‹ኢህአዴግ ከታሪክ እንዲማር››ባገኘው መድረክ ሁሉ ከመምከር ተቆጥቦ የማያውቀው ወጣቱ ፖለቲከኛ ሐብታሙ አያሌው በጸና መታመሙ ከተሰማ ረዘም ያሉ ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡
እጅግ ቀዝቃዛ ክፍል ውስጥ በማዕከላዊ መታሰሩ ሳያንስ ዝናብ በሚዘንብበት ሰዓት ከክፍሉ እያወጡት አሸንዳ ስር በማስቀመጥ ዝናብ እንዲቀጠቅጠው ያደርጉ እንደነበር ዘግናኙን ቅጣት የተከታተሉ እስረኞች ከተናገሩም ቀላል የማይሰኙ ወራቶች አልፈዋል፡፡
እጅግ ቀዝቃዛ ክፍል ውስጥ በማዕከላዊ መታሰሩ ሳያንስ ዝናብ በሚዘንብበት ሰዓት ከክፍሉ እያወጡት አሸንዳ ስር በማስቀመጥ ዝናብ እንዲቀጠቅጠው ያደርጉ እንደነበር ዘግናኙን ቅጣት የተከታተሉ እስረኞች ከተናገሩም ቀላል የማይሰኙ ወራቶች አልፈዋል፡፡
መንፈሰ ጠንካራው ሐብታሙ በጀርባ ህመም እየተሰቃየ መሆኑን ለፍርድ ቤት ተናግሮ የነበረ ቢሆንም ህገ ወጦቹ አሳሪዎች ታምሚያለሁ ማለቱን እንደ ድል በመቁጠር ህክምና እንዲያገኝ በምርመራ ወቅት እንዲተባበራቸው መደራደሪያ በማድረግ አቅርበውለት ነበር፡፡
ደምበኞቻቸውን ህጉ በሚፈቅድላቸው መሰረት ማግኘት ባለመቻላቸው ጠንከር ያለ ተቃውሞ ያሰሙት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ሐብታሙ መታመሙን ቃለምልልስ ባደረግኩላቸው ወቅት ነግረውኝ ነበር፡፡
አሁን ማዕከላዊዎች ሐብታሙን ሆስፒታል መውሰዳቸው ተሰምቷል፡፡ነገር ግን ሐብታሙ መርማሪዎቹ ህገ ወጥ ድርጊት በምርመራ ወቅት ሲፈጽሙበት የተመለከታቸው በመሆኑ እነርሱ ወደ ህክምና ወስደውት ጤንነቱን እንዲያገኝ ይረዱኛል ብሎ ሊያምን አይችልም፡፡
ለሐብታሙ የሚደረግ ህክምና እምነቱን ሊያሳድርበት በሚችልበት መንገድ፣ቤተሰቦቹ በተገኙበት ጠበቃው ሁኔታውን ሊከታተሉ በሚችሉበትና ፓርቲው አንድነት የሚያውቀው መሆን ይጠበቅበታል፡፡
—–ህክምና ማግኘት ተፈጥሯዊ መብት የመሆኑን ያህል በሚሰጠው ህክምናም ታካሚዎች እምነታቸውን ማሳደራቸው ተፈጥሯዊ መብት ተደርጎ ሊወሰድ ይገባዋል——
No comments:
Post a Comment