ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ወያኔ እያለ በሚጠራው እና ትግሉን በሰለጠነ መልኩበጠረጴዛ ውይይት እና የሀሳብ የበላይነት ሳይሆን ከጫካበመግባት ብረትን የኃያልነት ዋስትናበማድረግ በንጹሀን ዜጎች ደም ላይ ተረማምዶ የጫካ ባህሪውን ከነግሳንግሱ እንዳለ ተሸክሞከህዝቦች ፈቃድ ውጭበኃይል በህዝቦች ጫንቃ ላይ ተፈናጥጦ በሚገኘው የሽፍታ ቡድን የበላይነትየሚመራው በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በአፍሪካ ወደር የማይገኝለትአምባገነን እና አረመኒያዊስብስብ እንደሆነ በተደጋጋሚ ስገልጽ ቆይቻለሁ፡፡ ዴሞክራሲ በህዝብ ለህዝብ የተቋቋመ ህዝባዊአስተዳደር ከሆነ የወሮበላ አገዛዝመንግስት ደግሞ በዘራፊዎች እና በወሮበላዎች ለዘራፊዎች እናለወሮበላዎች የተቋቋመ የማፊያ ቡድን ነው፡፡
በዚህች ትችቴ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እያራመደ ያለውን የሀገር ውስጥየዲፕሎማሲ ፖሊሲ ለመቃኘት አይደለም፡፡ ሆኖም ግንትኩረት በማድረግ ለመዳሰስ የምሞክረውህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የተባለው የወሮበላ ስብስብ ቡድን በማራመድ ላይ ያለውን ዓለምአቀፍየዲፕሎማሲ ፖሊሲን ለመቃኘት ነው፡፡ በቅርቡ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢውስጥ አረመኒያዊ እና ግልብ መንፈስ የተጠናወተው አንድየጦር መሳሪያ ታጥቆ ኢትዮጵያውያን/ት ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ተኩሶ ለመግደል በርካታ ጥይቶችን ሲተኩስ የነበረውን እና ለግድያሀራራው ሳይሳካለትየቀረውን የወያኔ ወኪል ለመግለጽ የወሮበላ ዲፕሎማሲ እና የወሮበላዲፕሎማት የሚሉትን ቃላት እጠቀማለሁ፡፡
እንደ ሬውተርስ የዜና ወኪል አገላለጽ ‘ባለጠመንጃው ሰው’ እየተባለ ይጠራ የነበረው በአሜሪካየኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንደጅብራ ተገትሮበሰላማዊ መንገድ ጥያቄዎቻቸውንለማቅረብ ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢ በሄዱት በንጹሀን ኢትዮጵያዊያን/ት ዜጎች ላይ ሲተኩስየነበረው በስም ሰሎሞንታደሰ ገብረስላሴ የተባለው የወያኔ ባለሙሉ ስልጣን የደህንነት አታሼነበር፡፡ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 29/2014 የተደረገው የሰሎሞን ገብረስላሴ አስደንጋጩእናአሳፋሪው የእሩምታ ተኩስ ጉዳይ በዓለም አቀፉ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮበክብር እና ሞገስ ሳይሆን በቅሌት እና በውርደት፣በጥበበኛነት እና በምሁርነት ሳይሆንበጅላጅልነት እና በደንቆሮነት፣ በታጋሽነት እና በአርቆ አስተዋይነት ሳይሆን በግልፍተኝነት እናበቅርብ አሳቢነትሲታወስ ይኖራል፡፡
እንደ ሬውተርስ የዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ “የዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ቃል አቀባይ ከቀኑበ12፡15 ሰዓት በሰሜናዊ ምዕራብ ዋሺንግተን ዲ.ሲበሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢውስጥ ተኩስ እንደተሰማ ፖሊስ በስፍራው በመገኘት ተኳሹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወደ እስርቤት ልኮታል፡፡የዓይን እማኞች እንደገለጹት ከሆነ የጥይት ተኩሱ የተከናወነው ሰላማዊተቃዋሚዎች ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢ በተጠጉ ጊዜ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥርግቢ ውስጥ ነውብለዋል…“
“የወያኔን ኤምባሲ መውረር”
በሰላማዊ ተቃዋሚዎች የተወሰዱ በርካታ የቪዲዮ ክሊፖች እንደሚያስረዱት እና የኢትዮጵያሳቴላይት ቴሌቪዥን/ኢሳት አገልግሎት እንዳመለከተውበቅርቡ በኢትዮጵያ በኦጋዴን እናበጋምቤላ ክልሎች በወያኔ ገዥ አካል ታጣቂዎች በንጹሀን ዜጎች ላይ የተወሰደውን አረመኒያዊጭፍጨፋ እና ግድያበማስመልከት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት ተቃውሟቸውንለመግለጽ እና የወያኔው አምባሳደር ከሆኑት ከአቶ ግርማ ብሩ ጋር በጠረጴዛዙሪያ የፊት ለፊትውይይት ለማድረግ በሄዱት የሰላማዊ ተቃዋሚ ቡድን ግለሰቦች ጥያቄ ማቅረብ ምክንያት ነበር፡፡
አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ሰላማዊ ተቃዋሚ ከወሰደው የቪዲዮ ክሊፕ እንደሚታየው ሰላማዊተቃዋሚዎች በመጀመሪያ ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢለመግባት ሲያደርጉ የነበረውን ሁኔታ በግልጽያመለክታል፡፡ የተወሰደው የቪዲዮ ምስል የተሰባሰቡ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በኤምባሲው ቅጥርግቢበመግባት በግቢው ውስጥ ባለ መቀመጫ ቦታ ላይ የደረሱ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ የኤምባሲውሰራተኞች ለደህንነት ተብሎ ከታጠረው መስታወትበስተጀርባ ሆነው በመመልከት ላይ ነበሩ፡፡ሰላማዊ ተቃዋሚዎች አምባሳደሩን ማነጋጋር እንደሚፈልጉ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ በርካታዎቹ ሰላማዊተቃዋሚዎችድምጻቸውን ከፍ በማድረግ ጩኸት በማሰማት መፈክሮችን ያስተጋቡ ነበር፡፡ከመካከላቸው አንዱ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣ “ይህ የወያኔ ኤምባሲ እንጂየኢትዮጵያ ኤምባሲአይደለም፡፡“ ሌላኛው ሰላማዊ ተቃዋሚ ደግሞ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቀረበ፣ “ከአቶ ግርማ ብሩ(ከወያኔው አምባሳደር) ጋር ለመነጋገርእንፈልጋለን፡፡ ከእርሳቸው ጋር ስለኦጋዴን፣ ጋምቤላ እናስለአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ መወያየት እንፈልጋለን፡፡“ ሌሎች ሰላማዊ ተቃዋሚዎችደግሞየአንዳርጋቸው ጽጌ (ከጥቂት ወራት በፊት በወያኔ ገዥ አካል ከየመን ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያከተወሰዱት የግንቦት 7 የአመራር አባል) ምስልያለበትን ቲሸርት በመልበስ እርሳቸው ከእስርእንዲፈቱ ሲጠይቁ ነበር፡፡ ሌላ አንድ ሰላማዊ ተቃዋሚ ደግሞ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣“እስክንድር ነጋ(በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው እና በወያኔ ገዥ አካል የ18ዓመታትእስራት ተበይኖበት በአሁኑ ጊዜ ቃሊቲ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤትበመማቀቅ ላይ የሚገኘው)ጋዜጠኛ ይፈታ“ ሌላው ማንነቱ በውል ያልታወቀ ሰላማዊ ተቃዋሚ እንዲህ በማለት ጨኸትሲያሰማ ነበር፣ “በጎሳ ክፍፍልአገዛዝ ታመናል፣ እናም ሰልችቶናል“ በግልጽ እንዲህ የሚል ጥያቄአቅርቦ ነበር፣ “በእንደዚህ ያለ ወሮበላ አገዛዝ እስከ መቸ ድረስ ነው ስንገዛ የምንኖረው?እኛታመናል፣ እናም በዘራፊዎች እና በወሮበሎች መገዛት ሰልችቶናል!“
በኢሳት የተወሰደ የቪዲዮ ምስል እንደሚያሳየው ሁሉም ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዙት ነገሮች ሁሉከኤምባሲው ቅጥር ግቢ የተከናወኑ መሆናቸውን ነው፡፡ከአራት ሰላማዊ አመጸኞች መካከልአንደኛው የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ የያዘ ሲሆን ጥቁር ልብስ ወደ ለበሰው እና መሳሪያወደታጠቀው ገብረስላሴየሚባል የኤምባሲው አታሼ ሲቀርብ ያሳያል፡፡ ወዲያውኑም ገብረስላሴበማነጣጠር ወደ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች አቅጣጫ መተኮስ ጀመረ፡፡ ሆኖም ግንዒላማውን ስቷል፡፡ሰላማዊ አመጸኞች ያለምንም ፍርሀት ወደ ገብረስላሴ መቅረብ ጀመሩ፡፡ ማንነቱ በውል ያልታወቀአንድ ሰላማዊ ተቃዋሚ እንዲህበማለት ድምጹን ከፍ በማድረግ በድጋሜ ጩኸቱን ማሰማትጀመረ፣ “እኛ ወንጀለኞች አይደለንም፣ ግርማ ብሩን ጥሩልን፣ ከእርሳቸው ጋርለመነጋገርእንፈልጋለን፡፡“ ሌላው ሰላማዊ ተቃዋሚ ገብረስላሴን በድፍረት እንዲህ ይለው ነበር፣ “ወደ ፊትቀጥል፡፡ ተኩስ!“ በዚህን ጊዜ ገብረስላሴሽጉጡን ወደ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በማነጣጠር እነርሱንስሜታዊ እንዲሆኑ በመገፋፋት ወደ ኤምባሲው ዋና ህንጻ በመግባት የሽሽት ሙከራማድረግጀመረ፡፡ በዚህ ሂደት ላይም ገብረስላሴ ሽጉጡን ወደ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በመደገን በተደጋጋሚለማስፈራራት ሞከረ፡፡ በመጨረሻም ጥይቶቹንበሙሉ ተኩሶ ስለጨረሰ ሽጉጡ ጥይት አልባበመሆን የባዶ ሽጉጥ ድምጽ ሲያቃጭል ይሰማ ጀመር፡፡ ባለመሳሪያው እብሪተኛ ደንቆሮ ወደኤምባሲው ህንጻዘልቆ በመግባት አስተማማኝ ጥበቃ ባለበት ለእንግዶች ጊዚያዊ ማረፊያወደተዘጋጀው ወደ ሰራተኞች አካባቢ በመሸሽ ሄደ፡፡ በመጨረሻም አንድ ሰላማዊተቃዋሚ ወደባንዲራ መስቀያ ቦታው በመሄድ በመሀከሉ ላይ የኮከብ ምልክት ያለበትን የወያኔን ባንዲራከተሰቀለበት በማውረድ በኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማበመተካት የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ሲሰቅልታየ፡፡ በመጨረሻም ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢ ዘልቀው በመግባት ወደጊዚያዊማረፊያ ቦታው በመሄድ ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ መጮህ ጀመሩ፣”ነጻነት ነጻነት…“በማለት፡፡
ለተለያዩ ድርጅቶች የሚሰራው የምርመራ ጋዜጠኛ እና ዕውቁ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተሟጋችየሆነው አበበ ገላው ከሌላ ምንጭ ያገኘውን መረጃ ዋቢበማድረግ እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቧል፣“በዩኤስ አቃቤ ሕግ በዋሺንግቶን ከተማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው ቢል ሚለር በገብረስላሴላይ በመግደልሙከራ እና ታጥቆም በመገኘቱ ምክንያት ለህግ ቢቀርብ እስከ 30 ዓመታትበእስራት ሊያስቀጣ የሚችል የክስ መጥሪያ ወጥቶበታል“ብሎ ነበር፡፡ የአሜሪካመንግስት መምሪያቃል አቀፈባይ የሆኑት ጀን ፔንሳኪ የወያኔ ገዥ አካል የተኳሹን የገብረስላሴን ያለመከሰስ መብትለማንሳት እና ለህግ እንዲቀርብለማድረግ ፈቃደኛ ያለመሆኑን መግለጹን በማስመለከት እንዲህብለው ነበር፣ “ለኤምባሲው የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆኗል፣ እናም በአሁኑ ጊዜየወንጀልተጠርጣሪው ግለሰብ አገር ለቅቆ ወጥቷል፡፡“
አስቀያሚውን የጫካ ትዝታ በዋሺንግተን ዲ.ሲ መተግበር?
እስከ አሁን ድረስ በዋሺንግተን ዲ.ሲ የዲፕሎማሲ ታሪክ የወያኔ “ዲፕሎማሲ” በሰላማዊ መንገድጥያቂያቸውን ባቀረቡ ዜጎች ላይ መሳሪያ አውጥቶበመተኮስ ማስተናገድ የዴሞክራሲ አባትበሆነችው አሜሪካ ውስጥ ካሉ በየትኛውም ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በታሪክ ያልተሞከረየመጀመሪያው ሆኖተመዝግቧል፡፡ ሰሎሞን ገብረስላሴ አነጣጥሮ ተኳሽ ነውን? ጫካ ውስጥበነበረበት ወቅት ከደርግ ጋር ሲያካሂደው የነበረው የዚያ ጦርነት አስቀያሚ ትዝታድንገት ብልጭብሎበት ይሆን እንዴ? ሰሎሞን ገብረስላሴ በኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተቃውሟቸውን በሰላማዊመንገድ ለማሰማት በተሰባሰቡ ሰላማዊተቃዋሚዎች ላይ በየትኛውም የዲፕሎማሲያዊ ተቋም ላይተሞክሮ ያልታወቀውን ስልጣኔ የጎደለውን የደንቆሮዎች ድርጊት በመናፈቅ ተኩስከፍቶወገኖቻችንን ለመጨረስ መሞከሩ በእውነት በጫካ በነበረበት ጊዜ ወያኔን ሲቃወሙ የነበሩትንወገኖቻችንን ሁሉ ሲጨርስ እንደነበረው ሁሉ አሁንምያንን እኩይ ምግባር የዓለም የዴሞክራሲተምሳሌት በሆነችው አሜሪካ እምብርት ዋሺንገተን ዲ.ሲ. ላይ ልምዱን ለማስታወስ ያህልሲነሽጠው የክለሳ ስራመስራቱ ይሆን እንዴ? ‘ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባ’ እንዲሉ!
ገብረስላሴ የፈጸመው እኩይ ድርጊት በስነልቦና ሳይንስ ትምህርት ተመራማሪዎች ‘አስቀያሚ ትዝታ’በመባል የሚታወቀውን ከአዕምሮ ጋር ተቆራኝቶየሚኖረውን እና ሳይታሰብ እና በድንገት ቅጽበታዊበሆነ መልኩ በአንድ ምክንያታዊም ሆነ ኢምክንያታዊ ክስተት በሚፈጸምበት ጊዜ ላይ ግንፍልብሎበመውጣት ወደ ድርጊት ከሚሸጋገር ስነልቦናዊ ድርጊት ጋር ይመሳሰላል፡፡ ከዚህ አንጻር ገብረስላሴያልታጠቁ ሰላማዊ አመጸኞችን በኤምባሲው ቅጥርግቢ አካባቢ በተመለከተ ጊዜ በአዕምሮስነልቦናው ውስጥ ተቀርጾ የተነበበው በከፍተኛ ወኔ እና ከባድ መሳሪዎችን ታጥቆ በመምጣትየእርሱን የአማጺቡድን ወያኔን ለመውጋት የመጣ ሰራዊት መስሎ ነው የታየው፡፡ በግልብአዕምሮው ውስጥ ተጽፎ የሚታየው ይኸው ነው፡፡ ሌላ በጎ ነገር በቡድንም ሆንበግልያልለመዱትን እና ያላዩትን ነገር ለሰሎሞን ገብረስላሴ ከየትኛው ተሞክሮው ተቀምሮ በአዕምሮውጓዳ ውስጥ አድሮ ሊከሰት ይችላል ተብሎይታሰባል? ጀግናው ገብረስላሴ ያንን የመሰለ ድርጊትበሚጽምበት በዚያን ጊዜ የሀገሮች መስተጋብር ማስፈጸሚያ የሆነውን ኤምባሲን የሚጠብቅመስሎአልታየውም፡፡ ይልቁንም በአዕምሮው ላይ ተቀርጾ የኖረው እና አሁንም ያለው የወያኔን የመሬትውስጥ ምሽግ ጫካ በነበረበት ጊዜ ከጠላትለመከላከል የሚያደርገውን ቅጽበታዊ እርምጃመውሰድን ነው የሚያስታውሰው፡፡ ወዲ ገብረስላሴ በድል አድራጊነት በሚመስል መልኩ ሽጉጡንእያወዛወዘበዲፕሎማት ወግ ጥቁር ሱፉን ገድግዶ ለብሶ በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ሲተኩስበታላቋ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ለዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ በከፍተኛደረጃ የውጭ አገርየዲፕሎማት ሰው መቀመጫ ወንበር ላይ መሆኑን ፍጹም በሆነ መልኩ እረስቶታል፡፡ አይ ጫካመኖር! የጫካ አስተሳሰብ እኮ በጫካውውስጥ ያሸነፈ ይኑር የሚለውን የአራዊት አስተሳሰብንየተላበሰ ሆኖ ይገኛል፡፡ ወዲ ገብረስላሴ በጫካ ህይወቱ ጊዜ ጠላትን ለመከላከል እና አለቆቹንጠላትከሚያደርሰው ጥቃት ለመጠበቅ ከአዛዦቹ ይሰጥ የነበረውን ትዕዛዝ ተቀብሎ ይተገብርወደነበረበት የወያኔ አማጺ ቡድን እግረኛ ተዋጊነት ስራው ተመለሰእንጅ ዘመናዊ አስተሳሰብ እናየትምህርት ክህሎት ከሚጠይቀው ዲፕሎማትነት ጋር ትውውቅም ሆነ ዝምድና የሌለው መሆኑንበሚገባ ተግብሮ እናአስመስክሮ ወደ አገሩ ሳይሆን ወደ መፈንጫው ተመልሷል፡፡
ሰሎሞን ገብረስላሴ ስለ ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ተልዕኮ እና የውጭ ዲፕሎማት የኗሪነት ፖሊሲእና ህግ ጥበቃ ምን እንደሆነ እና ምን እንደሚመስልየማያውቀው መሆኑ በግልጽ ይነበባል፡፡አሜሪካ በውጭ የሚገኙ ኤምባሲዎቿን ከማንኛውም የጠላት ጥቃት ለመከላከል ፈጣን የሆኑ የባህርኃይልሰራዊቷን በማሰማራት ጥበቃ እንደምታደርገው ሳይሆን በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካየሚገኙትን የዲፕሎማሲ ፋሲሊቲዎችን ጥበቃ በሚመለከት ግንኃላፊነቱ የወደቀው በአሜሪካየመንግስት መምሪያ፣ በደህንነት አገልግሎቱ እና በአካባቢ የፖሊስ ወኪሎች የጋራ ጥረት ላይ ነው፡፡ከዚህ አንጻር የዋሺንግቶንከተማ ፖሊስ ለዲፕሎማሲያዊ ፋሲሊቲዎች ደህንነት ሲባል የተለያዩመንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ጥበቃ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነምለጥበቃው በተለይምዘብ ለተወሰኑ ፋሲሊቲዎች ወይም ደግሞ ለደህንነት ጉዳይ ሲባል እየተዘዋወሩ የሚጠብቁ ዘቦችንበመመደብ እና የፖሊስ ምልክትያለባቸውን ተሽከርካሪዎች በማሰማራት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡እንደዚሁም ደግሞ መረጃ የማይሰጠው የደህንነት አገልግሎቱ መስሪያ ቤት በዋሺንግትንዲ.ሲአካባቢ ላሉ የዲፕሎማሲያዊ ተቋማት ተገቢ የሆነ ጥበቃ ይሰጣል፡፡ ይህ የደህንነት አገልግሎትመስሪያ ቤት በዲፕሎማቱ ማህበረሰብ እናበዲፕሎማቶች ፋሲሊቲዎች ላይ ሊፈጸም የታሰበአስተማማኝ አደጋ መኖሩን ሲያረጋግጥ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
ያለመከሰስ መብት የተጎናጸፉት ዲፕሎማቶች በማንኛውም መልኩ የጦር መሳሪያን በመጠቀምሌሎችን ሰላማዊ በሆነ መልክ ተቃውሟቸውን በሚገልጹያልታጠቁ ወገኖች ላይ ጥቃት መሰንዘር፣ዲፕሎማቶች በእራሳቸው ሀገር በሌሎች ወገኖች ላይ ጥቃት ለማድረስ ሲባል የጦር መሳሪያ ደብቆመገኘት፣ ወይምደግሞ በድብቅ መሳሪዎችን በማከማቸት በዩናይትድ ስቴትስ ወይም በዩናይትድስቴትስ በሚኖሩ ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን በሚያካሂዱ ዲፕሎማቶችላይ ጥቃት መሰንዘርንየሚፈቅድ ህግ፣ ፖሊሲ ወይም ደግሞ ልምድ በፍጹም የለም፡፡ ዲፕሎማቶች አለመግባባቶችን እናውዝግቦችን በሰላማዊ እናበሰለጠነ መንገድ ለመፍታት የቃላት “ጥይቶችን” ይጠቀማሉ እንጅእንደ ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴ እየተገበረው እንደነበረው ቁጥር 38 የካሊበርሽጉጦችንአይጠቀሙም፡፡ ወዲ ገብረስላሴ በኤምባሲ ቅጥር ግቢ አካባቢ መሳሪያ በመተኮስ ያልታጠቁሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ለመግደል በተደጋጋሚባደረገው የግድያ ሙከራ በዋሺንግተን ዲ.ሲየዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ህሊና ቢስ እና የሞራል ስብዕናን የጣሰ የወንጀል ድርጊት ሆኖ ሲታወስይኖራል፡፡ይህ አስነዋሪ የወንጀል ድርጊት ወደፊት ለሚመጡት አስርት ዓመታት የወሮበላየዲፕሎማሲ እኩይ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ የሚያግዙ ለዓለም አቀፍ የህግእና የዲፕሎማሲተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የማስተማሪያ ጽሑፎችን ለማዘጋጀት ታላቅ እገዛን ያደርጋል፡፡
ወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱን ልታላቀቀውአትችልም፣
የዲፕሎማት ሰዎች ተቀራርቦ በመነጋገር፣ ስምምነት በማድረግ እና በመቻቻል (አብዛኛውን ጊዜበማታለል) ባለመግባባት የሚከሰቱ ውዝግቦችን ለመፍታትይፈልጋሉ፡፡ የወሮበላ ዲፕሎማቶችሁሉንም ችግሮች እና ከዚእነዚህ ክሶች ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ውዝግቦችን በመግደል፣በመደብደብ ወደ ዘብጥያበመወርወር እና የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን እና ጠላቶቻቸውንበማሰቃየት ይፈታሉ፡፡ ዲፕሎማሲ “በመንግስታት ተወካዮች መካከል የሚደረጉስምምቶችንለማምጣት የሚያገለግል ትምህርት እና የተግባር ተሞክሮ ነው፡፡“ ወሮበላ ዲፕሎማት ሰሎሞንገብረስላሴ የዲፕሎማት ትምህርቱን ያገኘው እናየቀሰመው ዙ ኢንላይ ከሚባለው ተረታዊየዲፕለማት ትምህርት ቤት ነው፡፡ “ሁሉም ዲፕሎማሲ በማንኛውም መንገድ ቢሆን የጦርነትቀጣይነት ነው፡፡“ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴ በዲፕሎማቲክ ያለመከሰስ መብትን መደበቂያ ምሽግበማድረግ ለአስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የዘለቀውን አከፊውንየወያኔን የጫካ ጦርነትወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለማምጣት ፈለገ፡፡
የሰለጠኑ ወሮበላ ዲፕሎማቶች ያለመከሰስ መብታቸው ተጠብቆ የሚመረጡት እና የሚላኩት እጅግአናሳ በሆነ አጋጣሚ ነው፡፡ አብዛኞቹ አገሮች ወደ ሌላአገር የሚያሰማሯቸውን ዲፕሎማቶችየሚመርጧቸው በመንግስት መስሪ ቤቶች ከሚመድቧቸው በከፍተኛ ደረጃ ካሉ ሰዎች መካከልነው፡፡ አብዛኞቹየሚመረጡት ዲፕሎማቶችም በከፍተኛ ደረጃ ትምህርት የቀሰሙ፣ ሰፊ ልምድያካበቱ እና ጠለቅ ያለ የፖለቲካ እውቀት ያላቸውን ዜጎች ነው፡፡ ብዙአገሮችም የዲፕሎማትሰዎቻቸውን ሾመው ወደመደቧቸው አገሮች ከመላካቸው በፊት ሙያዊ የሆነ እና ከሙያው ጋርአግባብነት ያለው ስልጠናበማዘጋጀት እንዲሰለጥኑ ያደርጋሉ፡፡
እጅግ በጣም ውሱን ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሀገር ቢሆን እንደ ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴያለውን ተራ ማይም ደንቆሮ መርጦ እንደ ዩናይትድ ስቴትስባለች አገር ላይ ዲፕሎማት ብሎአይልክም፡፡ በዲፕሎማቲክ መስኩ በጣም ቀልጣፎች ያልሆኑ አገሮች እንኳ ለዲፕሎማሲ ተልዕኮየመለመሏቸውን ሰዎችወደየሀገሮች ከመላካቸው በፊት ስለዲፕሎማሲ ስራ ሰልጠና ይሰጧቸዋል፡፡በዚህም መሰረት በየጊዜው ከሚለዋወጠው ዓለም አቀፍ ሁኔታ ጋር አብረውለመሄድ እንዲችሉእገዛ ያደርግላቸዋል፡፡ ያ የሚሰጠው ስልጠናም በትክክለኛው መንገድ በዲፕሎማሲ ስራ እና ተግባርላይ ትኩረት ያደረገ እንጅስለጦርነት ስልት እውቀት ወይም ዜጎችን በአገራቸው እንዴት መግደልእንደሚችሉ ለማሰልጠን አይደለም፡፡ ለምሳሌም ያህል አዘረባጃን የእራሷ የሆነ“የዲፕሎማሲአካዳሚ” አላት፡፡ ቡልጋሪያም የግሏ የሆነ የዲፕሎማሲ ማሰልጠኛ ተቋም አላት፡፡ እንደዚሁምደግሞ ጋና ኮፊ አናን የሰላም ጥበቃ ስልጠናማዕከል/Kofi Annan Peace Keeping Training Center የሚባል የዲፕሎማቶች ማሰልጠኛ ተቋም አላት፡፡ በሌላ በኩልም የግልየዲፕሎማቶችማሰልጠኛ ዩኒቨርስቲዎች ማለትም እንደ Tuft University’s Fletcher School of Law and Diplomacy እና ሌሎች ተቋማትም ከዓለምአቀፋዊድርጅቶች ጋር ዝምድና ያላቸው ድርጅቶች አሉ፡፡
ሊታምን በማይችል መልኩ የሚያስደንቀው እና የሚገርመው ነገር በአጠቃላይ የወያኔ የውጭ ጉዳይሚኒስቴር አመራር በዲፕሎማሲ የሙያ ዘርፎች ላይየሰለጠነ ወይም ደግሞ በዚህ ሙያ ላይ በቂልምድ ያለው ዲፕሎማት የለውም፡፡ ለምሳሌ ያህል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበላይ ቁንጮ የሆነውሰውየዲፕሎማሲ ሙያ ስልጠናም ሆነ ልምድ የላቸውም፡፡ ምንም፣ ባዶ! የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርቴዎድሮስ አድኃኖም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙትከአስመራ ዩኒቨርስቲ በስነሕይወት/Biology የትምህርት መስክ ነው፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በማስተር ኦፍሳይንስ በImmunology of Infectious Diሰዓሰስ በሚል ከሎንዶን ዩኒቨርስቲ ያገኙሲሆን የፒኤች ዲ ዲግሪያቸውን ደግሞ በህብረተሰብ ጤና/Community Healthየትምህርት መስክ በእንግሊዝሀገር ከሚገኘው ከኖቲንግሀም ዩኒቨርስቲ ተቀብለዋል፡፡ ለጤናሚኒስትርነት ተሾመው ነበር፡፡ በአንድ ጀንበር ምሽት ከመለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላእራሳቸውንየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገኙት፡፡ (እርግጠኛ ነኝ በአንድ ጀንበር ምሽት ደግሞ እራሳቸውንጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገኙታል)፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ለጠቅላይሚኒስትርነት መወጣጫነት የመጀመሪያ ደረጃ እና ለሚጠብቃቸው የጠቅላይሚኒስትርነትሹመታቸው ለይስሙላም ቢሆን ለማሟሻነት ቢጠቅም በሚል እኩይ ስሌት የተቀነባበረ ነው፡፡እርግጥ ነው አምባገነንነት እና ወሮበላነትበተንሰራፋባት የመጨረሻ ደኃ ሀገር ለዲፕሎማትነትመስፈርቱ ዘር እና ታማኝነት እንጅ ትምህርት እና ልምድ ምን ፋይዳ ይኖረዋል! (ሟቹ መለስዜናዊበአንድ ወቅት ስለሚኒስትሮቹ አሿሿም የትምህርት ብቃት ማነስ ጉዳይ በቴሌቪዥን ጥያቄበቀረበላቸው ጊዜ “ታማኝነት እንጅ ማይም ይሁኑ” በማለትየሰጡትን አስገራሚ እና ፈጣጣየስላቅ መልስ ልብ ይሏል፡፡)
ጉድ እኮ ነው ጎበዝ እንዴት አንድ ምንም ዓይነት የዲፕሎማትነት ልምድ እና በመስኩም አስፈላጊየሆነው ትምህርት ሳይኖረው ወይም ደግሞ ምንም መነሻመሰረት ሳይኖረው እንዲሁምበአምበሳደርነት (ስለዓለም አቀፍ ህግ እና ዲፕሎማሲ ፍጹም ባይተዋር የሆነ [ከኢትዮጵያ እሳትወደ ሳውዲ አረቢያ እረመጥ]በሚል ርዕስ ያቀረብኩትን ትችት ይመልከቱ) እንኳ ሳይሰራበድንገት እና ቅጽበታዊ በሆነ ሁኔታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነትን ያህል ከባድ ኃላፊነትየሚጠይቅየሚኒስትርነት ቦታን ይይዛል?
ለዚህ መልሱ ግልጽ እና አጭር ነው፡፡ አድኃኖም በዘር ሀረጋቸው ብቻ እና ብቻ ነው የወያኔየከፍተኛ ዲፕሎማት ስልጣን የተሰጣቸው፡፡ በእርግጥ ይኸጉዳይ የሚያስገርም አይሆንም፡፡ በአሁኑጊዜ በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ ምን ዓይነት የትምህርት ማስረጃ እና ብቃት አቅርቦ ነውጠቅላይ ሚኒስትርየነበረው? መለስ በርቀት የትምህርት ፕሮግራም በተልዕኮ ከእንግሊዝ ሀገርበቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የመጀመሪያ ዲግሪውን አገኘ፡፡ ለሁለተኛ ዲግሪውምከኢራስመስዩኒቨርስቲ የዓለም ብቸኛው ታላቅ አዋቂ ነኝ አያለ ሲፎከርበት የነበረውን የልማት ምጣኔሀብት/Development Economics የመመረቂያጽሁፉን ማጠናቀቅ ያልቻለ ሰው ነበር፡፡
ምናልባትም በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ለወሮበላ ዲፕሎማት ልዩ ስልጠና እየተሰጠ በብቃት ላይሳይሆን በዘር እና በታማኝነት ላይ ትኩረት በማድረግየሚኸድበት ስልት እውነተኛውንየዲፕሎማሲ ስራ አካሄድ እንዲበላሽ አድርጎታል፡፡ ለአፍሪካውያን/ት የወሮበላ ዲፕሎማቶችማሰልኛ ተቋም በቅርብ ጊዜውስጥ ከአፍሪከ ህብረት የለማኞች አዳራሽ፣ ለአፍሪካ አምባገነኖች እናወሮበሎች መሰብሰቢያ ከተሰራው አዳራሽ ፊት ለፊት በቅርብ ርቀት ላይ ይገነባልየሚል ግምትአለኝ፡፡ የሚያስገርም ጉዳይ ይሆናል፡፡
ከእውነታዎች ጋር ፊት ለፊት መጋፈጥ አለብን፡፡ አሳማን የከንፈር ቀለም መቀባት ይቻላል ቆንጆለማስመሰል፣ ሆኖም ግን ከዕለቱ መጨረሻ ያው ዓሳማዓሳማ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ እንደሰለሞን ገብረስላሴ፣ ግርማ ብሩ ወይም ቴዎድሮሰ አድኃኖም እና ሌሎች በርካታዎቹ ብሪፍ ኬዝ/ቦርሳ እና የይሰሙላክብር መስጠት ይቻላል፡፡ በቀኑ መጨረሻም እራሳቸው እራሳቸውን ሆነውያገኙታል፡፡ ወሮበላ ዘራፊዎች!
መንግስታዊ አገዛዝ ከወሮበላ (የጫካ አገዛዝ ጋር) ሲነጻጸር፣
የወያኔን አገዛዝ የወሮበላ አገዛዝ ነው በማለት በምገልጽበት ጊዜ ከምንም በመነሳት በጥላቻ ወይምደግሞ ለቡድኑ ክብር ካለመስጠት አይደለም፡፡አንዲሁም መለስ ዜናዊን “የአፍሪካ የለማኞችአለቃ” ነው በማለት ስገልጽ እራሱ በሚጠቀምባቸው ቃላት ላይ መሰረት አድርጌ ነው፡፡ የእራሴንቃላት እናሀረጎች እርሱ ከሚሰራቸው እውነታዎች በመነሳት ነው የምርጣቸው፡፡
የወያኔ አለቆች በምንም ዓይነት መልኩ ከወሮበላነት (የጫካ) አገዛዝ ወደ መንግስታዊ አስተዳደርበፍጹም ሽግግር አያደርጉም፡፡ በጫካው ዘመናቸውወጣት በነበሩበት ጊዜ የነበራቸው ልምድየምሁርነት አስተሳሰባቸውን፣ የሞራል ስብዕናቸውን እና የማህበራዊ ልማት እይታቸውን በጫካውየቅኝትአስተሳሰብ ብቻ እንዲወሰን አድርጎታል፣ ሸፍኖት ቀርቷል፡፡ ከዚያ አልፎ አንዳንዶቹ ዘመናዊእና ላቅ ያለ የአካዳሚ ትምህርት የማግኘት ዕድል ያገኙ አባላቱእንኳ ስልጣን ከያዙ በኋላበተመሳሳይ መልኩ ድሮ ወደነበሩበት የአስተሳሰብ አድማስ በመመለስ የአስተሳሰብ ግልብነት እናየሞራል ዝቅጠትን እና ባዶነትንአንጸባርቀዋል፡፡
የወጣትነት የመጀመሪያዎቹን ዓመታት በጫካ ውስጥ አማጺ ሆኖ ከማሳለፍ አንጻር ለመቀየርየማያስችል እና ቋሚ የሆነ የተቸከለ አስተሳሰብን ይፈጥራል፡፡በአካዳሚክ ዓለሙ ያሉም ሰዎችይህን ሲመለከቱቱ የአማጺያንን የጫካ ህይወት መኖር ያልረሱት እና በአዕምሯቸው ላይ የማይለቅችካል ስለሆነ ሆብስ“የመሆን ሁኔታ” እንዳለው በአእምሯቸው ላይ በጫካ አስተሳሰብ የተቃኘአንዳች የሆነ ነገር አንደሚፈጠር ነው። የእንግሊዝ ፈላስፋ የነበሩት ቶማስ ሆብስየሰለጠነመንግስት በሌለበት ጊዜ “እያንዳንዱ ሰው ከሌላው ሰው ጋር በጦርነት ይኖራል” በማለት የሙግትጭብጣቸውን አቅርበው ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳህይወት በመሆን የተፈጥሮ ህግ ላይ “ብቸኛ፣ ደኃ፣በጭካኔ የተሞላ፣ አውሬአዊ እና ኋላቀርነት አስተሳሰብን የተላበሰ ይሆናል“፡፡ ሆኖም ግን ሊነሳየሚችለውጥያቄ ሆብስ የመሆን ሁኔታ እዳሉት ለአስርት እና ግማሽ ዓመታት በአማጺነት በጫካሲኖሩ የነበሩት የወያኔ አማጺ አመራሮች ከጫካ ህይወታቸውወጥተው ስልጣንን በኃይል ነጥቀውበስልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጡ እና የሰለጠነ መንግስታዊ መዋቅር መሪዎች ከሆኑ በኋላበእርግጠኝነት ሊሆንየሚችለው ምንድን ነው? በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ሲመሩበት የነበረውንየመሆን ሁኔታ እርግፍ አድርገው ትተው የወሮበላነትን መንግስታዊ አገዛዝበሰለጠነ መንግስታዊአስተዳደር እንዲቀየር በማድረግ የህግ የበላይነትን በማስፈን እውነተኛ ሽግግርን ሊያመጡ እናህዝቡን በሚፈልገው መልክ ማስተዳደርይችላሉን?
አጋጣሚ ሆኖ ከእነርሱ አባባል ታምራዊ ሀረጎች በመዋስ “እድገት እና ትራንስፎርሜሽን”ለማምጣት የምሁራዊ እና የሞራል ብቃቱ ሳይኖራቸው ቀርቷል፡፡ለወያኔ አለቆች በሰለጠነማህበረሰብ ውስጥ ገብቶ አብሮ መኖር አሁን ብዙ ገንዘብ እና ሀብት ከመዝረፍ በስተቀር ለእነርሱህይወት በጫካ ውስጥ ይኖሩበትእንደነበረው ዓይነት ቀጣይነት ያለው ነው፣ ምንም ዓይነት ልዩነትየለውም፡፡ በእነርሱ የአስተሳሰብ አድማስ ምንም ዓይነት የተቀየረ ነገር የለም፡፡ ለ23ዓመታትበስልጣን እርካብ ላይ ተፈናጥጠው ከቆዩ በኋላ ምንም ዓይነት የተማሩት ቁም ነገር የለም፡፡አሁንም ቢሆን በጫካ በነበሩበት ጊዜ ሲያራምዱትየነበረውን ሚስጥራዊ የፖለቲካ ፍልስፍናበህዝቡ ላይ በመጫን ለመቀጠል ይፈልጋሉ፡፡ በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ የተጠያቂነት እናየግልጽነት ባህሪንአያራምዱም ነበር፣ አሁንም ቢሆን አንድን ታላቅ አገር በቁጥጥራቸው ስርአድርገው ስርዓት ባለው መልኩ ተጠያቂነት እና ግልጽነትን በተላበሰ ሁኔታመምራት ሲችሉ ይህንንመተግበር ተስኗቸዋል፡፡ በጫካ ውስጥ ሆነው ከደርግ ወታደራዊ አምባገነን ጋር ትግል ሲያደርጉበነበሩበት ወቅት ውሳኔ ሰጭነትበጥቂት የወያኔው መሪዎች ብቻ እና ብቻ ነበር፡፡ በዚያን ወቅትእነዚህ ጥቂት አመራሮች ይመሩት በነበረው ሰራዊት እና በአጠቃላይ በቁጥጥራቸው ስርአድርገውትበነበረው ህዝብ ላይ ጥሬ የሆነ አስተሳሰብን፣ ጭካኔ የተሞላበት ኃይልን ይጠቀሙ ነበር፡፡ ሰላማዊአማጺያንን እና የሰላ ትችት ያቀርቡባቸውበነበሩት ወገኖች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃመውሰድ ጀመሩ፡፡ ከእነርሱ ሀሳብ ጋር ስምምነት የማያደርጉ ዜጎችን ማግለል፣ እንደ ሰላይነትበመቁጠርመግደል እና ማጥፋት ጀመሩ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ መንግስታዊ ስልጣንን ከተቆናጠጡበኋላም የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን፣ ጋዜጠኞችን እናሌሎችንም ለስልጣናቸው አስጊናቸው ብለው የሚጠረጥሯቸውን ወገኖች ማዋከብ፣ ማሰር፣ መግደል እና ከሀገር እንዲወጡማድረግን ስራየ ብለውመተግበር ጀመሩ፡፡ ከእራሳቸው መካከል በሀሳብ በመለያየታቸውየተገነጠሉትን ተስፈንጣሪ ቡድኖች ርህራሄ በሌለው መልኩ አስወገዷቸው፣አዋረዷቸው!
በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ስልጣንን፣ ገንዘብን በመዝረፍ እራስን እንደማበልጸጊያ፣ የፖለቲካየበላይነት እና ማስፈራራትን እንደ መሳሪያ በመቁጠርይጠቀሙበት ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የወያኔአገዛዝ በሙስና የበከተ እና የሙስናው በሽታ በኢትዮጵያ አካል ላይ እንደ ነቀርሳ እየተሰራጨመሆኑን ሙስናንበኢትዮጵያ መመርመር/Diagnosing Corruption in Ethiopia በሚል ርዕስ የዓለም ባንክ አዘጋጅቶ ባወጣው በባለ550 ገጽ ዘገባው ላይበግልጽአስፍሮታል፡፡ ወያኔ በጫካ በነበረበት ጊዜ አመራር ላይ መሆን ማለት የእራስን ስብዕና መትከልየነበረ ሲሆን አሁንም ቢሆን በአሁኑ ጊዜ በህይወትየሌለው መለስ ዜናዊ በእርሱ ደቀመዝሙሮችእንደ ትንሹ አምላክ ያህል ይመለክ ነበር፡፡ የእነርሱ ከጫካ አገዛዝ ወደ መንግስታዊ አስተዳደርያደረጉትሽግግር የአንድ ሰው፣ የአንድ ፓርቲ የበላይነት የነበረውን የደርግ አገዛዝ በማስወገድበአንድ ሰው፣ በአንድ ፓርቲ የወያኔ አገዛዝ ተኩት፡፡ የወያኔ አመራሮችበደርግ አገዛዝ ላይ ያደረጉትለውጥ አለ ከተባለ “ለወያኔ ጥሩ የሆነው ነገር ሁሉ ለኢትዮጵያ ህዝብም ጥሩ ነው” የማለታቸውአምባገናናዊ አመለካከታቸውብቻ ነው!
ከወሮበላነት/ከጫካ አገዛዝ ወደሰለጠነ መንግስታዊ አስተዳደር የሚደረግ እውነተኛ ሽግግርየፍልስፍና እና የፖሊሲ ሁለቱንም ነገሮች ስርነቀል በሆነ መልኩመቀየርን ይጠይቃል፡፡ ይኸ ግንባዶ ተስፋ ሆኖ ቀርቷል፡፡ በተደጋጋሚ ጊዜ እንደምለው የወያኔ አመራሮች ትክክለኛ መንግስታዊመዋቅርን ይመሰርታሉወይም ደግሞ ትክክለኛ መንግስታዊ ስርዓትን ያራምዳሉ ማለት ሰይጣንከመጸሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እየጠቀሰ ያስተምራል እንደማለት ነው፡፡
ዴሞክራሲያዊ የመንግስት አስተዳደር መሰረታዊ የሆኑትን መርሆዎች ማለትም የህግ የበላይነት፣የስልጣን ክፍፍልን፣ የቁጥጥር እና የኃይል ሚዛንን እናህገመንግስታዊ የአስተዳደር ሂደትንበመተግበር በእውነታ ላይ የተመሰረተ ትችትን በትክክል ለተከናወኑ ስራዎች ደግሞ አድናቆትመስጠት እና መግባባትንይጠይቃል፡፡ የወያኔ ወሮበላ አመራሮች ለእንደዚህ ዓይነቶቹ ጉዳዮችእጅግ በጣም አነስተኛ የሆኑ ልምዶች ወይም ደግሞ የተግባር ተሞክሮ ጭራሹንምየላቸውም፡፡በዚህም መሰረት ማንም ቢሆን እነዚህ የወሮበላ ስብስብ አመራሮች በፖለቲካ ህይወታቸው ውስጥያልነበራቸውን እና በተሞክሮምየማያውቁትን ተጠያቂነትን እና ግልጸኝነትን ሊያሰፍን የሚያስችልየፖለቲካ ስርዓት ለህዝቡ ማስፈን እና መተግበር ይችላሉ ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡በጫካውስጥ በነበሩባቸው ጊዚያት ምንም ዓይነት ነጻ ምርጫ አካሂደው አያውቁም፣ በመሆኑም እ.ኤ.አበ2005 በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ በዝረራበተሸነፉበት ወቅት ተአምር የሆነ ያህልተገርመው ነበር፡፡ በዚያን ወቅት ታላቅ ትምህርትን ቀስመዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 በተደረገውአገር አቀፍ ምርጫ 99.6በመቶ የድምጽ ውጤት በማምጣት (በመዝረፍ አላልኩም) ድልተቀዳጅተናል፡፡ በጫካ በነበሩባቸው ጊዚያት የሚናገሯቸው ቃላት እራሳቸው ህግ ነበሩ፣ስለ የህግየበላይነት ምንም ዓይነት ሀሳብ አልነበራቸውም፡፡ አንድ ጊዜ ስልጣንን ከጨበጡ በኋላ የእነርሱቃል እራሱ ህግ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በእራሳቸውስልጣን ያስራሉ፣ ያሰቃያሉ፣ ይቀጣሉ፡፡ በጫካ ውስጥበነበሩበት ጊዜ እነርሱ እራሳቸው ዳኛ፣ ችሎት እና አስፈጸሚ ነበሩ፡፡ በስልጣን ላይ ባሉበትጊዜበጫካ ላይ ከነበሩበት ጊዜ የተለየ ነገር የላቸውም፣ ልዩነት አለ ከተባለም በጫካው ጊዜ ይፈጽሙትያልነበረ አሁን ዘመናዊ የመንግስት አስተዳደርመዋቅርን ከተቆጣጠሩ በኋላ ለይስሙላ የዝንጀሮፍርድ ቤቶችን በማቋቋም እነርሱ በሚፈልጉት መልኩ ውሳኔው እንዲሰጥ ማድረግ ነው፡፡ በጫካውስጥበፍርሃት እና በበቀል ነው የኖሩት፣ እናም የሲቪል ነጻነቶች እና የእነዚህ ነጻነቶች አተገባበርለእነርሱ ባዕድ ናቸው፣ ፈጽሞ አይተዋወቁምና፡፡ በአሁኑ ጊዜምህዝቡ በድንገተኛ መሬትአንቀጥቅጥ አመጽ ያስወግደናል በሚል ፍርሀት ውሰጥ ተቀርቅረው ሌት ቀን ሲባንኑ ይውላሉ፡፡እናም የሲቪል ነጻነቶች እናመብቶች ቅንጦት የሆኑ ነገሮች ሲሆኑ እነዚህ ቅንጦት የሆኑ ነገሮችምለእኛ ሳለይሆን ለምዕራባውያን ሰዎች ብቻ የተተው እንደሆኑ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ሆኖም ግንእነርሱ፣ የእነርሱ ደቀመዝሙሮች እና ደጋፊዎቻቸው ለሚሰሯቸው ወንጀሎች እና የሲቪል ወንጀሎችሳይቀር ያለመከሰስ መብትን በመጠቀምየተለያዩ ወንጀሎችን እየፈጸሙ እራሳቸውን በማስደሰት ላይይገኛሉ፡፡ በአጭሩ ከዚህ የእኩይ አስተሳሰብ ባለቤት ከሆነው የወሮበላ ቡድንዴሞክራሲያዊአስተዳደርን የተላበሰ ስርዓት በኢትዮጵያ ላይ ለማስፈን የሚያስችለል መንግስታዊ መዋቅር መጠበቅከባዶ ተስፋ የዘለለ ፋይዳአይኖረውም፡፡
ሰላማዊ ሰልፈኞችን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንዴት?
በአንድ ታትሞ በወጣ ዘገባ እንደቀረበው የወያኔ አገዛዝ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 29/2014በዋሽንግተን ዲ.ሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰላማዊሰልፍ ባደረጉ ወገኖቻችን ላይክስ ለመመስረት እንደሚንቀሳቀስ አሳውቋል፡፡ ዲና ሙፍቲ የተባሉት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይሚኒስቴር ቃል አቀባይ ይህንንጉዳይ በማስመልከት እንዲህ ብለዋል፣ “የዩናይትድ ስቴትስመንግስት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ገብተው ጸረ መንግስት የሆኑ መፈክሮችን እያሰሙየኢትዮጵያንባንዲራ በማውረድ ሁከት በፈጠሩት ሰዎች ላይ የኤምባሲውን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል እናበአጥፊዎች ላይ ክስ መመስረት እንዳለበትይጠበቃል፡፡“ በሌላ በኩል የወጣ ዘገባም እንደጠቆመውሰላማዊ ሰልፈኞች በአዲስ አበባ በሚገኘው የዩናይትስ ስቴትስ ኤምባሲ በመሄድ“ሰላማዊሰልፈኞች ለህግ መቅረብ አለባቸው” የሚል ጥያቄ ያቀረቡ መሆናቸውን አሳውቋል፡፡ “ በቪዲዮክሊፑ ላይ እንደሚታየው ሰላማዊ ሰልፈኞችየኢትዮጵያን ብሄር ብሀረሶቦች የሚወክለውን ባንዲራበማውረድ የጥንቱን እና የነጻነታችን አርማ ሆኖ ሲያገለግል የቆየውን አረንጓዴ፣ ቀይ እና ብጫቀለምያለበትን የህዝቦች ነባር ባንዲራ በክብር ወደነበረበት ቦታው መለሱት፣ አከበሩት እንጂአላዋረዱትም፡፡ ሰላማዊ ሰልፉ በወያኔ አገዛዝ የተቀነባበረ የመድረክላይ ተውኔት ነው፡፡
ሙፍቲ፣ ቴዎድስ አድሀኖም እና ሌሎች የወያኔ ደናቁርት ምን መመኘት እንዳለባቸው ጥንቃቄማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
መጀመሪያ፡ ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ጥፋተኛ ለማድረግ በሚደረገው የውንጀላ ብያኔ ላይ ግልጽ መሆንአለበት፡፡ በአሜሪካ አገር የፌዴራል ወይም የኮሎምቢያወረዳ ግዛት ወንጀል ስርዓት ኮድ ላይ“ሻጥር ለመስራት” የሚል የወንጀል ጥቅስ አይታወቅም፡፡ ምናባዊ የሆነ የወንጀል ክስ በመፈብረክክስ እንዲመሰረትቢያስቡ እና ህዝቡን ለማሳመን ጥረት ቢያደርጉ የእነርሱ የአስተሳሰብ አድማስበምን ያህል ጥልቀት እንደወረደ እና ስለአሜሪካ ህግ ያላቸውን ድንቁርናየሚያመላክት ነው፡፡(በእንደዚህ ዓይነት ፍጹም ድንቁርና የተጠናወታቸው ፍጡሮች “ኢትዮጵያ የምትመራ” መሆኗንስመለከት በጣም ተሸማቀቅሁ፣አዘንሁም!)
ሁለተኛ፡ የወያኔ ደናቁርት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አገር ማንኛውንም ዓይነት ባንዲራ የኮከብእና ነጠብጣብ ምልክት ያለባትን የአሜሪካን ባንዲራምቢሆን ማውረድ ወይም ማዋረድ ወንጀልአለመሆኑን ሊያውቁ ይገባል፡፡ እ.ኤ.አ በ1989 በቴክሳስ ግዛት ጆንሰን የዩኤስ አሜሪካንንባንዲራ እ.ኤ.አ በ1984የሬፐብሊካን ብሄራዊ ጉበኤ በዳህላስ፣ በቴክሳስ) ባቃጠለበት ወቅትጀስቲስ ዊሊያም ብሪናን በአጠቃላይ ሀሳብ ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ አስፍረው ነበር፣“በሀሳብመለያየትን የማስተናገድ መብት ማረጋገጥ የአሜሪካ የመጀመሪያው የህግ ነጻነት ማሻሻያችንየመሰረት ድንጋይ ነው፣ መንግስት በዜጎቹ መካከልአንድነትን የሚያጠፋ ነገር በመፈብረክ የዘፈቀደትዕዛዝ በመስጠት ተግባራዊ ማድረግ አይችልም፡፡“ ይላል፡፡ ስለሆነም ያ አንድ ዓይነት ባህሪ እናመርህያለው መንግስት የአንድነት መገለጫ የሆነውን ምልክት በመጣስ ከዚያ መርህ ጋር የሚጣረስትዕዛዝን ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡ በቀላል አነጋገር እንኳንስይህንን በሸፍጥ የተዘጋጀ የብሄርብሄረሰቦች የሸፍጥ ባንዲራ ከተሰቀለበት ማዕዘን ማውረድ ይቅርና ጥንታዊውን እና የተከበረውንያሜሪካ ባንዲራም በእሳትማቃጠል ህገመንግስታዊ መብት ነው፡፡
ሦሰተኛ፡ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት በጋዜጦች እና በድረ ገጾች የሚለቀቅ የዲፕሎማሲስራን እንደማይሰራ የወያኔ አገዛዝ ደናቁርት ሊገነዘቡትይገባል፡፡ እነዚህ ደናቁርት የዩናይትድስቴትስ መንግስት የሚፈልጉትን ነገር እንዲያደርግላቸው ከተፈለገ በመጀመሪያ ደረጃ የፕሮቶኮልስነስርዓትን ማክበርይጠበቅባቸዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ከውጭ መንግስታትየዲፕሎማቶች የተቃውሞ ጥያቄ ሲቀርብለት የውጭ መንግስታቱየሚፈልጉትን ለማግኘት ሲፈልጉእነዚህ ቅሬታ ለማቅረብ የሚፈልጉ መንግስታት መከተል ያለባቸውን ህጎች እና የአካሄድስነስርዓቶች በመከተል እንዴትምላሽ መስጠት እንደሚችል በጣም ዝርዝር በሆነ መልኩአስቀምጧል፡፡ የወያኔ ደናቁርት በቀጣይነት የሚደርስባቸውን ውርደት እና መሸማቀቅለማስቀረትበማሰብ ለእነርሱ ወገናዊነት እገዛን ለማድረግ የዩኤስ አሜሪካንን የመንግስት መምሪያ የውጭ ጉዳይሰነድ ቮሊዩም 5 የእጅ መጽሐፍ ቁጥር 1ንእንዲመለከቱ እጋብዛለሁ፡፡ (በነገራችን ላይስለዲፕሎማቶች ያለመከሰስ መብት መነሳት ጉዳይን በማስመልከት ጥያቄ አቅርባችሁልኝ ለነበራችሁአንባቢዎቸበግንባር በመገኘት ምላሽ ባለመስጠቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን ለዚህ ስራይጠቅማችኋል በሚል እሳቤ “Diplomatic and Consular Immunity: Guidance for Law Enforcement and Judicial Authorities“በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን በመረጃ የበለጸገ ሰነድ እንድታነቡትእጋብዛለሁ፡፡
አራተኛ፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤቶች እንደ ወያኔው የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶች ሳይሆኑተከላካዮች የተሟላ ህገመንግስታዊ መብት ያላቸው እናአስገድዶ ቃል ያለመቀበልን፣ ያለመደብደብእና በሰውነት ላይ የሚፈጸሙ የጥቃት ማስረጃዎችን ጭምር በማካተት አዘጋጅቶ ያስቀመጠ መሆኑንየወያኔደናቁርት ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ የወያኔ ደናቁርት እነዚህን የነጻነት ታጋይ ወገኖቻችንን በህግፊት አስቀርበው ለማስቀጣት ከልብ ፈልገው ከሆነ በዚህበአሜሪካ የህግ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትንእና የታጨቁትን ህጎች በሙሉ ማስወገድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
አምስተኛ፡ የህግ ስርዓት ቢኖር ኖሮ ግርማ ብሩ እና ሌሎች የኤምባሲው ሰራተኞች እንዳደረጉትሁሉ ገብረስላሴም በታላቁ የፍርድ ቤት ችሎት ቀርቦቃሉን መስጠት እና የማስተባበያ ማስረጃመስጠት የነበረበት መሆኑን የወያኔ ደናቁርት ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ በችሎት ፊት ቴዎድሮሰአድሃኖም እና የውጭጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረቦቻቸው ለተፈጠረው ነገር ሁሉ ቃል መስጠትየጽሁፍ ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ተከላካይ በግርማ ብሩ፣በገብረስላሴ፣በአድሃኖም እና በሌሎች ቀሪ ሰዎች ላይ መስቀልኛ ጥያቄዎችን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በመስቀለኛጥያቄዎች ሲጠበሱ ምነው ጫካ ገብተን ደርግንበተዋጋን በለው ሳይመኙ አይቀሩም።
ስድስት፡ ሶሎሞን ገብረስላሴ በጣም አስቸጋሪ ፈተና ሊያጋጥመው እንደሚችል መጠበቅይኖርበታል፡፡ ማስረጃ ለመስጠት ወደአሜሪካ የሚመለስ ከሆነየዲፕሎማት ያለመከሰስ መብትእንደሌለው ማወቅ ይኖርበታል፡፡ በጣም ከባድ በሆነ ወንጀል ክስ ምክንያት ምንም አይነትአስተያየት በዩናይትድ ስቴትስአሜሪካ አቃቤ ህግ በኩል አያገኝም። ያለመከሰስ መብቱእንደማይሰራ እና ክስ ተመስርቶበት ወደ ፍትህ አካል ከመቅረብ እንደማያመልጥ ሊታወቅይገባል፡፡ገብረስላሴ አንድ ጊዜ በዩኤስ አሜሪካ ከተገኘ እና ያለመከሰስ መብቱ ተነስቶ ጉዳዩ ፍርድ ቤትየሚታይ ከሆነ ወደ ፍርድ ቤት ችሎት ከመቅረቡበፊት ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ውሎ ካለምንምዋስትና በቀጥታ ወደ ዘብጥያ ሊወርድ እንደሚችል ሊገነዘብ ይገባል፡፡
ሶሎሞን ገብረስላሴ እና የወያኔ አለቆቹ ከፍተኛ የሆነ የሲቪል ህግ ያለበትን እና አስከ አሁን ድረስበህይወታቸው አይተውት በማያውቁት የፍትህ ችሎትላይ ይገለገላሉ የሚል ከጥርጣሬ የዘለለእምነት አለኝ፡፡ በገብረስላሴ ድርጊት ምክንያት በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ይደርስ የነበረውንጉዳት ከግምትውስጥ በማስገባት የወያኔ ኤምባሲ እና ገዥ አካል ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችልየረዥም ጊዜ የፍርድ ሂደት ሊኖር ይችላል፡፡ በዩኤስ አሜሪካ በሲቪልጉዳዮች ላይ የሚታየው እናየሚሰጠው ብይን የመረጃ መለኪያ መስፈርቱነ ባገናዘበ መልኩ በአብዛኛው በሚቀርቡትማስረጃዎች ላይ መሰረት ተደርጎሲሆን ይህንንም ለማሳካት ከባድ አይደለም፡፡
አብዛኞቹ አገሮች የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለማድረግ ስምምነት አድርገው ዲፕሎማት ልከውበመተባበር ከሚሰሩባት ሀገር ላይ የተላከው ዲፕሎማትወንጀል ሰርቶ ከዚያች ሀገር በመሸሽአምልጦ ወደ ሀገሩ የመጣን ዲፕሎማት በሀገራቸው ህግ መሰረት የሚቀጡ መሆኑን ማስተዋልአስፈላጊ ነገር ነው፡፡ሶሎሞን ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ባሉት የወያኔ አለቆቹ ቅጣት ሊጣልበትእንደማይችል ጥርጥር የለውም፡፡ ይልቁንም የወያኔን ኤምባሲ ከጠላት ለመከላከልባደረገውጀግንነት በወሮበላ ጓደኞቹ የበለጠ እንደሚወደስ እና ጀግና እንደሚባል መገመት ይቻላል፡፡
አገሮች እነርሱን በውጭ አገር ሄዶ ሊወክላቸው የሚችለውን ዲፕሎማት ለመምረጥ በአገሪቱ ካሉትየመንግስት ሰራተኞች መካከል በደረጃው እናበትምህርት ዝግጅቱ እና ብቃቱ ላይ በመመስረትእንዴት እንደሚመርጡ እና ለምንም የማይሆን የወሮበላ ዲፕሎማት ለምን መርጠውእንደማይልኩየእራሳቸው የሆነ ምክንያት አላቸው፡፡ እነዚህ የመንግስት ሰራተኞች በዲፕሎማትነት ተወክለውሲሄዱ ምን መስራት እንደሚጠበቅባቸው እናየሄዱበትን ሀገር ህጎች እና ደንቦች ማክበር ብቻምሳይሆን የእራሳቸውን አገር ክብር ሊያዋርዱ ከሚችሉ ነገሮች እራስን ንጹህ በማድረግ በጥንቃቄመራመድእና በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ ህዝቡ የእራሱን ፍርድ መስጠት እንዲችል መሰረት እንዲያዝዕድሉን መስጠት እንዳለባቸው ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
ዲፕሎማቶች ወንጀለኛ ከሆኑ የወሮበላ አፋኝ ስርዓቱ ታማኝ ሎሌዎች የሚመረጡ ከሆነ ገብረስላሴየሰራውን የመሰለ እኩይ ምግባር የተንጸባረቀበትዓይነት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ ስለሆነምወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱን ልታላቀቀውአትችልም።
ገብረስላሴ በመግደል ሙከራ ምክንያት የተባረረ መሆኑ እውነት ነው፡፡ ሆኖም ግን ህጉ ብቻ ነውእርሱን ነጻ ሊያደርገው የሚችለው፡፡ በአገሮች መካከልሊኖር የሚገባውን የዲፕሎማሲ ግንኙነትበማስመልከት የ1961ዱ የቬና ስምምነት አንቀጽ 31 የሚከተለውን መብት ያጎናጽፋል፣ ”አንድየዲፕሎማት ወኪልየሆነ ሰው ከሚቀበለው አገር የወንጀለኛ ህግ ያለመከሰስ መብቱን ተጎናጽፏል“ይላል፡፡ ወደድንም ጠላንም የህግ የበላይነት ማለት ሌላ ሳይሆን እንደዚህነው፡፡
አንደው በነገራችን ላይ….
“በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ በሶማሌ ሚሊሻዎች ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችልአስጠነቀቀ“
እ.ኤ.አ ኦክቶበር 15/2014 ሬውተርስ የተባለው የዜና አገልግሎት የዩናይትድ ስቴትስኤምባሲ የሚስጠንቂያ መግለጫ ሰጥቷል በሚል የሚከተለውን ዘገባአስነብቧል፣ “በቦሌ በሚገኙየምግብ ቤቶች፣ ሆቴሎች፣ ቡና ቤቶች፣ የእምነት ቦታዎች፣ የገበያ አዳራሾች እና ታላላቅ የመገበያያቦታዎች ሌላ ማስታወቂያእስካልተሰጠ ድረስ የአሜሪካ ዜጎች እንዳይደርሱ መራቅ አለባቸውምክንያቱም እነዚህ ቦታዎች ሊከሰቱ በሚችሉ በአሸባሪ ቡድኖች የጥቃት ኢላማ ውስጥናቸው“ይላል፡፡ ሬውተርስ በተጨማሪም እንዲህ የሚል ጥቆማ ሰንዝሯል፣ “የኢትዮጵያ ባለስልጣኖችባለፈው ዓመት መጫረሻ አካባቢ አልሻባብ በአዲስአበባ ከተማ ጥቃት ለመሰንዘር የአውጠነጠነውአስከፊ የሆነ የአጥፍቶ መጥፋት የሽብር አደጋ እንዳለ መረጃ ከደረሰው በኋላ የደህንነት ኃይሉበተጠንቀቅላይ መሆኑን“ ጠቁሞ ነበር፡፡
ይቅርታ አርጉለኝና ፣ ይኸ አስደንጋጭ ዜና ከተሰማ በኋላ የወያኔ ገዥ አካል እንደገና ሶማሊያንለመውረር እያደረገ ያለው ዝግጅት አለ ማለት ነውነው?እብደት ወይስ ብልሀት!? የዩኤስ ኤምባሲማስታወቂያ ኢትዮጵያ እንደገና ሶማሊያን እንድትወር የቀረበ ሀሳብን የመሞከረያ/መገምገሚያየዳግም ወረራ ወሬማናፈሻ ዘዴ ነውን? ዓላማው ይህ ከሆነ ሁሉም ነገር ሁሉ ፍጹም ውድቀትመሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ ባለፈው ሴፕቴምበር 23/2014 ከወያኔ ባለስልጣን ጋር በመሆን ከመጠንያለፈ ክብካቤ ሲያደርጉ መታየታቸው እና በቪዲዮ ክሊፕመለቀቁ ስለታሰበው ወረራ በትክክልእንድጠረጥር አድጎኛል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እንዲህ ሲሉተደምጠዋል፣ “…እኛ[ከወያኔ የልኡካን ቡድን አባላት ጋር] ሰላም ማስከበር እና በሰላማዊመንገድ የግጭት አፈታትን በሚመለከት አሰራሮቻችንን በማሻሻል እንዴት ውጤታማበሆነ መልኩመፍታት እንዳለብን ተወያይተናል፡፡ ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ ከዓለም ከማንኛውም ሀገር የተሻለችትሆናለች – ሰላምን ከማስከበር አንጻርከብዙዎቹ አንዷ ናት፣ በጣም መጥፎ ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜእና ግጭትን በማስወገድ ረገድ ከዓለም ውጤታማ የሆነ የውጊያ ኃይል ያላት ናት…“ በቅርብጊዜየተደረገው ማስታወቂያ የማይቀር የአሸባሪዎች ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል እና ሌላኛው ጫማየወደቀ መሆኑን የሚያመላክት ነገር ነውን?
ወደ ኋላ መለስ በማለት እ.ኤ.አ በ2006 አጋማሽ መለስ ዜናዊ በሶማሊያ ህዝብ ላይ ሙሉአስደንጋጭ እና አስከፊ የጦርነት ጥሪ ከማስተላለፉ እና ታንኮቹየሞቃዲሾን ከተማ ከመውረራቸውእና ከመርመርመርሳቸው ሁለት ወራት ቀደም ብሎ አልሻባብ እና ጂሀዲስቶች በኢትዮያ ላይ ጥቃትለመሰንዘር እየተባለብዙ ዲስኩሮች ተደርገው ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2006 “ጂሀዲስቶች እየመጡነው/Jihadists are coming“ በሚል ርዕስ ትችት ጽፌ ነበር፡፡ ጦርነቱከመካሄዱበፊት ይደረግ የነበረው የፕሮፓጋንዳ ስራ በጣም የሚያስደንቅ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ዴሴምበር14/2006 የዩኤስ አሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች የቀድሞእረዳት ዋና ጸሐፊ የነበሩት ጃንዳይፍሬዘር እንዲህ የሚል ውንጀላ ሰጥተው ነበር፣ “የዲፕሎማቲክ እና የደህንነት ባለስልጣኖችየእስልምና ህብረት ተዋጊዎችከሌላው ወገን እገዛ ለማግኘት እና ከእነርሱ ጎን መሰለፍ እንዲችሉበኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ“ የሚል ውንጀላ አሰምተው ነበር፡፡ እ.ኤ.አዴሴምበር27/2006 በስተሰሜን በኩል በ90 ማይሎች ርቀት ላይ የምትገኘውን ሰትራቴጂካዊየሆነችውን የጆሀርን ከተማ ከተቆጣጠሩ በኋላ የመለስ ዜናዊተዋጊ ኃይሎች ወደ ሞቃዲሾየሚያቃርበውን በረሀ መውረር ጀምረው ነበር፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ የእስላማዊህብረት ኃይሎችበኢትዮጵያ ላይ “ተጨባጭነት ያለው የደህንነት አደጋ ደቅነዋል” በማለትየወረራውን አስፈላጊነት እና ፍትሀዊነት አጸደቀች፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከትየዩናይትድ ስቴትስየመንግስት መምሪያ ቃልአቀባይ የነበሩት ጎንዛሎ ጋሌጎስ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ኢትዮጵያበሶማሊያ እየተደረገ ባለው የመሻሻል እድገትላይ በቅን ልቦና ላይ የተመሰረተ የደህንነት ስጋትተደቅኖ እንዳለ እና ህጋዊ እውቅና ያለው የሶማሊያ ጊዚያዊ የሽግግር መንግስት በጠየቀው እርዳታመሰረትኢትዮጵያ ድጋፏን እየሰጠች ነው፡፡“
ሶማሊያን የመውረር ዕቅድ በተግባር ለማዋል እየተሰራ ስለመሆኑ የማውቀው ነገር የለም፡፡ እውነትለመናገር ይህ አካሄድ አሁንም ቢሆን የሚፈይደው ነገርይኖረዋል የሚል እምነት የለኝም፡፡ እ.ኤ.አኦክቶበር 8/2008 “በሶማሊያ የመለስ ዜናዊ የሰላም አስከባሪነት ሸፍጥ ፍጻሜ/The End of Pax Zenawi in Somalia” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት ላይ እንዲህ የሚልጽሑፍ አስነብቤ ነበር፣ “እውነተኛው ጉዳይ ሲታይ ሶማሌዎች በመለስ ዜናዊ ወይም በሌላበማንምግለሰብ ወይም ቡድን በኃይል በሚደረግ ተጽዕኖ ሰላም ማምጣት አይችሉም ፍላጎትም የላቸውም፡፡ ሶማሊዎች እና ሶማሊዎች ብቻ ናቸውየእራሳቸውን ችግሮች መፍታት የሚችሉት፣እናም ይህንን በሚጻረር መልኩ የሚደረጉ ጣልቃገብነቶች ሁሉ አንድም የለየላቸው ውሸቶችናቸው፣ አለያምደግሞ ምንም ባለማወቅ የሚደረግ አሳዘኝ የሆነ የዋህነት ነው፡፡“
ወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱን ልታላቀቀውአትችልም።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment