Wednesday, October 30, 2013

የቦሌ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የድረሱልኝ ጥሪ አሰማች

ኢሳት ዜና :- የቦሌ ለሚ ቅ/ሩፋኤል የጻዲቁ አቡነ ኤዎስጣቲዎስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ ብርሀን ተከስተ ካሳሁን “የድረሱልን ጥሪን ይመለከታል” በሚል ርእስ ለለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ረዳትና የጅማ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ለሆኑት ለ ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጻፉት ደብዳቤ ላይ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ቤተክርስቲያኑዋን በ7 ቀናት እንዲያፈርሱ እንዳዘዙዋቸው ተናግረዋል።
ደብዳቤው ” ቤተከርስቲያኑ ከተመሰረተ 4 አመታትን አስቆጠረ ቢሆንም በ2001 ዓም እንደማንኛውም አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተነስቶ ካርታውን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን። በተለይም የመንግስት አካላት በተለያየ ወቅት  ቦታው ድረስ እየመጡ፣ ቦታው የኢንዱስትሪ ቦታ ስለሆነ አፍርሱ የሚል ትእዛዝ በተደጋጋሚ ደርሶናል። አሁንም በቀን 12/02/2006 ኣም በመ/ቁጥር ቦ/ክ/ከ/መዝ/9539/06 በተጻፈልን ደብዳቤ ቦታው ለልማት ስለሚፈለግ ቤተ ክርስቲያኑን በ7 ቀን እንድታፈርሱ ሲል በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳዳር የደምብ ማስከበር አገልግሎት ጽ/ቤት አሳውቆናል።” ይላል።
ደብዳቤው በማያያዝም “  የአካባቢው ህብረተሰብ አሁን በተረጋጋ መንፈስ የጸሎት ስነስርአትና አምልኮ ስነስርአት በሚፈጽምበት ወቅት በድጋሜ መጥተው በአስቸኳይ ቤተከርስቲያኑን እንድታነሱ የሚል ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ምእመኑን እጅግ አሳዝናል ( አስቆጥቷል)። ስለሆነም ጉዳዩ ጊዜ የማይሰጥ ስለሆነ ለብጹእ ወቅዱስነታቸው ደብደቤ እንዲጻፍልንና ቅዱስነታቸውም ለክቡር አቶ ድሪባ ኩማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳደር ከንቲባ አስቸኳይ ደብዳቤ እንዲጽፉልን ስንል በቅድስት ቤተክርስያን  ስም እንጠይቃለን ብሎአል። ከደብዳቤው ጋርም የህዝቡን አቤቱታ የያዘ 10 ገጽ ወረቀት ተያይዞ ቀርቧል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ደንብ ማስከበር አገልግሎት ጽ/ቤት በ12/02/06 ለሩፋኤል ቤተከርስቲያን በጻፈው ደብዳቤ ፣ ትእዛዙን የሰጠው የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት መሆኑን ጠቅሷል። በአቶ ጌታቸው አዲስ ፈለቀ የተጻፈው ደብዳቤ ቤተክርስቲያኑ በ7 ቀናት ውስጥ ካልተነሳ አስተዳደሩ ለሚወስደው እርምጃ ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን ይወስዷል ብሎአል።
የአዲስ አበባ ሀገረስብከትም ሆነ የፓትሪያርኩ ጽህፈት ቤት በጉዳዩ ላይ የሰጡት ምላሽ አልታወቀም።
የኦርቶዶክስ ሀይማኖት አንዳንድ አባቶች በቅርቡ መንግስት በቤተከርስቲያኑዋ ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽእኖ መንቀፋቸው ይታወሳል።

2 comments:

  1. egzare yerdane gene bantegna teru new
    beabune pawlose geza yederese poleticawe haymanotawi chiger endayderse bekdmea mesrat alebne

    ReplyDelete
  2. egzare yerdane gene bantegna teru new
    beabune pawlose geza yederese poleticawe haymanotawi chiger endayderse bekdmea mesrat alebne

    ReplyDelete