Monday, October 7, 2013

ዋሽንግተንን አሸብራ የተገደለችው ሴት ጉዳይ እየተጣራ ነው

ባለፈው ሐሙስ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ዋይት ሐውስ አጠገብ የደኅንነት መከላከያዎችን ጥሳ ለመግባት የሞከረችው ሴት ሁለት ፖሊሶችን አቁስላ ብትገደልም፣ ለምን ይህን ድርጊት እንደፈጸመች ምርመራ መጀመሩን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በአካባቢው በተፈጠረው ግርግር በአሜካውያን ላይ ከፍተኛ ፍርኃት የፈጠረው አጋጣሚ በሴትየዋ ግድያ ቢጠናቀቅም፣ ፖሊስ ጉዳዩን ከሽብርተኛነት ጋር እንዳላያያዘው ፎክስ ኒውስ ዘግቧል፡፡ የአንድ ዓመት ሕፃን ልጇን መኪናዋ ውስጥ ጭና ከፖሊስ ጋር የተሳደደችው የ34 ዓመቷ ሚርያም ኬሪ፣ የካፒቶል ሂል ሕንፃ መከላከያ ክትርን ጥሳ ለመግባት የፈለገችበት ምክንያት አልታወቀም፡፡

በሴትዮዋና በፖሊስ መካከል ካፒቶል ሂል አካባቢ የተደረገው ሰዶ ማሳደድ ግን አስደንጋጭ ነበር ተብሏል፡፡ ሴትየዋ በመኪና የገጨቻቸው ፖሊሶች በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ መባሉን ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡ የሟች እናት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ልጇን ከወለደች ወዲህ ድብርትና ጥሩ ስሜት አይሰማትም ነበር፡፡

No comments:

Post a Comment