Tuesday, October 8, 2013

የወያኔ ፍርሃት ተባብሷል።

ሻቢያን የሚያውቀው ወያኔ እንጂ ተቃዋሚዎች አይደለም ሁለቱም እንደ ፍጥርጥራቸው።እራሳችሁ ይለያዩ ወዳጅ ሁለቱ ናቸው ተቃዋሚው ላይ አታላኩ ተቃዋሚው ዝምድናም እንደሌለው ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል የሁለቱን ስራ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሃገርቤት ተቃዋሚዎች የሚያሰሟቸው ጥያቄዎች የራሳቸው እንዳልሆኑ እና እንደ እርሳቸው አባባል በተለያዩ ሃገሮች ያሉ ሌሎች ሃይሎች የሰጧቸው የቤት ስራዎች ናቸው፡፡
በዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር፤ ለምሳሌ ሰማያዊ ፓርቲ እና አንድነት ፓርቲ የታሰሩ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች እንዲፈቱ፣ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዳይገባ፣ የኑሮ ውድነት የመሳሰሉት ጉዳዮች እንዲሻሻሉ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች መልስ አያገኙም ማለት ነው፡፡ በውጭ ካሉ የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ በተመለከተ ግንቦት ሰባት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ባጭሩ ህልም ነው፤ ማለም ይችላሉ ያሉ ሲሆን በፓርቲያቸው ውስጥ መሰንጠቅ ስለመኖሩም ለተነሳው ጥያቄ ምኞት ነው መመኘት ትችላላችሁ የሚል ድፍን ያለ መልስ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተር ሀይሌ ነገሮች እያዣለጣቸው ነው ግን ***አንሰማም!!!***

ዶክተር ብርሃኑ ነጋና ግንቦት 7 ስራቸውን እየሰሩ ነው ምንም ጥርጥር የለኝም ! ሰርጎ ገቦች ወሬ ማናፈሱን ይቀጥሉ ግን አንሰማም!!!
ተቃዋሚ የሚባሉት ሲያዳልጣቸው ይታያሉ።እዚ ሲባሉ እዛ፣እዛ ሲባሉ እዚ ጉድ ነው ዘንድሮ።
ለማንኛው ሀገር ቤት ሆነው ተቃዋሚ ነን እያሉ የሚቀየሱትንም አንሰማም!
በውጪ ያሉትንም እንደዛው እየተለጠፉ የሚቀባጥሩትንም አንሰማም!
ፍትህ አጣን ብለው ከሀገር ቤት መፃፍ መናገር አልቻንም ብለው ተሰደው የወያኔ ጀሌ ሆነው የህዝብ አስተሳሰብ፣አመለካከት የሚያስቱትንም አንሰማም!
ጋዜጠኛዎች በነጻነት ያለ ጣልቃ ገብነት እንዲሰሩ እንጂ ትግሉን የሚመሩት ተቃዋሚዎች የሚዲያ እድል ባስፈለጋቸው ጊዜ እዳያገኙ አይደለም።
 ከኢህአዴግ ጋር የስጋ ዝምድና አላቸው እየተባሉ የሚጠረጠሩ ወዳጆቻችን መስለው የተቃዋሚውን ድርጅቶች ለመከፋፈል ሴራ የሚዶልቱ ጀሌዎች አይሳካላችሁም።አንሰማም!
ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከአንዳች ሀይል ኢህአዴግን ለመገዳደሪያ የሚሆን ገንዘብ እንዳገኙ የሚያሰማ ድምፅ አጋርተውናል፡፡ ችግሩ ግን ይህ ገንዘብ ከየት እንደተገኘ እርስ በርሳቸው ስምምነት ላይ አልደረሱም፡፡ አንዳቸው ከኤርትራ ነው ሲሉ ሌላኛው ደግሞ ከግብፅ ነው ይላሉ፡፡ በደንብ ጆሮ ጣል ብናደርግ ከኢህአዴግ መንግስት ነው የሚልም አይጠፋም፡፡ከምንም ይገኝ ከምንም መጥቀሙ ነው የሚፈለገው።

ደግሞ ምንድነው ማናፈስ እንዴ ወያኔ ለግንቦት 7 ወዳጁ ነው እንዴ?

 አንድ ሰሞን እኮ ወዳጆቻችን ያጋሩን ድምፅ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከሆነ ቦታ የተገኘውን ብር፤ ለእንትን ይሄን ያህል፣ ለእንትና ይሄን ያህል እያሉ ሲናገሩ ያስደምጣል፡፡ በዚህ ላይ ያስደነቀኝን ልናገር እና እመለሳለሁ ቆይ አዲስ መስመር ላይ እንገናኝ፡፡
ዶክተሩ የሆነውን ብር እዛው ለመከላከያ እና ደህንነቱ የተበጀተ ነው፤ ሲሉ ሰማናቸው፡፡ ይሄኔ በተለይ በኢህአዴግዬ ፍቅር የተለከፈ ሰው ክው!!! ማለቱ አይቀርም፡፡ ደህነነት እና መከላከያችን ከመንግስት ከሚመደብለት በጀት ውጪ በግንቦት 7 ደግሞ ሌላ በጀት አለው ማለት ነው፡፡ ይቺን ነው መፍራት፤ ዶክተሩ ስራቸውን ቀጥ ለጥ አድርገው እየሰሩ ነው ማለት ነው፡፡

ታድያ ለዚህ ነዋ የኢህአዴግዬ ገመናዋ ሁሉ ቀድሞ አደባባይ የሚሰጣው!!! እኔ ልሰጣልበል ወይስ አልበል! (በቅንፍም ይቅርብኝ እነ እንትና ሳይሉ እኔ ቀድሜ ልሰጣብል እነሱን ማሳጣት ሆንብኛል!) ከቅንፍ ስንወጣም ለኢሳትም የሆነ ብር ይሰጣል ሲሉ ዶክተሩ መናገራቸውን አዳመጥኩ፡፡ በእውነት ዶክተርዬ የተባረኩ ኖት፡፡እንዴበአሁኑ ጊዜ ማን እንደዚህ ያደርጋልየምር እኮ ኢሳትን ሁሉም መርዳት አለበት፡፡ ግንቦት 7 ከረዳው በጣም ጥሩ ጅምር ነው፡፡ እንኳን ሌላ ቀርቶ ግንቦት 20 ራሷ ኢሳትን መርዳት አለባት፡፡ እንዴ ኢቲቪ የማይሰራውን በሙሉ የሚሰራው ኢሳት አይደለ እንዴ…! ታድያ እንዲህ እንዲተጋገዙ ሁሉም የአቅሙን ቢያዋጣ ምን ችግር አለበት!
ወደ ዋናው መስመር ስመለስ ወዳጆቻችን "ፈልፍለው" ይፋ ባደረጉት መረጃ ዶክተሩ ለካስ አልተኙም ብለናል፡፡ እና ይበርቱ ልንላቸው ይገባል፡፡

 ከዚህ በፊት ገንዘቡ ከግብጽ ነው ሲባል ነበር፤

ግብፅ የምር ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ገንዘብ የምትረዳ ከሆነ ተጃጅላለች ማለት ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ ኢህአዴግ እንኳ ያንን ሁላ አድርጋለት አልተመለሰላትም፡፡ በእውኑ ሌሎቹማ ከኢህአዴግ የበለጠ ለሀገራቸው ተቆርቋሪ አይደሉምን…!

ገንዘቡ ከኤርትራ ነው፤

ወይ…. ኤርትራ….!!! አሁን ማን ይሙት ኤርትራዬ ከራሷ አልፋ ለሌላ ሰው ይሄንን ያክል ብር መስጠት ትችላለች…! ይሄንን ሃሳብ የሰነዘሩ ሰዎች በእርግጠኝነት ኤርትራዊያን ናቸው እንዳንል እነሱንም እኛ መለየት አንችልም እራሳቸው ይለያዩ እንጂ፡፡
 አላማውም ወያኔን በሚገባው ቋንቋ መልስ መስጠት ነው።

***የትም ፍጪው ኢህአዴግን አስወጪው***

ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ግንቦት 7 የሚባል ተቃዋሚ ፓርቲ መስርተው ሁለገብ በሆነ ዘዴ ኢህአዴግን ወግድ እለዋለሁ ብለውናል፡፡ ግንቦት 7 ይህ ከሆነለት የዘመናት ብሶት የወለዳቸው ሁሉ ተሰባሰበው ዋንጫ እንደበላ ሰው "የእርግብ አሞራ" "የእርግብ አሞራ""የእርግብ አሞራ"እያሉ የሚጨፍሩለት ደስታ የሚሆን ይመስለኛል፡፡ ታድያ ለዚህ አላማ ገንዘብ ከየትስ ቢያመጡ እኛ ምን አገባን…!?
ምነው እነሱ እረሱት እንዴ ከየት እየተረዱ አዲስ አበባ እንደገቡ???
ለማንኛውም አንሰማችሁም!!!!!!!!!!


ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment