Thursday, October 30, 2014

‪#‎Ethiopia‬ በገዥው የወያኔ መንግሰት ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻች መቼም ቢሆን አንረሳቸሁም፡፡

መቼም አንረሳችሁም !
ምርጫ 97 ተከትሎ ጥቅምት 22/1998 ዓ.ም በግፍ የተገደሉ፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና ከአገር የተሰደዱ ጀግኖቻችንን መቼም ቢሆን በታሪክ ይዘከራሉ፡፡በመሆኑም ከጥቅመት 20 እስከ 23 የሚቆይ የማህበራዊ ድረገፅ ንቅናቂ በሰፊው ይካሄዳል፡፡ የዚህ ንቅናቂ ዋናው ዓላማ በግፍ ግድያ ሕይወታቸውን ያጡ በክብር በማሰታወስ ፣ገዥውን የወያኔ መንግሰት ለመለወጥ ጊዜው አሁን መሆኑን ለማመላከት ነው፡፡

የፓርቲዎች ውስጣዊ ፈተና…


በአገራችን ኢትዮጵያ እታየ ያለው የመንግስት የአስተዳደር ሽባነት ለማጋለጥ እና አማራጭ መፍትሔ ለመስጠት፣ ከፍ ሲልም ለማስተዳደር በሰላማዊ መንገድ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች መኖራቸው የማይካድ ሃቅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እነኚኽ ፓርቲዎች በተለይ የሚያደርጓቸው ማናቸውም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴበገዥው መንግስት በኩል የሚደርስባቸው እስራት፣ግድያናእንግልት የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ዓመታ ተቆጥሯአል፡፡
በአገራችን የፖለቲካ ሥርዓት ሄደት ውስጥ ስልጣን በሰላማዊ መንገድ ከአንዱ ወደሌላው የተሸጋገረበት፣ለትምህርት እና ለምሳሌ የሚያገለግል፣ የቅርብ እንዲሁም የሩቅ ክስተት እጥረት ወይም ውስንነት የአገራችን የፖለቲካ ሂደት ዋንኛ ፈተና ነው፡፡ለዚህም ነው የስልጣን ሽግግር ጉልበትን መሠረት ያደረገ ብቻ የሆነው፡፡

ኦሮሞ ስለሆንኩ ብቻ ( ‪#‎BecauseIamOromo‬ )

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው አምንስቲ ኢንተርናሽናል ሰሞኑን ያወጣው ሪፖርት አነጋጋሪ ሆኗል። የሪፖርቱ አነጋጋሪነት የሚጀምረው ከርዕሱ ጀምሮ ነው። የሪፖርቱ ርእስ <<ምክኒያቱም ኦሮሞ ስለሆንኩ>> Because I am Oromo የሚል ሲሆን በኦሮምያ ክልል ውስጥ በገፍ እና በግፍ ስለሚፈጸመው ጭቆና ያወሳል።
አምንስቲ ኢንተርናሽናል በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ መንግስትን በሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲከስ ቆይቷል። የአሁኑ ሪፖርት ለየት የሚያደርገው በኦሮሞዎች ላይ በተለየ እየደረሰ ያለውን ጅምላ እስር፤ ማሰቃየት፤ ግርፋት፤ ስደት፤ መደፈር፤ የፍትህ ማጣት እና ሞት አካቶ ይዞ መውጣቱ ነው። በመቶ የሚቆጠሩ ምስክሮችን ቃል አካቶ የተዘጋጀው ሪፖርት የተለያዩ ሰለባዎችን ታሪክ ይዘረዝራል።

ፕሬዚዳንት ኦባማ ስለኢትዮጵያ ምርጫ ምን ያህል “ያውቃሉ”? ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ  

ፕሬዚዳንት ኦባማ .. 2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው “ምርጫ” ምን ያህል ያውቃሉ? 
ባለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ካለው የገዥው አካል የልዑካን ቡድን አባላት ጋር በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ ላይ በመገናኘት እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው ነበር…”በዚህ ዓመት ጠቅላይ ሚስትር [ኃይለማርያም ደሳለኝ] እና መንግስታችሁ በኢትዮጵያ ምርጫ ለማካሄድ የዝግጅት እንቅስቃሴ በማደረግ ላይ ትገኛላችሁ፡፡ ስለዚያ ጉዳይ ጥቂት ነገሮችን አውቃለሁ…እናም ስለሲቪል ማህበረሰቡ እና ስለመልካም አስተዳደር እንደዚሁም ኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ ያስመዘገበችውን አንጸባራቂ እድገት እና ተምሳሌትነት እንዴት አድርጎ ወደ ሲቪል ማህበረሰቡም ማሸጋገር እንደሚቻል ለመነጋገር ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥርልናል…“  

Tuesday, October 28, 2014

በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም ታዬ ብርሃኑ

chickens-dont-come-home-to-roostማህበረ ቅዱሳን ከበስተጀርባው ቡዙ ችግሮች ያሉበት ድርጅት እንደሆነ የአደባባይ ምሥጢር ነው:: ለአቡነ ቴዎፍሎስ መሞትና ብሎም አሁን በስደት ላይ ለሚገኙት ፓትሪያርክ መሰደድ ትንሽ የማይባል ሚና እንደተጫወተ ቡዙዎች የሚያውቁት ነው:: እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ከህወሃት መንግሥት ጋር በመመሳጠር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ቀላል የማይባል አደጋ አድርሷል::
እነሆ አሁን በተራው ማሕበረ ቅዱሳን በሰፈረው ቁና በሕወሃት እየተሰፈረ ነው::

Journalist Temesghen Desalegn sentenced to three years

Nairobi, October 27, 2014-The Committee to Protect Journalists condemns today’s sentencing of Ethiopian journalist Temesghen Desalegn to three years’ imprisonmenton charges of defamation and incitement that date back to 2012. A court in Addis Ababa, the capital, convicted Temesgen on October 13 in connection with opinion pieces published in the now-defunct Feteh news magazine, according to news reports. He was arrested the same day. Authorities have routinely targeted Temesghen for his writing. Temesghen’s lawyer said he plans to appeal the ruling, according to local journalists.

Monday, October 27, 2014

ሰበር ዜና –የካንጋሮው ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ 3 ዓመት

ሰበር ዜና –የካንጋሮው ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ 3 ዓመት

  • 194
     
    Share
index
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቱን ተጠቅሞ የፍትህ ጋዜጣና መጽሄትን ሲያዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ   ካንጋሮው ፍርድ ቤት 3 ዓመት የእስር ቅጣት ማስተላለፉ  ተመለከተ::

ሰበር ዜና – የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ጥያቄ ያነሳው የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ሰራተኛ ታሰረ

ነገረ ኢትዮጵያ
breaking news- ‹‹ደርግንም ሆነ ምኒልክን እናውቃቸዋለን፡፡ እናንተ ስለ እነሱ መጥፎውን ከምትገልጹልን እንደ 97 እንደማትገድሉና ነጻና ፍትሃዊ ምትጫ እንደምታደርጉ ንገሩን፡፡››
– ስልኩን እና የማስታወሻ ደብተሩን ካድሬዎች እና ደህንነቶች እየተጠቀሙበት ነው።…
-ስልጠናውን በደንብ አልተከታተላችሁም በሚል ተጨማሪ 8 ቀን ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
ገዥው ፓርቲ በሚሰጠው የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ጥያቄ የጠየቀና ስርዓቱን የተቸ የአንበሳ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኛ ታሰረ፡፡ ፋንታሁን የተባለው የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ሰራተኛ በስልጠናው ወቅት ጥያቄዎቹን በማንሳቱና ስርዓቱን በመተቸቱ መታሰሩን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

መክሸፍ እንደ እኔ ጉብኝት (በዓለማየሁ ገላጋይ) – ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ፍቱን መጽሔት ጥቅምት 15 ቀን 2007 ዓ.ም) የጉብኝት ጉዞው በማለት ተጀምሯል፤ ያለንበት መኪና ወደ አዲስ አበባ ደቡብ አፍንጫውን ቀስሯል፤ በመካከላችን ጸጥታ ረብቧል… ዕጣ ፈንታህ በዘመን እጅ ነው ዘመንት ሲፈቅድ የዘመንህ ‹‹ ጉዱ ካሳ›› ትሆናለህ፤ ስውር እስር ቤት ትገባለህ፤ እንደ እብድ ትታያለህ፤ በመገለል ዘብጥያ ባመደመጥ ዋርድያ ስር ትሆናለህ፡፡ እውነትህ እንደቅራቅንቦ ይቆጠራ ይናቃል… … ወይም …. ዘመንህ ሲፈቀድ ካሳ (ዩሐንስ) ትሆናለህ፡፡ ወደ መብት ድንበርህ ትገሰግሳለህ፡፡ አንገትህን ለክብርህ ትሰጣለህ፡፡ ከማንቁርትህ በታች ትመለሳለህ፡፡ ከአገጭህ በላይ ጠላት እጅ ትወድቃለህ …. የራስህ ‹‹መተማ-ዩሐንስ››ትመሰርታለህ… ጠላት የማይሻረው የደም ድንበር ትሆናለህ… … ወይም … ዘመንህ ግድ ሲል ካሳ (ቴዎድሮስ) ትሆናለህ፡፡ መቅደላ ላይ ትቆማለህ፡፡ እስህ ትጮሃለህ፣ መድፍህን ታጮሃለህ፣ ጥይትህን ትጠጣለህ፡፡ አሸናፊህን ተሸናፊ ታደርጋለህ፣ አማራኪህን ትማርካለህ… …የዚህ ዘመን ‹‹ካሳነት›› ምንድን ነው ….

‘አሸባሪ ብዕሮች’ ክንፉ አሰፋ

ashebari-beroch-300x152ይህች አጭር ጽሁፍ የተወሰደችው በአውስትራሊያ ከምትታተም “አሻራ” ከተሰኘች መጽሄት ልዩ እትም ላይ ነው።
የፈረንሳዩ አንባገነን ገዥ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት በአንድ ወቅት ስለ ነጻ ፕሬስ ሲናገር “ከአንድ ሺህ ሻምላዎች ይልቅ አራት ጋዜጦች የበለጠ መፈራት አለባቸው።” ነበር ያለው።
አንባገነኖች ፕሬስን ይፈራሉ። ይጠላሉም። የህዝብ መሰረት የሌላቸው፤ በራሳቸው የማይተማመኑ ሁሉ ነጻ ሃሳብን ይጠላሉ። ነፍጥን ብቻ ተማምነው በሕዝብ ጫንቃ ላይ የሚቀመጡ፤ እንደምን ነጻ አመለካከትን ሊቀበሉ ይችላሉ? ፍጹም አንባገነናዊነት በሰፈነባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች፤ ህግ አውጭው ህግ አስፈጻሚውን፣ ህግ አስፈጻሚው ደግሞ ህግ ተርጓሚውን እርስ-በርስ የሚቆጣጠሩበት እና የሚያስተከክሉበት አካሄድ የለም። ይህንን ቁጥጥር በጥቂቱም ቢሆን ተክቶ ይሰራ የነበረው ነጻው ፕሬስ ነው።

‹‹የነ እንትና ታቦት›› :ዳንኤል ክብረት

ዳንኤል ክብረት
St. E and St. Tዓርብ ዕለት የተከበረውን የአቡነ አረጋዊ በዓል ለማክበር አውስትራልያ አደላይድ ነበርኩ፡፡ እዚያ ከተማ የሚገኝ አንድ የድሮ ወዳጄ በፌስ ቡክ አገኘኝና አደላይድ መሆኔን ነገርኩት፡፡ ‹‹የት እንገናኝ›› ሲለኝ ‹‹ነገ (ቅዳሜ) የአቡነ አረጋዊን በዓል ለማክበር ስለምሄድ እዚያ እንገናኝ›› አልኩት፡፡ ‹‹አንተም እርሱን በዓል ታከብራለህ?›› አለኝ፡፡ በዓይነ ኅሊናየ ራሱን እየነቀነቀ ታየኝ፡፡ ‹‹እንዴት?›› አልኩት፡፡ ‹‹የእነ እንትና ታቦት አይደል እንዴ›› አለኝ የሆነ የኢትዮጵያ አካባቢ ጠርቶ፡፡ ‹‹ማን እንደዚያ አለ?›› ስል ጠየቅኩት፡፡ ‹‹ምን፣ የታወቀኮ ነው›› አለኝ፡፡ እየገረመኝ ተለያየን፡፡

ላ’ንዲት የገጠር ሴት (በውቀቱ ሥዩም)

ስትፈጭ የኖረች ሴት፣
መጁ በመጠኗ፣ ወፍጮውም በልኳ ፣
ጓያ ትፈጫለች
ጓያ ሽሮ ሲሆን ያበቃል ታሪኳ።
አስባው አታውቅም..
ወደ ኦናው ምድር ለምን እንደመጣች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ከና’ቷ ሆድ ወጣች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ጡት አጎጠጎጠች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ለባሏ ተሰጠች።
ተዚያን ቀን ጀምራ፣
ተዚያን ቀን ጀምሮ፣
ድንግል ድንጋይ ወቅራ፣
ትፈጫለች ሽሮ።

Hiber Radio:ዶ/ር ኑሩ ደደፎ የኦነግ ሊቀመንበር ሆነው ጄኔራል ከማል ገልቹን ተኩ; ቻይና በሕገ ወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ የገባ ጫት ሕዝቤን እያወከ ነው አለች

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 16 ቀን 2007 ፕሮግራም !

<... ገዢው ፓርቲ ሰሞኑን አንድነትን ለማዳከም ብሎ የሚአደርገውን ድራማ ተከትለን እሱን ስናስተባብል አንኖርም። ትግላችንን እንቀትላለን አንድነት ስብሰባ ሊጠራ ሲል የትኛውም ሆቴል እሺ እንዳይል ይከለከላል የአገዛዙ ቴሌቪዥን አይመጣም አሁን ግን ሶስት ሰዎች በእጅ ጽፈው ሄቴል ስብሰባ ተፈቀደ፣አባላት ያልሆኑን ጭምር በገዢው ፓርቲ በገንዘብ ተገዝተው የተሳተፉበት ስብሰባ ተደረገ ይሄ አንድነትን አያዳክመውም ይልቅ አሁን በአንድነት ውስጥ ስልጣን የያዘው ሀይል ለመንግስት ምን ያህል እንዳስፈራው የሚያሳይ ነው...>

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩም እንደገና ተከሰሰ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በኢትዮጵያ ውስጥ በነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች ላይ እየደረሰ ያለው ወከባ እስር አሁንም እንደቀጠለ ነው። በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው ከሃያ በላይ ጋዜጠኞች አገር ለቀው ተሰደዋል። ሌሎች ጋዜጠኞች “አሸባሪ” የሚል ቅጽል ተሰጥቷቸው በእስር ቤት ይማቅቃሉ። በጣት የሚቆጠሩት ብቻ አገር ቤት ሆነው የሚመጣውን ለመቀበል የተዘጋጁ ይመስላል። በቅርቡም ተመስገን ደሳለኝ ወደ እስር ቤት እንዲወርድ መደረጉ የሚታወስ ነው።
አሁን ደግሞ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና ማዕከላዊ ሄዶ ክሱን እንዲወስድ በስልክ ተነግሮታል። ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በራሱ ብዕር ስለሁኔታው ሲገልጽ እንዲህ ብሏል። “እንግዲህ፣ ‹‹ማዕከላዊ ናና ክስህን ውሰድ›› ተብያለሁ” ብሎ ይጀምራል፤ ዛሬ በላከው ማስታወሻ ላይ።

ሁለቱ ሙሰኛ ባለስልጣናት (ከእየሩሳሌም አርአያ)

የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አባይ ወልዱ ካስገነቧቸው ሁለት ቪላ ቤቶች አንዱን መሸጣቸውን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ። የሕወሐት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አባይ ወልዱ በክልሉ ካስገነቧቸው ሁለት ቪላ ቤቶች አንዱ የሆነውና በመቀሌ – ዓዲ ሃውሲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን ይህን ቪላ ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ወጪ ካስገነቡት በኋላ እንደሸጡት ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ አባይ ወልዱ በባለቤታቸው ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማርያም ስም በአዲግራት ከተማ ባለሶስት ፎቅ ዘመናዊና በውድ ዋጋ የተገነባ ቪላ እንዳላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል።

መቐለ በኣብራሃም ገብረመድህን ትወዛወዛለች; ትቆዝማለችም (በአምዶም ገብረስላሴ -ከትግራይ)

ድምፃዊ ኣብራሃም ገብረመድህን ባወጣው ኣዲስ የሙዚቃ ኣልበም መቐለ እየተወዛወዘችም እየቆዘመችም ትገኛለች።
ማነው መቐለን በኤርትራ ዘፈኖች ያበደች ከተማ ብሎ ፅፎላት የነበረው? ኣሁን መቐለ ከተማ በሁሉም ኣቅጣጫዎችዋ የኣብራሃም ዘፈኖች እየተደመጡባት ይገኛሉ።
Abraham gebremedhin
Abraham gebremedhin
ኣዲሱ የኣብራሃም ኣልበም የህዝቡ ነባራዊ ሁኔታ የሚያንፀባርቁ ሁነዋል።
በተለይ “…ማቻ ይስመዓኒ ኣሎ…”(ምቾት እየተሰማኝ ነው) የሚል ዘፈኑ የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ከህወሓት ባለስልጣናት ተጣብቀው ሃብት ያከማቹና በማከማቸት ላይ ያሉት ነጋዴዎች እና ከቀበሌ በላይ ያሉ ባለስልጣናት “ማቻ ይስመዓኒ ኣሎ” የሚለው ዘፈኑ በየሆቴሉ በየተሃድሶው እያዘዙ ያደምጣሉ፣ ይወዛወዛሉ። ምቾት ስለተሰማቸው ኣብረውት “ማቻ ይስመዓኒ ኣሎ” ይላሉ።

የሐብታሙ አያሌው የጤንነት ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል (በዳዊት ሰለሞን)

‹ኢህአዴግ ከታሪክ እንዲማር››ባገኘው መድረክ ሁሉ ከመምከር ተቆጥቦ የማያውቀው ወጣቱ ፖለቲከኛ ሐብታሙ አያሌው በጸና መታመሙ ከተሰማ ረዘም ያሉ ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡
እጅግ ቀዝቃዛ ክፍል ውስጥ በማዕከላዊ መታሰሩ ሳያንስ ዝናብ በሚዘንብበት ሰዓት ከክፍሉ እያወጡት አሸንዳ ስር በማስቀመጥ ዝናብ እንዲቀጠቅጠው ያደርጉ እንደነበር ዘግናኙን ቅጣት የተከታተሉ እስረኞች ከተናገሩም ቀላል የማይሰኙ ወራቶች አልፈዋል፡፡

የሟች ጋዜጠኛ ሚልዮን ሹርቤ ጉዳይ ሲያነጋግር…

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ጋዜጠኛ ሚልዮን ሹርቤ በስደት አለም ላይ በነበረበት ወቅት ህይወቱ አልፏል። ከዚያ ጋር በተያያዘ፤ በተለይ የሟች እህት እና ባለቤቱ የሰጡት ቃለ ምልልስ ግን አሁንም አነጋጋሪ እንደሆነ ነው። ኢሳት ቴሌቪዥንም ጉዳዩን በ”እንወያይ” አምዱ ላይ አየር ሰጥቶ ለህዝቡ ዝግጅቱን አስተላልፏል። ከተለያዩ ወገኖች የሚሰጡ ተጨማሪ አስተያየቶችም እንደቀጠሉ ናቸው።
ከኢሳት ዝግጅት በኋላ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም የደረሰውን መረጃ መሰረት አድርጎ እንደገለጸው ከሆነ፤ ከሚልዮን ሹርቤ ህልፈት በኋላ ቃል የሰጠችው ባለቤቱ ሰላም ውድነህ የገዢው ፓርቲ አገልጋይ ናት። እንዲህ በማለት ነው ፋሲል የኔአለም ስለሰላም ውድነህ ማንነቷን የገለጸው።

ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ከሜልበርን ኢትዮጵያዊ ጋር ተወያዩ – ወደ ሲድኒ አመሩ

(ቋጠሮ) – እውቁ ኢትዮጵያዊ ምሁርና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም በሜልበርን የሚገኘው ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን ባደረገላቸው ግብዣ መሰረት ባለፈው እሮብ ኦክተበር 15 ሜልበርን (አውስትራሊያ) ገብተዋል።
ድጋፍ ቡድኑ እኝህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር የህይወት ዘመናቸውን አብዛኛውን ክፍል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ፤ በግል ህይወትን ምቾት ላይ ሳያተኩሩ፤ ለህዝባቸውና ለሃገራቸው ሁለንተናዊ ደህንነት ላደረጉት አስተዋጾና ውለታ ምስጋና ለማቅረብ በማሰብ ያደረገላቸውን ግብዣ በጸጋ ተቀብለው፤ ረዥምና አድካሚውን ጉዞ ተቋቁመው፤ ባለፈው እሮብ ምሽት ሜልበርን ሲገቡ የዝግጅቱ አስተባባሪዎችና በርካታ አዳናቂዎቻቸው በደስታና በእቅፍ አበባ ተቀብለዋቸዋል።

ዘውድ ወይ ጎፈረ ብሎ መመዳደብም መፍትሄ ነው – ዳዊት ዳባ


 “ይምርጡን ሳናዳላ፤ ሳንገል፤ ሳናስር፤ሳንዋሽና ሳንሰርቅ ፍፁም በሆነ አገራዊ ፍቅር አክብረንህ እናስተዳድራለን ”። የምርጫ መሪ ቃል ብትሆን ያልኳት።
ጎሽ እንዲህ ነው መቅደም። አገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ዘጠኝ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል መስማማታቻውን ስሰማ ሀሴት ነው ያደረኩት።  መጀመርያ ዜናውን ስሰማ ጥሩ ነው አልኩ። አንድነትና መድረክ ስይካተቱ የሚፈለገውን ውጤት አያመጣም በሚል አላካበድኩትም ነበር። ደስታዬን ሙሉ ያደረገው  ከሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በኢሳት ላይ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እነዚህ ድርጅቶች  ሀይላቸውን ተጨማሪ ጉለበት የማድረግቸው እድሉ የሰፋ መሆኑን መስማቴ ነው። ፅሁፌን ብዴና እጄ ላይ ቢያስረጀውም ለማንኛውም ብዬ  ለቅቄዋለው።

ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (በዓለማየሁ ገላጋይ)

መክሸፍ እንደ እኔ ጉብኝት
ፍቱን መጽሔት ጥቅምት 15 ቀን 2007 ዓ.ም)
የጉብኝት ጉዞው በማለት ተጀምሯል፤ ያለንበት መኪና ወደ አዲስ አበባ ደቡብ አፍንጫውን ቀስሯል፤ በመካከላችን ጸጥታ ረብቧል…
ጣ ፈንታህ በዘመን እጅ ነው ዘመንት ሲፈቅድ የዘመንህ ‹‹ ጉዱ ካሳ›› ትሆናለህ፤ ስውር እስር ቤት ትገባለህ፤ እንደ እብድ ትታያለህ፤ በመገለል ዘብጥያ ባመደመጥ ዋርድያ ስር ትሆናለህ፡፡ እውነትህ እንደቅራቅንቦ ይቆጠራ ይናቃል…
… ወይም ….
ዘመንህ ሲፈቀድ ካሳ (ዩሐንስ) ትሆናለህ፡፡ ወደ መብት ድንበርህ ትገሰግሳለህ፡፡ አንገትህን ለክብርህ ትሰጣለህ፡፡ ከማንቁርትህ በታች ትመለሳለህ፡፡ ከአገጭህ በላይ ጠላት እጅ ትወድቃለህ …. የራስህ ‹‹መተማ-ዩሐንስ››ትመሰርታለህ… ጠላት የማይሻረው የደም ድንበር ትሆናለህ…

የወያኔ ወሮበላ ዲፕሎማሲያዊነት፣ ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ወያኔ እያለ በሚጠራው እና ትግሉን በሰለጠነ መልኩበጠረጴዛ ውይይት እና የሀሳብ የበላይነት ሳይሆን ከጫካበመግባት ብረትን የኃያልነት ዋስትናበማድረግ በንጹሀን ዜጎች ደም ላይ ተረማምዶ የጫካ ባህሪውን ከነግሳንግሱ እንዳለ ተሸክሞከህዝቦች ፈቃድ ውጭበኃይል በህዝቦች ጫንቃ ላይ ተፈናጥጦ በሚገኘው የሽፍታ ቡድን የበላይነትየሚመራው በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በአፍሪካ ወደር የማይገኝለትአምባገነን እና አረመኒያዊስብስብ እንደሆነ በተደጋጋሚ ስገልጽ ቆይቻለሁ፡፡ ዴሞክራሲ በህዝብ ለህዝብ የተቋቋመ ህዝባዊአስተዳደር ከሆነ የወሮበላ አገዛዝመንግስት ደግሞ በዘራፊዎች እና በወሮበላዎች ለዘራፊዎች እናለወሮበላዎች የተቋቋመ የማፊያ ቡድን ነው፡፡ 

በአርባ ጉጉ እና አካባቢው በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል መካድ አይቻልም – ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን

ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ከሸገር ራዴዮ ጣቢያ ጋር በ09/08/2014 ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ምንም እንኳ አማራውን አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ እርስ በራሱ የተምታታ ቢሆንም፣ አማራውን ህዝብ የለም ከማለት አልፈው በአርባ ጉጉ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ክደዋል። የፕሮፌሰር መስፍን ክህደት ’እስላም ኦሮሞዎች ክርስቲያን ኦሮሞዎችን ነበር የገደሉት’ ለማለት ከሆነ፣ ሀቁና መረጃዎቹ ከፕሮፌሰር መስፍን ክህደት ጋር እንደማይጠጣሙ በተከታታይ መረጃዎችን እየመዘዝን የአርባ ጉጉን እልቂት ለማቅረብ እንሞክራለን።

ተመስገን ደሳለኝ 3 አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት

temesgen1የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዛሬው ቀን በዋለው ችሎት 3 አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት፡፡ ፍትህን ሲያሳትም የነበረውና ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነው ማስተዋል ህትመትና ማስታወቂያ በ10 ሺህ ብር ቅጣት ተጥሎበታል፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጥቅም 3/2007 ዓ.ም የመንግስትን ስም ማጥፋት፣ ህዝብን ማነሳሳትና የህዝብን አመለካከት ማናወጽ በሚሉ ሶስት ክሶች ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን አሁን የተፈረደበት በትኛው እንደሆነ ባይታወቅም በአንደኛው ክስ ነው ተብሏል፡፡

Monday, October 20, 2014

“እኔ ብቻ” ቢያክሙት የማይሽር የወያኔ በሽታ

ዘረኝነት፤ ጎጠኝነትና ዕብሪት የወያኔ አዲሰ ባህሪያት ሳይሆኑ አስራ ሰባት አመት ጫካ ዉስጥ በቆየባቸዉ አመታትና ዛሬም ከጫካ ወጥቶ አገር እየመራ በቆየባቸዉ ሃያ ሦስት አመታት አብረዉት የኖሩ መታወቂያ ካርዶቹ ናቸዉ። ዘረኝነት፤ አማራ ጥላቻና የትግራይ ሪፓብሊክ ህልም ዋና ዋናዎቹን የወያኔ መሪዎች ደደቢት በረሃ ከገቡ በኋላ በድንገት የለከፋቸዉ በሽታ ሳይሆን ከና ከልጅነታቸዉ ተጠናዉቷቸዉ አብሯቸዉ ያደገ በሽታ ነዉ። ወያኔ ጨካኝ ነዉ፤ ወያኔ ዉሸታም ነዉ፤ወያኔ ከሃዲ ነዉ፤ ወያኔ ለኢትዮጵያ ዳርድንበርና የግዛት አንድነት ደንታ የሌለዉ ባዕድ አካል ነዉ። እነዚህ ሁሉ የወያኔን ማንነትና ምንነት በትክክል የሚገልጹ የወያኔ በሽታዎች ናቸዉ። በዛሬዉ ቆይታችን በልዩ መነጽር አብረን የምንመለከተዉ የወያኔ በሽታ ግን በአይነቱ ከእነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት በሽታዎቸ ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም በጠባይና በአገላለጽ ግን ለየት ያለ ነዉ።

ወያኔ፣ ፍትህ እና እኛ – ያሬድ ኃይለማርያም

ያሬድ ኃይለማርያም
ከብራስልስ፣ ቤልጅየም
ጥቅምት 5፣ 2007 ዓ.ም.
ያሬድ ኃይለማርያም ለ7 ዓመታት ያህል ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ካውንስል ጋር አብሮ የሠራና የኖቬምበር 1 እማ 2ቱን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከሃገር ብዙ ምስጢሮችን ይዞ በመውጣት ለአውሮፓ ሕብረት ያቀረበ ነው።
ያሬድ ኃይለማርያም ለ7 ዓመታት ያህል ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ካውንስል ጋር አብሮ የሠራና የኖቬምበር 1 እማ 2ቱን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከሃገር ብዙ ምስጢሮችን ይዞ በመውጣት ለአውሮፓ ሕብረት ያቀረበ ነው።
በመጀመሪያ “ወያኔ፣ … እና እኛ” በሚል ርዕስ የማቀርባቸውን ጽሁፎች ዋና ዓላማ ለአንባቢያን ግልጽ ላድርግ። ዛሬ አገራችን ለምትገኝበት አስከፊና ውስብስብ የፖለቲካ ሁኔታም ሆነ በየግላችን ለደረሰብንና ለገጠሙን ቁሳዊና መንፈሳዊ ኪሳራዎች ሁሉ ተጠያቂው ወያኔ ነው ብለን ስለደመደምን እርግማኖቻችን፣ ነቀፌታችን፣ ዝልፊያችን፣ ወቀሳችን፣ ውንጀላችን፣ ዛቻና ማስፈራሪያችን ሁሉ ወያኔ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው። እርግማንና ዝልፊያ ግፍንና ግፈኞችን ጠራርገው የሚያጠፋ ቢሆን ኖሮ ባለፉት ሃያ አመታት በወያኔ ላይ ያዘነብነው እርግማንና ውርጅብኞች ወያኔን ብቻ ሳይሆን የተቀሩትንም የአፍሪቃ አምባገነኖች ሁሉ ጎርፍ ሆኖ በወሰዳቸው ነበር። በጸሎታችንም ብዛታ እኛ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳንሆን ቀሪውም የአፍሪቃ ሕዝብ ከግፈኞች መዳፍ ነጻ በወጣ ነበር። ያ ግን አልሆነም። የሚያሳዝነው ታዲያ በጩኸታችን፣ በጸሎትና በእርግማን ለአሥርት ዓመታት የተሸከምናቸውን ግፈኞች ከጫንቃችን ላይ ማውርድ አለመቻላችን አይደለም።

አሰደንጋጭ ዜና – ኢቦላ መሰል በሽታ በኢትዮጵያ አሶሳ መከሰቱን አዲስ አድማስ የአካባቢውን የጤና ቢሮ ሃላፊዎች ጥቀሷ ዘገበ ።

አንድ ሰው በበሽታው ሞቷል
የክልሉ ጤና ቢሮ በሽታው ኢቦላ አይደለም ብሏል
በሽተኞች ላይ ደም ማስመለስና ማስቀመጥ ተስተውሏል
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምግብ መበከል ሊሆን ይችላል ተብሎ የተጠረጠረ ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ በሁለት ሰዎች ላይ መከሰቱንና አንደኛው መሞቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃብታሙ ታዬ ለአዲስ አድማስ የገለፁ ሲሆን የኢቦላ በሽታ በክልሉ በየትኛውም አካባቢ አልተከሰተም ብለዋል፡፡
1939914_305162646332436_4991882157842644625_nየተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በክልሉ በሚገኘው ባምባሲ የስደተኞች ጣቢያ በሽታው ተከስቷል ሲሉ ያሰራጩት መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የጠቆሙት የቢሮ ኃላፊው፤ ለጊዜው በትክክል ምንነቱ ያልታወቀው በሽታ የተከሰተው ከስደተኞች ጋር ምንም አይነት ንክኪ በሌለው የአሶሳ ከተማ መንደር 47 በሚባል አካባቢ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሁለቱ ሙሰኛ ባለስልጣናት /ከእየሩሳሌም አርአያ/

የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አባይ ወልዱ ካስገነቧቸው ሁለት ቪላ ቤቶች አንዱን መሸጣቸውን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ። የሕወሐት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አባይ ወልዱ በክልሉ ካስገነቧቸው ሁለት ቪላ ቤቶች አንዱ የሆነውና በመቀሌ – ዓዲ ሃውሲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን ይህን ቪላ ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ወጪ ካስገነቡት በኋላ እንደሸጡት ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ አባይ ወልዱ በባለቤታቸው ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማርያም ስም በአዲግራት ከተማ ባለሶስት ፎቅ ዘመናዊና በውድ ዋጋ የተገነባ ቪላ እንዳላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል።

Sunday, October 19, 2014

የቀድሞው የኢሕአዴግ ባለስልጣን አቶ ኤርሚያስ ለገሰ “ኢሕአዴግ በምርጫ ስልጣኑን ያስረክባል የሚል እምነት የለኝም” አሉ

የቀድሞው በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ስለ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ምርጫ፣ ስለ ምርጫ 97ቱ ግድያ ፣ ስለ አገዛዙ ያልተሳካ የዲያስፖራ ፖሊሲ ፣የሕወሃት ኢትዮጵያን እያተራመሰ ረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ ለመቆየት ማሰቡን ከውስ ተመልካች አንጻር ፈትሸውታል። ስለ ቀጣዩ መጽሐፋቸው መጠነኛ ፍንጭ ሰጥተዋል።

Breaking News: የቀድሞው የኦነግ መሪ ዶ/ር ዲማ ነገዎ ኢትዮጵያ ገቡ

(ዘ-ሐበሻ) ዶክተር ዲማ ነገዎ አዲስ አበባ መግባታቸውን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች አረጋገጡ::
የኦነግ መስራቾችና አንጋፋ መሪዎች፣ እነ ዶ/ር ዲማ ነግዎ፣ አቶ ሌንጮ ለታ የመሳሰሉት፣ የኦሮሞ ጥያቄ የመገንጠል ሳይሆን የዴሞክራሲ ጥያቄ ነዉ በሚል፣ ራሳቸውን ከኦነግ አግልለው፣ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፎረም (ኦዴፍ) የሚባል ድርጅት ማቋቋማቸውን ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ መግለጹዋ ይታወሳል::
የቀድሞው የኦነግ መሪ ዶ/ር ዲማ ነገዎ
የቀድሞው የኦነግ መሪ ዶ/ር ዲማ ነገዎ

ዘንድሮ በሚደረገው የኢትዮጵያ ምርጫ ላይ ለመሳተፍና ድርጅቱንም በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለማስመዝገብ ወደ አዲስ አበባ እንዳቀኑ የገለጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ጉዳዩ ብዙዎችን ማስገረሙን ገልጸዋል::

ተወዳጁ ድምፃዊ ናትናኤል አያሌው (NHATI MAN ) ከአገር ተሰደደ


 ማነው የሚለየው ይህ ትውልድ ፍም እሳት ነው በሚለው ስሜት ቀስቃሽ ዘፈኑ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አድናቆትና ዝናን ያተረፈው ድምፃዊ ናቲ ማን በወያኔ ዘንድ ፍም የሆነችውን ዘፈኑን ለአድማጭ ካደረሰ ጀምሮ ወያኔ ድምፃዊውን መላወሻ አሳጥቶት እንደነበርና የሚያደርሱበትን ችግር መቋቋም ስላቃተው ወደ አውስትራሊያ መሰደዱን ምንጮቻችን ገልፀዋል ።ይህ ድምፃዊ በአገር ቤትና በውጪ አገራት  በሚያቀርባቸው ስራዎቹ ላይ ፍም እሳ የሚለው ዘፈኑን በሚጫወትበት ግዜ ህዝብ ለማነሳሳት ሞክረሃል፣አላማህ ሌላ ነው፣ከጀርባህ ሌሎች ሰዎች አሉ በማለት የተለያዩ ዛቻና ማሰፈራሪያዎች ሲደርሱበት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

Saturday, October 18, 2014

የአሜሪካ መንግስት የሽብር መረጃ የሚጠቁመው ሕወሓትን ወይንስ አልሸባብን ? መረጃ አዘል ዘገባ – ምንሊክ ሳልሳዊ

- ሕወሓት አልሸባብን ሽፋን አድርጎ ፍንዳታ ለመፈጸም እንዳቀደ መረጃዎች ያሳያሉ።
- አሜሪካ ብሄራዊ ጥቅሟን ላለማጣት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ስራዎች እየሰራች ነው።
- አልሸባብ ላይ ማሳበብ ለምን አስፈለገ ?
በምስራቅ አፍሪካ ይንቀሳቀሳሉ ከሚባሉት የአሸባሪ ቡድኖች ስሙ በዋነኛነት የሚጠቀሰው አልሸባብ በቡድን ደረጃ የታጠቀ ሲሆ በመንግስታዊ ሽብርተኝነት ስሙ ተመዝግቦ የሚገኘው የሕወሓት ቡድንም ሌላኛው ነው። እንዲሁም ሻእቢያ በግርግር መሃል ለመሹለክለክ ቢፈልግም ሊቀናችው ካልቻሉ ግን በምክር እና ጥቆማ እንደ አልሸባብ ካሉ የሽብር ድርጅቶች ጀርባ ሲንቀሳቀስ ከመታየቱም አልፎ አሰልጣኞችን እስከ ሶማሊያ መላክ የደረሰ ድርጅት ነው።

አላወቅነውም እንጂ ይህ አገዛዝ የበሰበሰ ነው – ግርማ ካሳ

እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር፣ ኖቬምበር 17 ቀን 1996 ነበር። በሰርቢያ (የቀድሞ ዩጎስላቪያ) ፣ የክልል ምርጫ ይደረጋል። በቩክ ድራስኮቪች የሚመራዉ SPO ፣ በቬስና ፔሲች የሚመራዉ GSS እና ሌሎች ድርጅቶች በአንድ ላይ ሆነው አብላጫ ድምጽ ያገኛሉ። ነገር ግን በወቅቱ የነበሩ አምባገነን ባለስልጣናት፣ እነ ስሎቦዳን ሚሎሶቪች አጭበረበሩ። ከኖቬምበር 17 1996 እስከ ፌቡሩያሪ 11 1997 ድረስ፣ «ያጄድኖ» የሚል፣ ሕዝባዊ ተቃዉሞዎች በስፋት ተደረጉ። ባለስልጣናቱ፣ የሕዝቡ ሰላማዊ ተቃዉሞ አይሎ መምጣቱን ሲያዩ አፈገፈጉ። የተቃዋሚዎች ስብስብ በክልል ምርጫዉ ያገኙትን ምርጫ፣ ተቀበሉ። ሊበራል ዴሞክራቱ ዞራን ጂንጂች የአገሪቷ መዲና የቤል ግሬድ ከንቲባ ሆኑ።

ኢትዮጵያዊቷ በአትላንታ በጠጥቶ ማሽከርከር ለ1 ሰው መሞትና ለ3 ሰው መጎዳት ምክንያት ሆናለች በሚል ተጠርጥራ ታሰረች


  • 4340
     
    Share
kidist temesgen(አድማስ ራድዮ) ቅድስት ተመስገን እስር ቤት ገባች።
ቅድስት ተመስገን ጠጥቶ በመንዳት አደረሰች በተባለው የመኪና አደጋ፣ ለአንድ ሰው ሞትና ለሶስት ሰው መጎዳት ምክንያት ሆነች ተብላ ተጠርጥራ እስር ቤት ገባች። ቅድስት 39 ዓመቷ ሲሆን፣ አደጋውን ያደረሰችው እዚሁ ሜትሮ አትላንታ ነው፤ ከተጎዱት ውስጥ የፖሊስ ባልደረባም አለበት። ፖሊስ እንደሚለው ቅድስት፣ ሲግማን በተባለው መንገድ ላይ ካለ ቴክሳኮ ነዳጅ ማደያ ውስጥ ሁለት መኪና ገጭታ ለማምለጥ ሞክራለች፣ ፖሊስ ሲከታተላት ለማምለጥ ባደረገችው ጥረት ነው ይህ ሁሉ አደጋ የደረሰው ተብላ ተጠርጥራለች።

የደብተሮቹ ጥምጣም ሲፈታ….የታየዉ …. ማህበረ ቅዱሳንን ለቀቅ አርጉት እስቲ!

ከበሲሊዮስ ዘዓማኑኤል
mahibere-kidusan“ሚሉሽን በሰማሽ ገበያ በሎጣሽ”…..  ይላል ያሀገር ሰዉ ሲተርት! ህዝብ ምን እንደሚላችሁና እንዴትስ  ምዕመኑ እንደታከታችሁ በወቃችሁና አፈችሁን ሞልታችሁ ማህበረ ቅዱሳንን ለመዝለፍ….. “አሸባሪ“ ምናምን እያላችሁ ስለማታዉቁትና በልግፅ ስላለገባችሁ ነገር ለመዘባረቅ ባልደፈራችሁ! “የራሷ እያረረ የሰዉ ታማስላለች“ እንዲል አሁንም የሃገር ሰዉ … ደብተሮቹ የሚያስተዳደሩትን ደበርና አጥቢያ በአግባቡ መምራት ተስኗቸዉ ከሙስና ማፅዳት አቅቷቸዉ ሳለ  በሚሊዮኖች መንፈሳዊ የትግል ፅናት ለሃያ አራት ዓመታት ሲገነባ የነበረን ማህበር ለማፈረስ ሲዶሉቱና ሲፈርጁ መዋለቸዉ ሲታወቅ አንግት ያስደፋል!

አገሩን ያልተቀማው ተመስገን!

ከጌታቸው ሽፈራው
ህዝብን ተስፋ ካስቆረጠው 97 ምርጫ በኋላ አዲስ ነገረ ጋዜጣ የመረጃ ምንጭ፣ የመወያያ መድረክና ነቃሽ መሆን ችላ ነበር፡፡ ብዕርን አብዝቶ የሚፈራውና ህዝብ አማራጭ መረጃ ሲያገኝ እንቅልፍ የሚያጣው ገዥ ፓርቲ የአዲስ ነገር ጋዜጠኞችን ማዋከቡን ተያያዘው፡፡ ጫናው እየተጠናከረ በሄደበት አንድ ቅዳሜ ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ‹‹ይህ አገር የማን ነው?›› በሚል ስርዓቱ የሚያደርገውን አፈና፣ አዲስ ነገር ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ዘርዝሮ አስረዳ፡፡ አገሩ የኢትዮጵያውያን ቢሆንም ገዥዎቹ እንደነጠቁን፣ መስራት እንዳልተቻለ በድንቅ የጽሁፍ ችሎታው ቀምሮ አስነበበ፡፡ ተወዳጇ አዲስ ነገር ከዛ ቀን በኋላ ለአንባቢዎች አልደረሰችም፡፡ አገራቸውን የተነጠቁት የአዲስ ነገር ጋዜጠኞችም የተቀሙትን አገር ትተው ተሰድደዋል፡፡

አማረ አረጋዊ በበላበት መጮኹን ቀጥሏል!

ይሄይስ አእምሮ
Amare Aregawi“ውሻ በበላበት ይጮኻል” እንደሚባለው አማረ አረጋዊም የወያኔን የዘረኞች ሥርዓት ከውድቀቱ ለመታደግ በሚመስል ቀቢፀ ተስፋ ባለ በሌለ ኃይሉ ላንቃው እስኪበጠስ እየጮኸ ነው፡፡  የወያኔ የቁርጥ ቀን ውሾች ሁሉ ካላንዳች ይሉኝታ ጩኸታቸውን ሲያቀልጡት ማየት በተለይ የዚህ ዘረኛ የወሮበሎች ቡድን ፀሐይ መጥለቅ ከጀመረችበት ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በጣም የተለመደ ሆኗል፡፡ ለወያኔ መልካም ሽኝት፤ ለውሾችም መልካም ጩኸት እንዲሆንላቸው ከመመኘት ውጪ ምን ማድረግ ይቻላል?
ትግሬ መሆኔን ያላወቀ አንድ ጓደኛየ ዛሬ ጧት ሻይ ስንጠጣ “አንተ ይሄይስ፣ በትግርኛ መዝገበ ቃላት ‹ይሉኝታ› የሚባል ቃል የለም ሲሉ የሰማሁት እውነት ይሆን እንዴ?” አለኝ፡፡ መናደዴን እንዳያውቅብኝ ተጠንቅቄ “ውሻ፣ የውሻ ልጅ፤ አንተም እንደነሱ ልትሆን ነው?” አልኩት፡፡ “እንደነማን?” ሲለኝ ያላሰብኩበት ጥያቄ ስለነበር ወደጠየቀኝ ጥያቄ በቀጥታ አመራሁ፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን የመንግሥት ተቃዋሚ ሆኖ አያውቅም!!! – 10ሩ የኔ ወሳኝ ነጥቦች ስለማህበሩ

ከደብረጊዮርጊስ
ሰሞኑንን ስለማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክህነት ተደረጎ በነበረና “ፓትርያርክ” አቡነ ማቲያስ በመሩት ስብሰባ ላይ የደብር አለቆችና ተወካዮች የተናገሩትን በተለያዩ የመገናኛ መድረኮች ላይ በስፋት ሰምተናል። እንደኔ እይታ የተባሉትና የተደረገው ነገር ሊገጣጠምልኝ አልቻለም። ለመሆኑ ማኅበር ቅዱሳን መቼ ነው መንግሥትን ተቃውሞ የሚያውቀው? ማኅበረ ቅዱሳን ብዙ የመንግሥት ደጋፊ፣ ብዙ የመንግሥት ቀኝ እጅ የሆኑና የመንግሥት ባለሥልጣናት በአባልነት ያሉበትና የሚቆጣጠሩት፤ በመንግሥት ላይም ምንም ዓይነት ተቃውሞ እንዳያነሳ ወይንም እንዳያስተባብር በቅርብ የሚጠብቁት ማኅበር ነው። ሌላው ቀርቶ ስለ ሃገር ጉዳይ አይደለም በቀጥታ ቤተክርስቲያኗን የሚጎዳ ነገር እንኳን መንግሥት ቢፈጽም ማኅበረ ቅዱሳን አንዲት የተቃውሞ ብጣሽ ወረቀት መግለጫ አውጥቶ አያውቅም። እንዲያውም የመንግሥቱ ተባባሪ፣ በሃገርና በቤተክርስቲያን ላይ በደረሰውና እየደረሰ ባለው ውድመት ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተካፋይ ማኅበር ነው። እስኪ በተጨባጭ መረጃዎች እንየው፦

ሁነኛ።

ከሥርጉተ ሥላሴ 17.10.2014 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/
sr1ይቅርታ በመጠይቅ ጡሑፌን ብጀምር ይሻላል ብዬ ወሰንኩኝ። ባለፈው ወር በጀግና አበራ ሃይለመድህን ዙሪያ ወርሃዊ ተግባሬን አልከወንኩም ነበር – ባለመቻል። ስለሆነም ለአድናቂዎቹ – ለአክባሪዎቹ ፈለጉን ለመከተል ለቆረጡ ወጣት የነፃነት አርበኞች ይቅርታ ዝቅ ብዬ – እጠይቃለሁ። ዛሬ ግን በተለመደው አኳኋን ትንሽ ነገር ቆጣጥሬ እንሆ ከች ብያለሁ።
ዕንባ ከውስጥ ቁስለት የሚፈላ የሃዘን መግለጫ ርቁቅ ቋንቋ ነው። ዕንባ የመከፋት ድምጽ አልባ ዬእግዚዎታ ድምጽ ነው። ስለዚህም ዕንባ ጥሩ ተናጋሪ፣ እንዲሁም የውስጥን ስሜትን የሚቀበል የወጣለት ቅን አድማጭ ነው። ዕንባ የአሳር መግለጫነቱ የጭካኔ ግፋዊ አስተዳደር ማዬልን የሚያብራራ የሥጋ ጠብታ ልዩ ሰነድ ነው።

ፓትርያርክ ብፁዕ አባ ማትያስና ተግዳሮቶቻቸው

በተክሉ አባተ
አቡነ ማቲያስ
አቡነ ማቲያስ
ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከተሾሙ እነሆ ሁለት ዓመት ሊሞላቸው አራት ወራት ገደማ ይቀራቸዋል:: ቅድመና ድኅረ ሹመታቸውን ተከትሎ የውይይትና የክርክር መድረኮች በኢትዮጵያም በውጭውም ዓለም ተከፍተው ነበር:: የአምስተኛው ፓትርያርክ የብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ድንገተኛ ሞት አንዳች ለውጥ ለቤተ ክርስቲያኗ ያመጣ ይሆናል ብለው የገመቱና የተመኙ ብዙዎች ነበሩ::

ህወሃት በአማራ ነገድ ሕዝብ ላይ የሚያካሂደውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ የሚያስቆመው ማን ነው?

አንተነህ ገብረየ 
(ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተፈናቀሉ አማሮች፡ ፎቶ ፋይል)
(ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተፈናቀሉ አማሮች፡ ፎቶ ፋይል)
መግቢያ፦ የዛሬ ጹሑፌን ከሰሞኑ ክስተቶች እጀምራለሁ-በዋሽንግተን ዲሲ ከአሜሪካው ፕረዘደንት ጋር ልዩ ውይይት ያደረገው በደሳለኝ ኃይለማርያም የተመራው የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ማደጓንና በምግብ ራሷን መቻሏን ከአሜሪካው ፕረዝደንት ምስክርነት በማግኘቱና በመሞካሸቱ ጮቤ እንደረገጠና ስለወደፊቱ የህወሃት መንግሥትና አሜሪካ ወዳጃሞች ሆነው በጋራ ስለሚቀጥሉበት በየተራ የተደረጉት ንግግሮች ሁለቱንም ትእዝብት ውስጥ የሚከትና ነገ ቁጭትን የሚግት መሆኑ ባይዘነጋም ከሁለቱም ዘንድ በጣም ጽንፍ የሆኑትን ነጥሎ መጥቀስ አስፈላጊ ነው።አሜሪካ ብቻ ሳትሆን ሁሉም የበለፀጉ አገሮች ለሦስተኛው ዓለም አገሮች በተለይም በሕዝብ ላልተመረጡ ጨካኝ የአፍሪካ መሪዎች (un elected dictator african leaders) እርዳታ የሚሰጡት ዲያስፖራውን ጨምሮ የየአገራቸው ሕዝብ የሚከፍለውን የታክስ ገንዘብ መሆኑ ይታወቃል።

የውያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልኡካን ብድን በኖርዌይ ኦስሎ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው

የኖርዌይ አፍሪካ የንግድ ማህበር በኦክቶበር 16, 2014 ባዘጋጀው ሴሚናር ላይ ለመካፈል በማህበሩ ተጋባዠ በመሆን ወደ ኖርዌይ የመጡ የውያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቲዮድሮስ አድሃኖም እና በስዊዲን የኢትዮጲያ አምባሳደር የሆኑት ወይንሽት ታደስ እንዲሁም ሌሎች ተላላኪ የወያኔ ባለ ስልጣናት በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ፣ በኖርዌይ ኦስሎ እና በአካባቢው የሚኖሩ የድርጅቱ አባሎችና ደጋፊዎች በተገኙበት ታላቅ ተቃውሞ ገጠማችው::

የጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የአዙሳ ዩኒቨርሲቲ የክብር ስነ-ስርዓት መሰረዝና ያስከተለው ውዝግብ

ነሐሴ 6 2006ዓም የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛዉ ቋንቋ አገልግሎት በኢትዮጵያ መንግሥትና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን (ዳያስፖራ) መካከል ያለዉን ግንኙነት የገመገመ ዝግጅት ማቅረቡ ይታወሳል።
top_logo_newsበዝግጅቱ ዉስጥ ከተካተቱት በርካታ ርእሶች መካከል የካሊፎርኒያው አዙሳ ፓሲፊክ ዩኒቨርሲቲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሊሰጥ አቅዶ የነበረዉ የክብር ስነስርዓት የሰረዘበት ምክንያት አንዱ ነበር። ርዕሰ ጉዳዩን አስመልክቶ የተጠናከረ ዘገባ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ መሰራጨቱን ተከትሎ፤ አንዳንድ የአሜሪካ ድምጽ ጋዜጠኞች “ሆን ብለዉ እዉነትን አዛብተዋል።” የኢትዮጵያ ሕዝብ “የዳያስፖራዉን ድምጽ እንዳይሰማ አፍነዋል” የሚሉና በተለይም አዙሳ ዩኒቬርሲቲ ሽልማቱን እንዲሰርዝ ዘመቻ ካደረጉት አንዱ ጋዜጠኛና የፖለቲካ አክቲቪስት አቶ አበበ ገላዉ ቪኦኤ ላይ ያቀረባቸዉ ክሶች በራሱ ድረ ገጽ አዲስ ድምጽ፣ በኢሳትና በሌሎች የዳይስፓራ መገናኛ ብዙሃን ሲሰራጭ ሰንብቷል።

ሥነ-ኪን ወይስ ኪነ-ጥበብ? ሥነ-ጥበብስ ምንድን ናት? ዓላማ ግቧና ጥቅም አገልግሎቷስ?

art-music-dance-photo
ብዙውን ጊዜ ሥነ-ኪን ወይም የጥበብ ሥራ፣ ነገረ-ጥበብ ማለት እንፈልግና ኪነ-ጥበብ የሚለውን ቃልና ሥነ-ጥበብ የሚለውን ቃል እያጣረስን ስንጠቀም እንስተዋላለን፡፡ ኪነ-ጥበብ ወይም ኪነ-ጥበባት የሚለው ቃል ራሱ ግራ የተጋባ ቃል ነው፡፡ ልንጠቀምበት ፈልገን በምንጠቀምበት ቦታ ሁሉ ሰዋስዉ የተሳሳተ (Grammatically wrong) በሆነ መንገድ ነው፡፡ ቃሉ የግዕዝ ቃል ቢሆንም እነኝህን ሁለት ቃላት ማጣመር ግን የሰዋስው ስሕተትን ይፈጥራል፡፡ ምክንያቱም ኪን የሚለው ቃል ትርጉም ራሱ ጥበብ ማለት ነውና፡፡

The honorable Ato Gebru Asrat and his politics (Yilma Bekele)

gebru bookThe honorable Ato Gebru Asrat has written a very fat book that is five hundred pages long. I am assuming that the purpose of the book was to present himself as a person of vision and to show us his leadership ability and a map of the road to the future. Unfortunately, he has a handicap that cannot be glossed over since for many years he has operated as member of that infamous organization TPLF (ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ) that is still creating havoc in the life of our people and our country. It is a tough challenge for anyone to try to explain or to find justification for a party that is viewed by a vast majority of Ethiopians in a negative light. I doubt anyone envies the individuals dilemma.

“የዲግሪና የዲፕሎማ ወፍጮ ቤቶች” ተፈጭና ተመረቅ – አስተምሮ መለስ

degree mill
በእንግሊዝኛው አጠራር የዲፕሎማ/የዲግሪ ወፍጮ ቤት (diploma/degree mills) ይባላሉ፡፡ በርካታዎቹ ሠለጠነ በሚባለው ዓለም ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ “ወፍጮ ቤቶች” የ“ትምህርት መረጃ” ለማግኘት በጣም ቀላል ነው፡፡ ዋናው መስፈርት አስፈላጊውን “የትምህርት ክፍያ” መፈጸም ብቻ ነው ፡፡ ከዚያ በወርቅ ቅብ የተንቆጠቆጠ “የባችለር” ወይም “የማስተርስ” ወይም “የዶክትሬት (ፒ.ኤች.ዲ.)” ዲግሪዎችን ማፈስ ነው፡፡ በቀጣይ የሚሆነው የ…ሚ/ር ወይም የ…ሚኒስትር ደኤታ ወዘተ መሆንና “በሹመት መዳበር” ነው፡፡ ከዚያ ህዝብ አናት ላይ “በስያሜ” ተቀምጦ መጋለብ ነው።

ሰማያዊ፣ መኢዴፓና ኢብአፓ የምርጫ ቦርድን ስብሰባ ረግጠው ወጡ ከደቡብ ኅብረት ፕሮፌሰር በየነ ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል

eth election