በቅርቡ‹‹አስራ ሰባት መድፌ››የተሰኘ ፖለቲካን እያዋዛ በቀልድ መልክ የተረከበትን መጽሀፍ ለንባብ አብቅቷል ሃብታሙ ስዩም፡፡በራዲዩ ፋና ግጥምና መጣጥፎች በማቅረብ ከራዲዩ አድማጮች ጋር የተዋወቀው ሃብታሙ የገጣሚና ጸሀፊ በእውቀቱ ስዩም ታናሽ ወንድም ነው፡፡
ከፋና ወደ ሸገር ራዲዩ በመምጣትም መጠነኛ ነጻነት እንዳለው በሚነገርለት ሸገር 102 ራዲዩ አዝናኝ አስተማሪ ወጎችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ከራዲዩ መርሃ ግብር በተጨማሪ ሃብታሙ በሳምንታዊው አዲስ ጉዳይ መጽሔት በአምደኝነት ፖለቲካዊ ሽሙጦችን፣ለህይወት የቀረቡ ወጎችንና ቁም ነገሮችን ለአንባቢያን እያካፈለ ይገኛል፡፡
ከፋና ወደ ሸገር ራዲዩ በመምጣትም መጠነኛ ነጻነት እንዳለው በሚነገርለት ሸገር 102 ራዲዩ አዝናኝ አስተማሪ ወጎችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ከራዲዩ መርሃ ግብር በተጨማሪ ሃብታሙ በሳምንታዊው አዲስ ጉዳይ መጽሔት በአምደኝነት ፖለቲካዊ ሽሙጦችን፣ለህይወት የቀረቡ ወጎችንና ቁም ነገሮችን ለአንባቢያን እያካፈለ ይገኛል፡፡
በወ/ሮ መዓዛ ስር የሚተዳደረው ሸገር ሬዲዩ በተለይ 17 መድፌ የሚለው መጽሐፍ ለንባብ ከቀረበ በኋላ ሃብታሙ በራዲዩው የሚያቀርባቸው ዝግጅቶች የተለየ ሳንሱር የሚደረግባቸውና መቀስ የሚያገኛቸው እንዲሆኑ በስውር በመወሰኑ ሃብታሙ ደስተኛ አልሆነም፡፡
የሚያቀርባቸውን ፕሮግራሞች ሰርቶ የድምጽ ቀረጻ በማጠናቀቅ ለፕሮዳክሽን ማናጀሮች አስረክቦ ሲሄድ መልእክቶቹ እንዲቆራረጡ ይደረጋሉ፡፡በዚህ ክፉኛ የተበሳጨው ሃብታሙ ለሸገር ሃላፊ በደብዳቤ የተፈጸመበትን ወንጀል በመጥቀስ በእንዲህ አይነት ሁኔታ በሸገር ለመቀጠል እንደሚቸግረው በመግለጽ ድርጅቱን በፈቃዱ መልቀቁን ማሳወቁን ምንጮቼ ነግረውኛል፡፡ሃብታሙ በደብዳቤው ማሳረጊያ ‹‹ነጻ ሚዲያ ስትሆኑ እመጣለሁ››ማለቱንም የዜናው ምንጭ አውግቶኛል፡፡
ሸገሮች ግን በየፕሮግራማቸው መክፈቻና ማሳረጊያ ‹‹ሸገር የእናንተው ነው››ለምን ይሉናል፡፡የእኔ ነገር ረስቼው ለካ ኢትዩ ቻናል ጋዜጣም ‹‹የምንፈራው ውሸትን ብቻ ነው›› ብሎናል፡፡
No comments:
Post a Comment