Thursday, April 30, 2015

የወያኔ አፓርታይድ መንግሥት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ ከ100 በላይ ሰዎችን ለመክሰስ ምርመራ ማጠናቀቁን አስታወቀ

ሰማያዊ ፓርቲ መንግሥት ከስም ማጥፋት ዘመቻ ይታቀብ አለ
በኢትዮጵያውያን ላይ የአይኤስ አሸባሪ ቡድን የፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ ለማውገዝ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በተደረገው ሠልፍ ላይ፣ ሆን ብለው ብጥብጥ ያስነሱትና ሁከት እንዲፈጠር ያደረጉት፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና
አባላት መሆናቸውን ማረጋገጡን የፌዴራል ፖሊስ ገልጾ፣ ክስ እንዲመሠረት ለዓቃቤ ሕግ ማስተላለፉን አስታወቀ፡፡ በክሱም የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንና አባላትን ጨምሮ ከ100 በላይ ሰዎች ተካተዋል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ ጄኔራል ዳይሬክተር አቶ አሰፋ በዩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ተዘጋጅተውና ልምምድ አድርገው፣ በንብረትና በሰው ሕይወት ላይ አደጋ ለማድረስ፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴንና መላውን ዓለም ያሳዘነውን ሐዘን ሽፋን በማድረግ ሁከት ለመፍጠር ተዘጋጅተው የነበረ ቢሆንም፣ ሊከሽፍ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

Report: Egypt Preparing Large Assault Against ISIS in Libya Despite Opposition From Obama

Egypt is getting ready to launch a large air and ground attack against the Islamic State (ISIS/ISIL) in eastern Libya DebkaFile reports, quoting military and intelligence sources.
The Obama administration is reportedly opposed to the operation.
“Egypt is massing large-scale ground and air forces in the Western Desert along the Libyan border, in preparation for a military campaign to capture eastern Libya — Cyrenaica — from the Islamist State of Syria and Iraq — ISIS — occupation,” reports DebkaFile.

አልሸባብ አይሲስን ሊቀላቀል ነው ተጨማሪ የሽብር ስጋት በኢትዮጵያ

በሶማሊያ የሽብር ተግባራትን በመፈጸም የሚታወቀው አልሸባብ ደመኛና አረመኔውን አይሲስን ሊቀላለቀል መሆኑ ተሰማ፡፡አገራችንን በተጨማሪ የሽብር ስጋት ውስጥ እነደሚጥላት ተገምቷል፡፡
የሶማሊያን ስፊ ግዛት የሚቆጣጠረው አልሸባብ የማእከላዊ ስልጣኑን ካጣ ወዲህ በደረሰበት ወታደራዊ ኪሳራ የአለም አቀፍ አሸባሪው አልቃይዳ ክንፍ በመሆን እያካሄደ ባለው የደፈጣ ውጊያ ሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ርቋት በንጹሃን ደም የታጠበች መንግስት አልባ ጦር ሜዳ ከሆነች ከሁለት ዓስርት አመታት በላይ አስቆጥራለች።

“ልጄ! እንካንተ እኔም ባልተወልድኩ”

…. ስሙን ሞት ይጥራውና እንኳን በአንደበቴ በህሊናዬ ሲንከላወስ እጅጉን የሚኰሰኩሰኝ ያ! መናጢ፤አናጢ፤ ግምበኛ፤አትክልተኛ ነኝ’ ባይ ‘መጤ’ ‘የቀን ሠራተኛ’ ለካስ ዋናው ሙያው ‘የጨለማ ሠራተኛ’ ኖሮ ወያኔዎች ኢትዮጵያን ወረው
መዲናንችንን ሲቆርጣጠሩ ይኸ ‘እንግዳ ሰው’ ከምንጊዜው እንደ እስስት ተቀያይሮ፤ የቀን ቱታውን አውልቆ፤ዪኒፎርሙን ጠርንቆ፤መትረየሱን ታጥቆ ሰፈራችንን ፊታውራሪ ሆኖ ሲያምሰን፤ ሲያተራምሰን ከረመ። አይ እኛ! ምንኛ ተላላዎች፤ሰው አማኞች፤ የዋሆችም ኖረናል።
ይባስ ብሎ ለሥራ ክብር ባላቸው የተከበሩ ጎረቤቶቻችንና የሰፈራችን አረጋዊያን፤ አባ ምንተስኖትና እማማ ገላኒ በትልቁ ግቢያቸው አስጠግተው እንዳቅሙ መጠነኛ ክፍል አከራይተው ቡናና፤ጠላ አብረው እየጠጡ፤ወሬ እየለጠጡ፤ዓመት ባል፤አውዳ ዓመት እንደ ዘመድ፤እንደ ሃገር ሰው የተገኘውን ሁሉ እኩል ተካፍለው፤ አክብረው ቢያኖሩት ‘ባለቀን’ ሆነና ለውለታቸው ምላሽ ግቢያቸውን በሙሉ ወርሶ እነርሱን ከከተማ ዳርቻ አልባሌ ቦታ ቀበሌ ቤት ጣላቸው።

መሰረዝ ያለበት አስደንጋጭ እቅድ – ግርማ ካሳ

“መንግስት በሊቢያ በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ሰፋፊ ሰራዎችን ለመስራት በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ቴድሮስ በቤንጋዚ ያሉ ኢትዮጵያውያን በግብጽ መንግሰት በኩል፣ ትሪፖሊ ያሉትን ደግሞ ከሱዳን መንግሰት ጋር በመተባበር ከሊቢያ ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።” የሚል በዶር ቴድሮስ አዳኖም ፌስ ቡክ ገጽ ላይ አነበብኩ። የዝግጅቱን ዝርዝር ባላውቅም ዝግጅቶች እየተደረጉ ሊሆኑ እንደሚሉ ማንበቤ ትንሽም ቢሆን ደስታ ሰጥቶኛል።
በሊቢያ ከአሥራ አምስት በላይ የሚሆኑ ኃይላት አሉ። እነዚህ ኃይላት እርስ በርስ እየተቀናጁ በዋናነት ሦስት ቡድኖች ተፈጥረዋል። እነርሱም፡
መቀመጫዉን ቱብሩክ (ወደ ግብጽ ድንብር የተጠጋች ከተማ) ያደረገው በጀነራል ካሊፋ ሃፍተር የሚመራው ስብስብ ነው። ይህ ስብስብ ደርና ከምትባለዋና አይሰስ ከሚቆጣጠራት ከተማ በስተቀር፣ አብዛኛዉ ቤንጋዚ ጨምሮ፣ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ያሉትን ግዛቶች ይቆጣጠራል። ይህ ስብስብ በአለም አቀፍ ማህበረሰብ እንደ ሕጋዊ የሊቢያ መንግስት የሚቆጠር ሲሆን ከግብጽ መንግስት ጋር የቀረበ ግንኙነት አለው።

ክርክር 6፡ ኢህአዴግ እና 1997 ስብርባሪዎች!!!! ግርማ ሠይፉ ማሩ

በዛሬው ሰድስተኛ ዙር የምርጫ ተብዬ ክርክር ጉዳዩ በመሰረተ ልማት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ኢህአዴግ ጎምቱ ያላቸውን ሹሞቹን ለክርክር ይዞ የቀረበበት ቢሆንም ለእኔ ግን ትኩረቴን የሳበው የተከራከሩበት ርዕስ ሳይሆን ተከራካሪዎቹ ሰዎች እና ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ማለት የፈለኩት የመሰረተ ልማት በሚል ርዕስ ክርክር ስመለከት የተገነዘብኩት ጉዳይ ቢኖር ኢህአዴግ ክርክር እያደረገ ያለው የዛሬ አስር ዓመት ለሚዲያ ክርክር ድመቅት ይሰጥ ከነበረው ከቅንጅት ስብርባሪ ጋር አንደሆነ ተረዳሁኝ፡፡ ህብረትም ቢሆን አሁን በመድረክ በኩል በድሮ ግርማ ሞገሱ አይታይም፡፡ እውነቱን ለመናገር አሁን በክርክሩ ላይ የሚገኙት ሰዎች ኢህአዴግ በልኩ የሰራቸው፤ በእግራቸው ገመድ የተበጀላቸው ጭምር ናቸው፡፡ ምንም ቢሉ ማንም ምንም የማይሰማቸው፡፡

መንግስት በሰማያዊ ፖርቲ ላይ የከፈተውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በአስቸኳይ ያቁም!!! – ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ሰማያዊ ፓርቲ በየመን፣ ደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እየተከታተለ መንግስት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡ በእነዚህ ሀገራት ችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል በማውገዝና መንግስትም መፍትሄ እንዲሰጥ መግለጫ ከማውጣት ባለፈ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል እንዲያስቆም አዲስ አበባ ለሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ደብዳቤ በመጻፍ ፓርቲያችን የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በተመሳሳይ መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ እርምጃ ለመቃወም የጠራውን ሰልፍም በመደገፍ ሰማያዊ ፓርቲ የመጀመሪያው ተቃዋሚ ፓርቲ ነው፡፡

(የሊቢያው እልቂት ጉዳይ) እኛ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ነን!!

አፈንዲ ሙተቂ
ISIL የሚባለው ሰይጣናዊ ቡድን በምድረ ሊቢያ በዜጎቻችን ላይ የፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊት ያስቆጣኝ በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመሪያው ምክንያቴ በጥይት የተረሸነውና በስለት የታረደው ኢትዮጵያዊ ወንድሜ መሆኑ ነው፡፡ አዎን!! “ዘወትር በድህነት ከምንገላታ ወደ ውጪ ሄጄ ዕድሌን ብሞክር ይሻላል” በሚል የሃሳብ ምጥ ተነሳስቶ በምድረ ሊቢያ በኩል ወደ አውሮጳ ለመሻገር ሲሞክር በአረመኔው ቡድን የተያዘው ወገኔ ደም በረሃ አሸዋ ላይ እንደ ጎርፍ መፍሰሱ በእጅጉ ያንገበግበኛል!! ያስቆጣኛል!! ያስቆጨኛል!! ከአስከፊው የሰሃራ በረሃ የውሃ ጥም እና የሞት መልዕክተኛ ከሆነው የሜዲትራኒያን ባህር ጉዞ ተርፎ ወደ ማልታና ኢጣሊያ መድረሱ እንኳ እያሳሰበኝ ሳለ ከሁለቱ ሰይጣኖች በሺህ እጥፍ የሚብሰው ISIL የተባለ ሶስተኛ ሰይጣን በሊቢያ ምድር ላይ ወገኔን ጠልፎ እንደ በግ አጋድሞት ሲያርደው ማየቱ ይቅርና መስማቱ ራሱ ሲቃው የማይቻል ህመም ነው የሆነብኝ፡፡ የፈሰሰው ክቡር የሆነው የወገኔ ደም ነውና ስለርሱ ሞት እኔ ታምሜአለሁ (ብታምኑም ባታምኑም ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ የምርምር ስራዬን አቁሜአለሁ፤ እንኳንም የቢሮ ሰራተኛ አልሆንኩ)!!

የአንደበትህ ፍሬ ሕይወት እንጂ ሞት አይሁን!!! – ከተማ ዋቅጅራ

የልብ ሃሳብ የሚገለጸው በአንደበት ነው። የተሰወረን ሚስጢር የሚገለጸው በምላስ ነው። የሰው ልጅ ከግዜ ጋር ይሮጣል እውነተኛው እውነት ይዞ.. ሃሰተኛው ሃሰት ይዞ እየተቀዳደሙ ወደፊት ይሔዳሉ። ሃሰት በጥርርጥር የተሞላ ነው። ጥርጥርን የሚያስወግድ በእውነተኛ መንገድ የሄደ  ነው። የፍቅር እርሻ አራሽ፥ የፍቅር ዘር ዘሪ፥ የፍቅር ቡቃያ  አብቃይ፥ የፍቅር ሰብል ሰብሳቢ እውነትን ይዞ  ከሚሄደው ከልቡ የሚወጣ የሕይወት ቃል ነው።
አንደበት ትንሽ ሆና ሳለ ታላላቅ ነገሮችን የምትሰራ ቀላላ ሆና ሳለ ከበባድ ክንውኖችን የምታከናውን ሃያል ናት። ክብርም የምናገኝበት ውርደትም የምንቀበልበት በጎ የምንሰራበትም ክፉም የምናደርግበት ጽድቅና ሐጥያትም የሚከናወንባት ሕይወትንም ሞትንም የምናስተናግድበት በአንደበት ነው። ልብ ያቀናውን አንደበት ያወጣዋል… ልብ ያጠመመውን አንደበት ይገልጸዋል። ልብ ያሰበውም አንደበት ይናገረዋል።

ኤዶምንና ማህሌትን ብቻ ሳይሆን የ45 ሚሊዮን ሴቶች ክብርን ነው ያቀለሉት – ግርማ ካሳ

edom Jpurnalist
ኤዶም ካሳዬ ጋዜጠኛ ናት። ማህሌት ፈንታሁን ደግሞ «ሰለሚያገባን እንጦምራለን» በሚል የአለም አቀፍም ሆነ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት በሚፈቅድላቸው መሰረት፣ ብሎግ ከሚያደርጉ ዞን ዘጠኞች አንዷ ናት። ኤዴሞም ሆነ ማህሌት የጻፉት፣ የተናገሩት የተደበቀም ሆነ የተሸፈነ ነገር የለም። ለፍትህ ከመቆማቸው በቀር ያጠፉት ጥፋት የለም። ወንጀላቸው አገራቸውን መዉደዳቸው ነው። ሆኖም ሕወሃት «ሽብርተኞች» ብሎ ካሰራቸው ይኸው አንድ አመት ሆናቸው። ቢያንስ ከ27 ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት ተመላልሰዋል። አስቡት በአንድ አመት ዉስጥ ቢያንስ 27 ጊዜ !!!!!
የአገሪቷ ሕገ መንግስት በማረሚያ ቤት ያሉ እስረኞች በምን መልኩ መያዝ እንዳለባቸው በግልጽ አስቀምጧል። በአንቀጽ 19 ንኡስ አንቀጽ አንድ ላይ፣ እያንዳንዱ ዜጋ ፣ እስረኞችን ጨምሮ፣ ኢሰብአዊ ፣ ጭካኔ የተሞላባቸዉና ክብርን የሚነኩ ቅጣቶች ሊቀበል እንደማይገባ ያስቀምጣል። ሆኖም ረእቡ ሚያዚያ 14 ቀን፣ የአዲስ አበባ ሰልፈኞች እንዳሉት፣ ለሕወሃት ሕገ መንግስቱ ወረቀት ብቻ ነው።

የሰማዕታቱ ሰማዕትነት ለቤተ መንግስቱ እና ቤተ ክህነቱ የመጨረሻው የማስጠንቀቅያ ደወል ነው

cherkos addis ababa
ከጌታቸው በቀለ
(የጉዳያችን ልዩ ማስታወሻ)
ለሰማዕታቱ ለቅሶ አዲስ አበባ
ያለፈው ሳምንት እሁድ ለኢትዮጵያውያን እና ለመላው ዓለም አእምሮ የሚነሳ ግፍ ተፈፀመ። በአክራሪው አይ ኤስ ኤስ ስል ቢላዋ እና የጥይት አረር ሰላሳ ኢትዮያውያን ክርስቲያኖች ሊብያ ውስጥ ሰማዕትነት ተቀበሉ።ይህ መላው ዓለምን ያስደነገጠ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ቀልብ አስቶ ያስለቀሰ ጉዳይ ሌላ ሃዘን ተጨመረበት።ይሄውም ድርጊቱ ለመላው ዓለም የዜና አውታሮች በተለቀቀበት ሚያዝያ የሰንበት እለት ምሽት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገር ውስጡ ኢቲቪ ዜና ላይ ስለ ስማዕታቱ ለማየት እና የመንግስት የጉዳዩን አተያይ፣ቀጥሎም ስለሚወሰዱ እርምጃዎች ይናገራል ተብሎ ሲጠበቅ የዕለቱ የመጀመርያ ዜና ሳይሆን ቀረ።ኢቲቪ የቱርክን ውለታ በቀዳሚ ዜናነት በጨርቃ ጨርቅ ምርት እያደረገች ያለችውን፣

“ሞት የዘመኑ ዕለት እንጅ የመነኑ ዕለት አይደለም” – ከበልጂግ አሊ

“ከመሸ ተነሳሁ ከተፈታ በሬ፣ እደርስ አይመስለኝም ከእንግዲህ ሃገሬ።“ አገኘሁ እንግዳ ጀርመን ፍራንክፈርት በሚገኘው የመድኃኒዓለም ቤተክርስትያን ውስጥ በሊቢያ ለተሰው ዜጎቻችን ጸሎተ-ፍትሃትና ከዛም ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ ተገኝቼ ነበር። በደቡብ አፍሪካም ይሁን በሊቢያ በደረሰው ችግር ሁላችንም ሃዘን ገብቶናል።

ብሔራዊ ባንክን በማጭበርበር 25 ዓመታት የተፈረደበት ግለሰብ ቅጣቱ ተሰርዞ ክሱ እንደገና እንዲጀመር ተወሰነ

ቁርጥራጭ ብረቶችን ወርቅ በማስመሰል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ከ95.5 ሚሊዮን ብር በላይ አጭበርብሮ ተሰውሯል ተብሎ በሌለበት 25 ዓመታት ጽኑ እስራትና 180 ሺሕ ብር የተፈረደበት አቶ አስማረ አያሌው፣ የቅጣት ውሳኔው ተሰርዞ ክሱ እንደ አዲስ እንዲጀምር ተወሰነ፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዝያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ውሳኔውን ያሳለፈው፣ ግለሰቡ ‹‹በሌለሁበትና ባልተከራከርኩበት ይኼንን ያህል የእስራት ቅጣት ሊወስንብኝ አይችልም፤›› ብሎ በመከራከሩ ነው፡፡

የሳንቲም የመሰብሰቡ ተቃውሞ ስኬታማ በሆነ መልኩ እንደቀጠለ ነው

ረቡእ ሚያዝያ 21/2007 ህዝበ ሙስሊሙ ሀይማኖታዊና ህገ መንግስታዊ መብቶቹ እንዲከበሩለት ቢጠይቅም አሁንም ድረስ ከመንግስት ጠብ ያለ መልካም ምላሽ አላገኘም፡፡ እንዲያውም ከወትሮው በለየለት መልኩ መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እየፈፀመ ያለው ጭቆና ፍጥጥ ባለ ሁኔታ ተባብሶ የቀጠለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጋር የሚያገናኛቸው ሥውር መስመር እንኳ የሌላቸውን ዓለም አቅፍ ክስተቶች ሁሉ እየጎተተ ለዚሁ የጭቆናው ጉዞው ተጨማሪ መንደርደሪያ ማድረግን መርጧል፡፡ ይህም ሆነ በዚህ የበደል ደመና ባጠለለበት ድባብ ውስጥም ግን የመንግስትን መጠነ ሰፊ ጭቆና በመቋቋም ህዝባዊ ተሳትፎን በሚያረጋግጡ፣የመነቃቃትን ስሜት በሚፈጥሩ፣ ከአደጋ ነፃ በሆነ ክልል ውስጥ በተቀመሩና ለቀጣይ መጠነ ሰፊ ትግሎች መስፈንጠሪያ በሚሆኑ የትግል ስልቶች በአዲስ የትግል ምህዋር ላይ ትግላችንን አጠናክረን ቀጥለናል፤ አልሐምዱሊላህ! አሁን ላይ እየተገበርነው ያለነው የሳንቲም ማሰባሰብ መርሃ ግብርም የዚህ ተቃውሟችን አዲስ ምእራፍ አካል ነው፡፡

Monday, April 27, 2015

ባለቤት ያጣ ትውልድ እንደ በግ ሲታረድ – በዲያስፓራ የዓረና ትግራይ ድጋፍ ከሚቴ የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

በተወለዱባትና እትብታቸውን በተቀበረባት እናት ምድር ላይ እንደ ሰብኣዊ ፍጡር – እንደ ዜጋ በነፃነታቸው፣ በማንነታቸውና በኢት}ዮያዊነታቸው ኮርቶውና አልሞቶው በሰላም የመኖር አማራጭ ያጡና ተስፋው የጨለመባቸው ወገኖቻችን ሳይወዱ በግድ ስደት በመምረጥ መድረሻ አጥተው ሲንከራተቱና የሞት ፅዋን ሲቀበሉ የሚያሳይ በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪቃ፣ በሜዲተራኒያን ባህርና በየመን አካባቢ የደረሰባቸውን ዘግናኝና ልብ ሰባሪ ዜና ስንመለከት በዘመናችን ታይቶ የማይታወቅ እጅግ አስደንጋጭ በመሆኑ በጣም አዝነናል ተቆጥተናልም::
ኢትዮ}ያ ለዘመናት የነፃነት፣ የኩሩ ህዝብና የጀግና ሀገር ተምሳሌት እየተባለች በዓለም ማሕበረሰብ ዘንድ ወርቃማ ታሪክ ይዛ ተከብራና ታፍራ እንዳልቆየች ሁሉ ዛሬ ግን ገፀ ባህሪዋንና የነፃነት ድባብዋን በሀዘን ጨለማ ተቀይሮ ረሃብ፣ ስደት፣ ሞት፣ ውርደትና እልቂት የነገሠባት፣ ባለቤት ያጣች፣ የልቅሶና የዋይታ ምድር ሆና ስናያት በጣም ያሳዝነናል:: ይቆጨናልም::

የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የሴቶች ድርጅት አጭር መግለጫ

ላለፉት ሃያ አራት ዓመታት ያለ ኢትዮጵያዊ መንግስት የኖረው ሕዝባችን፣ በወያኔ/ የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር ሁለንተናዊ ጥቃት፣ሞት እና ስደት ሲፈራረቁበት ኖሮአል። በአገሩ የመኖር ተስፋ በማጣቱ ፣ሰብዓዊ መብቱ ተጥሶ በውርደት እንዲኖር በመገደዱ የተነሳ ወጣቱ ትውልድ ስደትን እንደ አማራጭ እንዲወስድ በረቀቀ መንገድ ተገዷል። ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ በሳውዲ አረቢያ፣ በየመን ፤በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በተፈጸመው ኢሰብዓዊ ተጋባርና አሰቃቂ ግድያ ጥልቅና ከባድ ሃዘን ተሰምቶናል አስቆጥቶናልም።

“የችግሩ መሰረታዊ ምንጭና መፍትሔው ፓለቲካዊ ነው’!! አቶ ኤርምያስ ለገሰ

daniel ermiasሰሞኑን በኢትዬጲያውያን ላይ የመከራ ዶፍ እየዘነበ ነው። ይህ የድቅድቅ ጨለማ ናዳ ባስከተለው አደጋ የተፈጠረው ቁጭትና መብከንከን ከቃላት በላይ ሆኗል። በኢትዬጲያውያን ዘንድ ከዚህ ውጭ የመተከዣ አጀንዳ ያለ አይመስልም። እንባ እንደ ጐርፍ እየወረደ ነው። የእናቶቻችን ደረት በእሳት የተለበለበ እስኪመስል ድረስ እየተደለቀ ነው። ወጣቶቻችን ከአረመኔዎች ጋር ግብግብ እየገጠሙ ነው። በመንገድ፣ በትራንስፓርት፣ በምግብ ቤት፣ በስራና በተለያየ አጋጣሚ የምናገኛቸው የባእድ አገር ሰዎች ሳይቀር የሀዘናችን ተካፋዬች መሆናቸውን እየነገሩን ነው። ነግረውን ብቻ አያቆሙም ። አያይዘው ፣
“ችግሩ ለምን እናንተ ኢትዬጲያውያን ላይ ባሰ?፣ ሀገራችሁን ትታችሁ ስደትን ለምን እንደ አማራጭ ወሰዳችሁ? ለምን እንደ ጨው ዘር ትበተናላችሁ?፣

ኳስ ጨዋታና ፖለቲካ (ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ)

ማስታወሻ፤
getachew
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማርያም የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አገዛዝ አለመጠቀሙን ለማሳየት ኢትዮሜዲያ ላይ አንድ ጽሑፍ አውጥቶ ነበር። ይህ የኔ ድርሰት የዚያ ተቃራኒው አስተያየት ስለሆነ መውጣት የሚገባው፥ እዚያው ኢትዮሜዲያ ላይ ነበር። ግን የኢትዮሜዲያ ባለቤት “በዚህ ድርሰትህ የትግራይን ሕዝብና ሕወሐት/ኢሕአዴግን አንድ አድርገሃቸዋል (“. . . TPLF a synonym with the Tigrai people.”) ብሎ ሊያወጣው አልፈቀደም። በእኔ አስተሳሰብ ይኸ ድርሰት ወያኔንና የትግራይን ሕዝብ አንድ አያደርግም። —-ሙሉውን ጋዜጣ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ 

“[ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቢያ ስለተሰውት ሰማዕታት ያወጣው መግለጫ] የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም” – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት
የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ አየሁት፡፡ መጀመሪያ ነገር ቋሚ ሲኖዶሱ ተሰብስቦ መክሮበታል ብዬ ለማመን ይቸግረኛል፡፡ የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም፡፡ ለመሆኑ ለሰማዕታት የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አጥታችሁ ነው? ይበልጥ ያስገረመኝ ደግሞ የሰማዕታቱ ዜግነት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምን እንደሚጠቅማት ነው፡፡ መንግሥት የዜግነትን ጉዳይ ቢያነሣ ኃላፊነቱ በዜጎቹ ላይ የተወሰነ ስለሆነ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን ‹መልዕልተ ኩሉ› የተባለቺውን ዘንግታው ነው የዜግነት ጉዳይ ያሳሰባት? ምንም ኢትዮጵያዊነታቸው የማያጠራጥር ቢሆንም፣ ጠላታቸው እንኳን የመሰከረላቸው ቢሆንም፣ ዓለም ያወቃቸው ቢሆንም፣ ለቤተ ክርስቲያን ግን ሱዳኖችም ሆኑ ሩዋንዳዎች፣ ሶማልያዎችም ሆኑ ጅቡቲዎች የተሠውትኮ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን የሰማዕትነት ክብሩ የሞተለት ክርስቲያናዊ ምክንያት ነው፡፡ የሞቱት ደግሞ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡

የሃዘኑ ድባብ በዱላ ታጅቦ… ክንፉ አሰፋ

የሃዘኑ ድባብ ከመብራቱ መቆራረጥ ጋር ተዳምሮ ጨለማውን አብሶታል። የአሁኑ መብራት መቋረጥ ግን ከወትሮ ፈረቃ ለየት ያለ ነው። ሆን ተብሎ የተደረገ ይመስላል። ከጥቂት ስፍራ በስተቀር ሁሉም ቦታ በአንዴ እንዲጠፋ ነው የተደረገው። ከሬድዋን  ሁሴን እና ከሃይለማርያም የቴሌቭሽን ዲስኩር በኋላ ሃገሩ ሁሉ ጨለማ እንዲሆን አደረጉ። ይህንን ለማድረግም በቂ ምክንያት ነበራቸው። ሃዘን ያልወጣለት ህዝብ አደባባይ ወጥቶ በአረመኔ ወታደሮች ሲቀጠቀት በማህበራዊ ድረ-ገጽ እንዲታይ አልተፈለገም።  ህዝቡ እርስበርስ መረጃ እንዲለዋወጥ መፍቀዱም አደጋ አለው። ስልኩም ጠፋ!
TPLf 3
          ለጥቂት ጉልበተኞች ግን ይህ መብራት ከቶውንም አይጠፋም። ግዜው እስኪደርስ፣ የሚመኩበት ጉልበታቸው እስኪፈታ ድረስ ይበራል። እስከዚያው ብዙሃኑ በጨለማ ይኖራሉ። 
          የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ግን ከቴድሮስ አድሃኖም ጋር ትንሽ የሚጣረዝ ይመስላል። ድህነታችን ለስደት እንደዳረገን ነበር ሃይለማርያም በአደባባይ ይናገሩ የነበረው። ተሳስተው ነው? ወይንስ በጥድፍያው ምክንያት አልተናበቡ ይሆን? ልማታዊ መንግስት ድህነት የምትለዋን አይጠቀምም።  ቴዎድሮስ አድሃኖም ግን በፌስ ቡክ ገጻቸው  “ሁላችንም ወያኔ ነን” አዎ አሁንም ሁላችንም ወያኔን ነን። ወያኔነት ልማት፣ ኩራትና ዴሞክራሲ ነው።..ይህን ችግር የሚፈታውም ወያኔነት ነው!” ብለውናል። በመስቀል አደባባይ ወታደራቸውን አሰልፈው የሰላማዊውን ህዝብ ሃዘን በወያኔነት ሲመልሱትም አሳዩን።  በሊቢያ፣ በየመን እና በደቡብ አፍሪካ በሰቆቃ ያሉ ወገኖች የሚሉትንም እየሰማን ነው። “የኛ የምንለው መንግስት የለንም! … ጨለማ ውስጥ ሆነን እየጸለይን ነው።”  ይህ ነው የወያኔነት ወጤት።   
          አቶ ሃይለማርያም ተሳስተው አንድ እውነት ተናገሩ። አንድ ነገር ቢጨምሩበት ጥሩ ነበር። ለስደቱ መንስኤ የፍትሃዊ ስርዓት እና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል መጥፋቱ መሆኑን። ለማንኘውም በውስጥ ግምገማ ላይ ይህችን ለምን እንደተናገሩ ያስረዱ ይሆናል።
          ለሃዘን የወጣ ህዝብ በአረመኔ ወታደሮች ሲቀጠቀት ሮይተርስ ከአዲስ አበባ አሳይቶናል። ዜጎች ሲቀጠቀጡ የሚያሳዩ የቪድዮ ምስሎች በማህበራዊ ድረ-ገሶች በስፋት ተበትነዋልል። ሬድዋን ሁሴን ግን ወታደሮቹ አንድም ሰው እንዳልነኩ ነገሩን። ታድያ ዥጉርጉሩን የፌዴራል ልብስ ያጠለቀ አይሲስ ነበር እንዴ በመስቀል አደባባይ ህዝቡን ሲያሸብር የነበረው?  ሃፍረት ያልፈጠረባቸው፤ የሰብአዊ ፍጡር ህሊና የሌላቸው ውሸታሞች ናቸውና ይህን ማለታቸው አይደንቅም።  ኢውሮ ኒውስ ከአዲስ አበባ በቀጥታ ያሳይ የነበረው ትእይንት ዘግናኝ ነበር። አይሲስ በንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸመውን የማይተናነስ ጭካኔ አሳዩን። ህጻን፤ ሴትና አዛውንት እንኳን ሳይለዩ ሁሉንም በጭካኔ ቀጠቀጡ።  የህዝብ ወገን ቢሆኑ በወገን፤ ለዚያውም በሃዘን ላይ ያለ ህዝብ ላይ እንዲህ አይጨክኑም። በእውነቱ ባእዳንም እንዲህ ባዘነ ህዝብ ላይ አይጨክኑም።  የ97ቱን ሰቆቃ አስታወሱን።   
          የታፈነው ህዝብ በአንድ ላይ ሆኖ ብሶቱን ሲገልጽ ሰማን።  ሬድዋን ሁሴን እንደሚሉት ከዚህ ረብሽ ጀርባ ሰማያዊ ፓርቲ አለበት። ከጨርቆስ እስከ ፈረንሳይ ለጋሲዮን፣ ከቦሌ እስከ ኮልፌ፤  ከዘነበወርቅ እስከ ሽሮ ሜዳ … ያለ  ህዝብ ሁሉ ሰማያዊ ፓርቲ ከሆነ ህዝብ ከናንተ ጋር አይደለምና ስልጣኑን ለሰማያዊ ፓርቲ ማስረከብ ነው ያለባቸው። አይገባቸው ይሆናል እንጂ በተዘዋዋሪ እየነገሩን ያሉት ህዝብ በሙሉ እንደጠላቸው ነው። ጥቂት ያሉትንም የህዝብ ቁጥር በምስል አየነው።

ሕገ ወጥ ጎብኚ እንጅ ሕገ ወጥ ስደተኛ የለም!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ስደት ሕዝባችንን ከቀየው እያፈናቀለ በአራቱም መዓዝናተ ዓለም ማንከራተት ማንቀዋለል ማንገላታት ከጀመረ አራት ዐሥርት ዓመታት ሞላ፡፡ በደርግ ጊዜ ከተሰደዱት በዘመነ ወያኔ የተሰደዱት እኅት ወንድሞቻችን እናት አባቶቻችን እጅግ ይበዛሉ፡፡ ስደተኛ ወገኖቻችን በየተሰደዱበት ሀገር እንደሰው ታይተው የሰውነት ክብር የተነፈጋቸውና ብሔራዊ ክብራችን የወደቀው የተደፈረው የተዋረደው በዘመነ ወያኔ ነው፡፡ የሚገርመው ወያኔም ያው ቢሆንም ጨፍጫፊ የምንለው ደርግ “የዜጎች መዋረድ መደፈር የሀገር መዋረድ መደፈር ወይም ብሔራዊ ውርደት ነው” የሚል እንደ መንግሥት ከአንድ መንግሥት የሚጠበቅ ጠንካራ አቋም ስለነበረው ሌላው ቀርቶ ሊገላቸው የሚፈልጋቸው ተቃዋሚዎቹ አምልጠው በስደት ባሉባቸው የጎረቤት ሀገራት ችግርና እንግልት ሲገጥማቸው ለያሉበት ሀገር መንግሥት ከባድ ማስጠንቀቂያ በመስጠት መብቶቻቸው እንዲጠበቅ ያደርግ ነበር፡፡ በዘመነ ወያኔ ግን የሀገራችንና የዜጎች ክብርና ሞገስ እጅግ በሚያስደነግጥ እጅግ በሚያሳዝን እጅግ በሚያሳፍር ደረጃ በመውደቁ የሀገራችንና የዜጎቿ ክብርና ሞገስ የትም ቦታ በማንም ምናምንቴ ሁሉ የሚደፈር የሚረገጥ መጫወቻ መቀለጃ ለመሆን በቅቷል፡፡

የት ሄደን እናልቅስ ?

yilikal
የት ሄደን እናልቅስ
የት ሆነን እንተንፍሰ
የወንድሞቼን ደም የት ሄጄ ልመልስ
ሀገር ነበር እኮ ሁሉንም ማስረሻ
ሀዘን ይሁን ስጋት ከሁሉ መሸሻ
ወንድሜ ሲቃጠል በሳውዝ አፍሪካ ላይ
ስጋዬ ቢታረድ በሊብያ ምድር ላይ
እህቴንም ባጣት በዛ በየመን ላይ
ሀዘኔ ቢበዛ ውስጤ ቢቆስልብኝ
መንግስት እንደሌለው ማንም ሲገልብኝ
ምንም እንኳን ባጣ ሄዶ ሚያተርፍልኝ
ደርሶ ሚያስጥልልኝ
እኔው ተነሳሁኝ እህህ ልለው
ሀዘኔን ቁጭቴን ሁሉን ላሳውቀው
አቅሜም እንኩዋን ባልችል ባልሆን ከጎናቸው
ሀዘኔን በሀገሬ ፍቅሬን ላሳያቸው
ሆ ብዬ ተነሳው በኢትዮጵያ ምድር ላይ

በአይሲስ የተጣሰው የቁርአን ቃል – “ሙስሊም ባልሆኑ ንፁሃን ሰዎች ላይ ግድያ የፈፀመ ሰው የጀነትን እጣን አያሸትም”

ኑርሁሴን እንድሪስ
በሁለቱ ታላላቅ እምነቶች ውስጥ (ክርስትና እና እስልምናን ማለቴ ነው) ለሰው ዘር በሙሉ የተላለፈ አንድ መለኮታዊ መልዕክት አለ፡፡ ይህ መልዕክት በሁለት ቅዱሳን መፃህፍት ውስጥ ቢገኝም መልዕክቱ ግን ተመሳሳይ ነው፡፡ የሰው ልጅን ነፍስ ማጥፋት የተወገዘ ተግባር መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ እና ቁርአን ያወሳሉ፡፡ ይህን መልዕክት ለሰው ልጆች የላከው ደግሞ የሰማይና የምድር ፈጣሪ እንዲሁም የሰው ልጆችን ጨምሮ በሁለቱ መካከል ያሉትን በሙሉ ያስገኘው አምላክ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ምዕራፎቹ ውስጥ የሰው ልጅ ግድያን ይከለክላል፡፡ በማቲዎስ 5፡21፣ ምፅአት 20፡13፣ ሮሜ 13፡14፣ ዘፍጥረት 9፡5-6 … ወዘተ፤ በጣም ብዙ አንቀፆች ሰውን መግደል የማይፈቀድ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በማቲዎስ 5፡21 ውስጥ የሰፈረው ቃል እንዲህ ይላል፡-

“ልጄ! እንኳን አንተ፤ እኔም ባልተወለድኩ!” – የንጎቻው

…. ስሙን ሞት ይጥራውና እንኳን በአንደበቴ በህሊናዬ ሲንከላወስ እጅጉን የሚኰሰኩሰኝ ያ! መናጢ፤አናጢ፤ ግምበኛ፤አትክልተኛ ነኝ’ ባይ ‘መጤ’ ‘የቀን ሠራተኛ’ ለካስ ዋናው ሙያው ‘የጨለማ ሠራተኛ’ ኖሮ ወያኔዎች ኢትዮጵያን ወረው መዲናንችንን ሲቆርጣጠሩ ይኸ ‘እንግዳ ሰው’ ከምንጊዜው እንደ እስስት ተቀያይሮ፤ የቀን ቱታውን አውልቆ፤ዪኒፎርሙን ጠርንቆ፤መትረየሱን ታጥቆ ሰፈራችንን ፊታውራሪ ሆኖ ሲያምሰን፤ ሲያተራምሰን ከረመ። አይ እኛ! ምንኛ ተላላዎች፤ሰው አማኞች፤ የዋሆችም ኖረናል።

የታሰርኩ ለታ ‹‹ለሁለት አመት ያላየሁትን ጓደኛዬን ላገኘው ቀጠሮ ነበረኝ›› በፍቃዱ ኃይሉ

እኔ እና አጥኔክስ 10፡45 አካባቢ ከቀነኒሳ ሆቴል እየወጣን ነበር፣ ያን ቀን አብረን ነው የዋልነው፡፡ መንገድ ላይ እንዳለን ስልክ ተደውሎ ማሂ በፖሊሶች መያዟን ሰማን፡፡ ወዲያው የማሂን መያዝ በተመለከተ ቲዊት ላደርግ ስልኬን ስነካካ የማላውቃቸው ሰዎች ሁለታችንንም ከበቡን፤ ስልካችንና ላፕቶፓችንንም ነጠቁን፡፡ ምንም አይነት የተለየ እንቅስቃሴ አላደረግንም፡፡ ዙሪያ ገባየን ሳይ ሰው የተለመደ እንቅስቃሴውን ቀጥሏል፡፡
(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)
(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)

የሚገርመው ለሁለት አመታት ያህል አግኝቼው የማላውቀው ጓደኛዬ ጋር ቀጠሮ ስለነበረኝ ወደዚያ እየሄድኩ ነበር፡፡ ከጓደኛየ ጋር ብዙ ጊዜ ለመገናኘት ፈልገን አልመችህ ሲለን ረጅም ጊዜ ሳንገናኝ ቆየን፡፡ በዛ ዕለትም ሳላገኘው ወደእስር ተጋዝኩኝ፡፡ የነጠቁኝ ስልክ በተደጋጋሚ ሲደወል እና መልዕክት ሲገባ ይሰማኛል፡፡ የቀጠርኩት ጓደኛየ ይሆናል እያልኩ አስባለሁ፡፡

(የሊቢያው እልቂት ጉዳይ) እኛ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ነን!!

አፈንዲ ሙተቂ
ISIL የሚባለው ሰይጣናዊ ቡድን በምድረ ሊቢያ በዜጎቻችን ላይ የፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊት ያስቆጣኝ በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመሪያው ምክንያቴ በጥይት የተረሸነውና በስለት የታረደው ኢትዮጵያዊ ወንድሜ መሆኑ ነው፡፡ አዎን!! “ዘወትር በድህነት ከምንገላታ ወደ ውጪ ሄጄ ዕድሌን ብሞክር ይሻላል” በሚል የሃሳብ ምጥ ተነሳስቶ በምድረ ሊቢያ በኩል ወደ አውሮጳ ለመሻገር ሲሞክር በአረመኔው ቡድን የተያዘው ወገኔ ደም በረሃ አሸዋ ላይ እንደ ጎርፍ መፍሰሱ በእጅጉ ያንገበግበኛል!! ያስቆጣኛል!! ያስቆጨኛል!! ከአስከፊው የሰሃራ በረሃ የውሃ ጥም እና የሞት መልዕክተኛ ከሆነው የሜዲትራኒያን ባህር ጉዞ ተርፎ ወደ ማልታና ኢጣሊያ መድረሱ እንኳ እያሳሰበኝ ሳለ ከሁለቱ ሰይጣኖች በሺህ እጥፍ የሚብሰው ISIL የተባለ ሶስተኛ ሰይጣን በሊቢያ ምድር ላይ ወገኔን ጠልፎ እንደ በግ አጋድሞት ሲያርደው ማየቱ ይቅርና መስማቱ ራሱ ሲቃው የማይቻል ህመም ነው የሆነብኝ፡፡ የፈሰሰው ክቡር የሆነው የወገኔ ደም ነውና ስለርሱ ሞት እኔ ታምሜአለሁ (ብታምኑም ባታምኑም ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ የምርምር ስራዬን አቁሜአለሁ፤ እንኳንም የቢሮ ሰራተኛ አልሆንኩ)!!

መከራችን መፍትሄ ሳያገኝና ሃዘናችንም ሳይበርድልን ሌላ ከባድ መርዶ ከወደ ሊቢያ ተሰማ

ከአብርሃም ተፈሪ (ሚኒሶታ)
ወዳጆች በቅድሚያ በያላችሁበት የከበረ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ!
ከዚህ ቀጥሎ የምታነቧት አጭር ጽሁፍ በስራ ገበታየ ላይ ሳለሁ በሃሳብ ወዲህ ወዲያ ስባዝን የሞነጫጨርኳት ሰሞንኛ ማስታወሻ ነች።
Abreham D
ሰሞኑን በኛ ኢትዮጵያኖች ላይ የደረሰብንን የሃዘን ማእበል እንዲህ ነው ብሎ ለመግለጽ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው። በደረሰብን ሃዘን ምክንያት ሁላችንም ልባችን ተሰብሯል ውስጣችንም በቁጭት ተቃጥሎ አሯል። የመን ውስጥ በጦርነት መሃል እየተሰቃዩና እየተገደሉ ስላሉ ወገኖቻችን አዝነን ምን ብናደርግ ይሻላል እያልን እየተወያየን ባለንበት ሁኔታ ሌላ አሰቃቂና ጥላቻን መሰረት ያደረገ ኢ-ሰብዐዊ ድርጊት ከደቡብ አፍሪቃ ተሰማ። በደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ከሃገራቸው ኢትዮጵያ በተለያየ ምክንያት ተሰደው በሰው ሃገር ደከመኝ ሳይሉ ቀን ከሌት ሰርተው በላባቸው የሚኖሩ መሆናቸውን ቀናው የሃገሬው ህዝብ የመሰከረበት የአደባባይ እውነት ነው።

መሰረዝ ያለበት አስደንጋጭ እቅድ – ግርማ ካሳ

“መንግስት በሊቢያ በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ሰፋፊ ሰራዎችን ለመስራት በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ቴድሮስ በቤንጋዚ ያሉ ኢትዮጵያውያን በግብጽ መንግሰት በኩል፣ ትሪፖሊ ያሉትን ደግሞ ከሱዳን መንግሰት ጋር በመተባበር ከሊቢያ ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።”  የሚል በዶር ቴድሮስ አዳኖም  ፌስ ቡክ ገጽ ላይ አነበብኩ።  የዝግጅቱን ዝርዝር ባላውቅም ዝግጅቶች  እየተደረጉ ሊሆኑ እንደሚችኑ ማንበቤ ትንሽም ቢሆን  ደስታ ሰጥቶኛል።

በሊቢያ ከአሥራ አምስት በላይ የሚሆኑ ኃይላት አሉ። እነዚህ ኃይላት እርስ በርስ እየተቀናጁ በዋናነት ሦስት ቡድኖች  ተፈጥረዋል። እነርሱም፡
መቀመጫዉን  ቱብሩክ (ወደ ግብጽ ድንብር የተጠጋች ከተማ) ያደረገው በጀነራል  ካሊፋ ሃፍተር የሚመራው ስብስብ ነው። ይህ ስብስብ ደርና ከምትባለዋና አይሰስ ከሚቆጣጠራት  ከተማ በስተቀር፣ አብዛኛዉ ቤንጋዚ ጨምሮ፣ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ያሉትን ግዛቶች ይቆጣጠራል። ይህ ስብስብ በአለም አቀፍ ማህበረሰብ እንደ ሕጋዊ የሊቢያ መንግስት  የሚቆጠር ሲሆን ከግብጽ መንግስት ጋር የቀረበ ግንኙነት አለው።

Thursday, April 23, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታድነው መታሰራቸው ታወቀ • 500 በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታስረዋል

self
(ነገረ ኢትዮጵያ) መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰልፈኛው ‹‹መንግስት በዜጎቻችን ላይ ለተፈፀመው አረመኔያዊ እርምጃ በቂ ምላሽ እየሰጠ አይደለም›› በሚል ባሰሙት ተቃውሞ በርካቶች ተደብደበው ከተሳሩና ሰልፉ ካበቃ በኋላ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው በሚል በርካቶች እየታደኑ መታሰራቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

እነርሱ አንገት የሰጡለትን ክርስትናእኛ ለመናገር ለምን ፈራነው?

በተለያዩ የባለ ሥልጣናትና የእምነትመሪዎች መግለጫዎች ላይ በሊቢያ ምድር የተሠዉትን ሰማዕታት በኢትዮጵያዊነታቸው ወይም በስደተኛነታቸው ብቻ አደጋ እንደደረሰባቸውተድርጎ እየተነገረ ነው፡፡ እነዚህ ክቡራን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የተሠዉትም እምነታቸውን አንለውጥም ስላሉ ነው፡፡አይሲስ የሠዋቸው በኢትዮጵያዊነታቸው አይደለም፡፡ አይሲስኮ ዜግነት የለውም፡፡ ዐረቦች፣ አውሮፓውያን፣ አፍሪካውያን እስያውያን የተቀላቀሉትአሸባሪና አሰቃቂ ድርጅትና አስተሳሰብ ነው፡፡ እንዲያውም ባለፈው ሰሞን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከእንግሊዝ ወደ አይሲስ ለመግባትያደረጉትን ጥረት በመገናኛ ብዙኃን ሰምተን ነበር፡፡ አይሲስ አገር የለውም፡፡

ሰበር ዜና ዛሬ ማታ በአዲስ አበባ ወያኔ ከየቤቱ ህዝቡን እያፈሰ ነው

IMG_5423
ከምሺቱ ፫ ሰሃት ጀምሮ በድፍን አዲስ አበባ አሸባሪው የወያኔ መንግስት መብራት በማጥፋት በ  በተገደሉት ወገኖቻችንና ለህዝቡ ግድ የሌለው የወያኔን ጉጂሌ በመቃወማቸው በዚህም የተበሳጨው የወያኔ መንግስት በለሊት ህዝቡን ከየቤቱ እያፈሰና በመኪና እያጋዘ ይገኛል ብዙ ወገኖቻችን ኣሁን ባደረሱኝ መረጃ መሰረት የከተማዋ መብራት በማጥፋት ልባቸው በሃዘን የተቃጠሉትን ወገኖቻችንን በጂምላ እያፈሰ ነው የትም እንዳደረሳቸው አልታወቀም ተብላል።

ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን ማራካሱን ቀጥሎበታል

ሳም ቮድ ሶን አንዳርጋቸው's photo.
ማምሻውን ፖሊሶችና ፌድራል ፖሊሶች ጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን ጉዳት የደረሰባቸው  ገለጹ
ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን በማርከስ ከዚህ ቀደም በገዳማት በመስጅዶች ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ ሲፈጸም መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለት በጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ድረስ በመዝለቅ ከፍተኛ ድብደባ መፈጸማቸውን በቦታው ላይ ድብደባ የተፈጸመባቸው  ገልጸዋል፡፡

ይህን ግለሰብ መመርመር ሳይኖርብን አይቀርም

Aseged Tamene's photo.Aseged Tamene's photo.
በሶሻል ሚዲያ (ፌስ ቡክ) Ahamab muhamad oromo የሚባል ሰው ከብሄር ጋር የተያያዙ ጠንከር ያሉ መልእክቶችን በአማርኛና በኦሮምኛ ሲያስተላልፍ ቆይቷል፡፡የኢትዮጵያን ባንዲራ ሲረግጥ የሚያሳይ የራሱን ምስልም በመለጠፍ ጥላቻውን ማሳየቱን ብዙዎች ያስታውሱታል፡፡
ግለሰቡ የፕሮፋይል ምስሉ የአሜሪካ መንትያ ህንጻዎች ሲጋዩ የሚያሰይ ፎቶ ግራፍ ካደረገም ረዘም ያሉ ግዜያት ተቆጥረው ነበር፡፡
ወንድሞቻችን በሜድትራንያን ባህር አካባቢ በአይ ኤስ አይ ኤሶች ግድያ ከተፈጸመባቸው በኋላም በታጣቂዎቹ እየተጎተቱ ሲወሰዱ የሚያሳይ ፎቶ ለጥፉበት ‹‹በኦሮምኛ ከአገራችን ውጡ››የሚል ጽሁፍ አስፍሮበታል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያቀረቡት አስቸኳይ ጥሪ

የተከበራችሁ ወገኖቼ፤ ከሰላሳ በላይ የሆኑ ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ከትናንት ወዲያ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓም ደርሶን ኢትዮጵያዊያን በያለንበት በመሪር ሀዘን ውስጥ ነን። ዛሬ “እግዜር ያጥናህ” ወይም “እግዜር ያጥናሽ” የሚባል ሰው የለም። ሁላችንም ሀዘንተኞች ነን። ካጣናቸው ቁጥራቸው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ወገኖቻችን አሁንም በአራዶች መዳፍ ውስጥ መሆናቸው ሀዘናችን እጅግ የበረታ ያደረገዋል። ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ ሆኖም በሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም ሊቢያ ውስጥ ናቸው። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሁንም ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ናቸው። ሌሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ደግሞ በየመን ከሰማይም ከምድርም በቦንብና በጥይት እየተማገዱ ነው።

Wednesday, April 22, 2015

መንግስት በአ.አ የጠራው ሰልፍ ወደ ተቃውሞ ተለወጠ * ሴቶች እና አዛውንቶችን ሳይቀር ደብደበ * አስለቃሽ ጭስ ተተኮሰ * የሕዝቡ ቁጣ አልበረደም

የአይ ኤስ አይ ኤስን ጭካኔ ለመቃወም ሰልፍ የወጡ ኢትዮጵያውያን አገራቸው ውስጥ ሌላ ጭካኔ ገጥሟቸዋል

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ለፖለቲካ ጥቅም ማግኛ ሲል የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ተቃውሞ ተለወጠ:: ማንኛውም ሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያደርግ የሚከለከለው ኢሕአዴግ ሕዝብን ወዳጅ መስሎ ቢቀርብም በመስቀል አደባባይ ዳግም ሕዝብን በመደብደብ ዳግም ራሱን ማዋረዱን ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ አመልክቷል::

አይሲስን ለመቃውም አደባባይ የወጡት የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች፣ አመራሮችና አባላት ታሰሩ

addia ababa
(ነገረ ኢትዮጵያ) ዛሬ መንግስት በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ በርካታ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት፣ አመራሮችና እጩዎች ታስረዋል፡፡ ሰልፉን ለመቀላቀል በጠዋቱ ወደ መስቀል አደባባይ በማቅናት ላይ የነበረችው ወይንሸት ሞላ ሰልፉ ላይ ሳትደርስ የታሰረች ሲሆን አሁን የት እንዳለች አልታወቀም፡፡

የሻማ ማብራት እና የጸሎት ጥሪ በአትላንታ እና አካባቢው ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች (ፍላየር)

የሻማ ማብራት እና የጸሎት ጥሪ በአትላንታ እና አካባቢው ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች (ፍላየር)
atlanta

ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ወንድሞቼን አሳልፌ አልሰጥም በሚል በአይሲኤል ሕይወቱን ያጣው ጀማል ራህማን

በሙስሊም ወገኖቻችን ኮራን
አበበ ገላው እንደጻፈው:-
ISIL
አረመኔዎቹ ወያኔዎች ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ከISIS ጋር የተሰለፉ ለማስመሰል አደገኛ ፕሮፓጋንዳ በመርጨት ላይ ናቸው። ይሁንና እውነታው ሙስሊም ወገኖቻችን ክርስቲያን ወገኖቻቸውን ከእርድና ጥይት ለመታደግ መስዋእት እየሆኑ መሆኑን ተረጋግጧል። ክርስትያን ወንድሞቼን አሳልፌ ለሞት አልስጥም ብሎ አብሮ ከተሰውት ኢትዮጵያዊያን መሃል ወንድማችን ጀማል ራህማን ይገኝበታል። ክርስቲያን ወንድሞቹን ለማትረፍ ከአረመኔዎች ጋር ሲሟገት እራሱ ተሰዋ። በታሪክ ለዘላለም የሚዘከር ታላቅና ቅዱስ መሰዋእትነት!! ነፍስህ ለዘላለም በገነት ስለምትኖር ይማርክ ልንህ ልንልህ አይቻለንም።

Tuesday, April 21, 2015

ሰበር ዜና! ሰልፉ አዲስ አበባን ሲዞር ሊውል ነው! የኢቲቪ ጋዜጠኞች ተደበደቡ


rally-ethiopia
መንግስት ያሳየውን ቸልተኛነት ለመቃወም በአዲስ አበባ ህዝቡ ነቅሎ አደባባይ ወጥቷል።
‹‹ኢህአዴግ ሌባ ሌባ፣ ኢህአዴግ ሌባ ሌባ!››
‹‹ይለያል ዘንድሮ የኢህአዴግ ኑሮ! ይለያል ዘንድሮ የኢህአዴግ ኑሮ!..
ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ!››
እያለ መፈክር እያሰማ ነው!
ከደቂቃዎች በፊት የኢቲቪ/ ኢብኮ ጋዜጠኞች በለቀስተኞች መደብደባቸው ተሰምቷል፡፡ የኢትቪ /ኢብኮ ጋዜጠኞች ለቅሶ ቤት ውስጥ ቀረጻ አድርገው ሲመለሱ ‹‹ሌቦች እናንተ ልታስተላልፉት አይደለም፡፡ ስለ እኛ ምን አገባችሁ?›› ተብለው እንደተደበደቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሀሙስ ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን

 በመላው ኢትዬጵያ የስራ ማቆም አድማ ይደረጋል፣ ታክሲዎች በህብረት ስራ ያቆማሉ።
በአዲስአበባ፣ በአዳማ፣ ባህርዳር፣ በጐንደር፣ በአምቦ፣ በወለጋ፣ በደብረብርሃን፣ በደሴ፣ በአርባምንጭ፣ በአዋሳ፣ በሁሉም ቦታዎች።
በዜጐቻችን ላይ በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በየመን፣ በተለያዮ አረብ ሃገራት እየተደረገ ያለውን እናወግዛለን። የቤተክርስቲያን አገልጋዬች መዘምራን፣ ዲያቆናት፣ ቀሳውስት በሙሉ ይመለከተናል የምትሉ በሙሉ ቢቻል የቤተክርስቲያን መዘምራን የዘማሪ ልብሳችሁን ለብሳችሁ ውጡ። ክርስቲያኑ ባጠቃላይ በሁሉም ቤተክርስቲያኖች እና አገልግሎት ቦታዎች ከጠዋቱ 8 ሰአት ይሰባሰብ ከዛ ጉዞ ወደ አደባባይ ይደረጋል።

Monday, April 20, 2015

“አይማረኝ አልምራችሁም” ቦኮ ሃራም ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት

boko
ደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ዓመጽና ግድያ ቦኮ ሃራም የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ፡፡ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ግጭቱንና ግድያውን እንዲያስቆም ገደብ ሰጠ፡፡ “አይማረኝ አልምራችሁም” አዘል መልዕክት ማስተላለፉ ተገልጾዋል፡፡
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ያዕቆብ ዙማ ልጅ የውጭ አገር ዜጎች ከደቡብ አፍሪካ መባረር አለባቸው በማለት ከተናገረ በኋላ የተነሳው ዓመጽና አሰቃቂ ግድያ በርካታዎችን ያስደነገጠና ያስቆጣ ሆኗል፡፡ ከኤድዋርድ ዙማ በተጨማሪ የዙሉው ንጉሥ ተመሳሳይ ንግግር በማድረጋቸው አፍሪካውያን በአፍሪካውያን ላይ ለማመን የሚከብድ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ ታይተዋል፡፡

“ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንሞክራለን”

እንደ ሚዲያ ወይም እንደ ጋዜጠኛ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊ ፍጡር ይህን እንጽፋለን፡፡ እንደ ክርስቲያን ወይም እንደ ሙስሊም ሳይሆን እንደ አንድ ሰው ይህን እንናገራለን፡፡
ሰብዓዊነት ከሙያ በላይ ነው፡፡ ሰብዓዊነት ከሃይማኖት በላይ ነው፡፡ ሰብዓዊነት ከዘር በላይ ነው፡፡ ሰብዓዊነት ከምን ዓይነት መጠሪያ በላይ ነው፡፡
በሊቢያ የሚገኘው የአይሲስ ተወካይ ቡድን 30 ኢትዮጵያውያንን አረደ፤ በጥይት ረሸነ፡፡ የዓለም ዜና ማሰራጫዎች ዘገባውን አቀረቡ፤ ኢትዮጵያውያን መታረዳቸውን አወጁ፤ ዓለም ቪዲዮውን ተመለከተው፤ ዜናውን አነበበው፡፡ እኛም በሃዘንና በእንባ አንብበነዋል፤ ተመልክተነዋል፤ (ፎቶም ሆነ ቪዲዮውን እዚህ ላይ አንለጥፍም)፡፡

የምናዝነው ስንት ሰው ሲሞት ነው? ከዳንኤል ክብረት

በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ስለሚሞቱት ዜጎቻችን የሚሰጡት መንግሥታዊ መግለጫዎች ሁለት ነገር የጎደላቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ሰብአዊ ስሜት፡፡ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ስለሌላው ሰብአዊ ፍጡር መከራና ስቃይ ሲሰማ መጀመሪያ አንዳች የኀዘን ስሜት ይሰማዋል፡፡ ከዕውቀት ይልቅ ስሜት ለሰዎች ቅርብ ነውና፡፡ ባለሥልጣን ቢሆን፣ ፖሊስ ቢሆን፣ ዳኛ ቢሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆን ሰው ነውና ስሜት አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ያዝናል፣ ይከፋዋል፣ ልቡ ይረበሻል፣ ሆዱ ይባባል፣ ኅሊናው ይደማበታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህም የመጀመሪያው ሥራው ማዘን ቀጥሎም ኀዘኑን በወጉ መግለጥ ነው፡፡ 

Friday, April 17, 2015

የደቡብ አፍሪካው የስደተኛ ጠልነት መነሻው ምንድነው? (የሰባት ኪሎ ወቅታዊ አጭር ትንተና)

ethiopia south africa
ደቡብ አፍሪካን በቅርቡ የማይከታተሉ ሰዎችን በእጅጉ ያስደነገጠ ቢኾንም በአገሪቱ ስደተኞች ላይ ያነጣጠረ ኹከት ሲካሄድ የአሁኑ የመጀመርያው አይደለም። እ.ኤ.አ በግንቦት ወር 2008 አሌክሳንደር በተባለ የጆሃንስበርግ ታውንሺፕ የተነሳ ኹከት ወደ ደርባን እና ሌሎች ከተሞች ተዛምቶ ቢያንስ ለዐርባ ስደተኞች መሞት ምክንያት ኾኗል። በኹከቱ ብዙ ንብረት ወድሟል። ከዚያ በፊት እና በኋላም ቢኾን ሌሎች በርካታ አነስተኛ ጥፋቶች ተፈጽመዋል። ይህ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ነው “በጉርብትና የሚኖሩ ሰላማዊ ስደተኞችን በእንደዚህ ዐይነት ጭካኔ ማቃጠል፣ መግደል እና መደብደብ ለምን?” የሚለው ጥያቄ ተደጋግሞ ይነሳል። በደቡብ አፍሪካ እንዲህ ዐይነት ከፍተኛ የኾነ ስደተኛ ጠልነት ለምን ተስፋፋ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ምናልባትም ወደ አገሪቱ የመጀመርያዎቹ የዴሞክራሲ ዓመታት መለስ ብሎ መመልከት አስፈላጊ ነው።

በሰሜን ጎንደር የጦር መሳሪያ ሽያጭ መጧጧፉ ተሰማ

ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ ወረዳዎች የጦር መሳሪያ ሽያጭ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጧጡፎ በመሸጥ ላይ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
በአለፋ ፣ ጣቁሳ፣ መተማ፣ አርማጭሆ፣ ቋራና በሌሎችም በርካታ ወረዳዎች አንድ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ45 ሺ እስከ 60 ሺ ብር በመሸጥ ላይ ነው። የጦር መሳሪያዎችን በብዛት የሚገዙት አርሶ አደሮች ናቸው።

‹‹ጆሮ ዳባ ልበስ›› የተባለው የሠብዓዊ መብት ጥሰት!

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት፣ በነጋሪት ጋዜጣ ታውጆ፣ በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጠባቂነት ወጥቶ፣ በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፕሬዚዳንትነት ነሐሴ 15 ቀን 1987 ዓ.ም በ106 አንቀጾች መጽደቁ የሚታወስ ነው፡፡
መሻሻል አለባቸው የሚባሉ አንቀጾች እንዳሉ ሆነው፣ በሕገ መንግሥቱ ረቂቅ ላይ ሕዝብ በደንብ አለመወያየቱም ሳይዘነጋ፣ እኔን ጨምሮ ብዙ ኢትዮጵያውያን በሕገ-መንግሥቱ መጽደቅ እንስማማለን፡፡
የኢህአዴግ ሥርዓትም ይህ ሕገ-መንግሥት የህጎች ሁሉ የበላይ መሆኑን፣ የሐገሪቷን ብዙ ችግሮች መፍታቱን፣ ለኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች፣ ህዝቦች እኩልነት መሰረት መጣሉንና ሕገ-መንግሥቱም የግድ መከበር እንዳለበት …ወዘተ. ዘወትር አስረግጦ ይናገራል፣ ይገልጻል፡፡ ከመርህ አኳያ፣ ሕገ-መንግሥቱ መከበር እንዳለበት ብዙዎቻችን የምንስማማበት ሀቅ ነው፡፡

በርካቶችን ያስደነገጥ አሰቃቂ ወንጀል።

የሰው ልጅ ይህን አይነት ተግባር ያደርጋል ለማለት የሚያዳግት። የባህር ዳርን ህዝብ ያሳዘነ የወንጀል ተግባር።

“ልማትን» የሚደግፉ, ቦንድ እንዲገዛ የሚቀሰቅሱም ሽብርተኛ እየተባሉ ነው – ግርማ ካሳ


“ሕግን» በመጥቀስ, ሕግን እንደ ዱላ በመጠቀም ዜጎች ላይ ግፍ እየተፈጸመ ነው. በፍትህ ስም, የሚፈጸም ግፍ ደግሞ ሞቴንስኪዮ የሕግ መንፈስ በሚል መጽሐፉ እንደጻፈው, የግፎች ሁሉ ግፍ ነው. ሞቴንስኪዮ “There is no greater tyranny than That wooden perpetrated under the shield of the law and in the name of justice.” ሲል ነበር የጻፈው.
ኢሕአዴግ በዋናነት ዜጎችን ለማሰር እየተጠቀመበት ያለው ሕግ የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ ተብሎ የሚጠቀሰው ሕግ ነው. በዚህ ሕግ መሰረት በሌሎች አገራት እንደምናየው በሕዝብ ላይ በተግባር ጥፋት የፈጸሙ, ወይንም ሊፈጸሙ ሲሉ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሽብርተኞ የታሰሩበት ሁኔታ የለም. ይህ ሕግ ሽብርተኞችን ለመወጋት ያለመ ሳይሆን, ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ሕግ ነው. በዚህ ሕግ መሰረት ማንኛውም ዜጋ ማንኛውንም ነገር ካደረገ “ሽብርተኛ» ተብሎ ወደ ወህኒ መወርወር ይችላል. የታሰሩ ሰላማዊ ዜጎችን ማንነት, ምን ይሰሩ እንደነበረ በመመልከት ብቻ, የጸረ-ሽብርትኝነት ሕጉ መስመር እንደሳተ ማንም በቀላሉ ሊደመድም ይችላል.

በአብራሃ ጅራና ከሱዳን ጋር በሚዋሰኑ የጎንደር አካባቢዎች በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሱዳን ጦር ሰራዊት ተኩስ በመክፈት ጉዳት አደረሰ፡፡

ሀሙስ እለት ሚያዚያ 1 2007 ዓ.ም እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ የሱዳን ወታደሮች ድንበር ተሻግረው ከሱዳን ጋር ወደ ሚዋሰኑ የጎንደር መሬቶች በመግባት የአካባቢውን ህብረተሰብ በጦር መሳሪያ ወግተው ከገዛ አገሩ ለማፈናቀል በወሰዱት አርምጃ ሁለት ሰዎች ቆስለዋል፡፡ ቁስለኞቹ አንደኛው የአብደራፊ 01 ቀበሌና ሁለተኛው የሆሩመር ነዋሪዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡
በተጨማሪም የሱዳን ወታደሮች በርካታ የግል ባለሃብት ካምፖችንና የቁም እንስሳትን በእሳት አቃጥለዋል፡፡
የሱዳን ጦር ሰራዊት የኢትዮጵያን ሉኣላዊነት በመግሰስ ድንበሯን አልፎ በመግባት በዜጎቿ ላይ የተኩስ ውርጅብኝና በንብረት ላይ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በአካባቢው ሰፍሮ ከሚገኝ የህወሓት አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በመሆኑም የሱዳን ጦር ድንበር ሰብሮ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በአካባቢው ህዝብ ላይ ያሻውን ያደርግ ዘንድ ፈቃድ አግኝቷል፡፡

ህወሓት የዓረና ኣባላት ለማሸበር፤ከመቶ አስር ሺ በላይ ምልሻዎች ኣስታጠቀ

ህወሓት የዓረና ኣባላት ለማሸበር፤ ለማሰርና ለማሰቃየት ከ 110,000(ከመቶ አስር ሺ በላይ) ምልሻዎች ኣስታጥቋል፡፡ ዛሬ የኛ ኣባላት በደቡባዊ ትግራይ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በምልሻዎችና በካድሬዎች እየተሰደቡ…እየተንገላቱና መብታቸው እየተነፈጉ ነው የዋሉት፡፡ ዓረና ወረቀት ይዞ ህወሓት ብረት ታጥቆ!
ህወሓት በትግራይ ከዚህ በፊት በተለያዩ ድራማዎች የታጀበ የይምሰል ምርጫዎች ያደርግ ነበር…ዘንድሮ ግን እውነተኛ ምርጫ ይቅርና የይምሰል ምርጫውም ከነአካቴው ያስቀረው ይመስላል፡፡

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ ከራሳችን ውጪ ለችግራችን ደራሽ መንግስት የለንም!

18206_502642079888454_782261106712844466_n 1907521_1416888335294454_5094790086299619072_n 11150458_502642179888444_2469264559864257823_n
የኢትዮጵያውያን የውርደት ዘመን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ሰሞኑን ከተከሰተው እጅግ አስከፊ ሁኔታ ላይ አድርሶናል፡፡ የመን ውስጥ በተከሰተው ጦርነት ተጎጂ የሆኑትን የውጭ ዜጎች መንግስታቶቻቸው ቀድመው ሲያስወጡ ለኢትዮጵያውያን ግን የሚደርስላቸው አልተገኘም፡፡ ይህንን ውርደትም ወገኖቻችን ‹‹የመን ውስጥ የቀረነው እኛና ውሻ ብቻ ነን፡፡›› ሲሉ እጅግ በሚያሳዝን መልኩ ገልጸውታል፡፡ ኢትዮጵያውያን ላይ የመድፍ፣ የሞርታርና የአውሮፕላን ድብደባ ሲዘንብባቸው በመከራ ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን ስልክ እንዲደውሉ በፌስ ቡክ ላይ በመለጠፍ ከማላገጥ ውጭ ምንም ያላደረገው የህዝብ ስልጣንን በሀይል የተቆጣጠርው ገዥው ፓርቲ ለራሱ ስልጣን ይጠቅሙኛል ያላቸውን የጦርነቱ ተሳታፊዎች ደግፎ መግለጫ ሲሰጥ የኢትዮጵያውያንን ስቃይ እጥፍ ድርብ አድርጎታል፡፡

በኢትዮጵያ የሚታየው የህንጻ ግንባታ የድህነት መሸፈኛ ጭምብል ይሆንን? ቢቢሲ ባወጣው ዘገባ ይህን ጉዳይ አጠያይቋል

የቢቢሲው ሌራቶ ምቤሌ ዘገባውን ሲጀምር በተዘዋወርንባቸው የአዲስ አበባ መንገዶች ሁሉ ካሜራችንን ስናወጣና ፎቶ ልናነሳ ስንሞክር ጠጋ ብለው ምን እንርዳችሁ የሚሉ ኢትዮጵያዊያንን ብዙ አግኝተናል ይላል.ይሁን እንጂ ስለአንዳንድ ነገሮች እንጠይቃችሁ ብለን ስንጠጋ ግን ይገጥመን የነበረው ዝምታ ነው የሚለው ዘጋቢው ኢትዮጵያዊያን ሀሳባቸውን በውስጣቸው ማስቀረት እንደሚመርጡ ይናገራል.

ወገን ይጠቃል፣ እነርሱ ዳንኪራ ይመታሉ – ግርማ ካሳ



የአልመነህ ዋሴ ዋዜማ ዘገባ መስረት፣ የናይጄሪያው ተመራጭ ፕሬዘዳንት መሀመድ ቡሃሪ ፓርቲ እና የሃገሪቱ የሲቪል ማህበረሰብ አባላት፣ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በዉጭ ሃገር ዜጎች ላይ የሚፈጸመዉን ጥቃት ካላስቆመ በናይጄሪያ ያሉ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎችን ለማዘጋት እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው። የ48 ሰዓት ገደብ የያዘ ማስጠንቀቂያቸዉን ሌጎስ ለሚገነው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ አስገብተዋል።

Wednesday, April 15, 2015

በምእራብ ኢትዮጵያ ለኩምሩክ ድንበር አቅራቢያ ጦርነት ተካሄደ።

ከወያኔያዊ ምርጫ በፊት የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ሊያሰጋ ይችላል ሲሉ ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።

ምንሊክ ሳልሳዊ
ወያኔ ራሱን ለማንገስ ከሚጠራው ምርጫ በፊት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር አከባቢዎች ጦርነት ሊካሄድ ይችላል ሲሉ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።በተለያዩ አጋጣሚዎች የተነሱ የሳተላይት ፍቶዎች በማስረጃነት በመጥቀስ ይህን ሰሞን በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከአፍሪካ ህብረት ሰዎች እና ከአከባቢው የፖለቲካ አዋቂዎች ጋር የተለያዩ ስብሰባዎችን የሚያካሂዱት ዋናው የዚሁ ጦርነት ስጋትና አከባቢው ላይ ብሄራዊ ጥቅማቸው ላይ ምን ሊከሰት ይችላል የሚለውን በመገምገም ላይ መሆናቸው ታውቋል።

የህወሃት በቀቀኖች ሚሚ ስብሃቱና ባለቤቷ ዘሪሁን ተሾመ በዲሲ – አርአያ ተስፋማሪያም


mimi
ጋዜጠኛ ሚሚ ስብሃቱና ባለቤቷ ዘሪሁን በዲሲ እንደሚገኙ ታውቋል። ባላፈው ቅዳሜ ከዲሲ ከሚተላለፈውና ንጉሴ በተባለ “ጋዜጠኛ” ከሚሰናዳው ራዲዮ ጋር ቃለምልልስ ያደረገው ዘሪሁን በዲሲ በሚገኙ የሃበሻ ሬስቶራንቶች ከባለቤቱ ጋር ሲዝናና ኢትዮጵያውያን እየሰደቡት፣ እያስፈራሩትና አንዳንዶች ደግሞ ስልክ እየደወሉ በሱማሊኛ ቋንቋ ተቃውሟቸውን ከመግለፅ ባሻገር “ኢህአዴግ አባረራችሁ እንዴ?” እያሉ በፌዝ የጠየቁት እንዳሉ ተናግሯል። መሳደብና ማስፈራራት በህግ እንደሚያስጠይቅና አግባብም እንዳልሆነ አያይዞ ተናግሯል።

በእርግጥም ስድብ የሚደገፍ አይደለም። ነገር ግን «ዛሚ» የተባለውና በእሱና ሚሚ ስም የሚታወቀው ራዲዮ የሚለቀው የስድብ ውርጅብኝ አግባብ ነው?..በሚሚ ያልተሰደበ፣ ያልተዘለፈ፣ ያልተንቋሸሸ ግልሰብና የህብረተስብ ክፍል አለ ይሆን?…”በራስህ ሊደረግብህ የማትሻውን በሌሎች አታድርግ” የሚባለው ለዚህ ነው።

የአባይ ልጅ ውሃ ጠማው!!

የሺ ዘመን እንቆቅልሽ የአበው ተረትና ምሳሌ፤
እነሆ ዛሬ ተፈታ ባዕድ፤ ባንዶች፤ የሸረቡብን ሴረኛ ውል እንደ ‘ውጫሌ’፤
ተጋለጠ፤ የወያኔ የትውልድ የዘመናችን ደባ አባይን ሲሸጡ እንዳልባሌ፤
ሃያ ዓመት ተወይኖብን ስንጠላለፍ በእዚመኛ፤ ዘውገኛ ተከልለን በቀበሌ፤
መንደር እንጅ አገር የለን፤ ኢትዮጵያን የነጠቀን የነገር ሰው ‘አፎሌ’፤
‘ሕዳሴ’ ብሎ አባይ ግድብ ትልቁ ሊጥ የተፈጨው፤ የተቦካው በአፈ - ጮሌ፤
በዲስኩር ራዕያቸው ሲያገምጡን የህልም አምባሻ ‘ደግ~ሰው’ ከመቀሌ፤
ጥሪት፤ሕይዎት እያስገበሩን ከጐጃም እስከ ወለጋ፤ ሸዋ፤ሀረር፤ አርሲ፤ከፋና፤ባሌ፤
ለካስ ቃል አባይ ኖረዋል፤ አፈር ቀማሹ ወደ ምድር ‘የሰረጉት’ ቀድመው በሃምሌ፤
ወንዛችንን እያቆሩ፤ ተስፋችንን የቀበሩ፤ ውሃ ያስጠሙን ‘የኛ ጌቶች’ የባዕድ ሎሌ፤
የኢትዮጵያን ‘እህል-ውሃ’ አስቀንነው ግብጽ፤ሱዳን ሲያስጋግሩ፤ካገር ሳይመክሩ ሽማግሌ፤

ወቅታዊ መርህ ሊሆን የሚገባው ‹‹ያገባኛል›› ባይነት! (ኢ-ሰብዓዊነትን መቃወም በራስ ሲደርስ ብቻ አይደለም) ኤልያስ ገብሩ

ባለፈው ዓመት ‹‹ስለ ሀገር ያገባኛል›› የሚል አዲስ መንገድ በማኅበራዊ ድረ-ገጾች ተጀምሮ ነበር፡፡ ይህ፣ በምንወዳት ሀገራችን ወቅቱ የሚጠይቀው ቃል ሲሆን ብዙዎች እውነተኛ መርህ አድርገው በተግባር ሊኖሩበት ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡
በእኔ አረዳድ፣ ‹‹ስለ ሀገር ያገባኛል›› ማለት ከምንም በላይ ሀገርን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ስለሀገር ህልውና መቆርቆር ማለት ነው፡፡ ለሀገር ሰላምና ደህንነት ዘብ መቆም ማለት ነው፡፡ ትክክለኛ ፍትህ እንዲረጋገጥ ድምጽን ማሰማት ማለት ነው፡፡ ሰብዓዊነት በተግባር እንዲገለጥ መንቀሳቀስ ነው፡፡ ለዓላማ መሬት ረግጦ ለመቆም መወሰን ማለት ነው፡፡ የዜጎችን በደል አይቶ አለማለፍ ማለት ነው፡፡ አስተዳደራዊ በደሎች ሲፈጸሙ ‹‹ለምን?›› ብሎ መጠየቅ ነው፡፡ አድርባይ እና የዳር ተመልካች አለመሆን ማለት ነው፡፡ ‹‹የሀገር ችግር የእኔም ችግር ነው›› ብሎ ማመን ነው፡፡ ከጥቂቶች ይልቅ ለሰፊው ህዝብ መወገን ማለት ነው፡፡ የተሻለች ሀገርን ለመፍጠር የራስን መልካም አስተዋጽኦ ማበርከት ማለት ነው፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 – ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው!

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracyለገዛ ራሱ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ቅን የሚመኝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህወሓትን ለማስወገድ ተግባራዊ ትግል ውስጥ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑን፣ ፋሽስቱን ህወሓት እንደመደገፍ ይቆጠራል።
ዛሬ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ የመሰማራት ሰፊ እድል ተፈጥሮለታል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ ኢትዮጵያዊያን ወደ በረሃዎችና ተራራዎች አቅንተዋል። ብዙዎች በመንገዱ ላይ ያሉ ጋሬጣዎችን ተቋቁመው እየተቀላቀሏቸው ነው። በደል የመረራቸው ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በቡድን ለነፃነታቸው ዘብ ቆመው በህወሓትና አገልጋዮቹ ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ይህ የሚበረታታ እና ተቀናጅቶ ሊጠናከር የሚገባው ጉዳይ ነው።

“ምስክር ፈላጊው ችሎት” – 27ተኛ የፍርድ ቤት ውሎ (ዞን 9)

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ከጎንዬሽ ጉዳዬች ውጪ ለ25ተኛ ጊዜ (በአጠቃላይ ለ27ተኛ ጊዜ) የተሰየመው ችሎት ዛሬም የደረጃ ምስክሮችን ሲያሰማ ውሏል፡። ከሳምነትት በፌት የተሰየመው ችሎት አቃቤ ህግ 41 ምስክሮች አሉኝ ነገር ግን ላገኛቸው ስላልቻልኩ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ቆይተው ተጨማሪ ማፈላለጊያ ጊዜ ይሰጠኝ በማለት ጠይቆ ለዛሬ የተቀጠረ ቢሆንም ዛሬም “የሽብር ተግባሩ “ ዋና ምስክሮች ባለመገኘታቸው ፍተሻ ላይ ተገኝተናል ያሉ አምስት ምስክሮች ተሰምተዋል፡። የምስክሮቸን ቁጥርም 35 ነው በማለት ቀይሮታል፡፡Ethiopian arrested zone 9 bloggers
ባለፈው የተሰሙት 13 ምስክሮች ሲሆኑ በዛሬው ችሎት ባልተካደ ነገር ላይ ሲመሰክሩ የዋሉት የደረጃ ምስክሮች
14ተኛ ምስክር ተወዳጅ ኃ/ማርያም ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 34 ሲሆን የመንግስት ሰራተኛ ናቸው፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ‹‹የመጣሁበት ኬዝ ግንቦት 7/2006 ዓ.ም በምኖርበት ልደታ 5ኛ አካባቢ የፌደራል ፖሊስ ታዛቢ ሁነኝ ብሎ ጠይቆኝ በታዛቢነት ያየሁትን ለመመስከር ነው፡፡ ማህሌት ጤና ጥበቃ ሚ/ር ትሰራለች መሰለኝ፣ እዚያ መስሪያ ቤት ፖሊስ ማህሌት ኮምፒውተርና ጠረጴዛ ላይ ያለውን ሲበረብር አይቻለሁ፡፡ መንግስት መስሪያ ቤት የምትጠቀምበት ኮምፒውተር ላይ የተገኙ ሰነዶች ላይ ማህሌት ስትፈርም እኛ ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡

ቴድሮስ አድሃኖም መዋሸቱን ቀጥሏል? ኢትዮጵያውያን አሁንም ከየመን ለመውጣት እርዳታ አላገኙም

(ECADF) ትላንት አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (Agence France‑Presse) እንደዘገበው ከሆን ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዲህ ብለዋል “ኢትዮጵያ በሁቲ አማጽያን ከስልጣን የተባረረውን የየመን መንግስት በቆራጥነት ትደግፋለች፣ ሳውዲ አረብያ የየመን መንግስትን ወደስልጣን ለመመለስ ጣልቃ መግባትዋም ትክክለኛ እርምጃ ነው” ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት ኃይለማርያም ኢትዮጵያ “በቆራጥነት ትደግፈዋለች…” ያሉት የየመን ምንግስት ፕሬዝዳንት አገር ጥለው በመሸሽ ሳውዲ አረብያ የሚገኙ ሲሆን አማጽያኑ ደግሞ ዋና ከተማዋን ሰንዓንና የወደብ ከተማዋን ኤደንን ተቆጣጥረው ይገኛሉ።
በቅድሚያ ከ50,000 በላይ ኢትዮጵያውያውያን መውጫ አጥተው በሳውዲ አረብያ የጦር አውሮፕላኖች እየተደበደቡ ባለበት ሁኔታ እና አማጽያኑ መላውን የመን እየተቆጣጠሩ ባለበት ሁኔታ ለተባረረው ይየመን መንግስት በግልጽ ድጋፍ መስጠት የሚያሳየው ነገር ቢኖር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የወያኔ አዛዦቻቸው ምን ያህል በየመን መውጫ አጥተው ለሚገኙት ለኢትዮጵያውያን ደንታ እንደሌላቸው ነው።

የት ሂዱ ነው? (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

መስፍን ወልደ ማርያም (አዲስ አበባ)
ዓለም ሁሉ ጠላን፤ በየትም አገር እየሄድን ‹‹የሙጢኝ!›› ከራሳችን መሬት በጉልበት እየተነቀልን፣ ከራሳችን ቤት እየተባረርን፤ ከተወለድንበትና ከአደግንበት አካባቢ እየተፈናቀልን፣ ጭራውን ቆልምሞ እንደሚሮጥ ባለቤቱ እንዳባረረው ውሻ በአገኘነው አቅጣጫ እየሮጥን፣ እጃችንን እያርገበገብን ‹‹የሙጢኝ!›› እንላለን፤ የፈራነውን ሞት በየመንገዱ እናገኘዋለን፤ ሞትን ሸሽተን ሞት ያጋጥመናል፤ የሞቱ ልዩነት አይታየንም፤ በየመንገዱ የሚያጋጥመው ሞት የውርደት ሞት ነው፤ የብቸኛነት ሞት ነው፤ ዘመድ-ወዳጅ ለቀብር የማይገኝበት ሞት ነው፤ ሠለስት፣ አርባ፣ ሙታመት የማይወጣበት ሞት ነው፤ ባዕድ ምስጥ ያላሳደገውን አካል የሚበላበት ነው፤ የሞት ሞት ነው፡፡Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopher
ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ከአገር አስወጥቶ ባዶ መሬት ብቻ ይፈልግ ይመስል የወያኔ ሎሌዎች በማስፈራራት ሁሉም አገሩን እየተወላቸው እንዲሄድ ያቀዱ ይመስላል፤ ጥንት ኢሰመጉ በምሠራበት ጊዜ በየጊዜው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን በማስፈራራት ሰላማቸውን ለመረበሽ ወደስደት ወይም ወደወንጀል ተግባር የሚመሩ የወያኔ አባለች ነበሩ፤ አሁን እንደገና ብቅ ማለት ጀምረዋል፤ ሕጋዊ ሥርዓት እየላላ ጉልበተኞች በግላቸው ለዘረፋና ለቅሚያ እየተሰማሩ ይመስላል፡፡