ያሳዝናል፤ ያስለቅሳል፤ያቃጥላል!!!
Prof. Mesfin Wolde-mariam
ኢትዮጵያውያን በገዛ አገራቸው መብቶቻቸውን ለማስከበርና የዕለት እንጀራቸውን ማግኘት ስለተሳናቸው፣ ሰብአዊ ክብራቸውና ኩራታቸው በአገራቸው ስለተገፈፈባቸው በምኞት እየተነዱ ሰብአዊ መብታቸውን፣ ክብራቸውንና ኩራታቸውን ሊያስከብሩ ወደማይችሉበት ይሰደዳሉ፤ መብቶቻቸውን ለማስጠበቅ በአገራቸው እየታገሉ ከመሰቃየት ይልቅ በውጭ አገር ውርደትን ተሸክሞ ለመክበር ይመርጣሉ፤
ሳይሆንላቸው ቀርቶ ተዋርደው ሲመለሱ የሚጠብቃቸው ያው ትተውት የሄዱት የጭቆና ሥርዓት ነው፤ በሳኡዲም ሆነ በሌሎች አገሮች በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ስቃይና መከራ በአጠቃላይ በሰዎች ላይ እንደደረሰ ስቃይና መከራ ስንመለከተው ያሳዝናል፤ ያስለቅሳል፤ ሰው በሰው ላይ ይህንን ያህል ጭካኔ ማሳየቱ ያቃጥላል፤ ግን በኢትዮጵያዊ ዓይን ስናየው በሳኡዲ የተደረገው እዚሁ እኛው በእኛው ላይ የምናደርሰው ይብሳል እንጂ አያንስም፤ ስሜታችን እንድናስብ ካላደረገን ከውስጥም ከውጭም የጥቃት ሰለባዎች መሆናችን ይቀጥላል፡፡Prof. Mesfin Wolde-mariam
ኢትዮጵያውያን በገዛ አገራቸው መብቶቻቸውን ለማስከበርና የዕለት እንጀራቸውን ማግኘት ስለተሳናቸው፣ ሰብአዊ ክብራቸውና ኩራታቸው በአገራቸው ስለተገፈፈባቸው በምኞት እየተነዱ ሰብአዊ መብታቸውን፣ ክብራቸውንና ኩራታቸውን ሊያስከብሩ ወደማይችሉበት ይሰደዳሉ፤ መብቶቻቸውን ለማስጠበቅ በአገራቸው እየታገሉ ከመሰቃየት ይልቅ በውጭ አገር ውርደትን ተሸክሞ ለመክበር ይመርጣሉ፤
No comments:
Post a Comment