Friday, November 22, 2013

የህወሓት እኩይ ተግባር እያደረ ይገለጣል!! (ኢንጂኔር አብደልውሀብ ቡሽራ – መቀሌ)

 ከሁለት ሳምንታት በፊት ወደ ሽሬ ለመሄድ ወደ መቀሌ አውቶብስ ተራ ሄድኩና በሰላም ባስ አውቶብስ ተሳፍሬ ጉዞየን ጀመርኩ:: እየተጓዝን እያለን በተቀመጥኩበት ወንበር አጠገብ ሁለት ሰዎች ነበሩ:: ሰዎቹ ከዛ በፊት አይቻቸው አላውቅም:: ሁለቱም አካል ጉዳተኞች ናቸው:: በመንገዳችን እየተጓዝን እያለን ሁለቱ ሰዎች የድሮ ትዝታቸው እያነሱ እያወሩ ነበሩና እኔም የነሱ ወሬ አዳምጥ ነበርኩ:: እንደዛ ቆየሁና ወሬያቸው ታሪካዊና የድሮ ትዝታቸው ስለጣመኝ በመሃላቸው ገባሁና ተዋወቅኩዋቸው:: እነዛ ሰዎች ሁለቱም የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች የነበሩና በትግሉ ጊዜ አካላቸው የተጎዱ መሆናቸው አወቅኩ::
እንደዚህ እያወራንና እየተጨዋወትን ረጂም ጊዜ አለፈ:: በጨወታችን ማሀል አንዳንድ ጥያቄዎች አቀርብላቸው ነበር:: እነሱም ለምጠይቀውን መልስ ይሰጡኝ ነበር:: በመቀሌ ከተማ ፍረስወአት የሚባል የእንጨትና የብረት ሥራዎች የሚሰራና ሥራው በአካለ ጉዳተኞች የሚካሄድ ድርጅት አለ:: ከአስር ዓመት አካባቢ በፊት በድርጅቱ ብዙ ረብሻዎች የሥራ ማቆም አድማና ሰላበማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ እንደአደረጉና በፀጥታ ኃይሎች እንደታገዱ አውቅ ነበር:: በዛን ጊዜ ያን ችግር በሚመለከት ብዙ ጊዜ በጋዜጦች ፅፌ ነበር:: የችግሩ መነሻ የሆነው በድርጅቱ ብልሹ አስተዳደርና በሰራተኞች መካከል የነበረ የአሰራር ብልሹነት ችግር ምክኒያት ነው:: ምክኒያቱም የአስተዳደር ሥራ በአካለ ጉዳተኞች ያልሆኑ ሰዎች ይካሄድ ስለነበረና እነሱ ደግሞ የሚፈጥሩት ችግር ነው:: ይህን ሁሉ እያነሳን ብዙ አወራን ሃሳብ ለሃሳብ ተለዋወጥን:: ህወሓት በመጀመርያ አደረጃጀቱ እንዴት ነበር? የሚል ጥያቄ አቀረብኩላቸው:: መጀመርያ ላቀረብኩት ጥያቄ ተሎ ብለው መልስ አልሰጡኝም:: ስለዚህ የኔ ጥያቄ ያስቸገራቸው መሆኑ ተረዳሁና ዝም አልኩ:: ከዛ በኋላ ቀጠልኩና ይህን አሁን ያለ የህወሓት (1/5) የሚል አደረጃጀት አሁን ነው የጀመረው? ወይስ ቀደም ብሎ ነው የሚል ጥየቄ ሰነዘርኩ:: ከዛ በኋላ ተዘግቶ የነበረ አንደበታቸው እንደገና ተከፈተና ብዙ ነገሮች መናገር ጀመሩ:: ከዛ በኋላ እየተግባባን ሄድንና ብዙ ነገሮች ለማወቅ ቻልኩ:: ለምሳሌ ወደ ህወሓት የገባው ሁሉ ለማለት ይቻላል በፍላጎቱና የቢሄር ጭቆና ለመታገል ብሎ ነው የገባው:: ነገር ግን ወደ ህወሓት ከተቀላቀለ በኋላ የህወሓት መዋቅር ምን ይመስል ነበር? የሚል ጥታቄ መነሳት ያለበት ጉዳይ ነው:: ህወሓት ከተመሰረተ ጀምሮ የሚከተለውን የአደረጃጀት መዋቅር የነበረው:: 1ኛ ከፍተኛ ታመኝ ካድሬ ወይም የማለሊት አባል:: 2ኛ የማለሊት አባል:: 3ኛ የማለሊት እጩ አባል:: 4ኛ የማለሊት መሰሶ (ዓንዲ ውዳበ) አባል:: 5ኛ ዋህዮ የመሰረታዊ ህዋስ አባል:: እነዚህ መዋቅሮች የህወሓት መሰረታዊ መዋቅሮች ናቸው:: ይህን ዓይነት አደረጃጀት ልክ እንደኮመኒስት አደረጃጀት ነው ምንም ልዩነት የለዉም:: ይህን መዋቅር በአርሶ አደሩ በከተማ ነዋሪ እንደታጋዮች አደረጃጀት እኩል ነበር:: ልዩ የሚያደርገው ግን በሕብረተሰቡ የሚደረግ የነበረ አደረጃጀት እስከ ቤተሰብ በቤት ውስጥ የመአድ አደረጃጀት ነበር:: ይህ ደግሞ ባል ለሚስቱ ሚስትም ለባሏ ልጆች ለወላጆቻቸው እንዲሳለሉና በቤተሰቡ አንድነት እንዳይፈጠር ያደርግ ነበር:: እስከ ባልና ሚስት ማፋታት ይደርሱ ነበር:: እንደዚህ እያወራን አክሱም ከተማ ደረስን እዛም ምሳችን በላን:: በምሳ ጊዜም ብዙ ነገሮች እያነሳን አወራን:: ነገር ግን ወሬያቸን በህወሓት ዙርያ ነው ሁልጊዜ የሚሽከረከረው:: እነዚህ ላይ የተዘረዘሩ መዋቅሮች የህወሓት መሰረታዊ አካሎች ናቸው:: በነዚህ መዋቅሮች አባል የሆነ ሰው ህወሓት እንዳለው መሆንና መሄድ አለባት:: ይህን ዋና መሰረታዊ ግዴታ ነው አለበለዚያ ከህወሓት አስተሳሰብ ወይም አመለካከት ለመውጣት ከፈለገ ወይም ከህወሓት አስተሳሰብ ለየት ያለ ሃሳብ ለሚሰነዝር ወይም የሚሞክር ሰው በራሱ ላይ የሞት ፍርድ እንደበየነ ማለት ነው:: እንደዛ ያደረገ ሰው ወድያውኑ ተይዞ ወደ 06 (ባዶ ሹሽተ) የሚባል እሱር ቤት ይወሰዳል:: ከዛ የሆኑ ቀናቶች ወይም ሳምንታት ወይም ወራት ታስሮ ከወጣ በጣም ዕድለኛ ነው:: አለበለዚያ ነበረ ሆኖ ይቀራል ማለት ነው:: ይህን ሁሉ እያወራን ሽሬ ደረስንና ሁላችን ወደ መጣበት ተሰማራን እኔ ግን የሰማሁትን ሁሉ መላልሼ ሳስብ ሳወጣና ሳወርድ ዋልኩና አደርኩ:: ነገሩ ሁሉ ገርሞኝ ራሴ በራሴን ማውራት ጀመርኩ እላቹሁለሁ እናንተም ሳትገረሙ አትረሩም!!:: ቀስ በቀስ ለጥያቄ መልስ እያገኘሁ ሄድኩ በተለይ ደግሞ ከዛ በፊት ስለአካል ጉዳተኞች ቀደም ብየ በጋዜጦች የፃፍኩ መሆኔ ከነገርኩዋቸው በኋላ በኔ ላይ የበለጠ አመኔታ ላድርባቸው ቻለና ከዛ በኋላ በኔ ላይ የነበራቸው ፍራቻ እየተዋቸው ሄደ:: እንደሚታወቀው በአመሪካ መንግስት እርዳታ የተቋቋመ የአካል ጉዳተኞች ድርጅት የሚያስተዳድሩት ሰዎች አካል ኢንጂኔር አብደልውሀብ ቡሽራ – መቀሌ ጉዳተኞች አለመሆናቸው አውቅ ነበርኩና ጥያቄዎቹ እዛ ዙርያ እንዲያተኩሩ አደረግኩ:: ምክኒያቱም ከብዙ ዓመታት በፊት እሱን የሚመለከት ብዙ ጊዜ ፅፌ ስለነበርኩና ከዛ የተያያዘ የቢሄር አስተዋፅኦ በሚል ሽፋን ብዙ ታጋዮች ዳንሻና ወደ ሌላ ሰፈራ በሚል ሰበብ ስለተባረሩ የህወሓት መሪዎች ይህን ዕድል በመጠቀም ብዙ ሐቀኛ ታጋዮች ያባረሩበት ጊዜ ስለነበረ እኔም ይህንን ሁኔታ በሚመለከት በተከታታይ በጋዜጣ ፅፌ ስለነበርኩ:: እነዚህ የተባረሩ ታጋዮች ጥያቄዎች ያነሱ ስለነበሩና ህወሓት ደግሞ እንደዛ ያሉ ጥያቄዎች ሲነሱ የራስ ምታት ስለሚሁበት ነው:: ለምሳሌ ስለኢርትራ ጉዳይ ማናቸውም ጥያቄ መነሳት የለበትም ባይ ነው ህወሓት:: ምክኒያቱም ህወሓት ሻዕቢያን ሊያስቀይም አይፈልግም:: ህወሓት ያን ሁሉ መዋቅር ለምን አስፈለገው? ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ ራሱን ለመጠበቅ ነው የሚል የሚሆን ይመስለኛል:: ምክኒያቱም ህወሓት ህዝብን አቅፎ ወይም በህዝብ ታቅፎ አይደለም የኖረው:: ህዝብ በማስፈራራትና ከህዝብ በመፍራት የኖረ ድርጅት ነው:: ምክኒያቱም ሁልጊዜ በሃይልና በአፈሙዝ የሚያምን ድርጅት መሆኑ ከጅምሩ ጀምሮ የታወቀ ነው:: ምንጊዜም ችግሮች ሲያጋጥሙት በውይይት ከመፍታት ይልቅ በጦርነት መፍታት ያስቀድማል:: ምክኒያቱም ሁልጊዜ እየተፈራ እንዲኖር ይወዳል ወይም አመራሩ እንደዚህ ይወዳሉ ማለት ነው:: የመሪዎቹ ዕቅድም ስትራተጂም እንገዛ ነው ጥይት ነው የሚቀናቸው:: ከነዛ ሰዎች ብዙ ካወራን በኋላ ወደ መተማመን ደረጃ ደረስን እኔም ቀለል አለኝና ላይ ያቀረብኩዋቸው ጥያቄዎችና መልስ ያላገኘሁባቸው ቀስ እያልኩ እንደገና መጠየቅ ጀመርኩ ነገር ግን ቀለል ያሉ ጥያቄዎ በማስቀደም ነው:: እነሱም ስለንሮ ውድነትና የአካለ ጉዳተኞች ንሮ ምን ይመስላል የሚሉ ዓይነት ናቸው:: እኔ ራሴም ብዙ ወንድሞችና ዘመዶች በትግል ጊዜ ታጋዮች የነበሩ ከፊሎቹ በጦርነት የተሰዉ እንደ ጃዕፈር ወሃብረቢና መንሱር ወዲ ካድራይ የመሰሉ:: ጃዕፈር ከኢድዩ ጋር በተካሄደ ጦርነት ሸራሮ ላይ የተሰዋ ነው:: መንሱር ወዲ ካድራይ ደግሞ የበጦሎኒ (ሻለቃ) መሪ የነበረና ምጉላት በሚባል ተራራ ላይ በተገረው ጦርነት የተሰዋ ነው:: ሌሎች ደግሞ በትግሉ የነበሩና የት እንደገቡ የማይታወቁ አሉ:: እነዚህ ሰዎች የት ሄዱ የሚል ጥያቄ እስከ አሁን መልስ አላገኘም:: በዚህ ላይ ደጋግመህ ጥያቄ ማቅረብ እንደወንጀል እንጂ እንደመብት አይወሰድም:: ስለዚህ እየፈሩ መጠየቅ ደግሞ አደገኛ ስለሚሆን ይቅር እየተባለ ቆይተዋል:: መጨረሻው ምን እንደሚሆን አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው:: ወደ መቀሌ ከተመለስኩ በኋላ ከነዛ ሰዎች አንዱ አገኘሁትና አብረን አንድ ቦታ ላይ ሻሂ ቡና ካልን በኋላ ወደ ቤት ወሰድኩትና እዛ ብዙ ጊዜ እየተገናኘን ጭውውታችን ቀጠልን:: ስለህወሓት ተነግሮ ወይም ተፅፎ የማያልቅ ታሪክ በየጊዜው እያነሳንና አዳዲስ ነገሮች እያገኘን እናወራለን:: እሱም እንደተለመደው የችግር ታሪክ ነው እንጂ ደስ የሚል ታሪክ አልነበረም:: እንደዚህ የሆኑበት ምክኒያት ላይ እንደተገለፀው የህወሓት መሪዎች በህዝቡ ውስጥ ሽብርና ፍራቻ እንዲሰፍን ስለያዘወትሩ ነው:: ምናልባት የስልጣን ዕድሜያቸው ያራዝምላቸው እንደሆነ ምን ይታወቃል በማለት ነው የሚመስለው:: ይህን ዓይነት አስተሳሰብ ጊዜ ያለፈበትና ደስ የማይል ሁኔታ ይፈጥራል:: ምክኒያቱም የህወሓት መሪዎች ቀና አስተሳሰብና ጥሩ ሥራ መስራት እንደድክመት አድርገው ስለሚያዩት ነው:: ይህን ደግሞ የደካሞች አስተሳሰብ መሆኑ አልተረዱትም:: ማንም ሰው ስለህወሓት ካወራህ እባክህ ተወይ ይለሃል ከፍራቻው የተነሳ እንጂ ስለህወሓት የሚለውን ነገር አጥቶ አይደለም:: ነጋዴ ከሆነ ተወይ ባክህ አምና የከፈልኩት ግብር ይበቃኛል አሁን ደግሞ ሌላ ምክኒያት ፈጥረው በግብር ይቀጡኛል ይላል:: ማንም ሰው ስለህወሓት ብታነሳለት ተው ባክህ እነዚህ ሰዎች ያው ናቸው እንደውሃ ቢወቅጡት እንቡጭ ናቸው ይላል ሌላ ደግሞ ያውም ብሶባቸዋል ይላል ስለህወሓት እረ ስንቱ:: ህወሓቶች ጎደሎቻቸው ብትነግራቸው ጎደሎውን በማረም ፈንታ ይባስ ብለው ይቀጥሉበታል ይለሃል አንዱ:: የነዚህ ሰዎች አካሄድና አሰራር ምኑ ቅጡ አይታወቅም ያው ነው ብትወቅጠው እንቡጭ ነው:: ይህን (1/5) የሚባል አደረጃለት ህወሓት አዲስ ፋሽን አመጣ ብየ አስብ ነበር ለካስ የድሮና ከመጀመርያው ጀምሮ ይጠቀምበት የነበረ ነው:: —- ኢንጂኔር አብዱልውሀብ ቡሽራ – abdulwehab2005@yahoo.com ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com

No comments:

Post a Comment