(EMF) “ባለቤት አልባ ከተማ” በሚል ርዕስ የተጻፈው መጽሃፍ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጾች መውጣት ከጀመረ ሰነበተ። ይህ የሆነበት ምክንያት አንድም የመጽሃፍ እጥረት በመኖሩ እና በተለይም በአገር ቤት መጽሃፉ ሊታተም ባለመቻሉ እና ኢትዮጵያ የሚገኙ አንባብያን መጽሃፉን ገዝተው ማንበብ ባለመቻላቸው ነው የሚል እምነት አለን። የታሪኩ ጸሃፊ በመጀመሪያው ገጽ ላይ “የማንም ያልሆነች፣ የማንም ያይደለች የግል ማስታወሻ” እንዳለው ሁሉ፤ ይህ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ታሪክ በመሆኑ በድረ ገጻችን ላይ ልናካፍላቹህ ወደድን።
ይህም ሆኖ ግን… ምንም ይሁን ምን አቅም እስከፈቀደ ድረስ የመጽሃፉን ኮፒ በዚህ መልክ ከማግኘት ይልቅ መግዛቱ ይመረጣል። መጽሃፉን በመግዛት በእጃችን የራሳችን የሆነ የታሪክ ማስታወሻ ይኑረን። ይህ ለህትመት ያበቃነው ጽሁፍ ከኛ ጋር ላይቆይ ይችላል። በመሆኑም አማራጩ እስካለ ድረስ ማንኛችንም መጽሃፉን ገዝተን ማንበብ ብቻ ሳይሆን በታሪክ መዘክርነት ልናቆየው ይገባል። በዚህ አጋጣሚ ደራሲውም ሆነ አሳታሚው ይህንን ማስታወሻ ለህትመት በማብቃታችን ቅሬታ ካላቸው በአስቸኳይ እንዲያሳውቁን በትህትና እንጠይቃለን።
No comments:
Post a Comment