Friday, November 1, 2013

4 ሺህ ዶላር ይዞ የተገኘው የናሽናል ጂኦግራፊ ፎቶግራፈር በጋምቤላ ታሰረ

(ፍኖተ ነፃነት) የናሽናል ጂኦግራፊ የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ ሮቢን ሃሞንድ በጋምቤላ ክልል በቁጥጥር ስር መዋሉን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ፓሪስ ከሚገኘው የኢትዩጵያ ኢምባሲ ቪዛ ያገኘው ሮቢን በኢትዩጵያ በተለያዩ ክልሎች በመዘዋወር ፎቶ ግራፍ የማንሳት እቅድ እንደነበረው ተነግሯል፡፡የፎቶግራፍ ጋዜጠኛው ከኢትዩጵያዊ ረዳቱ ጋር ለእስር የተዳረገው 4000 የአሜሪካ ዶላር በእጁ ይዞ በመገኘቱ ነው፡፡ወደ አገር የሚገባ ማንኛውም የውጪ አገር ዜጋ በእጁ የሚገኘውን ገንዘብ ማሳወቅ የሚገባው ቢሆንም ሮቢን ወደ አገር ሲገባ ከገለጸው ገንዘብ በላይ ይዞ መገኘቱ ለእስሩ እንደምክንያት ተወስዷል፡፡

በሲያትል የሃና ገዳዮች 37 እና 29 አመት ፍርድ ተወሰነባቸው

“ኢትዮጵያዊያን በፍርዱ ረክተዋል” ወ/ሮ ሙሉመቤት ረታ (በሲያትል የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር)
- “በእኔ አስተያየት ፍትህ ተበይኗል፤ ዳኛዋም ሆኑ ፍርድ ሰጭዎቹ (ጁሪዎቹ) በትክክል ጉዳዩን አይተው ወስነዋል ብየ አምናለሁ” ዶ/ር ሸክስፒር ፈይሳ
Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. October 30, 2013)፦ ከሁለት ዓመት በፊት ሃና ዊሊያምስ የተባለችውን ታዳጊ በቅዝቃዜ ደጅ ላይ በማዋልና በማሳደር አሰቃይተው ገድለዋል የተባሉት አሳዳጊዎቿ ኬሪ ዊሊያምስና ባለቤቷ ላሪ ዊሊያምስ የ37 ዓመትና የ29 አመት ጽኑ እስራት የተወሰነባቸው ሲሆን በሲያትል አካባቢ የሚኖሩ ትዮጵያዊያን በፍርዱ መደሰታቸውን በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

ሰላማዊ ትግል እና ባህሪያቱ – ስልጠና ክፍል ሶስት – አንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት

በአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት የተዘጋጀው የ5 ሳምንት ስልጠና የመጀመሪያው ክፍል (1) እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ረጅም የነፃነት ዘመን ሲኖራት በስልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋችም። ስለዚህ ስልጠና ክፍል አንድ “ኢትዮጵያ ምን ስትሰራ ነበር?” የሚል ጥያቄ አንስቶ ሁለት አብይ ክሎች ያሉት ሰፊ ታሪካዊ መልሶች ሰጥቷል። በመቀጠል ክፍል አንድ (2) የሰላማዊ ትግልን እድገት አስመልክቶ ከክርስቶስ ልደት በፊት አንስቶ ዛሬ እስካለንበት ዘመን ያደረገውን ጉዞ እና እድገት መርምሯል።
ክፍል ሁለት ደግሞ በሰላማዊ እና ትጥቅ ትግሎች መካከል ንፅፅራዊ ምርምሮች ማድረጉ ይታወሳል። በመቀጠል ሰላማዊ ትግል እና ትጥቅ ትግል የደጋገፋሉን? እና ሁለገብ የትግል ዘዴ ምንድን ነው? ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ሰጥቷል። በመጨረሻ የመንግስት ሽግግር ባህላችን በተለያዩ ዘመኖች በተደረጉ የመንግስት ሽግግሮች በኢትዮጵያ ላይ የፈጸመው በደል ተዘርዝሯል።

“እኔ ወደ ሀገሬ ለመምጣት ከማንም ጋር አልተደራደርኩም”ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ሰንደቅ ጋዜጣ ከዳዊት ጋር ያደረገውን ቆይታ እንደወረደ እንደሚከተለው



የአውራምባ ታይምሱ ጋዜጠኛ ዳዊት ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ በሀገር ውስጥ የሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ በ8ኛ ዓመት ቁጥር 425 የረቡዕ ጥቅምት 20/2006 ዓ.ም. ዕትሙ ከዳዊት ጋር ያደረገውን ቆይታ እንደወረደ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። ቃለምልልሱን ያደረገው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ ነው።

የቀድሞው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከሁለት ዓመታት ስደት በኋላ ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል። የጋዜጠኛ ዳዊት ወደ ሀገሩ መመለስ የሰሞኑ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል።
የጋዜጠኛ ዳዊት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ በበርካታዎችም ዘንድ የተደበላለቀ ስሜት እንዲፈጠር አድርጓል። “ከመንግስት ጋር ተደራድሮ ነው የመጣው” ከሚለው ጀምሮ “በአክራሪ የዲያስፖራ ፖለቲከኞች ጫና ደርሶበት ነው” እስከሚለው ድረስ ጉዳዩ በማወያየት ላይ ነው። በሀገሪቱ የፖለቲካ ሂደት ውስጥም ጋዜጠኛ ዳዊት ተሰዶ በድፍረት እንደገና ወደ ሀገሩ በመመለሱም እንግዳ ስሜት እንዲፈጠር ያደረገ ይመስላል። በዚህና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችም ባልደረባችን ዘሪሁን ሙሉጌታ አነጋግሮታል።

ህወሓት አይድንም፤ እያቃሰተ ነው (አስገደ ገብረስላሴ ከመቀሌ)

 ‹‹የህ.ወ.ሓ.ት  ትንሳኤ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ድላችን የማይቀር ነው ›› ስብሓት ነጋ
     በጌታቸዉ  አረጋዊ  የህ.ወ.ሓ.ት ኣባልና የድምፅ ወያነ ጋዜጠኛ  «ውራይና » የሚል በትግርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ለአራተኛ ጊዜ በነሃሴ ወር 2005 ዓ/ም የታተመ መፅሄት ስብሓት ነጋ  የህ.ወ.ሓ.ት   ፈላስፋ ቃለ መጠይቅ ያደረገበት መፅሄት በፅሞና  ኣነበብኩት። የመፅሄቱ ዋና ይዘት   ‹‹ህ.ወ.ሓ.ት እናድናት›› ነዉ የሚለዉ ስብሓት ነጋ በመፅሄቱ የተካተቱ ብዙ ስንክሳራዊ  ሃተታ ተናግሯል ።
  • አሁን ማለት የፈለግኩት በመፅሄቱ የተካተቱ በሙሉ መልስ ለመስጠት አይደለም፡፡ ምክንያቱም የስብሓትን ስንክሳር መልስ ለመስጠት  ከፈለኩ ግዜ አይገኝም  መፅሃፍም  ሊሆን የሚችል ነዉ። በመሆኑም አለፍ አለፍ በማለት  የስብሓትን አንኳር አንኳር ነጥቦች መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ።

አመፀኛው ንፋስ በልጅግ ዓሊ

አመፀኛው ነፋስ 

ባሰላው ባሰላው እንቢ አለኝ እንዝርቱ፣ 
ከታችም አይደለ ከላይ ነው ጥመቱ። 
የጎንደር ሕዝብ እንጉርጉሮ 

ኦክቶበር 28 እንደ ሃገሩ አቆጣጠር ጠዋት ጉልበተኛ ነፋስ ከባሕር ተነስቶ በደቡብ እንግሊዝ በኩል አድርጎ እያቆራረጠ 
ወደ ሰሜን ተፈተለከ። የባሕሩ ሰይጣን የላከውን ጉልበተኛውን ነፋስ የፈራው አዳሜ ፈረንጅ ሁሉ ተርበትብቶ እኛንም 
በሬዲዮንና በቴሌቪዚዮን ሲያርበተብተን ሰነበተ። 

አሳዛኝ ዜና- ስደተኞቹ በሙሉ አለቁ!

ከኒጀር ተነስተው ፣ ሰሃራ በረሃን በማቋረጥ አልጄሪያ ለመድረስ፣ ከዚያም ወደ ሌላ አገር ለመሻገር አንድ መቶ የሚሆኑ ስደተኞች በአንድ መኪና ታጭቀው ጉዞ ይጀምራሉ።
ሰሃራ በረሃን እንዳጋመሱ የተጫኑበት መኪና ይበላሻል። በዚያ በረሃ፣ መኪና ጠጋኝ ቀርቶ ፣ ቀና ቢሉ ሰማይ፣ ጎንበስ ቢሉ ድንጋይ ካልሆነ ምንም አልነበረም። የሚያደርጉት ጠፋቸው። ማንም የሚደርስላቸውም አልነበረም። በዚህ ሁኔታ ቀናት ተቶጠሩ። የቋጠሯት ጭብጦና እፍኝ ውሃ አለቀች። ቀስ በቀስም አንድ በአንድ እያሉ በውሃ ጥምና በረሃብ ይሞቱ ጀመር።