Saturday, November 23, 2013

የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባልና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ፋኩልቲ መጨረሻ አመት ተማሪ ዮናስ ከድር በደህንነቶች ድብደባ ደረሰበት

“ፓርቲዉንና በዩኒቨርስቲ ያለዉን እንቅሰቅሴ ሰልልን”
8፡00 ሰዓት ላይ በላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ረዳት ኢንስፔክትር ሀይለማሪያም ታረቀኝ በአርቡ ሰልፍ ላይ ለምርመራ ትፈለገላህ ተብሎ ይጠራል፡፡ በፖሊስ ጣቢያዉ ሲደርስም ወደ ቢሯቸው እንዲገባ ከተደረገ በኋላ ሁለት ደህንነቶች ተከትለዉ ሲገቡ ረዳት ኢንስፔክተሩ ቢሯቸዉን ትተዉ ይወጣሉ፡፡

ከዚህ በኋላ ደህንነቶቹ በጥፊ ፣ በቦክስ እና በእርግጫ ይመቱታል፡፡ “ብርሃኑ(ህዝብ ግንኙነት) እና ዮናታን(ወጣቶች ጉደይ) ጋር ለምን ትዉላለህ ከነሱ ጋር እንዳናይህ እነሱ ጀርባቸዉን አንተ አታዉቅም፡፡ ለምንድን ነዉ አርፈህ የማትማረዉ? መመረቅ አትፈልግም ወይ?፡፡ ዩኒቨርስቲ ዉስጥ ምንድነዉ ልትሰራ ያሰብከዉ? ምን ተልእኮ ተሰጥቶሀል?” እያሉ ሲጠይቁት ለሚመልስላቸዉ መልስ ሁላ ይመቱት ነበር፡፡
ቀጥለዉም “መንግስት በፓርቲዉ ላይ በቅርቡ እርምጃ ስለሚወስድ አንተ ራስህን አድን፡፡ ከኛ ጋር ስራ፡፡ እንደዛ ካደረግክ እኛ እናመቻችልሀለን ሁኔታዎችን፡፡ በዩኒቨርስቲም በፓርቲዉ ዉስጥም የሚደረገዉን እንቅስቅሴ እየተከታተልክ ለኛ ሪፖርት ታደርጋለህ፡፡” ዮናስ ይህን ጥያቄ አልቀበልም ፣ አልተባበርም ስላለና ዱላዉ ምንም ለዉጥ ሊያመጣላቸዉ ስላልቻለ “ከፈለግን በአንድ የስልክ ጥሪ ከዩኒቨርስቲ ልናስባርርህ እንችላለን፡፡ ተጠንቀቅ፡፡” የሚል ዛቻ እና ማስፈራራት ቢያደርጉበትም አቋሙን ሊያስቀይሩት ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡
ዮናስም ሊተባበራቸዉ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ በዚህ የተናደዉ አንዱ ደህንነት ስልኩን(የራሱን የዮናስን) ወርዉሮ ሊመታዉ ሲል ስቶት ከግድግዳ በማጋጨት ሰብረዉበታል፡፡
ከዚህ ሁሉ በኋላም “እንክተታተልሀልን በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ከፓርቲዉ ራስህ ካላራቅክ ከዩኒቨርስቲ እናስባርርሀለን፡፡ ልክ ነዉ የምናስገባህ ተጠንቅቅ፡፡” በማለት ለቀዉታል፡፡
ዮናስ ከድር የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባልና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ፋኩልቲ መጨረሻ አመት ተማሪ ነዉ፡፡

No comments:

Post a Comment