባ ለመሆን የሚገደዱ ብዙዎች እንደሚሆኑ መገመት ይቻላልi4።
በአረብ አገሮች የቤት ሠራተኞች ከባሪያ ያልተሻለ አያያዝ እንዳላቸው የሚያመለክቱ ሁለት ምሳሌዎችን ማየት ይቻላል፦ የሊቢያው ሞአመር ጋዳፊ ከሥልጣን ከመውረዳቸው ጥቂት ቀናት በፊት ለእንጀራ ልጃቸው ተቀጥራ ታገለግል የነበረች ተስፋ እንጂ ደሞዝ የሚባል ነገር የማተውቅ አንድ ኢትዮጵያዊት ኢሰብአዊ የሆነ ትእዛዝ ለመቀበል ስላመነታች እጅ እገሯ ታሥሮ የፈላ ውሀ በመላ አከላቷ ላይ እንዲፈስ በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባት ታውቋል። እንዲሁም ዓለም ደቻሳ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊት የቤት አገልጋይ አቤቱታ የማቅረብም ሆነ የመንቀሳቀስ ዕድል ተነፍጓት፣ በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስል ጽሕፈት ቤት ፊት-ለፊት መንገድ ላይ እየተጎተተችና እየተደበደበች ተገፍታ እንደ ዕቃ መኪና ውስጥ ስትጫን በአደባባይ የታየ ሲሆን ከሁለት ቀን በኋላ ተሰቅላ ሞታለች።
በአንድ አገር ውስጥ የሚደረግ የእርስበርሰ ጦርነት ለዜጎቹ ሰብአዊ መብት የማይቆረቀር መንግሥት በሌለበት አገር የባሪያ ፍንገላ ሕጋዊ ወይም ሕገወጥ በሆነ መንገድ ሲፈጸም ቆይቷል። “Internal Displacements in Ethiopia” በሚል ርዕሰ Chemin de Balexert የሚባል ለ”Norwegian Refugee Council/Global IDP Project”5 የሚሠራ ባለሙያ በጻፈው ላይ እንዳመለከተው ከ2,003 እስከ 2005 ዓ. ም. ድረስ ከግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በአገራችን ውስጥ ተፈናቅለዋል። ይህ መፈናቀል የቀጠለ ሲሆን በተለይም ኢሕአዴግ በሚያራምደው በዘር የተከፋፈለ አመራር ባስከተለው መዘዝ ብዙ ዜጎች በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ በኦጋዴን፣ ባሌ፣ ወለጋ፣ ሸዋ፣ ጅማ፣ ጋምቤላ፣ ወዘተ በተፈጠረባቸው የእርስ በርስ ግጭት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕዝቦች ተፈናቅለዋል። በአንድ በኩል እንደኮሚኒስቶች መሬትን ተቆጣጥሮ ገበሬውን የመንግሥት ጭሰኛ ሆኖ አልምቶ እንዳያድግ በማድረግ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ዝንታለም የኖሩበትንና የእርሻ መሬታቸውን ነጥቆ በልማት ካባ ለአረቦችና ሌሎች የውጭ ነጋዴዎች ሸጧል። አያቶቻቸው በደማቸው ያቆዩትን የኢትዮጵያ ግዛትና መሬታቸውን ለፖሊቲካ መሣሪያነት ከጎንደር ቆርሶ ለሱዳን፣ ከትግራይና አፋር ቆርሶ ለኤርትራ የተሰጠባቸው ኢትዮጵያውያን፣ እንዲሁም በየጊዜው በእምነታቸው ምክንያት ጠብ የተለኮሰባቸውና ሲያመልኩበት የኖሩበት ቤተክርስትያን እየተቃጠለ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ነው። ለእልፍ አዕላፍ ዘመናት የቆየውን የአገሪቷን ታሪክ በመካድ ከ100 ዓመት ወዲህ በተፈጸመ ወረራ የተገኘ በማሰመሰል የገዛ አገሩን ልዕልና የሚያቃልል የአገር መሪ ሊባል አይችልም። እስላሙን ከክርስትያኑ ሆን ብሎ በማጋጨት ሕዝቡን የመንግሥት ያለህ እንዲል አድርጎታል። እነዚህ የመፈናቀል ክስተቶች ዜጎችን ቀቢፀ ተስፋ ያደርጓቸዋል፤ ከተስፋ ማጣት የተነሣ ለኅልውና ሲሉ ሰብአዊ ክብራቸውን አዋርደው መብታቸውን ተነጥቀው ከአገር ተሰደው ለመሄድ ይገደዳሉ። ሕገወጥ በሆነ ጉዞ በዕቃ መጫኛ የብረት ሣጥን (container)፣ በኮንተሮባንድ ጀልባ ተጭነው ከቀይባህር ማዶ ለምሳሌ ወደየመን ለመግባት ሁለት ኪሎሜትር
4 http://www.mmo.gr/pdf/news/Migration_in_the_Middle_East_and_Mediterranean.pdf
5 http://reliefweb.int/node/77505
6
ያህል ዋኝተው በሞትና ሕይወት መካከል የሞቱት ሞተው፣ በዕድል የተረፉት የሚጠብቃቸው እሥር፣ በሽታና ረሀብ ነው። ወደ የመን ብቻ በዓመት እስከ 45,000 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ይገባሉ። “Yemen Times” በሚባለው ሳምንታዊ የየመን ጋዜጣ ላይ እ.ኤ.አ. ግንቦት 7 ቀን 2012 እንደተመለከተው በ2001 ዓ.ም 65,000 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ የመን የገቡ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤትን ጠቅሶ እንዳመለከተው 37,333 በሕገወጥ መንገድ የገቡ ሲሆን 616 ሚሆኑት የሞቱ ወይም ምን እንደደረሰባቸው ያልታወቀ መሆኑን ገልጿል። ይህን ሁሉ አበሳ ካዩ በኋላ ምርጫ ስለሌላቸው ከባርነት ባላነሰ መልኩ ሰብአዊ ክብራቸውን ቀንሰው ባይተዋር በሆኑባቸው አገሮች ከሰው በታች ሆነው ያገኙትን ሥራ ተብዬ ሠርተው ይኖራሉ፤ የሚገርመው አንደዚህ ከሚጉላሉት ስደተኞች መካከል ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መገደዳቸው ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በየወሩ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሴት ሠራተኞችን ለሳዑዲ አረቢያ ለመስጠት ከሳዑዲዎች ጋር ስምምነት ያደረገ ሲሆን በየወሩ 13000 ሴት ሠራተኞች ብቻ ወደሳዑዲ አረቢያ በሕጋው መንገድ እንደሚገቡና ከዚህ በተጨማሪ ያለፈቃድ የሚገቡት ቁጥር በብዙ ሺዎች እንደሚቆጠር ብሉምበርግ የሚባል የዜና አገልግሎት በያዝነው ዓመት ጥር ወር ላይ ዘግቧል። ድህነትን ለመሸሽ ወደ ኢጣሊያ ሲጓዙ ከነበሩ 470 የአድሪቃ ቀንድ ስደተኞች መካከል ሲሲሊ ደሴት ለመድረስ ትንሽ ሲቀራቸው የተሳፈሩበት ጀልባ ተገልብጦ ሲሰጥም 155 ብቻ መትረፋቸውን አልጀዚራ አሜሪካ ጥቅምት 4 2013 ዓም ዘግቧል። ባለፈው ሰኔ ወርም 43 ኢትዮጵያውያንና የሶማሌ ዜጎች በተመሣሣይ ሁኔት ድህነትን ለመሸሽ ባደረጉት ሙከራ በዕቃ ማጓጓዣ የብረት ሣጥን ውስት እንዳሉ ታፍነው ሞተዋል።
በሕገወጥ መንገድ ከአገር ወጥተው ምናልባትም የፖሊቲካ ነገር ተጨምሮበት የሚጠብቃቸው ሌላ አበሳ መሆኑን ስለሚያውቁ በማይታወቁበት አገር ሁኔታው አስገድዷቸው ባርነት ውስጥ ይወድቃሉ። መታወቅ ያለበት አንድ ዜጋ እትብቱ የተቀበረበትንና ባህሉ፣ ወጉና በአጠቃላይ ማንነቱ ታውቆና ተከብሮ ከሚኖርበት አገር ቤተሰቦቹንና ወገኖቹን ጥሎ ለመሰደድ የሚገደደው ቢቸገረው እንጂ በቅንጦት አለመሆኑን ነው።
በሌላ በኩል ከሳዑዲ አረቢያ ሕዝብ መካክል 23% የሚሆኑት የውጭ ዜጎች ሲሆኑ፣ ከሠራተኛው ቁጥር ውስጥ ደግሞ 66% የሚሆነው ላቡን አንጠፍጥፎ በምንዳ የሳዑዲዎችን አኮኖሚ የሚገነባው የውጭ ዜጋ ነው።
ባርነት በዓለምአቀፍ ሕግ እንዲቀር ከተደረገ በኋላ ዛሬም በ21ኛው መቶ ክፍለዘመንበ ዘመናዊ መልኩ ቀጥሏል። ዛሬ የውጭ ጠላት ሳይመጣብን ፍትሕ በመጓደሉና ድህነትን ለመሸሽ ከአገር የተሰደዱ ዜጎቻችን ቢመለሱ የሚጠብቃቸውን ስለሚያውቁ ከመሞት መሰንበት በሚል ሰብአዊ ክብራቸውን ቀንስው በባርት መኖርን በነዚያው የአረብ አገሮች ኮንትራት ፈርመው በዘመናዊ ባርነት በኢሰብአዊ አያያዝ ስለመከፈሉም ዋስትና በሌለው ምንዳ እያገለገሉ ይገኛሉ። የጉዞ ወኪል በሚል ሽፋን ላልታወቁ ሰዎችና ባልታወቁ አድራሻዎች ለምሳሌ ኢትየጵያውያን ሴት ልጆች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ይተላለፋሉ፤ ከአገር ሲወጡ የሚፈርሙት ኮንትራት መብታቸውን ሙሉ በሙሉ የሚከለክላቸው ሲሆን፤ በአንፃሩ ተቀባዩ ሰው ባለሙሉ መብት ስለሚሆን ከቤት ወጥተው እንዳይጠፉ የብዙ ወራት ደሞዛቸው ይያዝባቸዋል። የይለፍ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት በተቀባቀዮቻቸው እጅ ሰለሚያዝና እንደልብ የመዘዋወር ነፃነት ስሌላቸው ፈርመው የገቡላቸውን አሳዳሪዎቻቸውን ፈቃድ ከመፈጸም ሌላ አማረራጭ የላቸውም። ታዲያ ባርነት ቦቃ አለው? ሴቶች ዜጎቻችን በነዚሁ የድሮ ጌቶች አገር በቤት ሠራተኛነት ስም እየተቀጠሩ በተመሣሣይ ሁኔታ አካላቸውን የሚያስደፍሩበት ሕይወት ላይ መገኘታቸው ብቻ ሳይሆን ይህንኑ ጉድ እመቤቶቻቸው
7
ካወቁ እጅእግራቸው ታሥሮ ከሕንፃ የሚወረወሩና ወደባህር የሚጣሉት ሲታይ ባርነት ቅርጹን ቀየረ እንጂ በይዘቱ እንዳልተለወጠ መገንዘብ ይቻላል። በኅዳር 2006 ዓም እንደተከታተልነው የዘመናዊ ባርነት መገለጫ ከሆነው ውል ጋር በተያያዘ ሁኔታ ከ50,000 የሚበልጡ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኛ ሠራተኞች መብታቸው እንዲከበርላቸው በሰላማዊ ሠልፍ ጥያቄ ሲያቀርቡ በሳዑዲ አረቢያ ያጋጠማቸው እንደ አውሬ ቤት ለቤት እየተዳኑ መደብደብ፣ መዘረፍ፣ በገሃድ መደፈርና እስከግድያ የደረሰ ወንጀል መንግሥት ባሠማራቸው ፖሊሶች ጭምር መፈጸሙ የአደባባይ ወሬ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ዝምታ ለሰብአዊ መብት ጥሰቱ ተባባሪ ከሚያደርገው በስተቀር ምን ሊባል ይችላል?
እንግዲህ እንዳየነው ከ3,000 ዓመታት ገናና ታሪክ በኋላም በአገራችን ባርነት አለ፤ አንድ ድርጅት የሁሉም የበላይ ጌታ ፈላጭ ቆራጭ ነው፤ የሕዝቡን ሃይማኖቱንና የግል ሕይወቱን ጭምር መቆጣጠር ይዟል፤ የተለወጠው ቅርጹ ነው እንጂ ይዘቱ አይደለም። ጥቂቶችን ለማበልጸግ የሰው ልጅ ተወልዶ እትብቱ ከተቀበረበት አያት ቅድመ አያቶቹ በደማቸው ካቆዩበት አገርና ቀበሌ ቤት ንብረቱን ጥሎ ለስደት ከተዳረገ፣ ሰብአዊ ክብሩን ቀንሶ የጎዳና ተዳዳሪ ከሆነ፣ ከመሞት ለመሰንበት የሚያሳድረውን ጌታ የሚፈልግ ከሆነ፣ ዘመናዊ ባርነት አንጂ ነፃነት አይባልም። ባርነት ሰብአዊ ጭቆና ነው፤ ሰብአዊ ጭቆናም ባርነት ነው።
ነፃነት በስጦታ ወይም በቸርነት ስለማይገኝ ባርነትን ለማስቀረት የባሪያ ቤተሰብ የሆነው ሕዝብ በጋራ ለነፃነት መነሣት አለበት። ገዥውን ማስወገድ ባሮችን ነፃ እንደሚያወጣ ይታመናል፤ ባርነትን ጨርሶ ለማጥፋት ግን የባህል ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም ገዥው ተገዥ፣ ተገዥው በተራ ገዥ የሚሆንበት ራዕይ ወይም መንፈስ ካልጠፋ ባርነት እንደገና ቅርጹን ለውጦ ሊመላለስ ይችላል፤ መራሹ ኢሕአዴግ እንደ ባእዴንና ኦሕዴድ ያሉትን አሻንጉሊቶች አስከትሎ ሲመጣ “ፍትሕ፣ ዲሞክራሲ፣ ሰላም” የሚሉ የሚያማልሉ ተስፋዎችን ይዞ ነበር የገባው፤ በጠመንጃ፣ ኃይል ሕዝባዊ መፈክሮችን ለብሶ መጣ አንጂ ሕዝባዊ ውክልና አልነበረውም። ገዥው መንግሥት ሥልጣን ላይ ከመውጣቱ በፊት እኩልነትንና ፍትሕን በመከተል አንዲየውም በሶሽያሊስት ርዕዮተ ዓለም የጋራ ሀብት የሚበለጽግበትን መርህ በመፈክር ይዞ ቆይቶ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ እንደመንግሥትም እንደሞኖፖልም ሆኖ የአገሪቱን ሀብት ለጥቂት ቡድኖች የግል መጠቀሚያ እያደረገ ነው። ዲሞክራሲን ፍትሕ የጠማውን ሕዝባችንን በስሙ ተጠቀመበት እንጂ አንጀቱን አላራሰውም። ከሃያ ሁለት ዓመታት በኋላም ለሆዳቸው ያደሩ አጫፋሪዎቻቸውም የኋላ ኋላ ጌቶቻቸው ሲጥሏቸው ከሕዝብ ፍርድ ባያመልጡም ለዚያው ገዥ ቡድን ታማኝ ሆነው እያጀቡ ነው እንጂ የሕዝቡን ልዕልና አላስከበሩም። እንዲሁም በአገራችን እንደ አሸን የፈሉት ድርጅቶች መሪዎች እያንዳንዳቸው የመንገሥ ራዕይ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ከሆነ በዚህ ሂደት የሚገኘው ለውጥ አንዱን ጌታ በሌላ ጌታ ወይም ብዙ ጌቶች የመቀየር ህልም፣ ድህነትንና ዘመናዊ ባርነትን አንጂ ነፃነትን አያስገኝም። የሚያስፈልገው በመራሽነት ጠመንጃን ተማምኖ ወደሥልጣን መሮጥ ወይም ሥልጥንን የሙጥኝ ብሎ በሕዝባዊ መፈክር የቡድን ዓላማን ማራመድ ሳይሆን ሕዝቦች ተባብረው ልዕልናቸውን በጋራ እንዲያስከብሩ የማስተባበር አገልግሎት በመስጠት ፈቃዳቸውን መፈጸም ነው። ሆኖም ለሕዝብ አንታገላለን በማለት የሥልጣንና ጥቅም ራዕይ ይዘው የሚንቀሳቀሱ መሪዎችም ለሆዳቸው የተገዙ ባሮች ስለሚሆኑ የሩቅ ግብ ስለሌላቸው ለአገራችን ኋላቀርነት መፍትሔ ሳይሆን ችግር የሚጨምሩ ናቸው። ግለኝነትን ያላስወገደ መሪ ለሕዝብ ልዕልና ሊቆም አይችልም።
8
እኤአ ከ1950 እስከ 1970 ባሉት 20 ዓመታት ኢትዮጵያ አግኝታ የነበረው የውጭ አገር እርዳታ $600 ሚሊዮን ነበር፤ በደርግ ዘመን ከግብረሰናይ ድርጅቶች ከተቀበለችው እንደ እህል፣ መድሐኒት፣ ወዘተ በስተቀር የውጭ እርዳታ ቆሞ ነበር። የሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ እኩልነት፣ ፍትሕና ነፃነት ዓላማ ይዣለሁ በሚለው የኢሕአደግ መንግሥት ዘመናት ደግሞ በእርዳታ ብቻ ከውጭ በያመቱ በአማካይ $3.5 ቢሊዎን እየተገኘ የሥራ-አጡ ሕዝብ ቁጥር እየጨመረ መሄድና ሕዝባችን በድህነት ምክንያት ለዘመናዊ ባርነት መዳረግ የማይጣጣሙ ነገሮች ናቸው። የአገሪቷ የነፍስ ወከፍ ምርታማነት (GDP) ማደጉንና እኤአ በ2012 ዓም $1,200፤ የነፍስወከፍ የመግዛት አቅም $1,167 እንደሆነ የተዘገበ መሆኑን አይ ኤም ኤፍም አረጋግጧል (Ethiopia Economy Profile 2103)፤ ሆኖም ዘገባው የባለፀጎችን ገቢ ለደሀውም በማካፈል የሚገኝ ቁጥር ስለሆነ አሳሳች ነው።ትክክለኛው የነፍስ ወከፍ ገቢ በግልዕ አልተቀመጠም። ምክንያቱም የበለፅጉት ጥቂቶች ስለሆኑና የብዙሐኑ ቁጥር ለሥሌት የሚገባ እንጂ የጥቅሙን ተቋዳሽ ስለማያሳይ ነው። የአገሪቷን ጥቅም ተቋዳሾች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እስከሆኑ ድረስ 90 ሚሊዮን ሕዝብ የራሱ ባልሆነ ገቢ በስሌት ብቻ ምን ይጠቀማል?
ስለሆነም ዲሞክራሲንና ፍትሕን ለማግኘት በንድፈ-ሐሳብ ወይም ሥራ ላይ በማይተረጎም መፈክር ሳይሆን በትክክለኛ የሕዝብ ውክልና አገራችን ነፃ እስካልወጣች ድረስ እውነተኛ ነፃነት፣ እኩልነት ወይም ፍትሕ አይኖረንም። በየዋህነትም ቢሆን ከኛ በላይ ለሕዝብ አዋቂ የለም የሚሉ መሪዎች ጭልጥ ካሉ አምባገነኖች ስለማይለዩ አፉን ለጉመው የሥልጣን ኮርቻ ላይ ተቆናጠው እኛ እናውቅልሃለን በማለት ሕዝባዊ ከበሮ እየደለቁ ሕዝብን እንደፈረስ ከነዱ ወይም ከጎትቱ አመራራቸው በቅርጹም ሆነ በውጤቱ ጭቆና ሰለሚሆን በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለች ሦስተኛ ዓለም ሀገር የብዙኃኑ መረገጥ የከፋ ውጤት ያመጣል። የጥንት ባሪያ አሳዳሪዎች ሰውን መሸጥ መለወጥ የቻሉት ሕዝቦችን ነጣጥለው በመውረር ነው። ዛሬም ያልተባበረ ሕዝብ እጩ ባሪያ ከሚሆን በስተቀር ነፃነት ሊኖረው አይችልም። የጥቂት አምባገነኖች ቡድን እንደ ተራ ወንበዴ ያገራችንን ቅሪት ሙልጭ አደርጎ በመበዝበዝ ሕዝቦቻችንን ነጣጥሎ ግዞተኛ ሲያደርገው ጭቆናውን ተቀብሎ እየተረገጠ መኖር የሕዝባችን ምርጫ ሊሆን አይችልም። ሆኖም ይዋል ይደር እንጂ ፍትሕ የጠማው ሕዝብ ሲወስን ከፍርዱ ማምለጥ ስለማይቻል በትግል ውስጥ ያሉ መሪዎች የራሳቸውን ግላዊ ህልም ትተውና ለሕዝብ ፈቃድ ተገዥ በመሆን በወቅቱ ሕዝብን ለማገልገል አቋማቸውን ማስተካከል ይጠበቅባቸዋል።
በማጠቃለል፦ ዛሬ ዓለም ቤተሰብ እየሆነች በሄደችበት ዘመን በግላዊ ራዕይ እንደዝንጀሮ ተነጣጥሎ መሮጥ ለዘመኑ ትናንሽና ትላልቅ ተኩላዎች ከመመቸት በስተቀር ሌላ የረባ ፋይዳ አያመጣም። እውነተኛ ግላዊ እርካታ የሚገኘው የአገር ጉዳይ አስተማማኝ መፍትሔ ሲያገኝ ብቻ ነው። ምክንያቱም ዛሬ እየተከሠተ ያለው ብዙሐኑን ደሀ የሚያደርግ አቅጣጫ በወቅቱ መፍተሔ ካላገኘ የሚቀጥለው ትውልድ የሚጠብቀው የበለጠ ስደትና ባርነት ብቻ ነውና። አገር ደግሞ በተለያየ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ባህላዊና ማኅበራዊ አኗኗር የሚገለፅ የሕዝቦች ውህደት ሲሆን በየትኛውም አካባቢ የሚታይ መሠረታዊ ሰብአዊ ችግር እየተስፋፋ ብዙ ወገኖችን መጉዳቱ ስለማይቀር ሁሉም እስከሚጎዳ መጠበቅ የሚመረጥ አይደለም። ስለሆነም ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከፖሊቲከኞች ብቻ ተአምርን መጠበቅ የለበትም። አሁንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ድርጅቶች በአንድ በኩል እንወክለዋለን የሚሉትን ሕዝብ በሚገባ ሳያቅፉ በሌላ በኩል ደግሞ ተባብረው በጋራ አለመሥራታቸው የሚያያመለክተው ለሥልጣን የሚደረግ ግላዊ ሩጫን ወይም አምባገነንነትን ስለሆነ ለሕዝቡ መሠረታዊ ችግር መፍትሔ የሚያመጣ አቅጣጫን አይደለም። ዛሬ በአብዛኛው የፖሊቲካ ድርጅቶች የሚታወቁት ካላቸው ሕዝባዊ ፕሮግራም ይልቅ በታዋቂ መሪዎቻቸው ነው፤
9
ከነዚህ መሪዎችም አብዛኛዎቹ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተወሰኑ የሕዝብ ወገኖችን ብቻ እንወክላለን የሚሉ ናቸው። ሆኖም ዛሬ በትግል ወቅት የተለያየ ፍላጎት ያላቸውን የሕዝቦቻችንን ቤተሰቦች ለጋራ ዓላማ በማስተባበር ተሞክሮ አርዓያነትነት ያላሳዩ መሪዎች እንዴትስ ፌዴራላዊ አመራር ይከተላሉ ተብሎ ሊታመኑ ይችላሉ?
የስሞች መቀያየር ነፃነትን አያመጣም፤ ስለሆነም ተስፋ ማድረግ የሚገባው ከጠንካራ መሪዎች ይልቅ በጠንካራ ሕዝባዊ ድርጅት ላይ ነው። ምንጊዜም ሕዝባዊ መሠረት የሌለውና ሕዝቡ የማይቆጣጠረው ድርጅት ለአምባገነኖች ክፍተት ስለአለው ሕዝቡ በስሙ የተቋቋሙ ድርጅቶችን ሊቆጣጠር ይገባል። ስለሆነም ምንም በማያለያያው የአገሩ ጉዳይ ሃይማኖት፣ ጎሣ፣ ቋንቋ፣ ወዘተ ሳይወስነው ከሌሎች ወንድሞች - እህቶቹ ጋር በመወያየት የጋራ መፍትሔ መፈለግ አለበት።እውነተኛ የሕዝብ መሪዎች ለይስሙላ የዲሞክራሲ ካባ የሚለብሱ ሳይሆን ለሕዝቦች ፈቃድ ተገዥ ሆነው፤ ቋንቋን ለመለያያ ሳይሆን ለመግባቢያነት ብቻ በመጠቀም፤ ብሔርተኝነትንና ጎጠኝነትን አስቀርተው፤ ከሁሉ ሕዝቦችና የሕዝብ ወገኖች ጋር በጋራ በመቆም ሕዝቦችን ማገለገል ይጠበቅባቸዋል። ምሁራን ፋና ወጊ የሚሆኑበት፤ አገር ወዳዱ ሁሉ ከባርነት ለመውጣት እጅ ለጅ ተያይዞ ከእግዜር የተሰጠውን ሰብአዊ ክብር በኃይሉ ለመመለስ “United We Stand, Divided We Fall” ወይም “ድር ቢያብር አንበሳን ያሥር” እንደሚባለው ለጋራ ነፃነት፣ እኩልነት፣ ሰብአዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ግብ ሕዝቦች በጋራ እንዲሰለፉ የሕዝባዊ ድርጅት መሪዎች ሚና በሕዝብ ፈቃድ በመመራት ሕዝብን ማስተባብር ነው፤ ሕዝብ ደግሞ በጋራ ሲቆም በተለያየ ቅርጽ የሚገለጽን ባርነት እስከነአካቴው አጥፍቶ ልዕልናውን ሊያሰፍን ይችላል።
10
Works Cited
Al-Maamiry, Ahmed Hamoud. Oman and East Africa. New Delhi: Lancers Publishers,
1980.
Arab Slave Trade: “African Holocaust society. http://www.arabslavetrade.com.
Bird, Christiane. The Sultan’s Shadow: One Family’s Rule at the Crossroads of East
and West. New York: Random House, 2010.
Coupland, Reginald. The Exploitation of East Africa 1856-1890 the Slave Trade and the
Scramble. London: Faber and Faber Limited, 1939.
Davis, Robert C. Christian Slaves, Muslim Masters: White Slavery in the Mediterranean,
the Barbary Coast, and Italy, 1500-1800 (Palgrave Macmillan, London 2003) ISBN 978-1-4039-4551-
Dugard, Martin. Into Africa: The Epic Adventures of Stanley & Livingstone. New York:
Broadway Books, 2003.
Ethiopian Refugees in Norway: Stop Helping the Dictatore Meles Zenwai. http://www.ethiopianreview.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=37660
Fisher, Allan G. B., Humphrey J. Fisher. Slavery and Muslim Society in Africa. New
York: Doubleday & Company, INC., 1971.
Gordon, Murray. Slavery in the Arab World. New York: New Amsterdam Books, 1989.
Huntingford, G. W. B. The Galla of Ethiopia: The Kingdom of Kafa and Janjero. Ethnographic Survey of
Africa part II. Ed. Daryll Forde. London: International African Institute, 1955.
Huntingford, G. W. B. The Galla of Ethiopia: The Kingdom of Kafa and Janjero. Ethnographic Survey
of Africa part II. Ed. Daryll Forde. London: International African Institute, 1955.
Lewis S. Herbert. A Galla Monarchy: Jimma Abba Jifar, Ethiopia 1830-1932. Madison and Milwaukee:
The University of Wisconsin Press, 1965.
Manning, Patrick. Slavery and African Life: Occidental, Oriental, and African Slave
Trades. Cambridge 1990.
Masters of African Slavery since Antiquity. http://www.ethiomedia.com/broad/3656.html
11
Pankhurst, Richard. The Ethiopian Borderlands: Essays in Regional History from Ancient Times to the
End of the 18th Century, Asmara: Red Sea Press Inc., 1997.

Pasha, Romolo, G. Seven Years in the Sudan: Exploitations, Adventures, and
Campaigns against the Arab Slave Hunters. Ed. Fellin Gessi. London: Samson Low, Marston & Company Limited, 1892.
Segal, Ronald. Islam’s Black Slaves: The Other Black Diaspora. New York: Farrar,
Straus and Giroux, 2001.
Yemen Turns into hell for Ethiopians. Http://www.ethiopianreview.com/content/37994
i http://www.nytimes.com/2013/10/04/world/europe/scores-die-in-shipwreck-off-sicily.html?_r=0

No comments:
Post a Comment