በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዛሬ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በተቀሰቀሰ ሁከት ቁጥራቸው በውል ለማይታወቁ ወገኖቻችን አስቃቂ ግድያ እና በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ እየደረሰባቸው ላለው ስቃይ እና መከራ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚያደርገው የተዝረከረከ አሰራሩ ሲቃኝ። ይህ ጽሁፍ ሜይ 23 2013 የሳውዲ አረቢያ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ፡ሃገር ዜጎች የመኖሪያ ፈቃዶቻቸውን እንዲያስተካክሉ የ 7 ወር የምህረት አዎጅ በሰጠበት ወቅት በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ እንደ ዜጋ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ከህገወጥነት ለመታደግ የፓስፖርት እድሳትን ጨምሮ ዜጎቻችን ህጋዊ ለመሆን የሚያስችሎቸውን መሰል ተዛማጅ መረጃዎች በወቅቱ አንባሳድር መሃመድ ሃሰን እና ዲፕሎማቱ ሲደናበሩ የነበረበት የተዝረከረከ አሰራር….. ……
ማሳሰቢያ ይህ ጽሁፍ ከዛሬ 4 ወር በፊት በኢትዮጵይ ሃገሬ ከጅዳ የኢትዮጵያውያኑንን ብሶት በሪያድ አስመልክቶ ድህረገጾች ላይ ለንባብ በቅቶ የነበረ መሆኑንን ከወዲሁ ገልጻልሁ !=======================================================
ክፍል አንድ ( 1 )
የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መግስት የሚመካባቸው በሪያድ ከኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ጀርባ ያለው የተዝረከረከ አሰራር .« በድጋሚ የቀረበ »በ Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ
በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ሰሞኑንን የሳውዲ መንግስት ያወጣውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ ከጅዳ ቀጥሎ ብዛት ያላቸውን እድለኛ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን እያስተናገደ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል ። ይህ በዚህ እንዳለ ሰሞኑንን ኤንባሲ ውስጥ የሚገኙ ዲፕሎማቶች ወደ ኤንባሲ ቅጥር ግቢ የሚመጣውን ባለጉዳይ በአግባቡ በማስተናገድ ላይ መሆኑን አንድ ዲፕሎማት የሰጡኝን አስተያየት አብነት አድርጌ የዲፕሎማቶቹን መስተንግዶ በማድነቅ ወደ ሪያድ ተጎዤ ነበር።
በአንድ ወቅት አንድ በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት አቶ መስፍን ፡ነገሮች ሁሉ አለጋ በአልጋ የሆነ ያህል በኩራት እና በሙሉ ልብ ያወጉኝን ሁሉ ተቀብዬ ለኛዎቹ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ተወካዮቻችን ጥሩ ተሞክሮ ይሆናል በሚል ወደ ጅዳ ሰንቄ የመመለሰውን ልምድ ልመቅሰም በማሰብ ከጅዳ ወደ ሪያድ ከተማ አቀናሁ እዛም እንደደረኩ ሃሙስ ፓስፖርት ለመውሰድ ቀነ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩትን ከ1700 በላይ የሚሆኑ ባለጉዳዮች በምን ተአምር ሊስተናገዱ እንደሚችሉ ለመታዘብ ረፈድፈድ አድርጌ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ወደ ሚገኝበት ዲፕሎማቲክ ኮርተር አቀናሁ።
አካባቢው ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ በሴት እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን ተጨናንቆን የሳውዲ ልዩ የፀጥታ ሃይሎች ህዝብ ደንብ እና ስረአት ለማስያዝ ደፋቀና ይላሉ። ተራ የያዙ ሴት እህቶቻችን ሰልፍ በጣም ረዠም የመሆኑ ያህል መጨረሻውን ለማየት ለአይን ይታክታል ! የወንዶቹም እንደዛው ።ሁሉም ነገር ድብልቅልቅ ብሎል ! በተለይ በኢትዮጵያ ሰዓት አቕጣጠር ከሌሊቱ 10 30 አካባቢ መተው ወርፋ የያዙ ሴቶች እና ወንዶች እንዳሉ የኤንባሲው የጥበቃ ሰራተኛ ለአንድ ባልጀራው ሹክ ሲለው ሰማሁ። ሰለሁኔታው የበለጠ ለመረዳት ወደ ኤንባስው ቅጥር ግቢ መዝለቅ የግድ ስለነበር ውስጥ ለመዝለቅ ወደ መቢያው በር ተጠጋሁ ። እነዛ በዲስፒሊን የታነጹ የሳውድ ፖሊሶች ወዴት ነው የሚል ጥያቄ ቢጤ ጠየቁኝ። ምን ማለት እንደሚገባኝ፡ቀድም ብዬ ተዘጋጅቼበት ስለነበር ያልኩትን ብዬ ወደ ውስጥ እንድዘልቅ ጠይኳቸው ። ምላሹም አወንታዊ ስለነበር ፀሃይ ለጭንቅላት የቀረበች ያህል የሚንቀለቀለውን ሃይለኛ ሙቀትን መቋቋም ተስኗቸው የመግቢያውን የብረት በር ተደግፈው ተራቸውን ይጠብቁ የነብሩ ወገኖች ገለል ገለል አድርገው እንድገባ ጋበዙኝ። እኔም አመስግኜ በሩ ላይ ያለውን ኢትዮጵያዊ የጥበቃ ሰራተኛ ሰላም ብዬ ወደ ውስጥ ዘለኩ ።
ቀደም ብለው ወደ ኤንባሲው ቅጥር ግቢ ለመግባት እድል ያገኙ ብዛት ያላቸው ሴቶች ( በስማቸው የመጀመሪያ ፊደል )የስማቸውን መጠራት ይጠባበቃሉ። በሩ ላይ የዲያስፖራው ሀላፊ አቶ ተመስገን ስልችት ባለ የፊት ገጽታ ታጅበው እነዚህን ሴት እህቶቻችንን አንድ ረዘም ካለ ጎልማስ ጋር ስም እየጠሩ ፓስፖርት ለመስጠት የአቅማቸውን ያህል ይጥራሉ ። ከዚህ ባሻገር እኚሑ የዲያስፖራ ሃላፊ አልፎ አልፎ ከሴት እህቶቻችን ለሚቀርብላቸው ጥያቄ ለሰስ ባለው ድምጻቸው ማብራሪያ ይሰጣሉ ። እንደገባኝ ከሆነ ፓስፖርት የተዘጋጀው በመጀመሪያ የስም ፊደል ( በአልፋ ቤት ) በመሆኑ ወጣቱ ድምጹን ከፍ አድርጓ ስም ይጠራል ጀሚላ ጀማነሽ ጀማል ጂሃድ….. ወዘተ ። ክፋቱ ! አቤት ብሎ የሚቀርብ ግን አንድም ሰው የለም ! «ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ይሉሃል እንዲህ ነው»። ! ነገሩ ግራ ገብቶኝ ለ 10 ደቂቃ ያህል ቆም ብዬ ሂደቱን ማስተዋል ጀመርኩ ።
ከሚጠራው 50 እና 60 የስም ዝርዝር ውስጥ አንድ ሰው ብቻ የሚስተናገድበት ሁኔታ ከግዜ እና ውጭ በፀሃይ ከሚንቃቃው ወገናችን አንጻር የአሰራር ስህተት እንዳለ ተርዳሁ ። ያለወንጀላቸው በፀሃይ ግለት አናታቸው የሚበሳው ወገኖች ስቃይ ተሰማኝ ! ለሊት መጥተው ወረፋ በመያዛቸው ብቻ ወደ ግቢው የመግባት እድል ያገኙቱ ባለጉዳዮችን ስመለከት ከሚያቀርቡት ጥያቄ በመስተንግዶው የረኩ አይመስልም ። ገሚሱ እረ የፓስፖርት ያለህ እያሉ እሮሮ ያሰማል! ገሚሱ ምንም መረጃ የሌለን ሰዎች ምንድነው ማድረግ የሚገባ ይላሉ ! የኤንባሲው አመዘጋገብ እና ቀጠሮ አሰጣጥ ላይ ትልቅ ስህተት እንደነበር ሌላኛው ድክመት መሆኑንን ተርዳሁ ። ተመዝግቦ ቀጠሮ የተሰጠው ባለጉዳይ የምህረት አዋጁ የሚመመለከትውም የማይመለከተውም ኢትዮጵያዊ የመሆኑ የአሰራር ግድፈት የኤንባሲው ሰራተኞች በራሳቸው ግዜ የፈጠሩት የተዘበራረቀ መስተንግዶ አንዱ አካል መሆኑንን በተጨባጭ አረጋጋጥኩ።
በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች አቶ መስፍን ቀደም ብለው በኩራት ሲያስረዱኝ የነበረው የትኛውን ህብረትሰብ መስተንግዶ እንደሆነ ግራ ገባኝ። የመስተንግዶውን ድራማ ለመታዘብ በቆምኩበት ፡ የኤንባሲ ሰራተኛ መስያቸው ! አንዳንድ እንደኔ ግራ የገባቸው ሴት እህቶች እንደ ማክበር እያሉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በተላበሰ አጠራር አባባ አባባ እባኳዎን ! እባኳዎን ! በሚል አሳዛኝ፡ድምጽ እንድረዳቸው ተማጽኖአቸውን ያሰሙኛል ። ውስጤን ቢከነክነኝም እኔ እራሴ እንግዳ ስለሆንኩ የማውቀው መረጃ ስለሌለኝ ከነግሩ ጦም እደሩ ብዬ ወደ አቶ መስፍን ቤሮ ወደሚያስገባው የህንጻ በር አቀናሁ። የምህረት አዋጁ ከተጀመረበት ግዜ ጀምሮ የሚመጡትን እህት ወንዶሞቻችንን ለማስተናገድ ቀጠሮ ይሰጥ የነበር አንድ ደልደል ያለ ወጣት ቀጠሮ ሲሰጣቸው የከረሙትን ባለጉዳዩች ወደ ህንጻው ዘልቀው እንዳይገቡ በጉልበት ይከላከላል ። ወደ አቶ ተመስገን ቢሮ መግባት እንደምፈልግ ነግሬው በትህትና ወደ ህንጻው እንድገባ ፈቀደልኝ ። በአጋጣሚ አባሳደር መሃመድ ሃሰን በረዳ ላይ ቆመው አንድ ለእግርኳስ ግጥሚያ ወደ ሜዳ ገብቶ በተቃራኒው እየተመራ ያለ ደካማ ቡድን የሚያስተባብር አሰልጣኝ ይመስል ፡ በደከመ አንደበት « አንተ በዚህ ሂድ አንተ በዛ ግባ እያሉ » ያለምንም ውጤት እጃቸውን ወደ ሃላ አጣምረው ይንጎራደዳሉ። እያድረጉ ያለው ጥረት ከአንባሳደርነት ድረጃ አንጻር ማለፊያ ቢሆንም ህዝቡ እየተስተናገደ ያለበትን የተዝረከረከ አሰራር አለማየታቸው ነው ክፋቱ።
የአሳ ግማቱ እንዲሉ የሪያድ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች የተዝረከረክ አሰራር የቱ ጋር እንዳለ ለማወቅ የግድ ነብይ መሆን አይጠይቅም። እኚህ ክቡር አባሳደር ከቢሮቸው ወተው እያስተናገዱ ያሉት ለተሳትፎ ወይስ ለዜጎቻችን ጊዜያዊ ችግር መፍትሄ ለመሻት ? ክቡር አባሳደር ውጭ፡በጸሃይ ሃሩር እየነፈረ ያለውን ኢትዮጵያዊ ማየት ተስኖቸው ወይስ ግራ ገብቷቸው ? ለግዜው በሳቸው ሁኔታ ውስጤ በጣም በገነ ! አሁንም ወደ አቶ መስፍን ቢሮ ወደ ሚያዘልቀው ኮሪነር ላይ ሌላ ተይንት ገጠመኝ ። አንድ መልከመልካም ወጣት ከ30 በማይበልጡ ሴቶች ታጅቦ የ400 ሰዎችን ስም ዝርዝር የያዘ ሊስት እያገላበጠ ሰም ይጠራል ። እዚህም ማንም አቤት የሚል የለም ! አብዛኛው ተስተናጋጅ ከግቢ ውጭ ነው። ለማነው ጥሪው የሚተላለፈው ? ! ወጣቱ ከሰው ተግባቢ ቀልደኛ ብጤ ስለነበር ቀረብ ብዬ እንዴት ነው አሰራራችሁ የሚል ጥያቄ በፈገግታ ወርወር አደርኩለት ። ወጣቱም ሸሪፍ የሚባል እና የኤንባሲ ሰራተኛ መሆኑንን ገልጾልኝ በመጀመሪያ የስም ፊደል ቅደም ተከተል (በአልፋ ቤት ) ህዝቡን እያስተናገደ መሆኑንን አወጋኝ። ጥያቄን ጠንከር አድርጌ ውጭ በጸሃይ የሚንገላቱት እህቶቻችን እንዴት ሊሰሙህ ይችላሉ ? ደግሜ ጠየኩት ። በአልፋ ቤት ስለሆነ መስተንግዶው ውጭ ያሉት በቅደም ተከተላቸው ወደዚህ እንዲገቡ ይድረግ እና አሁን እየሰራን ባለው መልኩ እንስተናግዳለን አለኝ። አባባሉ ተገቢ ቢሆንም በወቅቱ እሱ ሲጠራቸው የነበሩ ተስተናጋጆች ስማቸው በዜድ የሚጀምር ከመሆኑ ጋር ወደ ጊቢው ያልገቡ አያሌ ኢትዮጵያውያኖች እንዳሉ ጥሪውን አቁሞ ስህተቱን ለአለቅቹ በማስረዳት አዲስ የአሰራር ስልት መቀየስ እንዳለባቸው ምክር ቢጤዬን ሹክ አልኩት « የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም እንዲሉ» ወጣቱ ዝም ብሎ ጥሪውን ተያያዘው ። በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች « አራባ እና ቆቦ የአሰራር ስልት » በተሰጠው መመሪያ መሰረት እይተሰራ ያለው ስራ ምን ያህል ውጤታም እንደሚያደርግ ባላውቅም። የወጣት ሸሪፍን ተዕይንት የሚከታተሉ ባለጉዳይ እህቶቻችን ነገሩ ስህተት እንደ ሆነ ቢያውቁም ከመሞት መሰንበት እንዲሉ ከሚቀዘቅዘው ክፍል ላለመውጣት መጨረሻውን እሱ ያብጀው በሚል እንደ አዝማሪ ስም የሚጠራውን ወጣት ከበው ( አጅበው )የግል ወሬያቸውን ይቆዝማሉ ። ወጣቱ ላንቃው እስኪ ሰነጠቅ ይጮሃል እዚህም አቤት ባይ የለም ! አልመጡም እየተባለ ፓስፖርት እና የስም ዝርዝዝር ሊስት ወደ መጣበት መሳቢያ እየገባ ይቆለፍበታል ።
ሰሞነኛው የሪያዶች ተሞክሮ ለጅዳ ተወካዩቻችን አብነት ይሆናል ያልኩት ሁሉ ገና ከመነሻው ትዝብት ደበዘዘ ። በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች የመስተንግዶ ብቃት ዛሬ በተግባር መፈተኑ ተሰማኝ፡፡ የምሳ ሰዓት ግዜ ያቸውን መስወአት በማድረግ ቢሮ አቸው ባለጉዳይ የሚያስተናግዱት ታታሪ ሰው አቶ መስፍን ያጫወቱኝ፡ ሁሉ የእንቦይ ካብ ሆነብኝ ። ጎበዝ ከጊዚያዊ ጭንቀት ለማምለጥ፡ባለ ጉዳይን በብጣሽ ወረቀት ቀጠሮ ሰጥቶ ማሰናበት እና በወቅቱ ኤንባሲዬ ነው ብሎ የመጣውን ወገን ፍላጎት አሞልቶ እንደ አመጣጡ መሸኘት ልዩነት እንዳላቸው አቶ መስፍን ሳያውቁት ቀረትው ይሆን ? አሁንም ጎዞዬን ወደ አቶ መስፍን ቤሮ ሳቀና ጅዳ ውስጥ በአይን ከምንተዋወቅ ሰው ጋር በአጋጣሚ ተገናኘን ሰላምታ ተለዋውጠን በቀጥታ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በመስተንግዶ ዙሪያ አንድ ሁለት እያልን ወሬያችንን በስፋት መቆዘማችንን ተያያዝ ነው ።
ከወዳጄ ጋር ጅዳ ከተማ በአይን ብንተዋወቅም ነዋሪነቱ ግን ሪያድ ነው ።ስለ ጅዳው ቆንስላ ጽ/ቤት መስተንግዶ ወጣት ነብዩ ሲራክ ከጅዳ በድህረ ገጹ ላይ የለጠፈውን ልክ በአካል ሄዶ እንዳየ ያወጋኝ ጀመር ። እኔም ስለሪያድ ኤንባሲ አንዳንድ መረጃዎችን ማወቅ ጉጉቴ ስለጨመረ የማውቀንም የማላውቀውንም እየተቀበልኩ የወዳጄን እንዳይከፋው የሚለውን ሁሉ ሰማሁ። በጣም ተግባባን ! የሪያድን ኤንባሲ ጓዳ ጓድ ጓዳ ላስጎብኝህ ብሎ የአሰራር ስህተት ወደ የሚፈበረክበት ክፍልን ለማሳየት እጄን ይዞ ወድ ፎቅ አመራን ። ልክ እንደ መኖሪያ ቤቱ ያስጎበኝ ገባ ። በቀኝ በኩል ያለው የአቶ ተመገን ቢሮ መሆኑንን ጠቅሷልኝ በሩ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ክፍት እንደሆነ ገለጸልኝ።
የኔ ጉጉት ቀደም ብሎ ወዳጄ የጠቀስልኝን የሪያድ ዲፕሎማቶች የአሰራር ድክመት ጓዳ ለማየት ብቻ ስለሆነ ጎደኛዬ የሚለውን ጆሮዬን ሰጥቼ ከማዳመጥ ውጭ ምንም አይነት አስተያየት ለመሰንዘር አልወደድኩም። አሁንም ወደ ተጠቀሰው ቦታ ለመድረስ ከሪያድ ጅዳ የትጓዝኩ ያህል ተሰማኝ ። የተባለውን ጉድ ለማየት የተጠቀሰው ቢሮ በር ላይ ደረስን በሩን አንኳኳን ማነው ! የሚል የጓልማስ ድምጽ ተሰማን””’ ይቀጥላል
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ
በኢንጂነር መሃመድ አባሳ
No comments:
Post a Comment