ኢትዮጵያዉያኖች በኢትዮጵያ ኤምባሲ ባደረጉት የተቃዉሞ ሰልፍ፣ ኮከብ ያለበትን የአገዛዙ ባንዲራ አንስተው፣ የጠራዉን የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ መትከላቸው ይታወቃል። መሳሪያ ያልታጠቁ፣ ወረቀትና ባንዲራ ብቻ በእጃችቸው የያዙ ሰላማዊ ዜጎች “ግርማ ብሩን ለማነጋገር እንፈልጋለን፣ ወንጀለኞች አይደለንም” በሚሉበት ጊዜ፣ አንዱ የኤምባሲ ጠባቂ፣ ጥይት መደቀኑና ሶስት ጊዜ መተኮሱ፣ በኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ሜዲያዎች ሁሉ በስፋት እየተዘገበ ነው።
መሳሪያ ባልያዙ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ጥይት መደቀኑ ብዙዎችን እያስቆጣ ባለበት ወቅት፣ የአገዛዙ አምባሳደር የሆኑት አቶ ግርማ ብሩ፣ ለኢትዮጵያ ፈርስት በሰጡት አስተያየት፣ ሠልፈኞቹን “ጋጣወጦች” ሲሏቸው፣ ጥየት የተኮሰዉን ግለሰብ ደግሞ “ስራውን በትክክል የሰራ” ሲሉ አሞግሰዉታል።
በሰልፉ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንን ላይ ክስ እንዲመሰረትና እርምጃ እንዲወሰድ ጠበቃዎች እንደሚቀጥሩ የገለጹት አቶ ግርማ ብሩ፣ “ተቃዋሚዎቹ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት ጠንካራ በመሆኑ የተናደዱ ናቸው” ሲሉም ከሰዋቸዋል። ከአሜሪካኖች ጋር በቅርበት ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ እየተነጋገሩበት እንደሆነም የተናገሩት አቶ ግርማ፣ ሰልፈኞቹ ተቃዉሞ እንዲያሰሙ ስለገፋፋቸው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚደረገው ዜጎችን የማሽበር፣ የማሰር መረን የለቀቀ የሰባአዊ መብት ረገጣ ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡
አምባሳደሩ ሰልፈኞችን ጋጣወጦች ቢሏቸውም፣ ህዝቡ በሰልፉ ለነበሩ ወገኖች ያለዉን አድናቆትና ክብሩን እየገለጸ ሲሆን፣ ብዙዎች በኤምባሲ የተሰቀለዉን ባንዲራ የሚያሳየዉንን ፎቶ የፌስቡክ ፕሮፋይላቸዉ እያደረጉ ነው። በርካታ በዉጭ ያሉ የተቃዋሚ መሪዎች፣ አክቲቪስቶችም በ ኤምባሲ የታየው በተጠናከረ መልኩ መቀጥል እንዳለበት ይናገራሉ።
አምባሳደሩ ሰልፈኞችን ጋጣወጦች ቢሏቸውም፣ ህዝቡ በሰልፉ ለነበሩ ወገኖች ያለዉን አድናቆትና ክብሩን እየገለጸ ሲሆን፣ ብዙዎች በኤምባሲ የተሰቀለዉን ባንዲራ የሚያሳየዉንን ፎቶ የፌስቡክ ፕሮፋይላቸዉ እያደረጉ ነው። በርካታ በዉጭ ያሉ የተቃዋሚ መሪዎች፣ አክቲቪስቶችም በ ኤምባሲ የታየው በተጠናከረ መልኩ መቀጥል እንዳለበት ይናገራሉ።
በጉዳዩ ላይ ያነጋግርናቸው የፖለቲካ ተንትታኝ “ በዲስም ሆነ እንደ ለንደን ብራሰልስ ባሉ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን፣ ለአገራቸው፣ ለሕዝባቸውና ለባንዲራቸው ክብር የቆሙትን የሚያኮሩ ኢትዮጵያዉያንን “ጋጠወጦች” ብሎ ለጠራው የወያኔ ቅጥረኛ ግርማ ብሩ ምላሽ መስጠት ይኖርብናል” ያሉት በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ ፣ በኤምባሲ የታየው ህዝቡን ኤነርጃይዝድ በማድረጉ አንጻር ፣ ትግል ብዙ እርምጃ ወደፊት እንደወሰደው ይናገራሉ።
No comments:
Post a Comment