የት ሄደን እናልቅስ
የት ሆነን እንተንፍሰ
የወንድሞቼን ደም የት ሄጄ ልመልስ
ሀገር ነበር እኮ ሁሉንም ማስረሻ
ሀዘን ይሁን ስጋት ከሁሉ መሸሻ
ወንድሜ ሲቃጠል በሳውዝ አፍሪካ ላይ
ስጋዬ ቢታረድ በሊብያ ምድር ላይ
እህቴንም ባጣት በዛ በየመን ላይ
ሀዘኔ ቢበዛ ውስጤ ቢቆስልብኝ
መንግስት እንደሌለው ማንም ሲገልብኝ
ምንም እንኳን ባጣ ሄዶ ሚያተርፍልኝ
ደርሶ ሚያስጥልልኝ
እኔው ተነሳሁኝ እህህ ልለው
ሀዘኔን ቁጭቴን ሁሉን ላሳውቀው
አቅሜም እንኩዋን ባልችል ባልሆን ከጎናቸው
ሀዘኔን በሀገሬ ፍቅሬን ላሳያቸው
ሆ ብዬ ተነሳው በኢትዮጵያ ምድር ላይ
በጀግኖቻችን ደም በፀናች ሐገር ላይ
በእንባዬ እየታተብኩ በህዝቦቼ ስቃይ ጉዞዬን ጀመርኩኝ ወደ አደባባይ
መንግስት እንኮን ራርቶ ወደ ህዝቡ እንዲታይ
ድንገት ሳላስበዉ ምኑንም ሳላውቀው
በእንባዬ እየታተብኩ ጉዞዬን ስጎዘው
መጣብኝ ወገኔ እኔኑ ሊመታ
በሐዘን ላይ ሐዘን ወደ ኔ ሊያመታ
እጅን አነሳኝ እግሩን ዘረጋብኝ
በጣም በጭካኔ ዱላ አሳረፈብኝ
ላዝን የወጣሁት ለ ገዛ ደማችን
አማራ ይሁን ትግሬ አንድ ነው ሕዝባችን
እስላም ክርስቲያኑ አንድ ነው ኑሮአችን
ኢትዮጵያዊነት ነው የኛ መለያችን
ምነው ጨከንክ ወገን በገዛ ደምክ ላይ
እናትክ በእንባ እንዲ ስትሰቀይ
ዋይ! ዋይ! ስትል እምዬ ልጇ ተበልቶባት
አንተ ግን መተካት በእርግጫ ገፋካት
የ 9 ወር ቤትን እማን እረሳካት
ቆም ብዬ ሳየው ማዝነው ለ ራሴ ነው
ግንምን ዋጋ አለው ሚያዝንበት ለሌለው ።
ገጣሚ ፍፁም
ከ ደቡብ አፍሪካ
ከ ደቡብ አፍሪካ
No comments:
Post a Comment