Friday, February 6, 2015

ህልም እንደ ፈቺዉ ነዉ – ሰመረ አለሙ

tplfአንዳንዴ አያድርስ ነዉ ነገር በየት በኩል እንደሚያፈተልክ አይታወቅም:: ኢትዮጵያ የምትወጋበትንም ሆነ የምትወጋበትን የጦር መሳሪያ ህወአት እየገዛ ለኤርትራ የሚያቀብለዉ ደባ ያልጣመዉ አንድ ወዳጂ በቅርቡ ወደ ኤርትራ በተወሰደዉ አንጀት አርስ ሄሊኮፕተር MI 35 ምክንያት ሲበሳጭ እኔም ያማደርገዉ ባጣ ብስጭት ጥቅም የለዉም መላ መፈለግ ነዉ ብዬ ብመክረዉም የዜግነት ግዴታህ እስከዚህ ድረስ ነዉ በማለት በንቀት ተመልክቶኝ ወደ ሰሜን አቅጣጫ ይዞ ተሰወረ።  ይህ መሳሪያን የሚያከበር  ትንታግ የሆነ የቀድሞ የአየር ወለድ ባልደረባ የእሱ መንገድ ከኔዉ  የተለየ ሁኖ ዉስጥ ዉስጡን ሲሰራ ቆይቶ በሀገር ፍቅር ሰሜት ልባቸዉ የነደደ ከዘር እና ሀይማኖት በላይ ዘራቸዉና እምነታቸዉ ኢትዮጵያዊ የሆነ በደግነት፤በጀግንነት፤በቆራጥነት መስፈርት ጣራዉን የነኩ በቅርብ የሚያዉቃቸዉን የ50 አለቃ ስንሻዉ በላይነህን፤ የ10 አለቃ ጣፋ ኢዶሳን፤ ቆራሄ ላይ በተደረገዉ ጦርነት ቦታዉን ሳይለቅ ለኢትዮጵያ ሀገሩ ሰማእት ስለሆነዉ ስለ ደጃዝማች አፈወርቅ አባቱ ዘወትር ሲተርኩለትና በኢትዮጵያዊነት መንፈስ እያነጹ ያሳደጉት የሀረሩ መምህር አብዱረህማን ኡስማን፤ በትምህርት ደረጃዉ እና በሀገር መዉደድ ስሜቱ የሚነገረለት ዘለቀ ማንደፍሮ፤ ከትግራይ የፈለቁ ጉዶች ኢትዮጵያ ላይ እንዲህ ያለ በደል ሲያደርሱ ቁጭቱን ለመወጣት ቀን ሲጠብቅ የነበረዉ የራስ አሉላ የልጅ ልጂ ነዉ ተብሎ የሚነገርለት ገ/መድህን ወ/ኢትዮጵያን ያካተተ በአካል ጥንካሬዉ፤ በወገን አፍቃሪነቱ ፤በሩቅ እይታዉ የታመነበት በኮማንዶ ቡድን መሪዉ በጌታቸዉ አበጋዝ አማካይነት በስዉር ምልመላ እና ስልጠና በማድረግ 150 አባላቱን በጥንቃቄ በ3 ቦታ በመክፈል በተለያየ ጊዜ ወደ ትግራይ ልኮ ሁኔታዉን ሲያዳምጥ ቆየ።

የትግራይ ነጻ አውጪዎች ኢትዮጵያን ማጥፋት ይችላሉን – ከሳሙኤል አሊ

ነብር ዠጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ መልኩን ሊቀይር አይችልም ይላል በታላቁ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ። ይህ ቃል የኔ ወይም የናንተ አልያም የወያኔዎች ቃል አይደለም ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ ሁሉን ማድረግ የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ነው። ኢትዮጵያዊ መልኩን ኢትዮጵያዊነትም ሊቀየር አይችልም ይላል እግዚአብሔር። ታዲያ  ወያኔ  ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተነሳው ከምን ተነስቶ ነው? የሰው ልጅ መጋፋት የሚቻለው ከሰው ጋር ሊሆን ይችላል ወያኔ ግን ከፈጣሪ ዘንድ ነውና ኢትዮጵያን ማጥፋት ከቶውኑ አይችልም። ወያኔዎች ኢትዮጵያዊ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያወቁ አልመሰለኝም። አዎ ኢትዮጵያዊ ማለት እግዚአብሔር የመረጣት አገር እግዚአብሔርን የሚፈራ ህዝብ የሚኖርባት መሬት.. በህገ ልቦና ገና  ህግ ሳይሰራ  ሊቀ ነብያት ሙሴም ህግን ከእግዚአብሔር ሳይቀበል በፊት እግዚአብሔርን በማምለክ የኖረች አገር ነች።

የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደር ከምርጫው በፊት የመሬት ይዞታውን እንዲመልስ እየጠየቁ ነው

• ‹‹ከምርጫው በኋላ ይመለስላችኋል ተብለናል›› አርሶ አደሮቹ የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደሮች ከምርጫው በፊት የመሬት ይዞታ ደብተራቸውን እንዲመልሱ እያሳሰቡ መሆኑን አርሶ አደሮቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ከወራት በፊት ጀምሮ የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታቸውን እንዲመልሱ ሲጠይቁ እንደነበር ያስታወሱት አርሶ አደሮቹ፤ አሁን ምርጫው መቃረቡን ተክትሎ ካድሬዎች ቤት ለቤትና ስብሰባ ላይ ከሚናገሩት በተጨማሪ በየ ቤተክርስቲያኑም አርሶ አደሮቹ የመሬት ይዞታቸውን እንዲመልሱ ጥያቄ እያቀረቡ ነው ብለዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብንና የኢትዮጵያ ፓሊስን በኢትዮጵያዊያን ለማስጠላት የሚደረገው ጥረት ከሽፏል!

ህወሓት ንፁሀንን ለመደብደብ የሚያበቃ በቂ ክፋት ያለው ልዩ ጦር ሲያሰለጥን ቆይቷል። ይህን ልዩ ጦር የፓሊስን መለያ እያለበሰ ነውረኛ ሥራዎችን እንዲሠራ በማድረግ በአንድ በኩል ንፁሀንን የመጉዳት በሌላ በኩል ደግሞ ፓሊስን በሕዝብ የማስጠላት መንታ ግቦችን ለማሳካት ተጠቅሞበታል። ይህ ልዩ ጦር በአለፉት ጥቂት ሳምንታት ባዶ እጃቸው ለተቃውሞ በወጡ ነብሰ ጡር ሴቶች ላይ ሳይቀር ባሳየው ጭካኔ፣ በሰማያዊ እና በአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ባደረሰው ድብደባ መጠን እና ባካሄደው የግለሰብ ንብረቶች ዝርፊያ የሥርዓቱ ባህርይ ፈጽሞ ከሰውኛ ተፈጥሮ እየወጣ እንደሆነ አመላካች ነው። በእነዚህ ድብደባዎች ወቅት በትግራይ ተወላጆች ላይ የተለየ ትኩረት በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስባቸው ተደርጓል።

ህወሓት ከወሎ ተጨማሪ መሬት ወደ ትግራይ ለመከለል ዝግጅት ላይ ነው

ናትናኤል መኮንን
 ከተመሰረተ 40 አመት ሊያስቆጥር ቀናት የቀረውና አሁንም በገንጣይነት ተግባሩ የቀጠለው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ከወሎ ተጨማሪ መሬት ለመከለል ዝግጅት ላይ መሆኑ ታወቀ፡፡ ለደሴ ሆስፒታል ባዛር በተደረገበት ወቅት ህወሓት አገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ባለሀብቶች በባዛሩ እንዲገኙ ያደረገ ሲሆን በወቅቱም ወሎ ውስጥ ሰፊ መሬት እንዲሰጣቸው አድርጓል፡፡ በተለይም ከቆቦ ወደ ወልደያ በኩል 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አላውሃ የተባለ ቦታ ላይ በርካታ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ደጋፊና አባል ባለሀብቶች መሬት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ውስጥ ለውስጥም ‹‹የትግራይ ድንበር አላውሃ ምላሽ ነው›› በሚል እያስወራ እንደሚገኝ የአካባቢው ነ…ዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

በአማራና ትግራይ ድንበር የተነሳውን ውዝግብ ለመፍታት የተጠራው ስብሰባ ተበተነ

ጥር ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራና በትግራይ ክልል ድንበሮች አካባቢ የተነሳውን ችግር ለመፍታት ከፌደራል መንግስት ፣ ከትግራይና ከአማራ ክልል የተውጣጡ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጥር 26 ቀን 2007 ዓም ከሁለቱም ክልሎች የተውጣጡ 300 ነዋሪዎችን ሰብስበው ያነጋገሩ ቢሆንም፣ መግባባት ሳይቻል በመቅረቱ ለየካቲት 4 በድጋሜ መቀጠሩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ሽፈራው ተክለማርያም፣ የአማራ ክልል ፕ/ት ገዱ አንዳርጋቸው፣ የትግራይ ክልል ፕ/ት አባይ ወልዱ፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ የሰሜን ምእራብ እዝ አዛዥ ሌ/ጄ ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ዘመቻ ሃላፊ ሜ/ጄኔራል ገብረእግዚአብሄር መብራቱ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣኖች በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል።

መቻቻል ወይስ መቻል !!!

በአገራችን ያለው የፖለቲካ አለመግባባት እንዲፈታ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብ እንሰማለን፡፡ በተለይ ተቃዋሚዎች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በየመድረኩ ጮኸዋል፡፡ የአገራችን ጉዳይ ያገባናል ያሉ ኢትዮጵያዊያን በተመሳሳይ ሁኔታ የእርቅ ጥሪውን ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በወያኔ/ኢህአዴግ በኩል ግን ማን ከማን ተጣላና ነው እርቅ የሚያስፈልገው? ሲባል ሰምተናል፡፡ ስለ ዛሬው ከመነጋገር ይልቅ ወደ ኋላ እየተመለሱ ያለፉትን ሥርአቶች ማውገዝ እንደ ባህል ተደርጎ ቆይቷል፡፡ ይህ ደግሞ ለማንም አይጠቅምም፡፡ የአገሪቱ ጉዳይ የዜጎቿ ጉዳይ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ማንም ስለማንም አውቅልሃለሁ የሚልበት ጊዜ ማክተም ያለበት አሁን ይመስለኛል።
ዛሬ ወደድንም ጠላንም የመቻቻልን መርህ አምነን መቀበል የግድ ነው፡፡ የፌዝ መቻቻል ሳይሆን የእውነት መቻቻል ማለት ነው፡፡ መቻቻልን ዛሬም ቻል በሚል መርህ ለማስኬድ ከተፈለገ የትም አያደርስም፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ልዩነትን በማጥበብ አገራዊ መግባባትን ለመፍጠር ከተፈለገ ተቀምጦ መወያየትን ይጠይቃል፡፡ ጎጂና ተጎጂ ተቀምጦ በልዩነት ላይ ለማውራት ጎጂው ቢያንስ አንድ እርምጃ ወደ ኋላ መመለስ የግድ ነው፡፡