‹‹ዳግመ አሉላ ››የሚል መጠሪያ የተሰጠው ግለ ታሪክ መጽሐፍ በመቀሌ በቅርቡ ተመርቋል፡፡መጽሐፉ በመጠጥ ቤት ውስጥ በተነሳ አንባጓሮ ህይወቱን ስላጣው የቀድሞው የህወሃት/ኢህአዴግ የጦር አመራር ሜጀር ጄኔራል ሐየሎም አርአያ የሚተርክ ነው፡፡ጸሐፊው በቅን ልቦና በመነሳሳት ‹‹ጀግና››በማለት የሚጠሩትን ተጋዳላይ ታሪክ የሚዘክር መጽሐፍ ለማዘጋጀት ገና ሲነሳሱ ሐሳባቸው በዋናነት በህወሃት ሰዎችና በሃየሎም የቅርብ ሰዎች አንቱታን እንደሚያገኝ ተስፋ ሰንቀው የነበረ ቢሆንም ደጃቸውን የረገጡባቸው የህወሃት አመራሮችና የሐየሎም ጓዶች የሚያውቁትን መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
መጽሐፉ በመከራ ተጽፎ ካለቀ በኋላ አዘጋጁ የማሳተሚያ ገንዘብ ለማግኘት ከዚህ ቀደም የመለስን የህይወት ታሪክ ለማሳተም ሲሽቀዳደሙ ለነበሩ ግለሰቦችና የህወሃት የኢንዳውመንት ድርጅቶች ደብዳቤ ይልካሉ፡፡ አንዳቸውም ምላሽ አልሰጡም፡፡ቢቸግራቸው አዘጋጁ በአሜሪካንና በአውሮፓ ለሚገኙ ሰዎች ደብዳቢ መላክ ጀመሩ ፡፡ ቀና ምላሽ በማግኘታቸው መጽሐፉ ለመታተም በቃ፡፡
መጽሐፉ ይመረቅ ዘንድ አዳራሽ አስፈለገ? መቀሌ ብዙ አዳራሽ የሚገኝባት ከተማ ብትሆንም ‹‹እሺ››የሚል ጠፋ፡፡አንድ የሆቴል ቤት ባለቤት የመጣ ይምጣ ብለው አዳራሽ ፈቀዱ፡፡መጽሐፉን ይመርቁ ዘንድ ለመቀሌ ከተማ ከንቲባ ወረቀት ተላከ፣የሕወሃት ሰዎች እንዲመጡና ‹‹ጀግናቸውን›› እንዲያወድሱ ተቀሰቀሰ፡፡አንዳቸውም ድርሽ ሳይሉ ቀሩ፡፡ለምን?
አስገራሚው ነገር የፓርላማ አባልና የሐየሎም አርአያ እህት የሆኑት ወ/ሮ አልማዝ አርአያ በዕለቱ በመቀሌ የነበሩ ቢሆንም ወንድማቸው የሚታወስበት መጽሐፍ ተዘጋጅቶ በምረቃው ስነ ስርዓት እንዲገኙ ቢጋበዙም የአውሮፕላን ትኬት ቆርጫለሁ ››በማለት ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡
እንዴት ነው ነገሩ ?ኢቴቪም ስለ ሐየሎም መጽሐፍ ምረቃ ምንም ያለው ነገር የለም፡፡ለምን?መልስ ያልተገኘለት ጥያቄ፡፡
No comments:
Post a Comment